ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም "ደብረ ሊባኖስ" በስማቸው ለተሰየመላቸው፤ ከዐለት ላይ ውኃ እያፈለቁ ድውያንን የሚፈውሱት ለታምረኛው አባት አባ ሊባኖስ (ዘመጣዕ) ዓለምን ፍጹም በመናቅ ለመነኑበት ነው ለመታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ፦ እርሳቸውም የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም "ደብረ ሊባኖስ" በስማቸው የተሰየመላቸው ናቸው፡፡ አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ፡፡ እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ወደጫጉላቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና "ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም" አላቸው፡፡ አባታችንም "ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?" ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኰሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና "ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድለህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ" አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል "ተራ ውሃ ነው" ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ "አምላከ አባ ሊባኖስ" ብሎ አመሰገነ፡፡ ❤ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው "ምትሃት ነው የሚያሳየው" ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው "አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን" ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው "ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኰሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል" አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን "ደብረ ሊባኖስ" ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም "ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ" አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ "ሊባኖስ ዘመጣዕ" የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡ ❤ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

photo content
+1

❤ ሊቀ ጳጳሳቱም ለመኰንኑ ይህንን ሃያ ሺህ የወርቅ ዲናር ሰጠው መኰንኑም ዐሥር ዐሥር ሺህ የወርቅ ዲናር እንደ ግብር ሆኖ በየዓመቱ እንዲከፈል ጽፊ አስፈረመው ጊዜውም ሲቀርብ ይህ አባት አባ ሚካኤል ከምዕመናን ሊሊምን ተነስቶ ወጣ በልበይስ ወደተባለም አገር ደርሶ አንድ ቀን ዋለ። ወደርሱም አንድ ምስኪን ድሃ መነኵስ ገባ ከሊቀ ጳጳሳቱም ቡራኬ ተቀቡሎ ተመልሶ በበር አጠገቡ ከረድኡ ጎን ቆሞ "አትዘን በልብህም አትተክዝ ከዛሬይቱ ዕለት እስከ አርባ ቀኖች ትድናለህ በላይህ ያለውን የእዳ ደብዳቤ ትቀበላለህና ለመኰንኑም ምንም አትስጠውም ብለህ ለአባት ሊቀ ጳጳሳት ንገረው" አለው። ያ ረድኡም እንዳለው ነገረው ደሃውንም መነኵስ ፈለጉት ግን አላገኙትም አርባ ቀኖችም ሳይፈጸሙ ያ መኰንን በክፉ አሟሟት ሞተ። በእርሱ ፋንታም ልጁ ተሾመ ለዚህም አባት ያንን የእዳ ደብዳቤ መለሰለት። ይህም አባት ድሃው መነኰስ ትንቢት እንደ ተናገረ ደብዳቤውን ተቀብሎ ቀደደው ከዕዳም ዳነ። ❤ ይህም አባት በታላቅ መከራና በኀዘን በሹመቱ ዘመን ሃያ ዘጠኝ ዓመት ከኖረ በኋላ መጋቢት20 ቀን በፍቅር በሰላም ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት20 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሑረትከ እግዚአብሔር ኬንያ። እምኢየሩሳሌም ለቢታንያ። ከመ ታንሥእ በድኖ ለአልዓዛር እኅወ ማርያ። ትሴፈወከ ነፍስየ ወትጸንከ ነያ። እሞተ ኃጢአት ታሕይዋ በዝንቱ አርአያ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 20። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦"እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ። ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም"። መዝ 43፥22። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 1፥12፣18 ያዕ 5፥8-14 እና የሐዋ ሥራ 24፥10-22። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 11፥17-46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው ጻድቅ ሰው ቅዱስ አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚች ምልክት ገናናነት ብዙዎች በጌታችን ላመኑበት በዓል፣ ለተጋዳይም በተአምራቷ ከ5,685 በላይ ሰዎችን በጌታችን እንዲያም ላደረገ ለቅድስት አስጠራጦኒቃ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓልና ለእስክንድርያ ሃምሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ሚካኤል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከተጋዳይዋ ከቅድስት ጽጌ ሥላሴ ከመታሰቢያዋና ከቅዱስ አስቃራን ቤተ ክርስቲያኑ ከከበረችበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ሰው አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚህ ምልክት ገናናነት ብዙዎች አመኑበት። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱና ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅድስት አስጠራጦኒቃ፦ የዚች ቅድስት አባቷ ጣዖት አምላኪ ነው እርሷ ግን በክብር ባለቤት በክርስቶስ የምታምን ናት ሥጋዋም እስቲከሣና እስቲደርቅ መልኳም እስቲለወጥ ድረስ በሥውር ትጾማለች ትጸልያለችም። ❤ ዐሥራ አምስት ዓመት በሆናት ጊዜ እናትና አባቷ "ምነው ያከሣሻል?" አሏት፡፡ እርሷም "እኔስ ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እጸልያለሁ" አለቻቸው፡፡ አባቷም በሰማ ጊዜ ወደ ጢባርዮስ ሒዶ የልጁን ሥራ ነገረው እርሱም ወታደሮች ልኮ ወደ ርሱ አመጣት። ለጣዖትም እንድትሰግድ መኰንኑ አባበላት እምቢ በአለችም ጊዜ ወደ ወህኒ ቤት አስገቧት እናቷም ክርስቲያናዊት ናት እየመጣች በክብር ባለቤት በክርስቶስ እምነት ታበረታታት ነበር። ❤ ከዚህ በኋላ የብረት የሆነ የሰሌዳ ክርታስ ይሠሩላት ዘንድ በእሳትም አግለው ክንዶቿ ከወገቦቿ ጋራ አንድ እስቲሆኑ እንዲያጣብቋት አዘዘ። ይህንንም በአደረጉባት ጊዜ ያንን የብረት ክርታስ ሰብራ በድኅና ወጣች ሕዝቡም ይህን አይተው በክብር ባለቤት በክርስቶስ አራት ሺህ ሰባት መቶ ያህል አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። ❤ ሁለተኛም ደግመው ከእሥር ቤት አስገቧት ጥፍሮች ያሉት የብረት በሬ ሠሩላት ሆዷን ያስወጓት ዘንድ ሊሰቅሏትም ወርሷ አቀረቡት ይህንንም በአደረጉባት ጊዜ በጌታ ኃይል በሬው ወዲያና ወዲህ ተከፈለ ሕዝቡም ይህን በአዩ ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ያህል ሰው አምነው በሰማዕትነት ዐረፋ። ❤ ከዚህም በኋላ መርዝን ከተመሉ እባቦች ጒድጓድ ውስጥ ጨመሯት በጸየለች ጊዜ እንደ ትቢያ ሆኑ። ሁለተኛም አራት ሰዎች የሚሸከሙትን ከባድ ደንጊያ አምጥተው በአንገቷ ላይ ሰቀሉ በጸለየችም ጊዜ ደንጊያው ወደ ሦስት ተከፈለ። ብዙዎች አረማውያንም በክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ❤ ለቅድስቲቱ ግን የብረት ምንቸት አዘጋጁላት በውስጡ የፈላ እርሳስ በላይዋ ያፈሱባት ዘንድ በነኩት ጊዜ በላያቸው ተሰብሮ የሚያሰቃዩአትን ገዳላቸው። ንጉሡም አይቶ ተቆጣ ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ምስክርነቷን ከምትፈጽምበት ቦታም በደረሰች ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች "አስጠራጦኒቃ ሆይ አንቺ ብፅዕት ነሽ ስምሽ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፏልና" የሚል ቃል መጣላት ከዚያም በኋላ በሰይፍ አንገቷ ተቆረጠች። በቅድስት አስጠራጦኒቃ በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። + + + ❤ አባ ሚካኤል፦ ይህም አባት በእስክድርያ ከተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ ሰባተኛ የሆነ ነው። በሹመቱ ወራት ብዙ ኀዘንና መከራ ደረሰበት። ጎሕ በሚባል አገር የተሾመ የዚህን ኃላፊውን ዓለም ክብር የሚወድ አንድ ክፉ ኤጲስቆጶስ ነበር። በአገረ ስብከቱም ውስጥ ደነውስር በሚባል አገር ያሉ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያናቸውን ሕንፃዋን አደሱ ሊያከብሩዋትም በፈለጉ ጊዜ የአገር ታላላቆች ከእርሳቸውም ሊባረኩ ወደው ሊቀ ጳጳሳት ልኮ እንዲያመጣቸውና ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ለመኑት እርሱ ግን አምቢ አላቸው ልመናቸውን መቀበል አልወደደም እነርሱም በራሳቸው ፈቃድ ይህ ክፉ ኤጲስቆጶስ ሳይፈቅድ ሊቀ ጳጳሳቱንና ኤጲስቆጶሳቱን ሁሉ ልከው አስመጧቸው ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልና ኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ በመጡ ጊዜ ምሳ አዘጋጅላችኋለሁ ብሎ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትቷቸው ሄደ "ማርታ ማርታ ብዙ በማዘጋጀት ብዙ ትደክሚያለሽ ግን ጥቂቱ ይበቃል" ያለውን የጌታችን ቃል አላሰበም በቁርባን ጊዜ ሊያልፍ ስለሆነ ሊቃውንቱና ኤጲስቆጶሳቱን የቅዳሴውን ሥርዓት ይጀምር ዘንድ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት ግድ ባሉት ጊዜ በሊቀ ጵጵስና ማዕረግና ክብር ተሰይሞ ተነሳ እርሱ ለሁሉ አባት የሆነ ስልጣኑም ከስልጣናቸው በላይ ነውና የቅዳሴውን ሥርዓት ጀመረ ያክፉ ኤጲስቆጶስም በሰማ ጊዜ በልቡ ሰይጣን አደረበትና ተቆጥቶ መጣ መስዋዕቱንም ከመቅደስ ገብቶ ከጻህሉ ውስጥ ነጥቆ መደ ምድር ወረወረው ሊቀ ጳጳሳቱም ሌላ መስዋዕት አምጡ ብሎ አዘዘ። አምጥተውለትም ቀድሶ ለሕዝቡ ሥጋውና ደሙን አቀበላቸውና አሰናበታቸው። ❤ በማግስቱም ይህ አባት አባ ሚካኤል ሕዝቡ ሰበሰበ ከእርሱ ጋራ ያሉትንም ኤጲስቆጶሳት ካህናቱንና የምዕመናን አንድነት ሰብስቦ ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ከሹመቱ ሽረው በእርሱ ፋንታ ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ። ይህም የአስቆሮቱ ሰው ለይሁዳ ሁለተኛው የሆነ የምስርን አገር ወደሚገዛ ስሙ አህመድ ወልደ በጥሎን ወደተባለው ሹም ሆደ ይህንን አባት አባ ሚካኤልን እንዲህ ሲል ነገር ሰራበት "በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ብዙ የወርቅና የብር ገንዘብ እንዳለ እንዲሁም አብያተክርስቲያናት የወርቅና የብር ነዋየ ቅድሳትን የተመሉ እንደሆኑ መኰንን ሆይ እወቅ" አለው። መኰንኑም ይህን አባት ወደ እርሱ አስቀርቧ ነዋየ ቅድሳቱን እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም "ሥጋዬን እንደፈለገህ አድርግ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር እጅ ናት" ብሎ ከለከለው። እጆቹንና እግሮቹን አስረው በእስር ቤት እንዲጥሉት አዘዘ። በእስር ቤትም ከአንድ ዓመት በላይ ኖረ። በእስር ቤት ውስጥ በኖረበት ዘመን ከለምለም እንጀራና ከጨው ከበሰለ አተር በቀር ሳይባላ ሁል ጊዜ ይጾም ነበር። ❤ ከዚህ በኋላ አንድ ጸሐፊ ምዕመን ዮሐንስ የሚባል መጥቶ ለዚህ ለከበረ አባት አባ ሚካኤል ዋስ ሆነው ለመኰንኑም አባ ሚካኤል ሃያ ሺህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ሆኖ ከወህኒ ወቶ ወደ ቤቱ ሄደ ጥቂት ቀንም ተቀመጠ። ታላላቆች ምዕመናንና የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት ዐሥር ሺህ የወርቅ ዲናር ሰበሰቡ ደግሞ የእስክንድርያ አገር ሰዎች ከምድራቸው አንዱን ለዐሥራ ሺህ ዲናር ሸጡ ሃያ ሺህ እስኪሞላ ሰበሰቡ።

photo content
+1

❤ ሊቀ ጳጳሳቱም ለመኰንኑ ይህንን ሃያ ሺህ የወርቅ ዲናር ሰጠው መኰንኑም ዐሥር ዐሥር ሺህ የወርቅ ዲናር እንደ ግብር ሆኖ በየዓመቱ እንዲከፈል ጽፊ አስፈረመው ጊዜውም ሲቀርብ ይህ አባት አባ ሚካኤል ከምዕመናን ሊሊምን ተነስቶ ወጣ በልበይስ ወደተባለም አገር ደርሶ አንድ ቀን ዋለ። ወደርሱም አንድ ምስኪን ድሃ መነኵስ ገባ ከሊቀ ጳጳሳቱም ቡራኬ ተቀቡሎ ተመልሶ በበር አጠገቡ ከረድኡ ጎን ቆሞ "አትዘን በልብህም አትተክዝ ከዛሬይቱ ዕለት እስከ አርባ ቀኖች ትድናለህ በላይህ ያለውን የእዳ ደብዳቤ ትቀበላለህና ለመኰንኑም ምንም አትስጠውም ብለህ ለአባት ሊቀ ጳጳሳት ንገረው" አለው። ያ ረድኡም እንዳለው ነገረው ደሃውንም መነኵስ ፈለጉት ግን አላገኙትም አርባ ቀኖችም ሳይፈጸሙ ያ መኰንን በክፉ አሟሟት ሞተ። በእርሱ ፋንታም ልጁ ተሾመ ለዚህም አባት ያንን የእዳ ደብዳቤ መለሰለት። ይህም አባት ድሃው መነኰስ ትንቢት እንደ ተናገረ ደብዳቤውን ተቀብሎ ቀደደው ከዕዳም ዳነ። ❤ ይህም አባት በታላቅ መከራና በኀዘን በሹመቱ ዘመን ሃያ ዘጠኝ ዓመት ከኖረ በኋላ መጋቢት20 ቀን በፍቅር በሰላም ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት20 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሑረትከ እግዚአብሔር ኬንያ። እምኢየሩሳሌም ለቢታንያ። ከመ ታንሥእ በድኖ ለአልዓዛር እኅወ ማርያ። ትሴፈወከ ነፍስየ ወትጸንከ ነያ። እሞተ ኃጢአት ታሕይዋ በዝንቱ አርአያ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 20። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦"እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ። ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም"። መዝ 43፥22። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 1፥12፣18 ያዕ 5፥8-14 እና የሐዋ ሥራ 24፥10-22። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 11፥17-46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት (፲፱) 19 ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ለቅዱስ አርስጥቦሎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አሰከናፍርና ለሚስቱ ማርታ፣ ለልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ ለዕረፍታቸው በዓልና ለሰባቱ ሰማዕታት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ቅዱስ አርስጥቦሎስ፦ እርሱም ጌታችን ከመረጣቸውና ከመከራው በፊት ወንጌልን እንዲሰብኩ ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቈጠረ ነው። ❤ በሃምሳኛው ቀን በዓልም መንፈስ ቅዱስ በላዩ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሕይወት በሚገኝበት በወንጌል ትምህርት ሐዋርያትን ተከትሎ በመሔድ አገለገላቸው። ብዙዎችንም ወደ ድኅነት መንገድ መልሶ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጥቆ የአምላክን ሕግና ትዕዛዝ ከማስጠበቁ የተነሣ ነፍሳቸውን አዳነ። ❤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህን ቅዱስ አብራጣብያስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። ወደርሷም ሒዶ በውስጥዋ ወንጌልን ሰበከ ብዙዎቹንም በቀናች ሃይማኖት እግዚአብሔር ወደ ማወቅ መለሳቸው። በፊታቸው ድንቆች ተአምራትን በማድረግ በሃይማኖት አጸናቸው ነገር ግን ከአይሁድና ከዮናናውያን ብዙ መከራ ደረሰበት። ብዙ ጊዜም ወደ ፈራጆች አደባባይ ወስደው በደንጊያ ወገሩት ጌታችንም ከመከራው ሁሉ ጠብቆ አዳነው መልካም ተጋድሎውንም በፈጸመ ጊዜ መጋቢት19 በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ❤ እነሆ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልክቱ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ አስታውሶታል። ከቅዱስ አርስጥቦሎስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከት ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን አሰከናፍርና ሚስቱ ማርታ፣ ልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ፦ ይህም አስከናፍር ብዙ ገንዘብ ያለው ባለጠጋ ነው። ለእግዚአብሔር ሕግ የሚጠነቀቅ ነበር ልጆቹንም መንፈሳዊ ምክርና ተግሣጽ በማስተማር አሳደጋቸው። በአደጉም ጊዜ የጥበብንና የተግሣጽን ትምህርት እንዲማሩ ተይሩት ወደምትባል አገር ሰደዳቸውና ትምህርታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ሊድራቸውና በሰርጋቸው ደስ ሊለው ሽቶ ያመጧቸው ዘንድ ላከ በመርከቡም ሁነው ሲመጡ ማዕከል ተነሥቶ መርከቡ ተሰበረ። እግዚአብሔርም ከሰጥመት አድኖ በየብስ አወጣቸው ዮሐንስ የተባለውን በአንድ ቦታ ማዕከል አውጥቶ ጣለው። ❤ ዮሐንስም ተስፋ በቆረጠ ጊዜ ወደ ቅዱሳን ገዳም ሒዶ መነኰሰ።ስለ ወንድሙ ስለ አርቃድዮስም እንተሞተ ተጠራጥሮ በጾም በጸሎትና በስግደትም ሥጋውን አደከመ። አርቃድዮስም ወደ ዮርዳኖስ ገዳም ገብቶ ከአንድ ቅዱስ አረጋዊ ሰው ዘንድ መንኵሶ እየተጋደለ ሦስት ዓመት ኖረ። ❤ አስከናፍር ግን ልጆች በማዕበል እንደ ሰጠሙ በሰማ ጊዜ ከሚስቱ ጋራ ማቅ ለብሰው አመድ አንጥፈው እያለቁሱ ተቀመጡ። በአንዲት ሌሊትም አስከናፍር በሕልሙ ልጁ ዮሐንስ በራሱ ላይ ከዕንቊ የተሠራ አክሊል ተቀዳጅቶ መስቀል ይዞ አየው። አርቃድዮስንም በኮከብ አምሳል የሆነ አክሊል በራሱ ላይ ደፍቶ አየ ከእንቅልፉም ነቅቶ ለሚስቱ ያየው ነገራት። ❤ ከዚህም በኋላ በየአድባራቱና በየገዳማቱ የልጆቻችንን ወሬ እንመርምር ዘንድ ተነሺ እንሒድ አላትና ወደ ዮርዳኖስ ሒደው ከመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ገዳም ደረሱ። ልጃቸውን አርቃድዮስን ያመነኰሰውን አረጋዊ አባትን አገኙት ችግራቸውን ነገሩት እርሱም "የክርስቶስ ወዳጆች አትዘኑ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመለሱ ልጆቻችሁን በሕይወት ታገኛላችሁ" አላቸው ደስ እያላቸውም ተመለሱ። ❤ ዮሐንስም በመስቀል በዓል ሊሳለም መጣ አረጋዊውም ጠርቶ ከአርቃድዮስ ከወንድሙ አገናኘው ተያይዘውም አለቀሱ። ደግሞ አስከናፍርን ከሚስቱ ጋራ ጠርቶ ከልጆቻቸው ጋር አገናኛቸውና በላያቸው ወድቀው እየሳሟቸው አለቀሱ። ❤ ከዚህ በኋላ ከዚያ አረጋዊ ዘንድ የምንኵስና ልብስ ለበሱ ሚስቱን ማርታንም ከሴቶች ገዳም አስገባት አገልጋዮችንም ነፃ አውጥቶ አሰናበተ። ገንዘቡንም ለድኆችና ለችግረኆች በተነ ከገዳምም ገብቶ በጾም በጸሎት ተወሰነ እንዲሁም የተባረኩ ልጆቹ በገድል በትሩፋት የተጠመዱ ሁነው ኖሩ ጌታችንንም ደስ አሰኙት በፍቅር በአንድነት መጋቢት19 ዐረፉ። የቅዱሳን አሰከናፍርና የሚስቱ ማርታ፣ የልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። + + + ❤ ሰባቱ ሰማዕታት፦ እነርሱም የግብጽ ሰው እለእስክንድሮስና እስክንድሮስ፣ ከጋዛ መንደር አጋብዮስ፣ ከቡንጥስ ከተማ ኒሞላስ ከጠራልብስ፣ ዲዮናስዮስ፣ ሮሜሎስና ተላስዮስ ከግብጽ አውራጃዎች የሆኑ ናቸው። ❤ እነርሱም በመንፈሳዊ ፍቅር ጸንተው ስለ ሃይማኖት ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ። በፍልስጥዔም ውስጥ ወደ አለው ቂሣርያ ደርሰው በመኰንኑ ፊቱ ቆሙ። በከሀዲው ከዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን ገለጡ መኰንኑም በጹኑ ሥቃይ አሠቃይቶ መጋቢት19 ገደላቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 19 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአርስጦቦሎስ ዘተፈነወ ለምሮ። ምስለ ሐዋርያት በጽዮን ውኂዘ መንፈስ ሰኪሮ። ጽሒፎ በእዱ እም አምኀ ማኅበሮ። እንዘ ያስተበፅዕ ወይዌድስ ግብሮ። በውስተ መልእክቱ ዘሮሜ ጳውሎስ ዘከሮ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት19። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦"ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 16፥3-17፣ 1ኛ ጴጥ 3፥7-15 እና የሐዋ ሥራ 22፥22-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል።ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

🌺መዝሙር ዘደብረ ዘይት🌺 እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ትርጒም፦ ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው እወቁ እንዳያስቷችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ ትዕግሥቱን ያዘወተረ እሱ ይድናል የሰው ልጅ በሚመጣ ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይል ይናወጣል ያንጊዜ የምድር ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ ከእግዚአብሔር ታዞ በሚደረግ የመለከት መነፋት፣ በአዕላፍ መላእክት አጀብ፣ በትእዛዝና በቃል ጌታችን ከሰማይ ወደምድር ይወርዳል በዚያች ሰዓት ከኃጢአት ሞት (በኃጢአት ከሚመጣ ፍርድ) ይማረን የሰንበት ጌታ እሱ ሕይወትን የሚሰጥ ነውና  የዕለቱ ምስባክ እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ  ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ መዝ ፵፱፥፫ ትርጒም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል አምላካችን ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነዳል ምሥጢር፦ እግዚአብሔር በሰባ ዘመን በረድኤት ተገልጦ ይመጣል መጥቶም ዝም አይልም በበጎዎቹ አድሮ ይፈርዳል አንድም በበጎዎቹ ካህናት አድሮ ክፉዎችን ካህናት ይዘልፋል እሳት በፊቱ ይነዳል ማለት ክፉዎች የሚጠፉበትን መቅሠፍት መናገር ነው አንድም እግዚአብሔር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሥጋ ማርያም ይገለጣል  መጥቶ ዝም አይልም ወንጌልን ያስተምራል አንድም አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን - ጻፎችና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ እያለ ይዘልፋል አይሁድ የሚጠፉበት መቅሠፍት በፊቱ ነው አንድም በዕለተ ምጽአት የተወጋበትን ኲናት/ጦር የተቸነከረበትን ቀኖት አስይዞ ይመጣል ጻድቃንን ንዑ ኀቤየ ብሎ ይጠራል ኃጥአንን ሑሩ እምኔየ ብሎ ያሰናብታል ጻድቃን የሚድኑበት ሕይወት ኃጥአን የሚቀጡበት መቅሠፍት በፊቱ አለ የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮ ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ ስለ ደብረ ዘይት በመጠኑ፦ አምስተኛው የዓቢይ ጾም ሰንበት ነው። የዘይት ተራራ (የወይራ ዛፍ ያለበት) ማለት ነው። ዳዊት መዝሙር ፳፩ን እየጸለየና እያዘነ ያለ ጫማ የወጣበት ተራራ ነው። ፪ሳሙ ፲፭፥፴፤ ምሥጢረ ምጽአቱ የተነገረበት ተራራ ነው። ማቴ ፳፬፥፫፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ልዩ ምስጋና ያቅረቡበት ተራራ ነው። ሉቃ ፲፱፥፴፯፤ ጌታችን ያድርበት የነበረ ተራራ ነው። ሉቃ ፳፩፥፴፯፤ ምሥጢረ ዕርገቱ የታየበት ተራራ ነው። ግብ ፩፥፲3፤

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤ ❤ መጋቢት፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ለሰማዕት ቅዱስ ፃና ጓደኛው የበግ ጸጒር ልብሶችን በመስራት የሚያገኘው ገንዘብ ለድኆች ይመጸውት ለነበረው ለከበረ ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ቅዱሳን ፃናና ኤስድሮስ፦ ፃና ግን ፈርማ በሚባል አገር ለአገረ ገዥው ከጦር ሠራዊቱ ውስጥ ወታደር ነበር እርሱም ከደቅስያ ሰዎች ወገን ነው ከበግ ጸጒር ልብሶችን ለሚሠራ ለኤስድሮስ ወዳጁ ነው። ሁለቱም ሠርተው ከሚያገኙት ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውታሉ። ❤ በአንዲት ሌሊትም ከእርሷ ጋር አክሊሎች ያሉ ድንግል ሴት በራሳቸው ላይ ስታኖረው ሁለቱም ራእይን አዩ። ከእንቅልፋቸውም በነቁ ጊዜ ያዩትን እንዴት እንዳዩ ተነጋገሩ። ምስክሮቹ ሊሆኑ የጠራቸው እግዚአብሔር እንደሆነ አውቀው እጅግ ደስ አላቸው። ❤ ከዚያም ተነሥተው ሒደው ወደ መኰንኑ ደረሱ ቅዱስ ፃናም ትጥቁን ፈትቶ በመኰንኑ ፊት ጣለው ሁለቱም በጌታችን በክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን ገለጡ። መኰንኑም ነገራቸውን ሰምቶ አሥረው ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ እስክንድርያ ቅዱስ ፃናን ላከው ቅዱስ ኤስድሮስን ግን በዚያው ተወው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ የእስክንድርያው መኰንን ቅዱስ ፃናን ወደ ፈርማ ከተማ መለሰው። ሁለቱ ቅዱሳንም ተገናኙ በመገናኘታቸው ደስ ብሏቸው በላያቸው በየአንዳንዳቸው የደረሰውን መከራ ተነጋገሩ። ❤ ዳግመኛም ለቅዱስ ኤስድሮስ ዐዘቅትን ይቆፍሩለት ዘንድ በዐዘቅቱም ውሰጥ እሳትን አንድደው ቅዱስ ኤስድሮስን እንጨምሩት መኰንኑ አዘዘ። ቅዱሱም ጥቂት እስቲጸልይ ይታገሡት ዘንድ ወታደሮቹን ለመናቸው ወደ ጌታችንም ነፍሱን ይቀበል ዘንድ ለሥጋውም ያስብ ዘንድ ጸለየ። ከዚያም ወደ እሳት ጒድጓድ ቀረበ ወደ እሳቱም ውስጥ ጨመሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ በሥጋውም ላይ ምንም ጒዳት አልደረሰም መልኩም አልተለወጠም። ❤ የቅዱስ ፃና እናትም ከሚወደው ጓደኛው ስለመለየቱ ታላቅስለት ነበር። ከዚያም ሥጋውን ተሸክመው ወሰዱ የስደቱም ወራት እስቲፈጸው በመልካም ቦታ አኖሩት። ❤ ቅዱስ ኤስድሮስ ምስክር ሁኖ በሞተ ጊዜ የቅዱስ ፃና እናት ብዙ መላእክት የቅዱስ ኤስድሮስን ነፍስ ይዘው በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ሲያሳርጓት አየች። እግዚአብሔር ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖችን በቅዱሳን ፃናና ኤስድሮስበጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት18 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለኤስድሮስ እምነ ሤመ ፀምር ግብረ እዱ። ዘይሁብ ምጽዋተ ለእለ ፈቀዱ። ምንዳቤያተ ፈጺሞ ወኵነኔያተ ለለ፩ዱ። በዕለተ ውዕየ ለዐዘቅት እሳት በነዱ። መላእክት ነፍሶ በስብሐት ወሰዱ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)የመጋቢት18። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe https://t.me/eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤ ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ንዑስ በዓላት አንዱ ለሆነው ለዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ለደብረ ዘይት እግዚአብሔር በሰላም በጤና አደረሰን። + + + ❤ የደብረ ዘይት መዝሙር፦ "እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዲኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኵሉ ኀይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኵሎሙ ኀጥአነ ምድር። ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚአ ለሰንበት። ትርጉም፦ ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል። የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ። ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው። ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምጽ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል። በዚች ዕለት ሞትን ከሚያስከትል ኃጢአት አብ ይማረን የሕይወት ባለቤት የሰንበትም ጌታ ነውና። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። +++ ❤ ደብረ ዘይት ❤ የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል ፡፡ ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ማለት ነው ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ በዚህ ዓለም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ሰዓት ከቅዱሳን ሐዋርያት ስለ ዓለም ፍፃሜ ምልክቶች የቀረበለትን ጥያቄ አስመልክቶ መልስ የሰጠበትን ዕለት በማስታወስ የሚከበር እሁድ “ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ። ንገረን ይህ መቼ ይሆናል ? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው ? አሉት ። ” ማቴ. ፳፬፥፫ ይህንን ሥርዓት የሰራው ደግሞ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ ነው ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የዓለም ፍፃሜ መድረስ አስመልክተው የሚታዩ ምልክቶችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ነግሯቸዋል ፡፡ “ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ። ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው .… የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል ከሁለትም ይሰነጥቀዋል እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል ። ” ማቴ. ፳፬፥፬‐፶፩ + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ። ወአምላክነሂ ኢያረምም። እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። መዝ 49፥3። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 4፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 3፥7-15 እና የሐዋ ሥራ 24፥1-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥1-36። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ነው። መልካም የደብረ ዘይት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe @eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊ ጻድቅ ከመቃብራቸው እስከ አሁን ድረስ ለበሽተኞች የሚሆን ፈዋሽ ቅባ ቅዱስ ለሚያፈልቁት ኤርትራ አገር የሚገኙ አምስት ታላላቅ ገዳማትን ለመሰረቱ ለታላቁ አባት ለአቡነ ዮናስ ለዕረፍት በዓላቸው መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ዮናስ፦ ከአባታቸው ንዋየ እግዚእ ከእናቻው ሂሩተ ማርያም ሕዳር 17 በ1357ዓ.ም በጉናጉና ቤተ መስቀል ተወለዱ ስመ ክርስትናቸው ሀብተ እግዚእ ተባሉ። ሀብተ እግዚእ ገና ልጅ እያሉ የበጎች እረኛ ሆነው እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ መልአኩን ልኮ 70 መዝሙረ ዳዊት አስተማራቸው ፍላጎታቸውም ወደ መንፈሳዊ ትምህርት እና ምናኔ ነበር። ከዛም ከተወለዱበት ቦታ ተነስተው ወደ ደብረ ሲና የምትባል ገዳም ሄዱ ከዛ የእናታቸው የሥጋ ወንድም አጎታቸውን አገኙ። አቡነ ዲያምኖስ የሚባሉ በጣም ትልቅ ባለጸጋ አባት አገኙ ከዛም በኋላ የመጡበትን ምንክንያት ለምናኔ መሆኑን ካወቁ በኋላ ሐዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን እና ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩዋቸው በኋላ በ14 ዓመታቸው በ371ዓ.ም ስርዓተ ምንኲስናን ተቀበሉ የምንኲስናቸውም ስም አቡነ ዮናስ ተባሉ። ዮናስ ማለት የዋህ ልክ እንደ ርግብ ማለት ነው። ባሕር ውስጥ ገብተው እየጸለዩ በቀን 5 የዛፍ ፍሬ ዋርካ ወይም 5 ፍሬ እየተመገቡ በከባድ ጾምና በጸሎት በመንፈስዊ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር። ❤ አቡነ ዮናስ ያደረጉት ተአምር። 1. ሶስት ሙታን አስነስትዋል። 2. ከኤርትራ በደመና ተጭነው ወደ ኢሩሳሌም ሄደው ቀድሰው ወደ ደብረ ጽጌ ገዳም ተመልሰው መክፈልት ይቀምሱ ነበር። 3. ዕረፍታቸው ቀን ሲደርስ በ5ቱ ገዳም የሚገኙ ልጆቻቸው ሰብስበው እኔ የዕረፍቴ ቀን እየደረሰ ነው ከእኔ በኋላ ልክ እንደእኔ አባት የሚኖናችሁ አባ ጳውሎስ ናቸው። እና ለእርሳቸው ልክ እንደ እኔ ታዘዙ አሏቸው። ልጆቻቸውም ይህን ሲሰሙ በጣም አዘኑ መጋቢት 17 ቀን 1452 በ92 ዓመታቸው በዐቢይ ጾም ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የዕረፍት በዓላቸው የሚከበረው ግን ጥር21 ቀን ነው። ልጆቻቸውም ከሀዘን ብዛት የተነሳ በትንሣኤ ቀን ምንም ሳያደርጉ ዝም አሉ። ከዚያም አቡነ ዮናስ ተገልጸው "ልጆቼ ከእኔ ሀዘን የጌታዬ ትንሣኤ ይበልጣል። እና አሁን ትንሣኤውን አድርጉ" አሏቸው ልጆቻቸውም ደግሞ "እኛ ምንም ነገር የለንም እና እንዴት እናደርግ" አሉ ጻድቁ አቡነ ዮናስ "ሦስት አጋዘኖች ወደ እናንተ ይመጣሉ እና እነርሱን አርዳችሁ በዓሉን አሳልፉ እንቢ ቢሏችሁ እንኳን በአቡነ ዮናስ ስም ገዝቷቸው" አሉ። ከዛ ጻድቂ እንዳሉ ሦስት አጋዘኖች መጡ ሁለቱ ታረዱ አንዱ ደግሞ ሊሮጥ ብሎ "በጻድቁ አቡነ ዮናስ ስም ቁም" ብለው ሲገስጹት ቆመ። 4 ጻድቁ አቡነ ዮናስ ካረፉ በኋላ በአምስቱም ገዳማት ዘይት ፈልቋል። በአሁን ጊዜ ግን በመቃብራቸው ብቻ ነው የሚገኘው። 5 ጻድቁ አቡነ ዮናስ የአምስቱ ገዳማት አባት ናቸው። 1.ደብረ ጽጌ 2.ደብረ ድሁሃን 3.ደብረ ሳህል 4.ደብረ ጽዮን 5.ደብረ ጸሪቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ አገር ውስጥ ይገኛል። 6. ጻድቁ ባህር ውስጥ ገብተው ሲጸልይ እጃቸውም ልክ እንደ ጸሐይ ያበራ ነበር። ❤ ቃል ኪዳናቸው፦ በዚህ ከባድ መንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወርደው ለአባታችን አቡነ ዮናስ እንደዚህ የሚል ትልቅ ቃልኪዳን ገባላቸው "ወዳጄ ዮናስ ሆይ ጾምህንና ጸሎትህን ተቀብዬልሀለው ከአሁን በኋላ ገድልህን የሰማ፣ ያሰማ፣ ያነበበ አስኬማህንና ቆብህን በስምህ የተቀበለ የ135 ሺ ከእናንተ ጋር የሚነግሱ ዓስራት አድርጌ ሰጥቼሀለው፤ በስምህ እና በጸሎትህ የተማጸነ ያለ ቁጥር እንደ ክረምት ዝናብ ምሬልሀለሁ ዝክርህን የዘከረ መጽሐፍ ገድልህን የጻፈ ያጻፈ፣ ለገዳሙ ዘቢብ፣ ዕጣን ፣ ስንዴ፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ንዋየ ቅድሳት የሰጠ፣ ገዳሙን ያነፀ፣ በስምህ የተማጸነ፣ ገዳምህን የረገጠ፣ እንደነጭ ሀር አነጻዋለሁ። ኃጢያቱ ልክ እንደ ቁራ ቢጠቁርም እንደነጭ በረዶ አነጸዋለሁ ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው። ከአባታች አቡነ ዮናስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ገዳሙ ካሳተመው ከአቡነ ዮናስ ስዕል ጀርባ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ። @sigewe @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊ ጻድቅ ከመቃብራቸው እስከ አሁን ድረስ ለበሽተኞች የሚሆን ፈዋሽ ቅባ ቅዱስ ለሚያፈልቁት ኤርትራ አገር የሚገኙ አምስት ታላላቅ ገዳማትን ለመሰረቱ ለታላቁ አባት ለአቡነ ዮናስ ለዕረፍት በዓላቸው መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ዮናስ፦ ከአባታቸው ንዋየ እግዚእ ከእናቻው ሂሩተ ማርያም ሕዳር 17 በ1357ዓ.ም በጉናጉና ቤተ መስቀል ተወለዱ ስመ ክርስትናቸው ሀብተ እግዚእ ተባሉ። ሀብተ እግዚእ ገና ልጅ እያሉ የበጎች እረኛ ሆነው እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ መልአኩን ልኮ 70 መዝሙረ ዳዊት አስተማራቸው ፍላጎታቸውም ወደ መንፈሳዊ ትምህርት እና ምናኔ ነበር። ከዛም ከተወለዱበት ቦታ ተነስተው ወደ ደብረ ሲና የምትባል ገዳም ሄዱ ከዛ የእናታቸው የሥጋ ወንድም አጎታቸውን አገኙ። አቡነ ዲያምኖስ የሚባሉ በጣም ትልቅ ባለጸጋ አባት አገኙ ከዛም በኋላ የመጡበትን ምንክንያት ለምናኔ መሆኑን ካወቁ በኋላ ሐዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን እና ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩዋቸው በኋላ በ14 ዓመታቸው በ371ዓ.ም ስርዓተ ምንኲስናን ተቀበሉ የምንኲስናቸውም ስም አቡነ ዮናስ ተባሉ። ዮናስ ማለት የዋህ ልክ እንደ ርግብ ማለት ነው። ባሕር ውስጥ ገብተው እየጸለዩ በቀን 5 የዛፍ ፍሬ ዋርካ ወይም 5 ፍሬ እየተመገቡ በከባድ ጾምና በጸሎት በመንፈስዊ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር። ❤ አቡነ ዮናስ ያደረጉት ተአምር። 1. ሶስት ሙታን አስነስትዋል። 2. ከኤርትራ በደመና ተጭነው ወደ ኢሩሳሌም ሄደው ቀድሰው ወደ ደብረ ጽጌ ገዳም ተመልሰው መክፈልት ይቀምሱ ነበር። 3. ዕረፍታቸው ቀን ሲደርስ በ5ቱ ገዳም የሚገኙ ልጆቻቸው ሰብስበው እኔ የዕረፍቴ ቀን እየደረሰ ነው ከእኔ በኋላ ልክ እንደእኔ አባት የሚኖናችሁ አባ ጳውሎስ ናቸው። እና ለእርሳቸው ልክ እንደ እኔ ታዘዙ አሏቸው። ልጆቻቸውም ይህን ሲሰሙ በጣም አዘኑ መጋቢት 17 ቀን 1452 በ92 ዓመታቸው በዐቢይ ጾም ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የዕረፍት በዓላቸው የሚከበረው ግን ጥር21 ቀን ነው። ልጆቻቸውም ከሀዘን ብዛት የተነሳ በትንሣኤ ቀን ምንም ሳያደርጉ ዝም አሉ። ከዚያም አቡነ ዮናስ ተገልጸው "ልጆቼ ከእኔ ሀዘን የጌታዬ ትንሣኤ ይበልጣል። እና አሁን ትንሣኤውን አድርጉ" አሏቸው ልጆቻቸውም ደግሞ "እኛ ምንም ነገር የለንም እና እንዴት እናደርግ" አሉ ጻድቁ አቡነ ዮናስ "ሦስት አጋዘኖች ወደ እናንተ ይመጣሉ እና እነርሱን አርዳችሁ በዓሉን አሳልፉ እንቢ ቢሏችሁ እንኳን በአቡነ ዮናስ ስም ገዝቷቸው" አሉ። ከዛ ጻድቂ እንዳሉ ሦስት አጋዘኖች መጡ ሁለቱ ታረዱ አንዱ ደግሞ ሊሮጥ ብሎ "በጻድቁ አቡነ ዮናስ ስም ቁም" ብለው ሲገስጹት ቆመ። 4 ጻድቁ አቡነ ዮናስ ካረፉ በኋላ በአምስቱም ገዳማት ዘይት ፈልቋል። በአሁን ጊዜ ግን በመቃብራቸው ብቻ ነው የሚገኘው። 5 ጻድቁ አቡነ ዮናስ የአምስቱ ገዳማት አባት ናቸው። 1.ደብረ ጽጌ 2.ደብረ ድሁሃን 3.ደብረ ሳህል 4.ደብረ ጽዮን 5.ደብረ ጸሪቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ አገር ውስጥ ይገኛል። 6. ጻድቁ ባህር ውስጥ ገብተው ሲጸልይ እጃቸውም ልክ እንደ ጸሐይ ያበራ ነበር። ❤ ቃል ኪዳናቸው፦ በዚህ ከባድ መንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወርደው ለአባታችን አቡነ ዮናስ እንደዚህ የሚል ትልቅ ቃልኪዳን ገባላቸው "ወዳጄ ዮናስ ሆይ ጾምህንና ጸሎትህን ተቀብዬልሀለው ከአሁን በኋላ ገድልህን የሰማ፣ ያሰማ፣ ያነበበ አስኬማህንና ቆብህን በስምህ የተቀበለ የ135 ሺ ከእናንተ ጋር የሚነግሱ ዓስራት አድርጌ ሰጥቼሀለው፤ በስምህ እና በጸሎትህ የተማጸነ ያለ ቁጥር እንደ ክረምት ዝናብ ምሬልሀለሁ ዝክርህን የዘከረ መጽሐፍ ገድልህን የጻፈ ያጻፈ፣ ለገዳሙ ዘቢብ፣ ዕጣን ፣ ስንዴ፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ንዋየ ቅድሳት የሰጠ፣ ገዳሙን ያነፀ፣ በስምህ የተማጸነ፣ ገዳምህን የረገጠ፣ እንደነጭ ሀር አነጻዋለሁ። ኃጢያቱ ልክ እንደ ቁራ ቢጠቁርም እንደነጭ በረዶ አነጸዋለሁ ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው። ከአባታች አቡነ ዮናስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ገዳሙ ካሳተመው ከአቡነ ዮናስ ስዕል ጀርባ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው ቅዱስ አልዓዛር ከሞተ በኋላ በአራተኛውም ቀን ከመቃብር ላስነሳበት ለተዓምራቱ በዓል፣ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑ ለአቡነ ይስሐቅ (ገሪማ) በሚሰሩት ስራ ገሪማ ለተባሉት ለመታሰቢያ በዓላቸውና ለአናጒንስጢስ ለቅዱስ ቴዎቅሪጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከታጋዩ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከሰማዕቱ ከቅዱስ ተላስስ፣ ከኤጲስቆጶስ ዮሴፍ ከመታሰቢያቸውና ከሊቀ ካህናት ኒቆር ከሥጋው ፍልሰት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለቃልከ እማእሰሪሁ ዘፈትሖ። ለፍቁር አልዓዛር ኃይለ ሥልጣነ ሞት ድኅረ ሞቅሖ። ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሠ ሰላም ወተራኅርኆ። አባ ወአቡየ እሴብሐከ ሰብሖ። ለአንቀጽከ ጸግወኒ መርኆ"። ትርጉም፦ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ቸር ማኅየዊ ለሚሆን ቃልህ ሰላምታ ይገባል። የሞትን ሥልጣን ሽሮ አልዓዛርን ከመቃብር አሰነሥቷልና። ፈጣሪዬ ኢየሱስ ሆይ የሰላምታ የቸርነትህን አባት ሆይ የቸርነትህን በር ትከፍትልኝ ዘንድ ልባዊ የሆነ ፍጹም ምስጋናን አቀርብልሃለሁ። መልክአ ኢየሱስ። + + + ❤ ጌታችን ቅዱስ አልዓዛር ከሙት እንዳስነሳው፦ ይህም ጻድቅ ሰው ከእስራኤል ልጆች ውስጥ ነው። ማርያምና የተባሉ ሁለት እኅቶች አሉት። ማርያም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሽቱ የቀባችው ናት። እርሱም በጌታ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው ስለ ምግባራቸውም ጌታችን ይወዳቸዋል ሁሉም ያላገቡ ደናግል ናቸው። ❤ ለሰው ወገን ሁሉ ላይ የተቆረጠውና የተወሰነው ሰዎችም ሊጠጡት ያላቸው የሞት ጽዋን እጁን ለሞት የሚሰጥበት ለዚህ ጻድቅ ጊዜው ሲደርስ እርሱም እጁን በመስጠት ዐረፈ። ❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ግን የሚሠራውን ያውቃልና መጀመሪያ ከሞት አላዳነውም ጠርቶ እስከሚያስነሳው ድረስ ሙቶ በመቃብር አራት ቀን እንዲኖር በዚህ በአራት ቀንም የጻድቃንን ማደሪያዎችንና የኃጥአንን የሥቃይ ቦታዎች እንዲያይ ተወው እንጂ አላዳነው ያን ጊዜም ታላቅ ምልክት ትሆናለች። ❤ ከአራት ቀኖችም በኋላ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ "አልዓዛር አልዓዛር ና ውጣ" ብሎ ከመቃብር ውስጥ ጠራው ያን ጊዜ እጆቹና እግሮቹ እንደታሠሩ ሙታኖችንም እንደሚጠቀልሏቸው በሰብን ፊቱ ተጠቅልሎ ወጣ። እጆቹና እግሮቹ እንደ ተጠቀለሉና እንደ ታሠሩ ከመቃብር የመውጣቱ ምክንያት ሰዎች ሁሉ መሞቱን እንዲረዱ ሌሎችም ይህ በመካከላቸው በስምምነት የሆነ ነው ብለው እንዳያስቡ። ስለዚህም እንደ ገነዙት ሁኖ እንዲወጣ ጌታችን አዘዘው ይችም ምልክት እንድትሆን። ከሀዲዎችም በመቃብር ውስጥ ሕያው እንደነበር ቢያስቡም እጆቹና እግሮቹ ፊቱም እንደ ተጠቀለሉ እንዴት ይወጣ ነበር እኛ የክርስቲያን ወገኖች ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከአራት ቀኖች በኋላ አልዓዛርን ያስነሳው እርሱ እንደሆነ እናምናለን እንታመናለንም እርሱ በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ አለውና። ❤ ለጌታችንና ለፈጣሪያችን ለመድኃኒታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱና ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ክብር ስግደት ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለቴዎቅሪጦስ አናጉንስጢስ፤ ስምዐ ዘተከለለ ወአክሊለ ስብሐት ዘተቀጸለ በስመ ኢየሱስ ዘፈጸመ በድረ"። ትርጉም፦ በምስክርነት የተቆረጠ ለኾነ፤ በኢየሱስ ስም ገድሉን የፈጸመ ኾኖ የክብር አክሊልን የተቀዳጀ ለኾነ ለአናጉንስጢስ ለቴዎቅሪጦስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ አናጒንስጢስ ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ፦ ይህም ቅዱስ የሮሜ አገር ሰው ነው። ዐላውያንም ለጣዖት እንዲሠዉ ክርስቲያኖችን ይዘው በአስገደዷቸው ጊዜ ከእርሱ ጋር ያዙት ወደ ንጉሥም አቀረቡት ያንጊዜ የዐሥራ አምስት ዓመት ልጅ ነበር። ❤ ንጉሥም "በማመጣብህ ሥቃይ ትፈተናለህን ወይስ ለአማልክት ትሠዋለህ" አለው። ቅዱስ ቴዎቅሪጦስም እኔስ ለክብር ባለቤት ለጌታዬ ለፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እሠዋለሁ" አለው። ንጉሡም "ቴዎቅሪጦስ ሆይ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ" አለው። እርሱም "ንጉሥ ሆይ መሥዋዕቴን እንድታይ ና" አለው ንጉሡም ወደ ጣዖቱ ቤት እንዲወስዱትና በዚያ እንዲሠዋ አዘዘና እርሱም በበር ቆመ። ቅዱሱም በጸለየ ጊዜ ንውጽውታ ሁኖ አጽቀላጽዮስ የሚሉት አምላካቸው ተሰበረ። ንጉሡም እንደ ዘበተበት አይቶ አፍንጫውን ቆርጠው አሥረው በወህኒ ቤት እንዲያስገቡት አዘዘ። በማግሥቱም አውጥተው በብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩት ደግመው ጥልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ በውስጡም እንጨት ረብርበው ሥጋው ከመለያያው እስቲቦጫጨቅና ቅልጥሙም ከአጥንቶቹ እስቲፈስ ድረስ ወረወሩት። በዚህም ሊያጠቁት አልቻሉም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእርሱ ጋር አለና። ❤ ከዚህ በኋላም አማልክቶቻቸው የሚበቀሉት መስሏቸው ከአማልክቶቻቸው ቤት አስገብተው በዚያ ዘጉበት ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ ግን ከጣዖታቱ ላይ ያለውን ወርቅ ቀጥቅጦ በሥውር ይዞ እየወጣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች መጸወተው። ተመልሶ ሲገባም በደጃፉ እንደ ቀድሞው ራሱ ይዘጋል። ❤ በስምንተኛውም ቀን ንጉሥ መጣ ከደጃፍም ሁኖ አየ አማልክቶቹም ተጥለው ተሰባብረው የከበረ ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ ሲዘብትባቸው አገኛቸው። እውነተኛ ቅዱስ ቴዎቅሪጦስንም የሆድ ዕቃው እስኪታይ እንዲሰነጣጥቁት አዘዘ። ደግመው ወደ ጨዋታ ቦታ እንዲያስገቡትና በላዩ አንበሶችን እንዲያስገቧቸው አዘዘ። አንበሶችም ቁስሎቹን ላሱለት። ዳግመኛም ሕዋሳቱ ከሚያጣብቅ ቦታ እንዲያስገቡት መላ አካላቱም ታጥፎ እስቲቆለመም እንዲያሠቃዩት አዘዘ። በዚህም ተሽብሮ አላሸነፉትም ንጉሡም ብርታቱን አይቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ። ❤ የከበረ ኤጲስቆጶስ ኤሞሬዎስና ሕዝቡ ሁሉ በጸሎት እየተራዱት ቅዱስ ቴዎቅሪጦስን ተከተሉት በቅዱሳን ሰላምታ ተሳልመውት ተሰናበቱት ባለወግ ወታደርም ሰይፉን አንሥቶ መጋቢት17 አንገቱን ቆረጠው ምስክርነቱንም ፈጸመ። የአናጒንስጢስ ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ አማላጅነቱ በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት17 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ገሪማ መድምመ ዘአርአየ ዲበ ዕፅ ዘአዕረገ ብዕራየ ወዲበ በውድ ዘአውረደ ሥርናየ"። ትርጉም፦ በውድማ ላይ ሥንዴን ያወረደ ወደ ዕንጨት ላይም በሬን ያወጣ፤ ድንቅ ነገርን ያሳየ ለኾነ ለአባ ገሪማ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለቴዎቅሪጦስ አመ ተቀሥፈ አባለ። እስከ ሥጋሁ ተበጽለ። እለ ርእይዎ አንከሩ እንተ ተውህበቶ ኃይለ። ሶበ ቅብዐ ጽጌ እምነ ቊስሉ ፈልፈለ። ለአንፈ ኵሉ ዘይጼኑ ኮለ"። ትርጉም፦ ሥጋው እስኪቦጨቅ ድረስ ሰውነቱ የተገረፈ ለኾነ ለቴዎቅሪጦስ ሰላምታ ይገባል፤ ያዩትም የተሰጠችውን ኃይል አደነቁ፤ ለአፍንጫ ኹሉ እንደ እንኮይ የሚሸትት የአበባ ዘይት ከቊስሉ በመነጨ ጊዜ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 17።