cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Event Addis/ሁነት አዲስ

https://eventaddis.com ለአስተያየትና ማስታወቂያ: @Tmanaye

Больше
Рекламные посты
7 093
Подписчики
+3124 часа
+1227 дней
+57530 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
የአርአያ ሰው ሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት"የአርአያ ሰው ሽልማት" በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ተቋሙ የሚያዘጋጀው አርአያ ሰው ሽልማት ባለፉት ስድስት ዓመታት ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አጋርነት፣ ድጋፍና ዕውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮም ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የአርዓያ ሰው የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን  የቀጥታ ስርጭት  ሽፋን ያገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5344Loading...
02
በእነ አርቲስት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ መዝገብ ከተከሰሱት ከ5፣7፣8ተኛ  ተከሳሾች ውጪ ያሉት በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። በዚህ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ፣ ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ)ን ጨምሮ 17 ሰዎች በ50 ሺህ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት እንደወሰነ ተሰምቷል። መረጃው የSirak Temesgen ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5713Loading...
03
የሐሙስ መረጃዎች የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ! መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቅሱ! 📍ሙዚቃ - የድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም የድምጻዊው ዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። "ጋፊኮ" አልበም ስምንት የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። ጉቱ አበራ ከዚህ ቀደም ሀዋንሀዋ፣ ዴሚ፣ አነቱ፣ኢዮሌ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም። -የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።14 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበሙ ግጥም እና ዜማው በራሱ በወንዲ ማክ ተሰርቷል። በፍቅር፣ በማህበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተነግሯል።ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። - የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል።አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል። - በቅርቡ በሮፍናን ኑሪ "ኖር " አልበም ውስጥ "መንገድ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊት የሰማናት ትውለደ ኢትዮጵያዊቷ lri Di በእንግሊዝኛ "Sound of Rain" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠችውን ገሚስ አልበሟን ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደምትደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።Iri Di ከድምጻዊነቷ ባሻገር የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጊታሪስት ነች።ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ወየ መላ ፣ ባርዴዴ፣ ሌት ናይት ቡና የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች። - ተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው የተጫወቱ ድምፃውያ የሙዚቃ ስራቸውንም ያቀርባሉ።በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። 📍ሥነጽሑፍ ፣ ኪነጥበብ ፤ የሀሳብ ውይይት - በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት መምህርና ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የሕይወት ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና የሚወዷቸውን በኢትዮጵያውያን የተጻፉ ሰባት መጻህፍትን የሚጠቁበት መርሐግብር ይካሄዳል ።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ሰኔ 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል። - በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  (ወመዘክር አዳራሽ) "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።በመጀመሪያው ወር  “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ቀን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ሀሳብ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል። - "አውደ ፋጎስ" 39ኛው ዙር የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ሰኔ 16 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ ይካሄዳል።በዚህኛው ዙር " የ "የማ" ወንዶች በአሊጎሪካዊ እና ነገረ ፍካሬ እይታ "በሚል ርዕሰ ጉዳይ በደራሲ ቢኒያም አቡራ መነሻ ሀሳብ አቅራቢነት በሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ አወያይነት ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይካሄዳል። - "ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ መድረክ" የፊታችን እሁድ ሰኔ 16 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መገናኛ ዋኣች ሕንፃ ላይ በሚገኘው "ጣዕም ባህላዊ ምግብ ቤት" ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።በዝግጅቱ ላይም ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎችም የሥነጽሑፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። 📍ሥነጥበብና (ሥዕል ) በዕይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች - የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ከቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ በእይታ ይገኛል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። - የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል። - የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ከአርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል። -የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ከግንቦት 23 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ በእይታ ይገኛል።እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል። አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ ቀን: ሰኔ 13 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ: https://eventaddis.com ቴሌግራም: @EventAddis1
7023Loading...
04
Media files
6830Loading...
05
በዕይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች 📍የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ከቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ በእይታ ይገኛል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። 📍 የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል። 📍የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ከአርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል። 📍የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ከግንቦት 23 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ በእይታ ይገኛል።እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 1447Loading...
06
የጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ወንድም ሁለቱም ኩላሊቶቹ ፌል አድርገዋል በሀገራችን የሚገኝ ስመጥር እና ልበ ቀና ጋዜጠኛ ነው ጌጡ  ለሀገሩና ለወገኑ ቀድሞ ደራሽ ሲሆን በዙሪያው ያሉ ወዳጆቹ ስለ መልካምነቱ አውርተው አይጠግቡም :: ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተከታይ ባለው ማህበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነት ለረጅም ዓመታት በታማኝነት  መረጃዎችን እያቀረበልን በርካታ መልካም ተግባሮችንም እየከወነበት ይገኝል ::   ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚለቃቸው ማስታወቂያ አዘል መልዕክቶች ላይ የሚሰጡ አስታየቶች እና ትችቶችን ሳይ ይህንን ለመፃፍ ተገደድኩ :: የጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ታናሽ ወንድም በአሁኑ ሠዓት  ሁለቱም ኩላሊቶቹ ፌል አድርገው ለረጅም ጊዜያት በሳምንት 3 ጊዜ የዲያለሲስ ህክምና እያደረገ ይገኛል:: ለብዙዎች የደረሠው መልካሙ ጌጡ  እስካሁን ድረስም ጉዳዩን በግል እና በቤተሰብ ደረጃ በመያዝ ድጋፍ አልጠየቀም በገፁ አማካኝነት በሚገኝ መጠነኝ የማስታወቂያ ገቢ አማካኝነት የወንድሙን ከፍተኛ የህክምናውን ወጪ ለመሸፈን ጥረት እያደረገ ይገኛል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4311Loading...
07
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን ጨምሮ ብዛታቸው 20 እንደሆኑ በፖሊስ ለፍርድ ቤት የቀረበ ማመልከቻ ላይ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። አማኑኤል በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ግለሰቦችን ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ፖሊስ በድጋሚ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት የጠየቀ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆች የተጨማሪ ምርማራ ጊዜ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግ ሰፊ ክርክር አድርገዋል። ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን ጨምሮ ለሌሎቹም ጠበቃ ሆነው ከቀረቡት ጠበቆች መሐል አንዱ የሆኑት ጠበቃ አያሌው እንደገለጹልኝ ከሆነ፤ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተከሳሾችን በተናጠል ዘርዝሮ እንዲያቀርብ ያዘዘውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አለማድረጉን በክርክሩ ላይ በማንሳት፤ በቀጠሮ ማራዘሚያ ጥያቄው ላይ በተቀመጠው ምክንያት መሰረት "በማሕበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት" ተብሎ የተጠቀሰው ወንጀል ማሕበራዊ ሚዲያ አደባባይ ላይ ያለ ምንም የተለየ ጊዜ የሚያስጠይቅ ጉዳይ አለመሆኑን አንስተው ተከራክረዋል። ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ጠበቆች ባነሱት የመከራከሪያ ሃሳብ መሰረት የተከሳሾች ምርመራ መዝገብ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ አቤቱታ እና ዝርዝር ማስረጃዎች በመመልከት የዋስትና መብት ፈቃድን ወይም የጊዜ ቀጥሮ ፈቃድ ላይ ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት የፊታችን ሐሙስ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጠዋት 4፣00 ሰዓት ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። መረጃው የያሬድ ሹመቴ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 5992Loading...
08
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሊታደስ ነው አምስት ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሙሉ ህንፃ እድሳት ሊደረግለት እንደሆነ ተነግሯል። ዛሬ ሰኔ  11 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ህንፃ እድሳትን ለማከናወን ከሀብታሙ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ  ጋር የውል ስምምነት አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ህንፃ ሙሉ ጥገና እንደሚደረግለትና የጥገና ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የአንድ ዓመት ጊዜ እንደሚወስድ በስምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በእውቁ አርክቴክት በጋሻውበዛ ተስፋሚካኤል በደርግ ጊዜ የተነደፈ ሲሆን በጥሬ ህንጻ (brutalism) የዓለም ህንጻዎች መዝገብ የሰፈረ ብቸኛው የአገራችን ዘመናዊ ህንጻ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 5275Loading...
09
በአንጋፋው ወመዘክር አዳራሽ "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር ነው በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  (ወመዘክር አዳራሽ) "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ነባሩ የሐሳብ ክምችታችን ነው። በዚሁ ክምችት አጠገብ ተቀምጠን አንዳንድ ሐሳቦችን በወር ለአንድ ቀን ከአንድ ቀንም ለአንድ ሠዓት ተኩል ረግተን ብንወያይ ደህና ነው " ብሏል። በመጀመሪያው ወር  “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ቀን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ምልከታ ላይ ሃሳቦችን ውይይት ይካሄዳል ተብሏል። በዚህ ውይይት ላይ መነሻ ሀሳብ በይኩኖ አምላክ መዝገቡ የሚቀረብ ሲሆንበኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ውስጥም ውይይቱ ይካሄዳል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 4674Loading...
10
የድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበም ! ከኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ዓለምአቀፏ ድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበሟን የፊታችን ሀሙስ ትለቃለች። በቅርቡ በሮፍናን ኑሪ "ኖር " አልበም ውስጥ "መንገድ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊት የሰማናት ትውለደ ኢትዮጵያዊቷ lri Di በእንግሊዝኛ "Sound of Rain" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠችውን ገሚስ አልበሟን ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደምትደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ከደቡብ ኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ድምጻዊት Iri Di በእንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋቸው በተለያዩ መድረኮች ላይ  የሙዚቃ ስራዎቿን አቅርባለች። Iri Di ከድምጻዊነቷ ባሻገር የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጊታሪስት ነች። ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ወየ መላ ፣ ባርዴዴ፣ ሌት ናይት ቡና የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች። የቀደመ ሙዚቃዎቿን በስሟ በተከፈተው የዩቲዩብ ቻናሏ https://youtu.be/okSTVC-FJtw?si=csHO8TRQeybxIC0Q መከታተል ትችላላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 35512Loading...
11
የድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበም ! ከኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ዓለምአቀፉ ድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበሟን የፊታችን ሀሙስ ትለቃለች። በቅርቡ በሮፍናን ኑሪ "ኖር " አልበም ውስጥ "መንገድ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊት የሰማናት ትውለደ ኢትዮጵያዊቷ lri Di በእንግሊዝኛ "Sound of Rain" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠችውን ገሚስ አልበሟን ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደምትደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ከደቡብ ኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ድምጻዊት Iri Di በእንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋቸው በተለያዩ መድረኮች ላይ  የሙዚቃ ስራዎቿን አቅርባለች። Iri Di ከድምጻዊነቷ ባሻገር የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጊታሪስት ነች። ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ወየ መላ ፣ ባርዴዴ፣ ሌት ናይት ቡና የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች። የቀደመ ሙዚቃዎቿን በስሟ በተከፈተው የዩቲዩብ ቻናሏ https://youtu.be/okSTVC-FJtw?si=csHO8TRQeybxIC0Q መከታተል ትችላላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10Loading...
12
የድምጻዊ ፍፁም ቲ አልበም አርብ ይለቀቃል የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል። "አያዳላም" አልበም ይጣራል ፣ድክም አለኝ፣ እኔ አልዋስም፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አስር የሙዚቃዎች ስራዎችን ይዟል ተብሏል። ከእነዚህም የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ለአንዱ የሙዚቃ ቪዲዮ ተዘጋጅቶለታል። ድምጻዊ ፍፁም ቲ ይህን አልበም ለመስራት ከአሜሪካ አትላንታ ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ እንደቆየ አስታውቋል። ድምጻዊው ፍፁም ቲ "አዲስ አባ" በተሰኘው ሙዚቃ ስራው በርካቶች ያስታውሱታል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 36610Loading...
13
የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሟን በዚህ ዓመት ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም ለአድማጭች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ የ29ኛ ዓመት ልደቷን እያከበረች የምትገኘው ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"መጠሪያዬ" የተሰኘዉ ሶስት ዓመት የለፋሁበት ብዙ ያየሁበት የመጀመርያ አልበሜ ነሐሴ 17 ይለቀቃል " ብላለች። በተጨማሪም "ከዚህ በኃላ የምለቃቸዉ ፎቶዎች ላይ ስለ አልበሙ አንድ አንድ ነገሮች እላችዋለው አዳዲስ ነገሮችም አሉ "ስትል ሀሳቧን አስፍራለች። ይህ የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ" መጠሪያዬ" የተሰኘ አዲስ አልበም ሶስት ዓመት ገደማ እንደፈጀም ተነግሯል። ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ከዚህ ቀደም ኩርፊያ  ፣ ጥፍጥ አለኝ ፣ ተው ፣አበባዬ ፣እናነዬን ጨምሮ ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 43416Loading...
14
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ መጽሐፍ ለንባብ በቃ የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 10 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደቀረበ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፉ ነው ተብሏል። መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። መጽሐፉን በጃፋር ፣በእነሆ እና በእውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች ላይ ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 6414Loading...
15
አርቲስት መስከረም አበራ የክብር እንግዳ የሆነችበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር  ረቡዕ ሰኔ 12  2016 ዓ.ም ይካሄዳል። በዕለቱ አርቲስት መስከረም አበራ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ትገኛለች። እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ። ማስታወሻ :ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 5977Loading...
16
የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘው አልበም ባንድ ካምፕ ዴይሊ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ከሙዚቃዊ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ባሳለፍነው ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል እንደተለቀቀ ይታወሳል። በሙዚቃ ሞያ ውስጥ ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ በመሆን ከ17 ዓመታት በላይ ያሳለፈው ሙዚቀኛ  ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘የላቁት ደጋጎች’ አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያወጣው አልበም ነው፡፡ የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም  ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ተመርቋል። በ1999 ዓ.ም ጆርጋ ከጓደኞቹ ጋር በመሰባሰብ የቀረጸው ይህ አልበም የጆርጋ መንፈስን ያንጸባርቃል ተብሏል። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 የተመሰረተውና ዋና መስሪያ ቤቱን አሜሪካ ካሊፎርንያ ያደረገው ባንድ ካምፕ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ አስታውቋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
1 3682Loading...
17
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የተዘጋጀው የሥነጽሑፍ ሥልጠና በሚመጣው የክረምት ወቅት ይካሄዳል በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በየዓመቱ የሚዘጋጀው የክረምት የሥነጽሑፍ ስልጠና ዘንድም ለዘጠኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል። ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስምንት ዙሮች በርካታ የሥነጽሑፍ ወዳጆች ስልጠናውን እንደወሰዱ ተነግሯል። በልቦለድ ክሂል ፣በልቦለድና ኢ ልቦለድ፣ በግጥም ፣ በፎክሎር ፣ በሥነጽሑፋዊ ታሪክ ፣በሥነሂስ በሌሎችም የሥነጽሑፍ ዓይነቶች ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ምዝገባ እንደተጀመረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ለበለጠ መረጃ በተከታዩ ስልክ ቁጥር ደውሉ  0911448297 ተብላችኋል። 📍ሼር ያደርጉ: ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 28720Loading...
18
ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ዕውቅና ተሰጠው ቴክሳስ ዳላስ የሚገኘው አድዋ የታሪክና የባህል  ህብረት  በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት በግለ ታሪክ ዘርፍ ጋዜጠኛ  ዕዝራ እጅጉን ልዩ ተመስጋኝ አድርጎታል። ጋዜጠኛ ዕዝራ፣ ጸሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድን የመሠሉ የሀገር ባለውለታዎችን የህይወት ታሪክ በሲዲና በዲቪዲ ያሳተመ ሲሆን ይሄንኑ ታሪክ በእንግሊዝኛ  አዘጋጅቶታል። በተጨማሪም ከ20ዐ9 አንስቶ ባለፉት 7 ዓመታት የ45 ሠዎችን ታሪክ በሲዲ ሠርቶ  ለማስመቅ ችሏል። በተጨማሪም በአገራችን  ታዋቂ የሆኑ እንደ ማማ በሰማይ ፤ ማህሌት፣ የአክሊሉ ማስታወሻ፤ የመሳሰሉት 30 የሚጠጉ መጽሀፎችን ወደ ድምጽ በመቀየር ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች እዝራ እና ድርጅቱ "ተወዳጅ ሚዲያ" መላ ዘይደዋል። በተጨማሪም የታዋቂ ኢትዮጵያን ታሪክ በባለታሪኮች እና በልጆቻቸው አሰሪነት ተጠይቆ 14 መጽሀፎችን አዘጋጅቷል፡፡ እዝራ ታሪክን የሚሰንድበት "ተወዳጅ ሚዲያ" የተሰኘ የራሱ ድረገጽ፤ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ያለው ሲሆን ወደ ፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ በአንድ ገጽ ብቻ ታሪካቸውን ጽፈው እንዲልኩ እየጣረ እንደሚገኝ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል። በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት 16 የሚሆኑ ተሸላሚዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የቱሪዝም አባት አቶ ኃብተስላሴ ታፈሰ ፣አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ፣ጸሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ዶክተር  እንዳለጌታ ከበደ እና ሌሎችም  ይገኙበታል ተብሏል። የአርአያ ሠው ሽልማት ሰኔ 13 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ የሽልማት ሥነሥርዓት ይከናወናል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 2882Loading...
19
#ዮቶር_ድግስ የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል። በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ከድምጻዊያኑ በተጨማሪም ኢትዮ ለዛ ባንድ፣ ሻኩራ ባንድ፣ ብርኩማ ባንድ የተሰኙ ባንዶች ድምጻዊያንን ያጅባሉ ተብሏል። በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። አለማየሁ ደመቀ ከ1991 ዓ.ም አንስቶ ከ250 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1 : ኮብላዩ ካሕን” እና በቅርቡ ለንባብ የበቃውን “ዮቶር 2 ” ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ያበረከተ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት በሙያው፣ በክህሎቱ እና በተሰጥዖው አገር እና ወገንን ሲያገለግል እንደቆየ ይታወሳል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 46410Loading...
20
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ተመረጠ፡፡ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዜናዎቹ የምናዉቀውና በያዝነው አመት መጀመሪያ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥንን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ "የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ እንደተመረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" መቀመጫውን በህንድ ሙምባይ ከተማ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። የጋዜጠኞችን ሙያዊ ክህሎት እና ቤተሰቦቻቸውን  ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጠኞችን "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በሚል ስያሜ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ለማስተባበር እየሰራ ያለ ተቋም ነው። ዋና ዋና አምስት መርሆችን አሉኝ የሚለው ድርጅቱ ጋዜጠኝነትን ማስፋፋት እና የጋዜጠኞችን አኗኗር ማሻሻል ላይ አልሞ የሚሰራ ነው፡፡  ኢቨንት አዲስ ከጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን ባገኘው መረጃ  "ድርጅቱ በዋናነት የጋዜጠኞችን የመኖሪያ ቤት፣ የጤና፣ የጋዜጠኛ ልጆችን በትምህርት መደገፍን ጨምሮ የጋዜጠኞችን ክህሎት እና የድህረ ጡረታ ፈተናዎች ላይ ትኩረቱ አድርጎ ይሰራል፡፡" "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በኢትዮጵያ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰንን በበጎ ፍቃደኛ ተወካይነት ሲመርጥ ፤ በዋናነት ለዚሁ ስራ በጎ ፈቃደኛ እና ተነሳሽነት ያላቸውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችንም የሚያካትት መሆኑንም ሰምተናል፡፡ ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 8725Loading...
21
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል። ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 8168Loading...
22
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች! በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው። ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። #Ads ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 85714Loading...
23
የድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ ታናሽ ወንድም የሆነው ድምጻዊ ኤርሚያስ ሞላ አዲስ የቅብብል ነጠላ ሙዚቃውን አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ለአድማጮች አድርሷል። ሙዚቃው በኤርምያስ ሞላ እና የኢትዮጵያን አይዶል ምርጥ አምስት ተወዳዳሪ በነበረችው በእርገት ሰለሞን(ናኒ) በቅብብል የተሰራ ነው። "እስከወዲያኛው " የሚል ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃው በዳዊት ተስፋዬ (ደጃፍ ፖድካስት) ግጥሙ ተጽፎለታል። የሙዚቃው ዜማ እና ቅንብሩ በራሱ በኤርሚያስ ሞላ ተሰርቷል። ከጀርባ በርካታ ሰዎች ተሳትፈውበታል። የሙዚቃ ቪድዮውን በኤርምያስ ሞላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
601Loading...
24
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡ በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 9006Loading...
25
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል። ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል። ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል። የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 7173Loading...
26
"ሜላድ"አውደርዕይ ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል"ሜላድ የብራና ማዕድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 እና ነገ እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም አዘጋጅቷል። ይህ አውደርዕይ ከዛሬ ቅዳሜ ከጠዋት 3፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 5803Loading...
27
የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ የሥዕል ወዳጆች በተገኙበት ለእይታ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ የፊታችን ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 76015Loading...
28
ድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 5665Loading...
29
የድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል። ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል። አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል። አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል። 📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
10Loading...
30
የኔ መኪና እና የኔ ዴልቨሪ አገልግሎቶች ይፋ ሆኑ ቲዎስ ቴክኖሎጂ "የኔ መኪና" እና "የኔ ዴልቨሪ" የተሰኙ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰናዳ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል። "የኔ መኪና" የትራንስፖርት ዘርፉን ከማዘመን አኳያ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን በተለይም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣንና በተሽከርካሪ ባለንብረቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ክፍተት በመናበብ ስራቸውን ምቹ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረግም በላይ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ማሳደስ ያለባቸውን ነገሮች በማስታወስ ከቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት የሚያድን ሶፍትዌር እንደሆነ ተገልጿል። ሌላኛው "የኔ ዴሊቨሪ" ሶፍትዌር ሲሆን የተለያዩ ዶክመንቶችን፣ ሰነዶችን፣ እቃዎችን እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ቴከኖሎጂ በመጠቀም ለግለሰቦች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሆስፒታሎች ለማድረስ የበለጸገ ሶፍትዌር እንደሆነ ተነግሯል። ቲዎስ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በማበልጽግ እየሰራ የሚገኘ ድርጅት ነው። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 4365Loading...
31
ካውሰር ( ሻሊና ሄልዝ ኬር)የተሰኘ ድርጅት አራት የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ያስተዋውቀበትን ኩነት አካሄድ ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አስተዋውቋል። ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው። ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል። ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል። የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን  ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል። ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22  የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል። ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 3634Loading...
32
በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል። በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል። www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው። ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 5122Loading...
33
በኢትዮያዊያው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል። በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል። www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው። ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
10Loading...
34
ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የማይ ሶሮባን ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል” የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ጉብዝና ያሽልማል › በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡ በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3መቶ ሺ በላይ ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡ ውድድሩ በአጠቃላይ ስድስት ዙሮች ሲኖሩት አምስቱ ዙሮች በየከተሞቹ የተከናወኑ ሲሆን የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው ዙር የፍጻሜ ውድድር ከሁሉም ከተሞች የየከተማው አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የአይነት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል። በዳኝነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኮተቤ መምህራን ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሳተፉ የየከተማ ተወካዮቻቸውም በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ተገልጿል። የመዝጊያው መርሃግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል። ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዛሬ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል። ቴሌግራም: @EventAddis1
1 9254Loading...
35
መጻሕፍትን አሳትሞ ለአንባቢያን የማቅረብ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው ተባለ ከዚህ ቀደም በዓመት እስከ አምስት መጻሕፍት የማሳተም ስራ ሲሰሩ የነበሩ አሳታሚ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ለሙሉ የህትመት ስራ ማቆማቸውን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሸገር ይህንን የሰማው በአንድ የመፀሀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቶ ደራሲያንን እና መፀሀፍ ሻጮችን ባነጋገረበት ወቅት ነው፡፡ የወረቀት ዋጋ መወደድን ተከትሎ አሳታሚዎች መፀሀፍቶቻቸውን እንዳያሳትሙ አድርጓቸዋል የተባለ ሲሆን በዚህ ሁሉ ችግር ታትሞ ለገበያ ቢቀርብም አንባቢ አይኖረውም ይላል ኤዞፕ መፀሀፍት መደብር፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ መፀሀፍቱ የሚሸጡበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ ሸገር ያነጋገራቸው ደራሲ ኩሪ አየለ በበኩላቸው መፀሀፍ ማሳተም አስቸጋሪ እየሆነብን መጥቷል ያሉ ሲሆን ይህ ችግር በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ነባር ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን ወደ ዘርፉ የሚመጡ ጀማሪ ደራሲያንንም ያሳጣናል ብለውናል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንባቢያን ቁጥር መቀነስ ደግሞ ሌላኛው ዘርፉን ወደኋላ የሚያስቀር ችግር ነው ይላሉ፡፡ ሸገር ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ፀሀፊያን እና ደራሲያን እንዳሉት መንግስት ከቀረጥ ነፃ ወረቀት እንዲገባ እና በህትመት ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በተጨማሪም ባለሀብቶች የህትመት ኢንዱስትሪው ላይ እና የወረቀት ማምረት ስራ ላይ ሊሳተፉ ይገባል ይላሉ፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ ደግሞ በደራሲያንም ሆነ በአንባቢያን ላይ የሚታየው ችግር ይስተካከላል ይላሉ፡፡ 📍መረጃው የፋሲካ ሙሉወርቅ( ሸገሬ ሬድዮ) ነው ቴሌግራም: @EventAddis1
1 7272Loading...
36
የሐሙስ መረጃዎች የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ! ሚዲያዎች መረጃውን ስትጠቀሙ ምንጭ ጥቀሱ 📍መጽሐፍ - የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም አንድ መጽሐፍ በአንድ ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ለህትመት ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። "ቡና እና ምልኪ" የተሰኘውና ከዓመት በፊት ለንባብ ይበቃል ተብሎ የዘገየው መጽሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፅ በሚደረግ ቅድም ክፍያ እንደሚታተም ገጣሚው አስታውቋል። ገጣሚው በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በሀርድ ኮፒ ያጌጠ ምልኪና ቡና ከቅዳሜ ጀምሮ 1000 ኮፒ ህትመት በ1000 ብር ብቻ እጃችሁና የመጻሕፍት ሼልፋችሁ ላይ ለማኖር ዝግጅት አድርጉ" ብሏል። -የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ "የጊዜ ሠሌዳ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን ዛሬ በሚካሄደው የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ በገጣሚዋ ተፈረሞ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል። ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል። -የገጣሚና የህግ ባለሞያው ደሱ ፍቅርኤል "እስከ መቅደስ " የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።ገጣሚ ደሱ ከዚህ ቀደም "ሀገሬን ሰቀሏት" እና "ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል። መጽሐፉን በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ታገናላችሁ ተብላችኋል። -የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል።ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። 📍ሙዚቃ -የድምጻዊት ሔዋን ገብረወልድ "ያንተን" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ  ለአድማጮች ይደርሳል። በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ ገጣሚ ምልእቲ ኪሮስ በግጥም ምረታብ ደስታ በዜማ ተሳትፈዋል።ሙዚቃ ቅንብርና ማስተሪንጉን ስማአገኘሁ ሳሙኤል ሰርቷል። -የድምጻዊት ሜላት ቀለመወርቅ "ዋይ" የተሰኘ ሙዚቃ ነገ አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።በዚህ የሙዚቃ ስራዋ ላይ በግጥምና ዜማ ምህረትአብ ደስታ ሲሳተፍ ቅንብር፣ሚክሲንግ፣እና ማስተሪጉን ደግሞ ሔኖክ ድለቃ ሰርቷል። -ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ "የኔ ትውልድ" በተሰኘ የአሜሪካ ጉዞ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያካሄድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። የሙዚቃ ዝግጅቱን በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታ ግዛትን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ እንደሚያቀርብ ገልጿል። ሮፍናና ከወራት በፊት ዘጠኝ በሚል ርዕስ "ሀራንቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል። 📍 ቴአትር -የ"እያዩ ፈንገስ" 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ  ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት  እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸው የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር።የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል። - "እሳት ወይ አበባ" ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ላይ የተመሰረተው "እሳት ወይ አበባ" ግጥማዊ ዳንስ ተውኔት በብሔራዊ ቴአትር ከሰኔ 14 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መድረክ እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።ይህ ሙከራዊ ተውኔት ባሳለፍነው ጥቅምት 2 2016 ዓ.ም ነበር ዘወትር አርብ ሲቀረብበት ከነበረው የአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የተሰናበተው። በምትኩም "የሁለት ጌቶች አሽከር" የተሰኘ ተውኔት ሲቀርብም ቆይቷል። 📍ኪነጥበብ ዝግጅት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል። አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሀሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዕለቱም አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ በክብር እንግድነት ትገኛላች ተብሏል። 📍የሥነጥበብ አውደርዕይ (ሥዕል) - የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል። -የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ ለእይታ ይበቃል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል። 📍ፊልም "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም በቅርቡ ለተመልካች ይቀርባል። በኪም ፊልምስ ተዘጋጅቶ በከአብ መልቲሚዲያ የቀረበው የያለው ደስታ (ራስ) "ጃንሞራ" የተሰኘ ፊልም ከሰኔ 21 ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በዚህ ሀገርኛ ፊልም ማርታ ጎይቶም፣ ነብዩ እንድሪስ ፣ እንግዳሰው ሀብቴ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል። አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ ቀን: ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ: https://eventaddis.com ቴሌግራም: @EventAddis1
1 75410Loading...
37
ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል ተከፈተ የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከዛሬ ሰኔ 5 እስከ የፊታችን 9 2016 ዓ.ም የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል። ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል። በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል። ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 7756Loading...
38
የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ተከፈተ አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
1 7685Loading...
39
የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ ከዛሬ ሰኔ 05 እስከ ፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የዘንድሮው አራተኛው የኢትዮጵያ ኤለክትሪሲቲ አውደርዕይ"ኃይል ቁጠባ፣ አረንጓዴ አፍሪካ"በሚል መሪ ቃል የሚከናውን ሲሆን በዚህ አውደርዕይ ላይ አምራቾች ምርቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን ይዘው ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
10Loading...
40
እያዩ ፈንገስ ተውኔት አይቀርብም ተባለ የእያዩ ፈንገስ 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ነገ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 በራስ ሆቴል ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በነገው እለት እንደማይቀርብ አዘጋጆቹ ስለማሳወቃቸው ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል። የተወኔቱ አዘጋጆች ወደፊት ተለዋጭ ፕሮግራም ሲኖር ለተመልካቹ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ገልፀዋል። በተጨማሪም "ለ10ኛ ዓመት በዓላችን መልካሙን ሁሉ ለተመኛችሁልንና በጠመዝማዛው መንገዳችን አብራችሁን ለነበራችሁ ወገኖቻችን ምስጋናችን ወሰን የለውም" በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት "አጀንዳዬ"  "ፌስታሌ" እና በቅርቡ ከመድረክ በታገደው "ቧልቲካ" በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ መድረኮች ለታደሚያን ሲቀረብ ቆይቷል። ዘወትር ሐሙስ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የነበረው የእያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ባሳለፍነው ጥር 2 2016 ዓ.ም ለህዝብ እንዳይታይ እንደተከለከለ ይታወሳል። 📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ ! ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
2 05117Loading...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአርአያ ሰው ሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት"የአርአያ ሰው ሽልማት" በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ተቋሙ የሚያዘጋጀው አርአያ ሰው ሽልማት ባለፉት ስድስት ዓመታት ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አጋርነት፣ ድጋፍና ዕውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮም ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የአርዓያ ሰው የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን  የቀጥታ ስርጭት  ሽፋን ያገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Показать все...