cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Event Addis/ሁነት አዲስ

https://eventaddis.com ለአስተያየትና ማስታወቂያ: @Tmanaye

Больше
Рекламные посты
7 056
Подписчики
+3824 часа
+1227 дней
+57030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ መጽሐፍ ለንባብ በቃ የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 10 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደቀረበ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፉ ነው ተብሏል። መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። መጽሐፉን በጃፋር ፣በእነሆ እና በእውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች ላይ ይገኛል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አርቲስት መስከረም አበራ የክብር እንግዳ የሆነችበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር  ረቡዕ ሰኔ 12  2016 ዓ.ም ይካሄዳል። በዕለቱ አርቲስት መስከረም አበራ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ትገኛለች። እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ። ማስታወሻ :ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘው አልበም ባንድ ካምፕ ዴይሊ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ከሙዚቃዊ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ባሳለፍነው ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል እንደተለቀቀ ይታወሳል። በሙዚቃ ሞያ ውስጥ ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ በመሆን ከ17 ዓመታት በላይ ያሳለፈው ሙዚቀኛ  ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘የላቁት ደጋጎች’ አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያወጣው አልበም ነው፡፡ የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም  ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ተመርቋል። በ1999 ዓ.ም ጆርጋ ከጓደኞቹ ጋር በመሰባሰብ የቀረጸው ይህ አልበም የጆርጋ መንፈስን ያንጸባርቃል ተብሏል። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 የተመሰረተውና ዋና መስሪያ ቤቱን አሜሪካ ካሊፎርንያ ያደረገው ባንድ ካምፕ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ አስታውቋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የተዘጋጀው የሥነጽሑፍ ሥልጠና በሚመጣው የክረምት ወቅት ይካሄዳል በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በየዓመቱ የሚዘጋጀው የክረምት የሥነጽሑፍ ስልጠና ዘንድም ለዘጠኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል። ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስምንት ዙሮች በርካታ የሥነጽሑፍ ወዳጆች ስልጠናውን እንደወሰዱ ተነግሯል። በልቦለድ ክሂል ፣በልቦለድና ኢ ልቦለድ፣ በግጥም ፣ በፎክሎር ፣ በሥነጽሑፋዊ ታሪክ ፣በሥነሂስ በሌሎችም የሥነጽሑፍ ዓይነቶች ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ምዝገባ እንደተጀመረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ለበለጠ መረጃ በተከታዩ ስልክ ቁጥር ደውሉ  0911448297 ተብላችኋል። 📍ሼር ያደርጉ: ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ዕውቅና ተሰጠው ቴክሳስ ዳላስ የሚገኘው አድዋ የታሪክና የባህል  ህብረት  በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት በግለ ታሪክ ዘርፍ ጋዜጠኛ  ዕዝራ እጅጉን ልዩ ተመስጋኝ አድርጎታል። ጋዜጠኛ ዕዝራ፣ ጸሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድን የመሠሉ የሀገር ባለውለታዎችን የህይወት ታሪክ በሲዲና በዲቪዲ ያሳተመ ሲሆን ይሄንኑ ታሪክ በእንግሊዝኛ  አዘጋጅቶታል። በተጨማሪም ከ20ዐ9 አንስቶ ባለፉት 7 ዓመታት የ45 ሠዎችን ታሪክ በሲዲ ሠርቶ  ለማስመቅ ችሏል። በተጨማሪም በአገራችን  ታዋቂ የሆኑ እንደ ማማ በሰማይ ፤ ማህሌት፣ የአክሊሉ ማስታወሻ፤ የመሳሰሉት 30 የሚጠጉ መጽሀፎችን ወደ ድምጽ በመቀየር ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች እዝራ እና ድርጅቱ "ተወዳጅ ሚዲያ" መላ ዘይደዋል። በተጨማሪም የታዋቂ ኢትዮጵያን ታሪክ በባለታሪኮች እና በልጆቻቸው አሰሪነት ተጠይቆ 14 መጽሀፎችን አዘጋጅቷል፡፡ እዝራ ታሪክን የሚሰንድበት "ተወዳጅ ሚዲያ" የተሰኘ የራሱ ድረገጽ፤ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ያለው ሲሆን ወደ ፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ በአንድ ገጽ ብቻ ታሪካቸውን ጽፈው እንዲልኩ እየጣረ እንደሚገኝ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል። በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት 16 የሚሆኑ ተሸላሚዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የቱሪዝም አባት አቶ ኃብተስላሴ ታፈሰ ፣አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ፣ጸሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ዶክተር  እንዳለጌታ ከበደ እና ሌሎችም  ይገኙበታል ተብሏል። የአርአያ ሠው ሽልማት ሰኔ 13 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ የሽልማት ሥነሥርዓት ይከናወናል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ዮቶር_ድግስ የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል። በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ከድምጻዊያኑ በተጨማሪም ኢትዮ ለዛ ባንድ፣ ሻኩራ ባንድ፣ ብርኩማ ባንድ የተሰኙ ባንዶች ድምጻዊያንን ያጅባሉ ተብሏል። በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። አለማየሁ ደመቀ ከ1991 ዓ.ም አንስቶ ከ250 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1 : ኮብላዩ ካሕን” እና በቅርቡ ለንባብ የበቃውን “ዮቶር 2 ” ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ያበረከተ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት በሙያው፣ በክህሎቱ እና በተሰጥዖው አገር እና ወገንን ሲያገለግል እንደቆየ ይታወሳል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ተመረጠ፡፡ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዜናዎቹ የምናዉቀውና በያዝነው አመት መጀመሪያ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥንን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ "የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ እንደተመረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" መቀመጫውን በህንድ ሙምባይ ከተማ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። የጋዜጠኞችን ሙያዊ ክህሎት እና ቤተሰቦቻቸውን  ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጠኞችን "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በሚል ስያሜ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ለማስተባበር እየሰራ ያለ ተቋም ነው። ዋና ዋና አምስት መርሆችን አሉኝ የሚለው ድርጅቱ ጋዜጠኝነትን ማስፋፋት እና የጋዜጠኞችን አኗኗር ማሻሻል ላይ አልሞ የሚሰራ ነው፡፡  ኢቨንት አዲስ ከጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን ባገኘው መረጃ  "ድርጅቱ በዋናነት የጋዜጠኞችን የመኖሪያ ቤት፣ የጤና፣ የጋዜጠኛ ልጆችን በትምህርት መደገፍን ጨምሮ የጋዜጠኞችን ክህሎት እና የድህረ ጡረታ ፈተናዎች ላይ ትኩረቱ አድርጎ ይሰራል፡፡" "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በኢትዮጵያ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰንን በበጎ ፍቃደኛ ተወካይነት ሲመርጥ ፤ በዋናነት ለዚሁ ስራ በጎ ፈቃደኛ እና ተነሳሽነት ያላቸውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችንም የሚያካትት መሆኑንም ሰምተናል፡፡ ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል። ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች! በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው። ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። #Ads ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ ታናሽ ወንድም የሆነው ድምጻዊ ኤርሚያስ ሞላ አዲስ የቅብብል ነጠላ ሙዚቃውን አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ለአድማጮች አድርሷል። ሙዚቃው በኤርምያስ ሞላ እና የኢትዮጵያን አይዶል ምርጥ አምስት ተወዳዳሪ በነበረችው በእርገት ሰለሞን(ናኒ) በቅብብል የተሰራ ነው። "እስከወዲያኛው " የሚል ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃው በዳዊት ተስፋዬ (ደጃፍ ፖድካስት) ግጥሙ ተጽፎለታል። የሙዚቃው ዜማ እና ቅንብሩ በራሱ በኤርሚያስ ሞላ ተሰርቷል። ከጀርባ በርካታ ሰዎች ተሳትፈውበታል። የሙዚቃ ቪድዮውን በኤርምያስ ሞላ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ ተብላችኋል። ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
Показать все...