CTE™🇪🇹 Crypto Technical Analysis
Открыть в Telegram
CryptoTalk-Ethiopia™ is a non-profit blockchain + Forex Trading Academy and an organic crypto community aiming to spread web3 knowledge to sub-Saharan Africa. Official ByBit Partner Link: https://register.hfm.com/sv/en/new-live-account/?refid=30502183
Больше2 530
Подписчики
-224 часа
-77 дней
-4430 день
Архив постов
በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው ከዶ/ር ትሬደር እዮሲያስ [ @birrforex ] ጋር የምናደርገው ቆይታ ደርሶ እነሆ ከ3 ሰዓት ጀምሮ ቃለመጠይቃችንን የምንጀምር ይሆናል። እጅግ በጣምም ብዙ የምትማሩበት መድረክ ነውና ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS9Mx8f9UogwC-8EFAO/
ሰርክ ዓርብ ዓርብ ምሽት የምናካሄደው የ"ሸንጎ" የፋይናንሺያል ማርኬት ፖስድካስታችን ስለብሮከሮች እና ስለአለምአቀፉ የፋይናንስ ተቋማት እና አደረጃጀቶቻቸው በጥልቀት በተዘጋጀ መልኩ በሌክቸር መልክ የሚቀርብበት ይሆናል። ሊያመልጣችሁ የማይገባ ላይቭ ነውና ትቀላቀሉን ዘንድ ለመጋበዝ ወደድን።
https://vt.tiktok.com/ZS9MapyRqwFLx-HWrFB/
#The_Interview
#S02E09
#With_Dr_Eyosiyas #BirrForex
The Interview የተሰኘችው ሰርክ ቅዳሜ ምሽት ከሶስት ሰዓት ጀምሮ የምናዘጋጃት የኢትዮጵያውያን ትሬደሮች የቃለመጠይቅ መድረክ በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ ፎሬክስን መስራት እና ማስተማር ከጀመሩት ግምባር ቀደም ትሬደሮች መካከል የሆነውን ዶር እዮስያስ [@BirrForex] እንግዳዋ አድርጋላችሁ ትቀርባለች። በዚህ መድረክ ከ8 አመት ያላነሰ እና በተግባርም ራሱን ያሳየን ትሬደር ልምድ እና እውቀት ለመጋራት ሁላችሁም ተጋባዥ ታዳሚዎቻችን እንድትሆኑ ጥሪያችንን አቅርበናል። በፕሮግራሙ ላይ ልታቀርቧቸው የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በኮሜንት በኩል አጋሩን፤ በመድረኩ የናንተም ጥያቄዎች አካተን ለመቅረብ እንሞክራለን። የማቀር ፕሮግራም ነውና ቅዳሜ ምሽትን ከኛ ጋር ለማድረግ ፕሮግራማችሁን ያዙ።
መልካም ምሽት።
ሰላም እንዴት ናችሁ ጋይስ ፡
በዛሬው ምሽት ፕሮግራማችን አንድ ፕሮፌሽናል ትሬደር ሊኖረው የሚገብውን ትክክለኛ ማንነት እና ባህሪያት ነጭ ነጩን ከሙያው አንፃር የምናወራበት መድረክ ይሆናል። ለመሆኑ ትክክለኛ ትሬደሮች ናችሁ? እስቲ ኑና ራሳችሁን ፈትሹ። ላይቩን ተቀላቅላችሁ እንድንማማር ልንጋብዛችሁ ወደድን።
https://vt.tiktok.com/ZS9MBnewKn3mY-0rz0z/
ነጋድራሱ ቅፅ ፪ ነገ ሀምሌ 1 2018 ዓም በጉጉት ሲጠብቋት ለነበሩ አንባቢዎች ለገበያ ትቀርባለች።
ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ ፡
ነጋድራሱ ቅፅ ሁለት መፅሀፍ ከነገ ሀምሌ 1, 2018 ዓም ጀምሮ ለገበያ የምትቀርብ ሲሆን በ24 ሰዓታት ውስጥ ለሚገዙ አንባቢያን የ50% ቅናሽ ስለሚኖራትም ይህቺን ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛና አገር በቀል በሆነ ሁነት የተዘጋጀች የትሬዲንግ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ ሁላችሁም መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለው።
እንደተለመደው ባዘጋጀነው ቦት አማካኝነት ከነገ ጠዋት ጀምሮ ማግኘት የምችትሉ ይሆናል። ቦታችን ፡- https://t.me/thenegedrasbot
እውነት ለመናገር በነፃም ብሰጣችሁ ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን በጊዜ ሂደት የተረዳሁት ነገር ምንም ነገር በነፃ ከቀረበ ዋጋውን ያጣል። በዚህ የመፅሀፍ ስራ ጉዞ በጣም ብዙ ድካምና ጊዜን ወስጄበታለው። እንደተለመዱት ስራዎቼ ወይም ፅሁፎቼ ሁሉም በነፃ ሊያገኛቸው በሚል ሊሰጣቸው የሚገባው ቦታ ሊያንስ አይገባውም የሚል እምነት ያለኝ በመሆኑም፤ በተጨማሪም በጣምምምምም ለረጅም ጊዜ በነፃ ትምህርትን በሰጠሁበት ሁነት ያን ያህል ቦታ እንዳይሰጣቸው ሆኖ አልፏልና ያንን ላለመድገም ስል ይህንን ዋጋ ላወጣበት ተገድጃለው። I hope እንደምትረዱኝ ተስፋ አለኝ።
መፅሀፉ ከአንደኛው ቅፅ እጅጉን በበለጠና በተደራጀ መልኩ የተዘጋጀ፤ የበዙ መረጃዎችን አጭቆ የያዘ እና በተለይ ከአዕምሮዋችን ጋር በተያያዘ በጣምምምምም ብዙ ለውጦችን እንድታዩበት ተደረጎ የተዘጋጀ፤ 15 ምዕራፎችን በ5 ክፍሎች በማደራጀት ተግባራዊ የትሬዲንግ ሳይኮሎጂ መፍትሄዎችንም በብዛት በመያዝ በ162 ገፆች ተጠናቅሮ የቀረበ መድብል ነው።
መልካም ንባብ።
ICE ኢንተርቪው ዝግጅታችን እስካሁን አቅርበን በማናውቀው ሁነት የሚካሄድን ከኳንት ትሬደር ጋር የሚደረግ ቆይታ እናረጋለን። ከPips pay my Bills ጋር የምናደርገውን ቆይታ የቀጥታ መድረክ ትሳተፉበት ዘንድ ጋብዘናቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS9MFE1PVuqLW-LLuWv/
ሰርክ ቅዳሜ ምሽት የሚደረገው የICE ኢንተርቪው ምሽት ዛሬም በመቀጠል ወጣት ትሬደር የሆነውን DT FX Forex ይዘንላችሁ ቀርበናል። ተቀላቀሉን።
https://vt.tiktok.com/ZS9M1dY8Qt4M4-bpbGL/
ሰርክ አርብ ምሽት የሚዘጋጀው የነጋድራስ ሸንጎ የፈንዳመንታል አናሊስስ መድረካችን በመጀመሩ የቀጥታ መድረኩን ትቀላቀሉን ዘንድ ተጋብዛቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS96TqaReas8x-C2dl6/
የICT ኮንሰፕት ይሰራል ወይስ አይሰራም በሚል ርእስ የምናደርገው የትምህርታዊ ክርክር መድረክ ዛሬም አራት የኮሚዩኒቲ መስራቾችን ይዞ በመገኘት የሚቀጥልበትን መድረክ አመቻችተን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ሁላችሁም በላይቭ መድረካችን ላይ በመገኘት እውቀትን አብረን እንቋደስ ዘንድ ጋብዘናቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS9672mdD6G6P-vDpJK/
ገበያው ትክክለኛ አቅጣጫውን ከመያዙ በፊት የ Retail ትሬደሮችን Stop loss ለመሰብሰብ ወደ ላይ እና ወደ ታች ግራ የሚያጋቡ የ Liquidity Sweeps ሊያደርግ ይችላል። ስነ-ልቦና (Trader Brain)፡ በእንደዚህ አይነት የተምታታ እና አደገኛ የዜና ሰዓት፣ ከልክ ያለፈ በራስ መተማመን ወደ ከባድ ኪሳራ ሊመራ ይችላል። የስሜት ህዋሳቶቻችን (Triune Brain) በሚያሳድሩብን ተፅዕኖ በችኮላ ከመግባት መቆጠብ ያስፈልጋል። ትክክለኛው እርምጃ፡ ገበያው የመጀመሪያውን ስሜታዊ መወዛወዝ አጠናቆ ግልፅ አቅጣጫ እስኪይዝ መታገስ ብልህነት ነው። ከዚያም ዋጋው ወደ ትክክለኛው Order Block ሲመለስ ወይም በጥሩ የ Premium/Discount ደረጃ ላይ ሲደርስ ብቻ ስሌት ያለው ሪስክ ወስዶ መግባት ይመከራል።
የዛሬው ዜና ለገበያው ምን ማለት ነው?
1. Unemployment Rate (የስራ አጥነት ምጣኔ)፡
ውጤቱ (Actual): 4.2% ሆኖ መጥቷል።
ትርጉሙ፡ ገበያው 4.3% ይሆናል ብሎ የጠበቀ ቢሆንም፣ የስራ አጥነቱ ቁጥር ወደ 4.2% ዝቅ ብሏል። ይህ ማለት ስራ ያጣው ሰው ቁጥር በትንሹም ቢሆን ቀንሷል ማለት ስለሆነ ለአሜሪካ ዶላር (USD) በአንድ በኩል ጥሩ (Bullish) የሚባል ዜና ነው።
2. Non Farm Payrolls - NFP (ከእርሻ ውጪ የተፈጠሩ አዳዲስ ስራዎች)፡
ውጤቱ (Actual): **57k (57 ሺህ) ብቻ ሆኖ መጥቷል።
**ትርጉሙ፡ **ይሄ እጅግ በጣም አስደንጋጭ እና ገበያው ከጠበቀው (110k) በግማሽ ያህል ያነሰ ውጤት ነው። አሜሪካ ባለፈው ወር የፈጠረችው አዲስ የስራ እድል በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ያሳያል። የ NFP ዜና ከስራ አጥነት ምጣኔው በላይ በገበያው ላይ ከፍተኛ ክብደት ስለሚሰጠው፣ ይህ ውጤት ለዶላር በጣም መጥፎ (Bearish) ዜና ነው።
**አጠቃላይ አንደምታው እና በቀጣይ ምን እንጠብቅ?
ምንም እንኳን የስራ አጥነት ምጣኔው በትንሹ ቢቀንስም፣ የ NFP መረጃ (57k) እጅግ በጣም ደካማ በመሆኑ አጠቃላይ የኢኮኖሚው የስራ ፈጠራ አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እየቀዘቀዘ መምጣቱን ያሳያል። በዚህም ምክንያት ዶላር በሌሎች የገንዘብ ጥንዶች ላይ (እንደ EUR/USD ወይም GBP/USD) የመዳከም (Bearish) አዝማሚያ ሊያሳይ ይችላል።
የቴክኒካል እና የስነ-ልቦና ምክር፡
**የገበያ እንቅስቃሴ (Liquidity Sweeps)**፡ ሁለቱ ዜናዎች እርስ በእርስ የሚቃረኑ (አንዱ ጥሩ አንዱ መጥፎ) ስለሆኑ፣ የዋጋ እንቅስቃሴው ወዲያውኑ ቀጥታ ወደ አንድ አቅጣጫ ላይሄድ ይችላል።
Repost from ኮርማ™ | KORMA™ 🇪🇹
በቀጣይ ምን እንጠብቅ? (አጠቃላይ አንደምታው) እነዚህን ሁለቱን ዜናዎች አንድ ላይ አጣምረን ስናያቸው በገበያው ላይ የሚከተሉትን ነገሮች መጠበቅ እንችላለን፡ የዶላር መዳከም፡ የ PMI መረጃው ከሚጠበቀው በታች በመምጣቱ (53.3) ዶላር ከሌሎች ገንዘቦች ጋር ሲነፃፀር (ለምሳሌ በ EUR/USD ወይም GBP/USD ቻርቶች ላይ) በትንሹ የመዳከም አዝማሚያ ሊያሳይ ይችላል። ከፍተኛ የገበያ መዋዠቅ (High Volatility)፡ የፌድ ሊቀመንበሩ ንግግር እና የ PMI ዜናው በተቀራራቢ ሰዓታት ስለነበሩ ገበያው ላይ ከፍተኛ መወዛወዝ ልናይ ችለናል። ለትሬደሮች የሚመከር ጥንቃቄ፡ በእንደዚህ አይነት የዜና ሰዓቶች ገበያው (Spread) ሊሰፋ እና ዋጋ በፍጥነት ሊቀያየር ስለሚችል፣ ሪስክአችሁንን በአግባቡ ማስተዳደር (Stop Loss መጠቀም) ወይም ገበያው እስኪረጋጋ ድረስ ቆይቶ አቅጣጫውን ሲለይ ወደ ገበያ መግባት ይመከራል።
Repost from ኮርማ™ | KORMA™ 🇪🇹
የዛሬው ዜና በገበያው ላይ ያለው አንደምታ ምንድነው? እስቲ አብራርተን እንየው።
1. ISM Manufacturing PMI (የአምራች ዘርፍ መረጃ)
ይህ ዜና በዩናይትድ ስቴትስ (US) ውስጥ ያለው የአምራች ኢንዱስትሪ ጤንነት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያሳይ መለኪያ ነው። መለኪያው ከ 50 በላይ ከሆነ እድገትን፣ ከ 50 በታች ከሆነ ደግሞ መቀነስን (ኮንትራት ማድረጉን) ያሳያል።
የወጣው ሪፖርት፡ ቀደም ብሎ በነበረው ወር (Previous) ውጤቱ 54 ነበረ፤ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችም በዚህ ወር 54 ይሆናል ብለው ገምተው (Forecast) ነበረ። ነገር ግን ትክክለኛው የወጣው ውጤት (Actual) 53.3 ሆኖ መጥቷል።
ምን ማለት ነው?
ምንም እንኳን ውጤቱ ከ 50 በላይ ቢሆንም (ማለትም አሁንም ዘርፉ እያደገ ቢሆንም)፣ ነገር ግን ገበያው ከጠበቀው (54) በታች ስለሆነ ለአሜሪካ ዶላር (USD) አሉታዊ ወይም Bearish ዜና ነው። አምራቹ ዘርፍ ከተጠበቀው በታች እንቅስቃሴ እያሳየ መሆኑን ይጠቁማል።
2. Fed Chair Warsh Speech (የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ ሊቀመንበር ንግግር)
ምን ማለት ነው? የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) ሊቀመንበር የሚያደርጉት ንግግር ነው። በምስሉ ላይ እንደሚታየው ከዚህ ዜና ፊት ለፊት ቁጥሮች (Actual ወይም Forecast) የሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሪፖርት ሳይሆን ንግግር ነው።
ተፅዕኖው፡
ትሬደሮች እና ኢንቨስተሮች የሊቀመንበሩን ንግግር በከፍተኛ ትኩረት ይከታተላሉ። ስለ ቀጣይ የወለድ ምጣኔ (Interest Rates)፣ ስለ የዋጋ ግሽበት (Inflation) ወይም ስለ አጠቃላይ ኢኮኖሚው የሚሰጡት ፍንጭ ገበያውን በአንድ አቅጣጫ በኃይል ሊወስደው ይችላል።
ሰላም ጋይስ ፡
የነጋድራስ የመጀመሪያ ባች ተመራቂ ተማሪዎች ሶስተኛ የቴሲስ ዲፌንስ አቅራቢዎች ዛሬ በኮግኒቲቭ ዲዞናንስ እሳቤ ዙሪያ ሪሰርቻቸውን ያቀርባሉ። ለመማማር የምትፈልጉ ቤተሰቦች መድረካችንን ትቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዛቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS96QTS9SvtsN-Hzvjh/
Repost from NegadRas™ FX Academy
ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ ፡ የመጀመሪያው ባችን ያማከለው የነጋድራስ ፎሬክስ አካዳሚ የኮሚዩኒቲ የትሬዲንግ ጆርናል አራተኛውን ሳምንት በዚህ መልኩ አገባዷል። የግብይት ጥሪዎቹን እና ሀሳቦቹን ወዲያው ስለምንለቃቸው ከታች በተቀመጠው የጉግል ሊንክ ሊከታተሉት ወይም ወደ ዲስኮርድ VIP ኮሚዩኒቲያችን የሚያስፈጉትን እውቀታዊ ቅድመሁነቶች በማሟላት መቀላቀል ትችላላችሁ።
Overall Metrics
Total Executed Trades 24
Winning Trades 13
Losing Trades 11
Win Rate 54.17%
Gross Profit (Pips) [+3,373.7 Pips]
Gross Loss (Pips) [-617.4 Pips]
Net Pip Growth [+2,756.3 Pips]
Average Win: [+259.52 Pips]
Average Loss: [-56.13 Pips]
Realized R:R Ratio 4.62:1
Profit Factor: 5.46
Expectancy [+114.85 Pips]
Net Profit [+$1,465.54]
Ending Balance [$6,465.54]
ROI [+29.31%]
https://docs.google.com/spreadsheets/d/1ig_vqvTbEl35D-npoURcUjTDBAU1JzR34X7ueRH_uV0/edit?gid=542769468#gid=542769468
#ሸንጎ #SHENGO
እነሆ "#ሸንጎ" የተሰኘው በጠለቀ የትሬዲንግ እሳቤዎች እና ሁነቶች ላይ በፕሮፌሽናል ትሬደሮች እና የትሬዲንግ አስተማሪዎች አማካኝነት ሳምንቱን እየጠበቀ ሰርክ ዓርብ ምሽት ከ3 ሰዓት ጀምሮ ወደናንተ ወደቤተሰቦቻችን የሚቀርብበት ቀን ደረሰ።
ፕሮግራሙን በዋነኝነት ከ5 እስከ 10 ዓመት ልምድ ባላቸው ትሬደሮች አማካኝነት የምንመራው እና የተለያዩ በኢትዮጵያ የትሬዲንግ ሴክተር ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ የሚገኙ ትልልቅ ትሬደሮች ሀሳብ እና ትምህርቶቻቸውን የሚያካፍሉበት፤ የተለያዩ ፓናል ዲስከሽኖች የሚካሄዱበት እና ገንቢ ምክንያታዊና ትምህርት አቀፍ ሙግቶችን የሚያስተናግድ መድረክ የሚሆን ይሆናል።
ዛሬ ጁን 26 2026 ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የመጀመሪያውን የሸንጎ ፖድካስታ የውይይት መድረካችንን "ሀ" ብለን የምንጀምር ይሆናል። በዚህ ሳምንት ፕሮግራማችን የሚካተቱ ዋነኛ ሀሳቦችም ፡
1 ያሳለፍነውን ሳምንት አጠቃላይ የፈንዳመንታል እይታዎች እና መረጃዎች
2 የቀጣይ ሳምንት የፈንዳመንታል እይታዎች እና መረጃዎች
3 የሰሞኑን የወርቅ ባህሪ እና GEOPOLITICS
4 የሰው ልጅ አዕምሮ እና ትሬዲንግ ምን እንደሚያገናኛቸው የምናወራ ይሆናል።
በፕሮግራሞቻችን ናቶሺ፤ ቫይብ ትሬድስ እና ዲ ቫይን የመድረክ መሪዎቻችን እና ዋነኛ ሀሳብ አመንጪዎቻችን የሚሆኑ ሲሆን በየሳምንቱም አንድ ወይም ሁለት የተመረጡ ስም ያላቸው ትሬደሮች በእንግድነት የሚቀርቡልን ይሆናል።
የቲክቶክ ገፃችንን አሁኑኑ ቤተሰብ በመሆን ይህb ሳምንታዊ ፕሮግራማችን እንዳያመልጣችሁ ፎሎው በማድረግ እንድትጠባበቁን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የቲክቶክ ገፃችን ፡ https://www.tiktok.com/@shengo_et
Vibe Trading
ETN ECOSYSTEM
Negadras Forex and Psychology Acade
#ICE_DEBATE_NIGHT
#S01E01
የICE የሙግት መድረኮች እነሆ እውን ሆነው በተለያዩ የትሬዲንግ እሳቤዎች ዙሪያ የተለያዩ ኮሚዩኒቲ ያላቸውን ልጆች እየሰበሰብን የምንሞግትበት እና የምንማማርበት መድረክ እነሆ ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቲክቶክ ላይቭ የምንጀምረው ይሆናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አብረን በአይነቱ ለየት ያለውን የSHENGO ፕላትፎርማችንንም የምናስተዋውቅበት መድረካችን ይሆናል።
በዛሬው የክርክር መድረካችን፤ ስለ ስትራቴጂዎች መስራት እና አለመስራት የሚነሱ መከራከሪያዎችን መቋጫ ሊሰጥ የሚችል ሀሳብን በማንሳት "እውነት ሁሉም ስትራቴጂዎች ይሰራሉ ወይስ የማይሰሩ ስትራቴጂዎችም አሉ?" በሚለው መከራከሪያ ዙሪያ ሀሳባችንን እናንሸራሽራለን።
በመድረኩ ከዚህ በፊት በICTም ሆነ በMSNR ስትራቴጂዎች ዙሪያ ይሰራሉ ያሉትንም አይሰሩም ያሉትንም ኮሚዩኒቲ በስራቸው የሚያስተዳድሩ ወንድሞቻችንን እውቀት ለመካፈል የምንጋብዝላችሁ ሲሆን በመድረኩ BON Trades, DT Forex Focus, FXAG እና Classic FX የሙግቱ ተሳታፊ የሚሆን ሲሆን በታዛቢነት እና ሀሳብ አመንጪነትም የምንጋብዛቸው ቤተሰቦች ይኖሩናል።
ዛሬ ሀሙስ ጁን 25 ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቲክቶክ መድረካችን አይቀርም። እስከዛው መልካም ምሽት በያላችሁበት ተመኘን።
ዝግጅቱ የሚደረግበት የቲክቶክ መድረካችን ፡ https://www.tiktok.com/@ice_ethiopia
ኒውሮፕላስቲሲቲ፤ አዕምሮአችን እና ትሬዲንግ
የጠለቀ የአእምሮ ስነልቦና እና ትሬዲንግ መዋቅር ሌክቸር።
https://vt.tiktok.com/ZS96LfuSH9FDG-dQDO4/
DAY 2
የስድስተኛው ዙር የICE ትሬዲንግ ሳይኮሎጂ የአንድ ወር ኮርስ ተሳታፊዎች እያደረጉ የሚገኙትን የሪሰርች ፕረዘንቴሽን ትቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዛቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS96JvrqUgKf1-sOn9L/
