ru
Feedback
Assaye Derbie

Assaye Derbie

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Assaye Derbie

Канал Assaye Derbie (@asayede) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 14 207 подписчиков, занимая 2 672 место в категории Блоги и 2 385 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 14 207 подписчиков.

Согласно последним данным от 13 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -181, а за последние 24 часа — -13, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 35.61%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 12.54% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 5 062 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 783 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 25.

📝 Описание и контентная политика

Описание канала не предоставлено.

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 14 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Блоги.

14 207
Подписчики
-1324 часа
-467 дней
-18130 день
Архив постов
ለፋኖዎች‼️ አሳዬ ደርቤ ▬▬▬▬ ➔ፋኖን የመከፋፈልና የማጥፋት ዓላማ አንግበው የሚመጡ ሃይሎችን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ባግባቡ የማታውቋቸውን ወጣቶች አባሎቻችሁ አታድርጉ፤ ➔ባንዳንድ ጉዳዮችና ችግሮች ዙሪያ ማብራሪያ ከሚሰጡ ቃለ አቀባዮች ውጭ በእናንተ ሥም ሚዲያ ላይ እየቀረበ ሕዝብንም ሆነ ፋኖን የማይጠቅም ንግግር የሚያደርግ አካል እንዲኖር አትፍቀዱ፤ ➔በሳምንት ውስጥ የተወሰኑ ቀናትን በመምረጥ እያንዳንዱን የአማራ ወጣት የሚያሳትፍ የአካል ብቃት እና የፋኖነት የሥልጠና መርሐ ግብር አዘጋጁ፤ ➔የትግል መርሓችሁ አንዱ ዞን ሲጠቃ ሌላ ዞን ላይ ተቀምጦ የወረራ ወረፋ መጠበቅ ሳይሆን ጥቃት በተከሰተበት ስፍራ ሁሉ ፈጥኖ መገኘት እንዲሆን በክልል ደረጃ የሚያስተሳስር አደረጃጀት መሥርቱ፤ ➔በመሀከላችሁ ሽኩቻ እንዳይነግስ የእናንተ እውቅና በሌለው እክል እርዳታ የሚጠይቅ የፋኖ አባል እንዲኖር አትፍቀዱ፤ ➔ከጥቃት የምትጠብቁት ወገን እንጂ ሥጋት የምትፈጥሩበት አካል አይኑር፥ ➔እያንዳንዱ ተግባራችሁ ከካሜራ የራቀ ይሁን፤ ➔በሰነድ የሚወጣውን የመንግሥት ዛቻ እና በፌስቡክ የሚሰራጨውን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ስትመክቱ ሥልጠናው እንዳይረሳ... ብዛታችሁን ከሥማችሁ ጋር ለማመጣጠን ሞክሩ፤

ከሕዝብ ጉያ ሳታወጣ- ሰለባህን አትቅጣ‼️ አሳዬ ደርቤ ▬▬▬ የትኛውም የብአዴን አመራር ከሥልጣን ሊነሳ የሚችለው አንድም የመንግሥትን አካሄድ ሲቃወም፣ አንድም የሕዝብን በደል ተጋርቶ ሲያልጎመጉም የተገኘ ቀን ነው፡፡ አለቀ፡፡ በተረፈ ለሥርዓቱ ታማኝ መሆኑን እስካረጋገጠና የሕዝብን ጉዳይ ‹‹ምን አገባኝ›› በሚል ስሜት ማለፍ እስከቻለ ድረስ በስነ ምግባር ጉድለትም ሆነ በኪራይ ሰብሳቢነት ጎዳና ውስጥ ተዘፍቆ ቢገኝ የሚያባርረው ቀርቶ የሚገመግመው አይኖርም፡፡ እንደውም የተሻለ ሥልጣን ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር ከዓመታት በፊት አቶ ዘርዓይ አሰገዶምን እና አባይ ወልዱን ተጋፍጠው የህውሓት ውድቀት ላይ ጉልህ ሚና የተጫወቱት አቶ ገዱና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዛሬ ከሥልጣን የተገፉት በሆነ መድረክ ላይ የሕዝብን ሕመም የሚጋራ ንግግር አድርገው ካልሆነ በቀር ‹‹የአማራን ሕዝብ ባግባቡ እያገለገላችሁ አይደለም›› ተብለው አይመስለኝም፡፡ ያመኑበትን እውነታ ያለምንም ማቅማማት በመናገር እና ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል የሚታወቁት አቶ ጸጋ አራጌና አቶ ዮሐንስም ተመሳሳይ እጣ ያጋጠማቸው ‹‹ለዙፋኔ እስከታመኑ ድረስ ቢሞስኑ ምን አገባችሁ›› ተብለው ካልሆነ በቀር በሥልጣናቸው ሲባልጉ ተገኝተው አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን… በብልሹ ሥርዓት ውስጥ የሹመት እድገት የሚያገኙ አመራሮች መባረር ቀርቶ መታሰር የሚገባቸው ሲሆኑ የሚባረሩት ደግሞ የተሻሉት መሆናቸው እርግጥ ነው፡፡ በዚህም መሠረት አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ አቶ ጸጋ አራጌን እና አቶ ንጉሡን ከሥልጣናቸው ያነሳው አካል በቅርቡ ደግሞ ጠባቂዎቻቸውን ማንሳቱን እየሰማን ነው፡፡ ከሕዝብ የሚነጥል ጥፋት ቢያገኝባቸው ኖሮ ዶክመንታሪ ሠርቶ ከማሰራጨት ወደኋላ የማይለው መንግሥት የፈጸሙት ጥፋት ከሕዝብ የሚቀላቅል መስሎ ስለታየው ከወንበርም አልፎ ወደ መቃብር ሊያወርዳቸው ድምጹን አጥፍቶ እየተሳበ ነው፡፡ ሆኖም ግን የማካቬሌ አስተምህሮ ‹‹ከሕዝብ ጉያ ሳታወጣ- ተቀናቃኝህን አትቅጣ›› የሚል ምክር የሚሰጥ በመሆኑ… ይሄን ተልዕኮ የወሰዱ ተላላኪዎችም እኒህ አመራሮች ከመንግሥት ጥርስ ውስጥ ባስገባቸው ጥፋት ፈንታ በሥልጣን ዘመናቸው የፈጸሙትንና በሕዝብ የሚታወቀውን ስህተት መንቀስ ጀምረዋል፡፡ እኔ ግን እልኻለሁ… እንዲህ ያለው መንቻካ ክስ በትናንት ጥፋት ተጸጽተው ወደ ትክክለኛ ጎዳና ለመግባት የሚያስቡ ባለሥልጣናትን የሚያከስም መሆኑን አውቀህ እኒህን አመራሮች ከሥልጣናቸው ባለፈ ጠባቂዎቻቸውን እስከማንሳት ያደረሰውን ምክንያት ወይም ጥፋት እስክታውቅ ድረስ ጠባቂያቸው ሁን፡፡ #Share

photo content

ክርስቲያን ታደለ አሳዬ ደርቤ ▬▬▬ ➔የተባ አንደበትና ብሩህ ጭንቅላት የተሰጠው፤ ➔በድምጹ ለመረጠው ሕዝብ ድምጽ በመሆን ላይ የሚገኝ፤ ➔በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነው የሕልውና አደጋ መነሻውም ሆነ
ክርስቲያን ታደለ አሳዬ ደርቤ ▬▬▬ ➔የተባ አንደበትና ብሩህ ጭንቅላት የተሰጠው፤ ➔በድምጹ ለመረጠው ሕዝብ ድምጽ በመሆን ላይ የሚገኝ፤ ➔በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነው የሕልውና አደጋ መነሻውም ሆነ ማርከሻው አራት ኪሎ ግቢ ውስጥ እንደሚገኝ ተረድቶ በገብስ ገብሱ ፈንታ ነጭ ነጩን ማመላከት የጀመረ... ➔ ኢትዮጵያንም ሆነ አማራን ለመታደግ ዓላማን አውቆ እና ዒላማን ጠብቆ ተራራውን በጽናት መጋፈጥ እንጂ የሤራ ሊቆችን በመለማመጥና በዙሪያቸው በመርመጥመጥ የጥፋት ድግሳቸውን ማስቀረት እንደማይቻል የተገነዘበ፤ ➔"ሕዝባዊ ስጋትን በመጣል- ግላዊ ምቾትን ማስቀጠል" የሚለው የእራስ ወዳዶች ፍልስፍና የማይገዛው፤ ➔"የኔ" የሚላቸው ሰዎች በጥቅም ተደልለው ሲኮሰምኑ በትችቱ ማረም፣ ሲጀግኑ ደግሞ በአድናቆቱ ማፈርጠም የሚሻ ብርቱ ወዳጅ ያለው 😆

ጃልመሮና ደብረ ጽዮን የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣን ሆነው ቢሾሙ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ካዘጋጁት ሰነድ የላቀ የዘመቻ እቅድ ጽፈው ፋኖ ላይ ሊዘምቱ አይችሉም። ለአንድ መሪ ያለውን ታማኝነት ለመግ
ጃልመሮና ደብረ ጽዮን የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣን ሆነው ቢሾሙ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ካዘጋጁት ሰነድ የላቀ የዘመቻ እቅድ ጽፈው ፋኖ ላይ ሊዘምቱ አይችሉም። ለአንድ መሪ ያለውን ታማኝነት ለመግለጽ ወገንን ማጥቃት እጅግ ይቀፍፋል‼️

ለአማራ ክልል ባለሥልጣናት አሳዬ ደርቤ ▬▬▬ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ይቅርና ከጥቂት ወራት በፊት በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሳችሁትን ግፍ ለመጻፍ ሳስብ ዘልዛላ ታሪካችሁ እረዝሞ ከሊዮ ቶልስቶይ መጽሐፍ በላይ ግዙፍ ገጽ ያለው ይሆንብኛል፡፡ ታላቁን ሕዝብ እንዴት እንዳዋረዳችሁት ሳሰላስል ፋኖን ለመመታት ማሰባችሁ ቀርቶ አመራር ሆናችሁ መቀጠላችሁ ያስገርመኛል፡፡ ቆይ እኔ እምለው… ➔የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ የሚያወድም ወራሪ ጦር ሲመጣ ሕዝቡን በዞን ከፋፍላችሁ፣ የድርጅታችሁን ገንዘብ ተከፋፍላችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ እና ለእራሳችሁ የአውሮፕላን ትኬት ገዝታችሁ… ማምለጫ ቀደዳ ስትፈልጉ የነበራችሁ ጉዶች ዛሬ ላይ ፋኖን ለማጥፋት የሚያስችል ሰነድና እቅድ ለማዘጋጀት የበቃችሁት የአማራን ሕዝብ ምን ያህል ብትንቁት ነው? ➔የአማራ ወጣት የትጥቅ ጥያቄ ሲያቀርብ እንቢ ብላችሁ መጋዘን ሙሉ ጦር-መሣሪያ ለወራሪው ሃይል ጥላችሁ እንዳልሸሻችሁ… በክትክታ ዱላ ማርኮ የታጠቀን ፋኖ ትጥቅ ለማስፈታት የደፈራችሁት ስንት ዳብል ውስኪ ብትጠጡ ነው? ➔መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈጽመው ነፍሱን እና ትጥቁን የሚቀሙ፣ የዙፋን ጥያቄያቸውን ንጹሐን በመግደል የሚገልጹ እልፍ አእላፍ አማጺያን ባሉበት ሁኔታ... ከሠራዊቱ ጎን ቁሞ አብሮ ሲሞት የነበረውንና ወደፊትም አብሮ ለመሠዋት የተዘጋጀውን ፋኖ ከመከላከያ ጋር ማጋጠም የፈለጋችሁት የአማራን ሕዝብ ምን ያህል ብትጠሉት ነው? ➔በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ የሚኖረው አማራ በኦ-ያኔ እና በሸኔ ከበባ ውስጥ ወድቆ እየተሰቃዬ ባለበት ጊዜ… ሌሎች አካባቢዎች ላይ ወረራ በሚፈጽሙና ንጹሐንን በሚያወድሙ ኃይሎች ፈንታ ክልሉን የመከላከል ተግባር ይዞ የተደራጀውን ፋኖ ለማክሰም የሚያስችል ሰነድ ተቀብላችሁ ለማስፈጸም የበቃችሁ ከትሕ-ኦነጎች ምን ያህል ገንዘብ ብትቀበሉ ነው? ➔ይሄስ የጥፋት እቅድ በፋኖ ላይ የተዘጋጀው የትኛውን ክልል ወርሮ ነው? የትኛውን የመንግሥት ሠራዊት አጥቅቶ ነው? የስንት ባለሥልጣናትን ሕይወት ነጥቆ ነው? የትኛው የአማራ ሕዝብ ‹‹ፋኖ ስጋት ስለሆነብኝ አጥፉልኝ›› ብሏችሁ ነው? እርግጥ በፋኖ ሥም የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ አጭበርባሪዎች በገዛ ሕዝባቸው ላይ አንዳንድ ጥፋት ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን በውጫዊ ኃይሎች የትጥቅ ድጋፍ ኢትዮጵያን የማፍረስና መንግሥትን የመገርሰስ ዓላማ አንግበው በምድሩ ላይ ከተቀፈቀፉት አማጺያን ጋር ሲወዳደር የእነዚህ ኃይሎች ጥፋት መከላከያን ለማዝመት ቀርቶ የአገርም ሆነ የመንግሥት ስጋት ሊሆን አይችልም፡፡ እናንተ ግን በአማራዎች ወንበር ላይ የተቀመጣችሁ የትሕ-ኦነጎች አሽከር በመሆናችሁ የምስራቅ አማራን ፋኖን በመምታት ታማኝነታችሁን መግለጽ ፈለጋችሁ፡፡ አንድ ነገር ልንገራችሁ…? በአማራ ሕዝብ ላይ እንደ ሠራችሁት ወንጀል ቢሆን ኖሮ ፋኖ ነበር ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ እናንተ መምጣት ያለበት፡፡ መከላከያ ሠራዊቱም ቢሆን ትናንት አብሮት ሲሞት ከነበረው ፋኖ ላይ በመተኮስ ፈንታ ‹‹በጓዶቼ ሞት ላይ ተደራድራችሁብኛል›› ብሎ እናንተን ነበር መውቀስ የነበረበት፡፡ በተረፈ... ፋኖ ላይ የጀመራችሁትን ዘመቻ ተግባራዊ ማድረግ የምትችሉት የአማራን ሕዝብ ከሕልውና ስጋት ነጻ ያደረጋችሁ ቀን ብቻ ነው፡፡ ወይም ደግሞ መላው አማራን ማጥፋት የቻላችሁ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የምትጀምሩት እንጂ የምትጨርሱት ዘመቻ አይኖራችሁም፡፡ እናም ፋኖን ለማጥፋት የነደፋችሁትን እቅድ መሰረዝ ካልቻላችሁ ገመድ ሆኖ የእናንተ አንገት እንደሚሸመቀቅ ጥርጥር የለውም፡፡

በብአዴን ፍቃድና እገዛ በፋኖ ላይ እየተወሰደ ያለው የጥፋት እርምጃ ባፋጣኝ ይቆም ዘንድ እጠይቃለሁ። "የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ተቃውሟቸውን መግለጽ አለባቸው" እላለሁ።

ጋበዝኳችሁ

አገር ማፍረስ የሚሻ ኃይል ሥልጣን በያዘበት ዘመን አማራ ሆኖ እንደ መገኘት ሕመም ነው። ድካምም ጭምር...‼️ ➔ሰኞ-ትሕነግ ይዘምትብኻል። ➔ማክሰኞ- ኦነግ ይጨፈጭፍኻል። ➔ሮብ- ኦህዴድ ይወነጅልኻል
አገር ማፍረስ የሚሻ ኃይል ሥልጣን በያዘበት ዘመን አማራ ሆኖ እንደ መገኘት ሕመም ነው። ድካምም ጭምር...‼️ ➔ሰኞ-ትሕነግ ይዘምትብኻል። ➔ማክሰኞ- ኦነግ ይጨፈጭፍኻል። ➔ሮብ- ኦህዴድ ይወነጅልኻል። ➔ሐሙስ- ብልጽግና ሤራ ይጠነስስብኻል። ➔አርብ- አማራን የሚወነጅል ሪፖርት አምነስቲ አውጥቶ ያስነብብኻል። ➔ቅዳሜ- ጦርነቱን ሲመራ የከረመው መንግሥት ሪፖርቱን መቀበሉንና እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ይነግርኻል። ➔እኁድ- አንዱ ቦታ ላይ ጥቃት ደግሰው ይጋብዙኻል። ይህ ሁሉ ዘመቻ ታዲያ "የኢትዮጵያን ፍርሰት ለማቀላጠፍ ቀድሞ መመታት ያለበት ሃይል የቱ ነው?" ተብሎ ሲጠየቅ የአማራ ሕዝብ መልስ ሆኖ በመገኘቱ እንጂ የተለየ ኃጢያት ስላለበት አይደለም። ምንም እንኳን የአማራ ሕዝብ ባሁኑ ሰዓት እራሱን እንጂ አገር መጠበቁን ያቆመ መሆኑን ያቆመ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተስማሙ ውጫዊና ውስጣዊ ኃይሎች ግን "የሩዋንዳን እልቂት አማራ ላይ ሳንፈጽም አንገነጥልም" በሚል አቋም 24/7 ጥቃት መደገሳቸውን ቀጥለዋል። ግን እያንዳንዱን ጥቃት ተቋቁመን እንደምናልፈው አልጠራጠርም‼️‼️

የሰሞኑን የአብን መግለጫ ማለፊያ ነው። ግን ከዚያ ባለፈ መልኩ ከመንግሥት ተነጥሎ መውጣትና ከፍተኛ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ነገ ከትሕነግ ጋር መሥራት ሲጀምር ከመገፍተር አሁኑኑ ፍቺ መፈጸም ይበጃል።

የእስክንድርን ቃለ-መጠይቅ በግርምት ውስጥ ሆኜ ተከታተልኩት። ጋዜጠኛው በብዙ ነገሮች ነጥብ ሊያስጥለውና ከሕዝብ ጋር ሊያጣላው ሞክሮ ነበር። እስኬው ግን የሚገርም ብቃቱን እና እውቀቱን ብቻ ሳይሆን
የእስክንድርን ቃለ-መጠይቅ በግርምት ውስጥ ሆኜ ተከታተልኩት። ጋዜጠኛው በብዙ ነገሮች ነጥብ ሊያስጥለውና ከሕዝብ ጋር ሊያጣላው ሞክሮ ነበር። እስኬው ግን የሚገርም ብቃቱን እና እውቀቱን ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ከፍታውን ማሳየት ቻለ። እሳት ሆኖ ቃለ-መጠይቁን የጀመረው ጋዜጠኛም እንደ በረዶ ቀዝቅዞ ፕሮግራሙን አጠቃለለ። እናም እልኻለሁ... የእስክንድርን አስተሳሰብ ማወቅ የምትሻ ሁሉ ፍረጃውን ትተህ ይሄን ቃለመጠይቅ እንዲትመለከት ጋብዤኻለሁ።

በርካታ ንጹሐን በተጨፈጨፉበት እለት ጋዜጠኞችን እና ሚዲያዎችን ሰብስቦ ለማሳ ጉብኝት የሚወጣው "የኦሮሚያ ብልጽግና" ድምጽ አልባ ጭፍጨፋን በማመቻቸቱ ሊወገዝ ሲገባው አሚኮን ሲዘልፍ ማየት ያስገርማል
በርካታ ንጹሐን በተጨፈጨፉበት እለት ጋዜጠኞችን እና ሚዲያዎችን ሰብስቦ ለማሳ ጉብኝት የሚወጣው "የኦሮሚያ ብልጽግና" ድምጽ አልባ ጭፍጨፋን በማመቻቸቱ ሊወገዝ ሲገባው አሚኮን ሲዘልፍ ማየት ያስገርማል። ለማንኛውም ግን የአማራ ብልጽግና ድምጹን በማጥፋት ፈንታ ተገቢውን መልስ መስጠት ወይም ደግሞ የጌቶቹን መግለጫ Share በማድረግ ስምምነቱን መግለጽ ይጠበቅበታል።

የኦሮሚያ ብልጽግና መግለጫ‼️ አሳዬ ደርቤ ➔እጅግ አደገኛ በሆኑ ግጭት ቀስቃሽ ቃላቶች የታጨቀ፤ ➔ጽንፈኝነትን በማውገዝ ጀምሮ- ጽንፍ በያዘ ዛቻ የተጠናቀቀ፤ ➔በስሜትና በግንፍልተኝነት የተሞላና ከኃላፊነት መንፈስ ሙሉ በሙሉ የራቀ፤ ➔በአማራ ክልል የምትገኘውን አውራ ጎዳና ቀበሌን ወደ ኦሮሚያ ክልል የወሰደ፤ ➔ቁጣውን ለሕዝብ አከፋፍሎ ‹‹የአማራ ጽንፈኞች ከክልላችን ገብተው የፈጸሙት ጥቃት መላው ሕዝባችንን አስቆጥቷል›› በሚል ድምዳሜ የእርስ በእርስ እልቂት መለኮስን የወደደ፤ ➔የአማራ ጽንፈኛ ከሚለው ሃይል በተጨማሪ በአማራ ብልጽግና እና በክልሉ ሚዲያዎች ላይ የቁጣ መዓት ያወረደ፤ ➔የኢሰመጉ መግለጫን እና እውነትን በካዴ መልኩ ‹‹የአማራ ጽንፈኞች ከክልሌ ገብተው ጥቃት ፈጽመዋል›› በሚል ክስ ምንጃር ሸንኮራ ገብቶ የአማራ ገበሬዎችን ለመምታት ያቀደ…… እጅግ አደገኛ መግለጫ ነው፡፡ ከሁለት ወር በፊት ከ200 በላይ አማራዎች በወለጋ ሲገደሉ ቁጣውን ቀርቶ ኀዘኑን በወጉ መግለጽ የተሳነው አካል… ዛሬ ላይ ዛቻውን እና የጥፋት እቅዱን ይዞ እንዲመጣ ያስገደደው ምክንያትም… ሰለባ ይሆን ዘንድ የፈረደበት የአማራ ሕዝብ በአገር ሥም ለብልጽግና ወንበር በመታገልና በየስፍራው በመገደል ፈንታ እራሱን መከላከል መጀመሩ ነው፡፡ ስለሆነም የአማራ ጉዳይ የሚገደን ኃይሎች ሁሉ በተረኝነት እና በዘረኝነት መሃከል የሚወዛወዘው ይህ ሥርዓት በተግባሩም ሆነ በንግግሩ ውስጥ የሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች ሁሉ የሮዋንዳን እልቂት የመድገም እቅድ መኖሩን የሚገልጹ ስለሆኑ... ሕዝባችን እንዲጠነቀቅ ከማድረግ ባለፈ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ማሳወቅ ግድ ይለናል፡፡ #Share

ስለ ብልጽግና ሳስብ:- ከኢትዮጵያ አስከሬን ውስጥ የሆነች ሕጻን የማዋለድ እቅድ ይዞ በፕሮግራም የሚንቀሳቀስና.... ይሄንንም ሕልሙን ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ በጨረሰ ማግስት "ተገረሰሰ" በሚል ሥም ''ኦነግ ሸኔ' ሆኖ የሚከስም ይመስለኛል። አብዛኞች እንደሚሉት "ልፍስፍስ መንግሥት" ሳይሆን አገር የማፍረስ ዓላማ ያለው "ጠንካራ ድርጅት" ሆኖ ይታየኛል፡፡ እናም ‹‹ይበቃኻል›› በሚል አቋም አገር ለማትረፍ የሚጥሩ ሃይሎችን እያከሰመ ‹‹ተዳክመኻል›› በሚሉት ነቃፊዎቹና ደጋፊዎቹ ላይ "ክክክክክክ" እያለ ሲስቅ ይሰማኛል። 😁

ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የገባውን መከላከያ ሠራዊት አስወጥቶ የክልል ልዩ ሃይል ማከማቸት ያስፈለገበት ምክንያት ምን ይሆን? ብልጽግና ሆይ የደገስከው ፕሮጀክት ለማንም ስለማይበጅ ብትተወው ይሻላል!

እንደ ግሩም ጫላ እና ቴዎድሮስ አድሃኖም ካሉ በዓለም አቀፍ ሥም ከሚንቀሳቀሱ ዘረኞች ጋር ሲነፃፀሩ ወለጋና መተከል ጫካ ውስጥ ያሉት ታጣቂዎች ምስጉን ናቸው።
እንደ ግሩም ጫላ እና ቴዎድሮስ አድሃኖም ካሉ በዓለም አቀፍ ሥም ከሚንቀሳቀሱ ዘረኞች ጋር ሲነፃፀሩ ወለጋና መተከል ጫካ ውስጥ ያሉት ታጣቂዎች ምስጉን ናቸው።

የመንግሥት መግለጫ‼️ አሳዬ ደርቤ የኑሮ ውድነት- ከአቅሜ በላይ ሆነ- እያልክ አትንጫጫ በርበሬ ያጣህ ቀን- ቀይወጡን ተውና- ተመገብ አልጫ፡፡ በሆነ ባልሆነው- መሪህን አትውቀስ- መንግሥትን አታማር
የመንግሥት መግለጫ‼️ አሳዬ ደርቤ የኑሮ ውድነት- ከአቅሜ በላይ ሆነ- እያልክ አትንጫጫ በርበሬ ያጣህ ቀን- ቀይወጡን ተውና- ተመገብ አልጫ፡፡ በሆነ ባልሆነው- መሪህን አትውቀስ- መንግሥትን አታማር ዘይት ሲቸግርህ- ቦለቄ ቀቅለህ- ንፍሮ በልተህ እደር፡፡ ጤፍ ከሰው ተወድዶ- የነጠፈ ለታ- እንጀራ ከሞሰብ ሙዝና ፓፓያ- አቦካዶ ጨምቀህ- በዳቦ ተመገብ መንግሥት ዝናብ እንጂ- ከደመና መሃል- መቼም መና አያዘንብ፡፡ የስንዴ ምርጥ ዘር- የአፈር ማዳበሪያ-‹‹አጣን›› የምትሉ በዘንድሮው ክረምት- እህሉን ተውና- ባሕር ዛፍ ትከሉ፡፡ በቤንዚን አቅርቦት- ታክሲ የጠፋ ቀን- እንደ እንጀራ ወጡ ስለ ኦጋዴን ነዳጅ- ባወራሁት ወሬ- ከምታላግጡ የኢትዮጵያ ትንሳኤ- እስቲመጣ ድረስ- ወክ ልትበሉ ውጡ፡፡ በተረፈ… በራብ እና ጥይት- እንደ ክረምት አግቢ- ሕዝባችን ቢረግፍም ማዳበሪያ ጠፍቶ- የአርሶ አደሩ ማሣ- እንዲሁ ቢከርምም ዜጎች ጠባቂ አጥተው- በአሸባሪ ጥቃት- ተጨፍጭፈው ቢያልቁም፤ ኢትዮጰያችን እንደሁ- ብልጽግናን ይዛ- መሻገሯ አይቀርም፡፡

አማራ ባልሆን ኖሮ አሳዬ ደርቤ ▬▬▬ ➔ለእኩልነት ጥያቄው ‹‹የአማራ የበላይነት አይመለስም›› የሚል መልስ ሰላሳ ዓመት ሙሉ ሲያስተናግድ ከኖረው… ➔በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ብሔረሰቦች ሐቀኛ ፌደራሊዝምን የተገበረው እሱ ሆኖ ሳለ የአማራን ንጹሐን ማጥቃት የፌደራሊስት መገለጫ ባደረጉ ሃይሎች በአሀዳዊነት ከሚፈረጀው… ➔‹‹ኢትዮጵያን የሚወድድ መሪ ሁሉ መሪዬ ነው›› በሚል መርሕ አዲስ ንጉሥ አራት ኪሎ አስገብቶ ሲመለስ ‹‹የአጼዎቹን ሥርዓት አይመለስም›› የሚል ከንቱ ንግግር ከሚያስተናግደው… ➔‹‹በልፋቴ ያገኘሁትን ንብረት አታውድሙብኝ›› ለሚል ቅሬታው በልፋቱና በጥናቱ ያገኘው ውጤት ተቀንሶ "ወደ ዩኒቨርስቲ አትገባም›› ከሚባለው… ➔‹‹በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በአንድ ጀምበር ሲገደሉ መንግሥት የት ሄዶ ነበር?›› ብሎ ሲጠይቅ ሥልጣን ከያዙ ነፈዞች አንደበት ‹‹ይሄ ጩኸትህ ነው የሚያስገድልህ›› የሚል መልስ ከሚሰጠው… ➔በእድር ፈንታ በዶዘር ሲቀበር ከርሞ ሌሎች ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ‹‹ሰው ከእነ ነፍሱ አቃጠልክ›› ተብሎ ከሚወነጀለው… ➔ለአገር ቀጣይነት ሲል በቋንቋ መስፈርት የሚያገለግልና የሚበድል ውዳቂ መንግሥት ተሸክሞ ሲያንዘፋዝፍ ከኖረው…. ➔‹‹አንዲት ሀገር›› የሚል ንግግሩ ‹‹አንዲት ሃይማኖትና አንዲት ማንነት ማለትህ ነው›› ተብሎ ከሚፈረጀው… ➔‹‹ሰለባ ያደረገኝ ሕገ-መንግሥት ይሻሻልልኝ›› ብሎ ሲጠይቅ ‹‹ሁሌ ሟችና ተፈናቃይ በመሆን ፈንታ ገዳይና አፈናቃይ ሆነህ ችግሩን አገራዊ ካላደረግከው በስተቀር ለአንድ ሕዝብ ብለን ሕገ-መንግሥት አናሻሽልም›› የሚል መልስ ከሚሰጠው… የአማራ ሕዝብ አብራክ ባልወጣ ኖሮ... ለዚህ ሕዝብ ጥያቄዎች የትኛውንም መስዋዕትነት የምከፍል የሌላ ብሔር ተወላጅ እሆን ነበር፡፡ ከአማርኛ በተጨማሪ አፍ በፈታሁበት ቋንቋ ‹‹በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ይብቃ›› ማለቴ አይቀርም ነበር፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአማራ ፈንታ የሆነን ብሔር በጥንት ትርክት ለመከራ እየዳረገ በደም የተቦካ እንጀራ የሚያሞሶካ ቢሆን ኖሮ… የዚያ ሕዝብ ድምጽ ከመሆን ባለፈ ልክ እንደ ጎንደር ‹‹እዚያ ማዶ የሚፈስሰው ደም የኔም ደም ነው›› የሚል አመጽ እለኩስ ነበር፡፡ ገባህ?? ግን ከአንዳንዱ ሲሳይ፣ ያንዳንዱ ስቃይ ትርጉም ስላለው እንኳንም ከዚህ ሕዝብ አብራክ ወጣሁ‼️