ru
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Открыть в Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Больше
1 862
Подписчики
-224 часа
-167 дней
-6030 дней
Архив постов
🔆Power Geez 2017 🦋#Share🦋 👩‍💻 @TechnologyMasterPage 👨‍💻

በፓርኪንሰንስ በሽታ የተጠቁ ሴሎችን ድብቅ ባሕርያት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት መለየት ተቻለ፡፡ ተመራማሪዎች ከፓርኪንሰንስ ተጠቂዎች የተወሰዱ የቆዳ ሕዋስ ናሙናዎችን አዳዲስ ባሕርያት አርቲ
በፓርኪንሰንስ በሽታ የተጠቁ ሴሎችን ድብቅ ባሕርያት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት መለየት ተቻለ፡፡ ተመራማሪዎች ከፓርኪንሰንስ ተጠቂዎች የተወሰዱ የቆዳ ሕዋስ ናሙናዎችን አዳዲስ ባሕርያት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን በማጣመር መለየት መቻላቸው ተገልጿል፡፡ ከዘጠና አንድ የበሽታው ተጠቂዎች እና ጤናማ ሰዎች የተወሰዱ ከሚሊዮን የተሻገሩ የቆዳ ሕዋስ ምስሎችን በመጠቀም ውጤቱ እንደተገኘ ተዘግቧል፡፡ በኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን በበለፀገው የሮቦቲክ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከሕመምተኞቹ የተወሰደውን ናሙና በመተንነተን እስካሁን ያልታወቁ አዳዲስ ባሕርያት መገኘታቸው ታውቋል፡፡ NYSCF Global Stem Cell Array ተብሎ የሚታወቀው የፋውንዴሽኑ እጅግ ዘመናዊ የሮቦት ሥርዓት ብዛት ያላቸውን የሕዋስ ምስሎች ለመለየት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱ የተገኙ የሕዋስ ምስሎችን ለዚሁ ወደተዘጋጀ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በማስገባት የጋራ ባሕርያቸውን ለመለየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱዛን ኤል. ሶሎሞን እንደተናገሩት እንደ ፓርኪንሰንስ ላሉ ውስብስብ በሽታዎች በተለመደው መንገድ መድኃኒት ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አመርቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን በምርምሩ የተደረገው ጥረት ውጤታማ የሆነ አዲስ መድኃኒት ለማግኘት መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡ ኔቸር ኮምዩኒኬሽንስ ተብሎ በሚታወቀው ጆርናል ላይ ለሕትመት የበቃው ምርምር የኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን እና የጉግል የምርምር ክፍል ውጤት መሆኑን ኒውሮሳይንስ ኒውስ ድረ-ገጽ ዘገቧል፡፡ #Technology_News #የቴክኖሎጂ_ዜና t.me/TechnologyMasterPage

✳️ ብዙ ሰዎች የማያዉቋቸው የGSM ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች! 1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0902** ከሆነ ወደ *21*090215**# ይደውሉ ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ! ➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ *21*0144**# በ0144** ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል 2. ስልክዎ ቢዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ 3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ 4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ! 5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል 6. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ #31#የሚደውሉት ቁጥር ከዛ መደወል ▫️አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር እናስገባለን በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል ➥ሁላቹም ብትሞክሯቸው ጥሩ ነው ➲Forward , Like , Comment #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። t.me/TechnologyMasterPage Fb.com/TechnologyMasterPage

በጽሁፍ ውስጥ የተደበቁ ስሜቶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመግለጽ ብልሀት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን
በጽሁፍ ውስጥ የተደበቁ ስሜቶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመግለጽ ብልሀት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሴንቲሜንት አናሊስስ #SentimentAnalysis ይጠቀሳል፡፡ ይህ ሥርዓት በአገልግሎት እና ምርት አቅራቢነት ወይም ከደምበኞች ጋር በተለያየ ምክንያት የሚያገናኝ ሥራ ያላቸው ተቋማት የደምበኞቻቸውን ግብረ-መልስ እውነተኛ ትርጉም ወይም ስሜት የሚረዱበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ሥርዓቱ ናቹራል ላንጉዌጅ ፕሮሰሲንግን ከማሽን ለርኒንግ ጋር አሰባጥሮ በመጠቀም በጽሁፍ የሰፈረ ግብረ-መልስ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል፡፡ ሴንቲሜንት አናሊስስ በሦስት መንገዶች ይከወናል፡፡ አንደኛው ቀድመው በተቀመጡ ሕግጋት ወይም የቋንቋው መዝገበ ቃላት መሠረት የሚተገበር ነው (Rule or Lexicon based approach) ፡፡ ሌላኛው በጊዜ ሂደት ከዳታ በሚማር የማሽን ለርኒንግ ስልት ይከወናል (Automated or Machine Learning approach)፡፡ ሦስተኛውና ተመራጩ እንዲሁም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሁለቱን በጥምረት የሚጠቀመው ነው (Hybrid approach)፡፡ በዚህም መሠረት በኢሜል፣ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና መሰል መድረኮች ደንበኞች ካሰፈሯቸው ተቋሙን የተመለከቱ ያልተደራጁ ጽሁፎች ውስጥ ጠቃሚ እይታዎች ይጠናቀራሉ፡፡ እንደ ቴክታርጌት ትንተና ይህ ሥርዓት በዓረፍተ ነገር፣ በሐረግ፣ በአንቀፅ እና ከዛም ደረጃ በላይ በሚገኙ ጽሁፎች ላይ መተግበር ይችላል፡፡ #Technology_News #የቴክኖሎጂ_ዜና t.mr/TechnologymasterPage

✳️ የሰዎችን ድምጽ በማዳመጥ በልብ ድካም የመጠቃት እድልን የሚያሰላው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት 🚩በተዘጉ የደም ቧንቧዎች ምክንያት ከፍ ያለ ቀጭን ድምጽ ያላቸው ሰዎች የልብ ችግሮች ሊገጥሟ
✳️ የሰዎችን ድምጽ በማዳመጥ በልብ ድካም የመጠቃት እድልን የሚያሰላው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት 🚩በተዘጉ የደም ቧንቧዎች ምክንያት ከፍ ያለ ቀጭን ድምጽ ያላቸው ሰዎች የልብ ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትን ተመስርተው ተመራማሪዎች አሳወቁ፡፡ 🚩ተመራማሪዎቹ የልብ ደም ስሮቻቸውን ሁኔታ ለመገንዘብ ኤክስ ሬይ የታዘዘላቸውን መቶ ስምንት ታማሚዎች በመመልመል ቮካሊስ ሄልዝ በተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልክ መተግበሪያ ላይ የሰላሳ ሰከንድ የድመጽ ናሙና እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡ 🚩በሦስት የተለያዩ ደረጃዎች ወደመተግበሪያው የሚቀዱት የድምጽ ናሙናዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ ተተንትነው ከውጤት አመላካች ጋር ይቀርባሉ፡፡ 🚩አስር ሺህ የድምጽ ቅጂዎች ሥርዓቱን ለማሰልጠን አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው አመላክቷል፡፡ 🚩ሥርዓቱ ሰማንያ አይነት የድምጽ ሁኔታዎችን መገንዘብ እንደሚችልና ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ የልብ ደም ስር መዘጋት ችግርን አመላካች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 🚩በተመራማሪዎቹ ገለጻ የሰው ልጆች ጆሮ እና አዕምሮ የማይለይለዩትን የድምጽ ሁኔታ ቴክኖሎጂው በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት ሊቆጠሩ ወደሚችሉ የውጤት መግለጫዎች በመቀየር ማስቀመጥ እንደቻለ አብራርተዋል፡፡ 🚩በአሜሪካ የማዮ ክሊኒክ ባልደረባ እና ምርምሩን የመሩት ዶ/ር ጃስክንዊል ሳራ እንደተናገሩት ምርምሩ ሐኪሞችንም ሆነ በተግባር ላይ ያሉ የልብ ምርመራ መንገዶችን ለመተካት ያሰበ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከተለመዱት መንገዶች ጋር አጣምሮ ለመጠቀም ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ነው፡፡ #የቴክኖሎጂ_ዜና #Technology_News ©Technology Master Page ════❁✿❁ ═══════ t.me/TechnologyMasterPage

ብዙ ጊዜ ሞባይል ስንገዛ የምንገዛውን ሞባይል ጥራት ለመለየት ስለምንቸገር በቅርብ ያገኘነውን ሰው በመጠየቅ በምስክርነት እንወስናለን ፡፡ የስሞች መብዛትም አንዱ ችግር ነው፡፡ሳምሰንግ ፣ኖኪያ፣ ኤልጂ፣አፕል፣ወዘተ ወዘተ እየተባለ ይሄ ያ ይበልጣል ሙግትም አለ፡፡ እስቲ ለዛሬ ከሞባይል ቀፎ መሰረታዊ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ፡፡ የመጀመሪያው ▪የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ አንድሮይድን ና ቴክኖ አንድሮይድን ይጠቀማሉ እንበል፡፡ ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ መሆኑ በሞባይል ቀፎዎች መሀል ያለውን ያገልግሎት ጥራት፣ ከዘመነው (አፕዴት ቴክ ) ጋር ያለውን መግባባትና ችሎታ፣ለቫይረስ ያለመጋለጥ ብቃትን ጨምሮ ከከባድ ድረ ገጽና አፕሊኬሽን ጋር ተጣጥሞ የመስራት አቅሙን ማሳየቱ ጥቂቶቹ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ የሞባይል ቀፎን ባሕርይ ወሳኝ ምዕራፍ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው፡፡ ከሞባይል ቀፎ አንፃር አንድሮይድ ባሁኑ ወቅት ከዊንዶው እና ማክ የተሻለ የኪስን አቅም ባማከለ መልኩ ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡ ሁለተኛው ▪ማነፃፀሪያ ደግሞ ዋይ ፋይ፣ ብሉቱዝ፣ ዩኤስቢ፣ ጂፒኤስ፣፣ ቱጂ፣ ስሪጂ፣ ፎር ጂ የመሳሰሉትን መያዙና በተጨማሪም ሁለትና ከዚያ በላይ ሲም መቀበሉ ሲሆን ከዚህም በላይ ኖርማል ሲም ጂ ኤስ ኤም እና ruim (cdma sim ) ባንድ ላይ መያዙ ነው፡፡ የፋይል አደረጃጀት ስርአታቸው ለአጠቃቀም ቀላል መሆንና እንደፈለግነው መቀየር መቻሉና ምቹ መሆናቸው ደግሞ ሌላው መለኪያ ነው ፡፡ ለምሳሌ ተች ስክሪን፣ ስክሪን ጋድጌትስን መቀይር መቻሉና በፋይል ማናጀር በምንፈልገው መንገድ መቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ‘እንደዚህ ሁንልኝ’ ስንለው የሚሆንልን ስማርት ፎን ደስ አይልም ? ሶሰተኛው ▪ማነፃፀሪያ የራሱ የሞባይሉ ሜሞሪ ( ፎን ወይም ኢንተርናል ሜሞሪ) ምንለው ነው፡፡ ይህ ሜሞሪ አቅሙ በጨመረ ቁጥር ዋጋውም አብሮ መጨመሩ እሙን ሲሆን ለቀፎዎች የዋጋ ልዩነት መሰረትም አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ቀፎዎች የምንከትላቸውን የውጭ ሜሞሪዎችና አብሮአቸው የተሰራውን ሜሞሪ ባንድ አይነት ስለማይጠቀሙ በፍጥነት፣ በጥራትና በአቅማቸው ላይ የሚያመጣው ልዩነት ትልቅ ነው፡፡ ቀፎዎች (TIF card)ቲፍ ካርድና ኤስዲ(SD card) ካርድን(ሞባይላችን ላይ ምንከታቸው ሜሞሪዎች ማለቴ ነው) ሲጠቀሙ ፍጥነታቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የሚጭኑት አፕሊኬሽን ውስንና ቀጥታ ፍሰት (Real Time access) ነው፡፡ ➛ስለዚህ ቀፎ ስንገዛ የራሱን ሜሞሪ አቅም ማስተዋል ግድ ይላል፡፡ አራተኛው ▪ የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ‘ፎን ክሎክ’ የሞባይል ቀፎውን ሲስተም ሃርድዌር ፍጥነት ሚወስን ነው። ➝ ለምሳሌ ድረ ገፅ ለይ አንድ ሞባይል ያለምንም መቆራረጥ ከዩቱብ ወይንም ከኛው ድሬትዩባችን ላይ ቪዲዮ ቢያጫውት የክሎክ ፍጥነቱንና የቢዩልት ኢን ሜሞሪን(phone memory) ጥራት ያሳያል፡፡ በተጨማሪ ቪዲዮ ኮሊንግ ያለችግርና (ፍሪዝ) በእስካይፒ መጠቀም ከቻልን በርግጥም የቀፎዎችን ግሩም ጥራት ያሳየናል፡፡ ➝እዚህ ጋር ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባልኝ ምፈልገው አሁን ያለው የአገራችን የኔትዎርክ ችግር በቀፎው እንዳይሳበብ የኔትዎርኩን ሁኔታም ማየት መልካም መሆኑን ነው፡፡ አምስተኛ የባትሪ ጥራትና ቆይታ ነው ፡፡ አንዳንድ ሞባይሎች ባትሪ ሙጥጥ አያረጉ ‘‘እረ የቻርጀር ያለህ!’’ እያሰኙ ስንቱን አስጨንቀዋል፡፡ በርግጥ የሞባይል አቅምና ያገልግሎት ጥራት በጨመረ ቁጥር ባትሪ አጠቃቀምም አብሮ ቢጨምርም ብዙ ሞባይል አምራቾች የሞባይል ባትሪ ጥራትን በማሻሻል እነዚህ ቀፎዎች ለ18 ሰኣት አንዲያገለግሉ አርገው ሰርተውልናል፡፡ ሌላው ባትሪን በተመለከተ ማየት ያለብን የተሻለ ሞባይል ለመግዛት የባትሪ ማኔጅመንት ፕሮቶኮል አውቶማቲክና ማኑዋል አማራጭ እንዳለው ማጣራት ነው፡፡ የባትሪ ቀበኛ ከሆኑት ስክሪን ብራይትነስና ቫይብሬት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከጀርባ ሳናያቸው የሚስሩ አፕሊኬሽኖች መኖር፣ ቫይረስና አንቲ ቫይረስ ማኔጅ ማድረግና የመሳሰሉትን መቆጣጠሪያ ሶፍት ዌር መጫን የባትሪን ቀይታ ለማራዘም የምጠቁመው ተጨማሪ መፍተሄ ነው። በመጨረሻም ▪የተሻለ ሞባይል ለመያዝ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ኢሜይል፣ የጽሑፍ መልዕክት፣ ካሜራ ጥራት፣ ምቾት፣ ሰክሪን ስፋትና የተመረተበትን ቀን ማረጋገጡ ጠቃሚ ነው!! t.me/TechnologyMasterPage

✅ Data Usage Manager 👉 ከመጠን በላይ አይጠቀሙ...የኢንተርኔት ዳታ አጠቃቀምዎን ይከታተሉ! ✅ ይህ መተግበሪያ የኢንተርኔት አጠቃቀማችሁን ለመከታተል እንዲሁም የትኛዎቹ አፕሊኬሽኖች ላይ ብዙ ኢንተርኔት access እያረጋችሁ እንዳለ ምታውቁበት እንዲሁም ገደብ ምታበጁበት ነው። 📍 ሌሎች ተጨማሪ አፕሊኬሽኖች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ t.me/TechnologyMasterPage

✅ App_name👇 📍 XML backup & restore or E2pdf backup & restore App_size 28MB 📍ጥቅሙ ምንድነው ❓ ➠ 1️⃣ጥቅሙ ስልካችን ላያ ያለን sms ወደ pdf መቀየር ➠ 2️⃣ በአንድ አመታት ውስጥ የተደዋወልነውን ስልክ ማን እንደወለ ለስንት ደይቃ እንዳወራን እስከ ስሙ እስከ ቀንና ሰአቱ በpdf ያስቀመጥልናል ➠ 3️⃣ contact ላይ የመዘገብነውን ወደ pdf መቀየር ....... መተግበሪያውን እንዴት ልጠቀመው ❓ ➳ 1️⃣ በመጀመሪያ መተግበሪያውን በማውረድ መክፈት ➳ 2️⃣ ከዚያም pdf backup (printable) አሚለው ስር ያለውን CLICK TO CONTINUE ሚለውን በመንካት የሚመጡ ዝርዝሮች ሚፈልጉትን መርጠው ሲነኩ የfile ስም አስገባ ይላል በማስገባት export to pdf ሚለውን በመንካት አለቀ ከዚህ በሁዋላ የስልክወ ፊይል ማናጀር ላይ ገብተው የዚህ app ስም የያዘ ፎልደር ውስጥ ያገኙታል 👍 t.me/TechnologyMasterPage

+1
✅ App_name👇 📍 XML backup & restore or E2pdf backup & restore App_size 28MB 📍ጥቅሙ ምንድነው ❓ ➠ 1️⃣ጥቅሙ ስልካችን ላያ ያለን sms ወደ pdf መቀየር ➠ 2️⃣ በአንድ አመታት ውስጥ የተደዋወልነውን ስልክ ማን እንደወለ ለስንት ደይቃ እንዳወራን እስከ ስሙ እስከ ቀንና ሰአቱ በpdf ያስቀመጥልናል ➠ 3️⃣ contact ላይ የመዘገብነውን ወደ pdf መቀየር ....... መተግበሪያውን እንዴት ልጠቀመው ❓ ➳ 1️⃣ በመጀመሪያ መተግበሪያውን በማውረድ መክፈት ➳ 2️⃣ ከዚያም pdf backup (printable) አሚለው ስር ያለውን CLICK TO CONTINUE ሚለውን በመንካት የሚመጡ ዝርዝሮች ሚፈልጉትን መርጠው ሲነኩ የfile ስም አስገባ ይላል በማስገባት export to pdf ሚለውን በመንካት አለቀ ከዚህ በሁዋላ የስልክወ ፊይል ማናጀር ላይ ገብተው የዚህ app ስም የያዘ ፎልደር ውስጥ ያገኙታል 👍

👇Microsoft office Word Features by Image (Screen Shoots) I am considered share blow for you! #So Read they, because they are the best.

✅ በቲውተር ፖስት የምናደረገው በፌስቡክ አካውንታችን ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡ - ይህን ለማድረግ የሚከተለውን Step ይከተሉ፡- - በቲውተር አካውንታችን Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ.... - በመቀጠልም በ Setting ውስጥ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ወደታች በመሄድ Apps የሚለውን ይጫኑ.... - በመቀጠልም Apps የሚለውን ስንከፍት Facebook Connect የሚል ምርጫ እናገኛለን፡፡ እሱን ምርጫ በመጫን የፌስቡክ አካውንታችንን በማስገባት የቲውተር አካውንታችንን ከፌስብከ አካውንታችን ጋር በቀላሉ ማገናኘት እንችላለን ማለት ነው፡... - አስፈላጊ ከሆነም ሁለቱንም በማገናኘት በፌስቡክ ፖስት ያደረግነውም በቲውተር ፖስት እንዲሆን እንዲሁም በቲውተር ፖስት ያደረግነውም ደግሞ በፌስቡክ ፖስት እንዲሆን ማድረግ ይቻላል... - የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር ጋር ማገናኘታችን በዋነኝነት በቲውተር ከ140 ፊደላት በላይ የያዘ መልዕክት ማስተላለፍ ስለማይቻል በፌስቡክ የፈለግነውን መልዕክት ስንፅፍ በቲውተር ላይም ለሚገኙ ሰዎች የፅሁፉን ሙሉ መልዕክት በሊንክ ስለሚያስቀምጥልን በቀላሉ እንዲደርሳቸው ማድረግ ያስችለዋል፡፡ ✅Telegram channel t.me/TechnologyMasterPage

✍️✍️✍️Important shortcut keys for computer✍️✍️✍️✍️✍️✍️ ✍️Ctrl +A----------------------select all ✍️Ctrl +C----------------------copy ✍️Ctrl +X----------------------cut ✍️Ctrl +Z----------------------undo ✍️Ctrl +B----------------------bold ✍️Ctrl +I----------------------italic ✍️Ctrl +U----------------------underline ✍️Ctrl +V----------------------paste ✍️F1----------------------help ✍️F2----------------------rename selected object ✍️F3----------------------find all files ✍️F4----------------------open file list drop down in dialoges ✍️F5----------------------refresh current window ✍️F6----------------------shifts focus in windows explorer ✍️F10----------------------activates menu bar options ✍️ALT+TAB----------------------cycle b/n open applications ✍️ALT+F4----------------------quit program close current window ✍️ALT+ENTER---------------------- opens propreties dialoge ✍️ALT+F6----------------------switch b/n current program window ✍️ALT+SPACE----------------------system menu for the current window ✍️ALT+c----------------------open drop down lists in dialog box Backspace ----------------------switch to the parent folder ✍️Ctrl+esc----------------------open start minu ✍️Ctrl+alt+del----------------------open task manager reboot the computer ✍️Ctrl+tab----------------------move through property tabs ✍️Ctrl+drag----------------------copy fileesc----------------------cancel lastoutlook shortcut keys ✍️alt+s----------------------send the emialctrl+c----------------------copy selected files ✍️ctrl+x ----------------------cut selected text ✍️ctrl+p----------------------open print dialog box ✍️ctrl+k----------------------complet name/emailtyped in the adderss bar ✍️ctrl+b----------------------bold highlighted selection ✍️ctrl+i----------------------italic highlighted selection ✍️ctrl+u----------------------underline highlighted selection ✍️ctrl+r----------------------reply to an email ✍️ctrl+f----------------------forwared an email ✍️ctrl+n----------------------create a new email ✍️ctrl+shift +a----------------------create a new appointment to calender ✍️ctrl+shift+o----------------------open the outbox ✍️ctrl+shift+i----------------------open the inbox ✍️ctrl+shift+k----------------------add a new task ✍️Ctrl+shift+c----------------------create a new contact ✍️Ctrl+shift+j----------------------create a new journal entryword shortcut keys ✍️ctrl+a---------------------- select all content of the page ✍️ctrl+b---------------------- bold highlighted selection ✍️ctrl+c----------------------copy selected text ✍️ctrl+x----------------------cut selected text ✍️ctrl+o----------------------open option ✍️ctrl+p----------------------open the print window ✍️ctrl+f----------------------open find box ✍️ctrl+i---------------------- italic highlighted selection ✍️ctrl+k---------------------- insert link ✍️ctrl+u---------------------- underline highlighted selection ✍️ctrl+y----------------------redo the last action performed ✍️ctrl+z---------------------- undo last action ✍️ctrl+g----------------------fined and replace option ✍️ctrl+v----------------------paste ✍️ctrl+j---------------------- justify paragraph alignment. ✍️ctrl+l----------------------align selected text or line to the left ✍️ctrl+q-----------align selected paragraph to the left ሌሎችን መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ ለማግኘት ይህን 👇 Link SHARE አድርጉ ╔════════════ 🔘 t.me/TechnologyMasterPage

📍 ንስር ✅ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምን መፍትሔ ይኖረው ይሆን? t.me/TechnologyMasterPage #Technology_News

📍 ተስፋ ✅ ከዊልቸር ሌላ መንቀሳቀሻ አማራጭ የሌላቸው ህጻናት እንዲራመዱ ለማስቻል እየተሰራበት ስለሚገኘው ቴክኖሎጂ ጥቂት እናካፍላችሁ፡፡ t.me/TechnologyMasterPage #Technology_News

✴️ የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ ልጥፎቻችን ስለ አዕምሮ ጤናችን ምን ይናገራሉ? 🏳️ የአሜሪካው ዳርትማውዝ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ሬዲት በተባለው የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ የሚለጠፉ አስተያየቶችን መ
✴️ የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ ልጥፎቻችን ስለ አዕምሮ ጤናችን ምን ይናገራሉ? 🏳️ የአሜሪካው ዳርትማውዝ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ሬዲት በተባለው የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገፅ የሚለጠፉ አስተያየቶችን መሠረት አድርጎ የሰዎችን የአዕምሮ ጤናማነት የሚለይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ማበልፀጋቸው ተነገረ፡፡ 🏳️ የተመራማሪዎቹ ትኩረት እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና ሌሎች የስሜት ቀውሶች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለምርምሩ የሚሆን ዳታ የስሜት ቀውሶቹ ተጠቂ መሆናቸውን ካመኑ እና ምንም አይነት የሚታወቅ የአዕምሮ እክል ከሌለባቸው ሰዎች ተሰብስቧል፡፡ 🏳️ ይህ ዳታ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱን ለማሰልጠን ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱም ይዘቶቹ "ደስታ" "ንዴት" "ሐዘን" "ፍርሐት" "ስሜት አልባ" ወይም ድብልቅ ስሜቶችን ያንጸባርቃሉ የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ እንደሚቻል ተመላክቷል፡፡ 🏳️ ሥርዓቱ ከልጥፉ ይዘት ባሻገር ስሜት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ቴክኤክስፕሎር አስነብቧል፡፡ 🏳️ ሰዎች በፈቃደኝነት የሚለጥፏቸውን ይዘቶች መሠረት አድርጎ በቀላሉ ባሕርያቸውን ለመረዳት የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጾች ጥሩ አማራጭ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ 🏳️ ምርምሩ የአዕምሮ የጤና እክልን ስር ሳይሰድ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ የምሁራኑ እምነት ነው፡፡ ════❁✿❁ ═══════ t.me/TechnologyMasterPage

✴️ ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1- 🚩ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtual Reality)(VR) 🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ማለት አሁን ካለንበት የገሀዱ ዓለም አውጥቶ ወደ ሌላ የዲጅታል
✴️ ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1- 🚩ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtual Reality)(VR) 🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ማለት አሁን ካለንበት የገሀዱ ዓለም አውጥቶ ወደ ሌላ የዲጅታል ዓለም የሚዘፍቅ (Immerse) አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው። 🚩ለምሳሌ እናንተ ቤታችሁ ውስጥ ናችሁ እንበል ወይም ቢሮ ውስጥ ወይም ታክሲ ውስጥ ናችሁ...ወዘተ....ባጭሩ አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በህይወታችሁ "ባየሁት!" ወይም "ባደረኩት!" ብላችሁ ወደ ምትመኙት ዓለም መጓዝ ብትመኙስ? ወይም 🚩አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በአራዊቶች የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ መሆን ብትፈልጉስ? ሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ከሻርኮች ጋር መዋኘት ብትመኙስ?....ወይም ደግሞ አውሮፕላን ማብረር ብትፈልጉ... 🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ካላችሁበት ዓለም ሳትንቀሳቀሱ ወደ ተመኛችሁት ዓለም የሚወስድ እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው። ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት እንደ መነፅር ዓይናችን ላይ የምናጠልቀው መሳሪያ (Head-mounted Device) ያስፈልገናል። Part 1 ════❁✿❁ ═════ #Technology_News #የቴክኖሎጂ_ዜና t.me/TechnologyMasterPage