cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

The Christian News

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት። @TCNEW

Больше
Рекламные посты
4 920
Подписчики
-324 часа
+107 дней
+7930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#ቤተ #በአዲስ አበባ በሆሳዕና ለረጅም አመት እያገለገለች የምትገኘዉ ቤተምህረት #አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል። #አድራሻ ፦ ከቡልጋሪያ #ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል። #ቤተ ምህረት እንገናኝ 🙏🙏
Показать все...
👍 16 9🔥 1👏 1🕊 1
#የአርሰናል ደጋፊዎች በቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረቡ። በኬንያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ከድል በኋላ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ምስጋና አቀረቡ በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የሚገኙት የአርሰናል ደጋፊዎች ቅዳሜ እለት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቡድናቸው ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 0 በመርታቱ አድናቆትን ከማትረፍ ባለፈ በአንድ አጥቢያ ቤተክርስትያን በመሰባሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ደጋፊዎቹ የመድፈኞቹን ማሊያ ለብሰው በእሁድ ጠዋት አገልግሎት ላይ ቡድናቸው ላሳየው አስደናቂ ብቃት በደስታ ውዳሴ እና ምስጋና አቅርበዋል።በመጪው የውድድር ዘመን ለአርሰናል ቀጣይ ስኬት ተስፋ በማድረግ ጸሎት አቅርበዋል። ከታዳሚዎቹ መካከል ጋዜጠኛ ኬኔዲ ሙሪቲ በፀሎት ስነ ስርዓቱ ላይ የተነሱትን ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቱን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።የሰሜን ለንደኑ አርሰናል አንድ ጨዋታ ከሚቀረው ማንቸስተር ሲቲ እኩል እና ከሊቨርፑል በአምስት ነጥብ ዝቅ ብሎ ተቀምጧል። ፎቶዎቹ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን የፈጠሩ ሲሆን አንዳንዶቹ በደጋፊዎች ላይ አፌዜዋለሁ፡፡
Показать все...
😭 11👍 4 2🙏 1🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ራስን ማጥፋት የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ Assisted Suicide #ወይም በእገዛ ራስን ማጥፋትን እየተቃወሙ ይገኛሉ። ይሄንን ያውቁ ነበረ። በአለማችን 15 ሃገራት በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ይፈቅዳሉ። በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ማለት፣ #አንድ #ሰው ራሱን ሲያጠፋ በሃኪም እገዛ ህጋዊ በሆነ መንገድ የህይወት ጉዞውን ማብቃት ማለት ነው። የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት ይሄንኑ ድርጊት በሃገሪቱ ህጋዊ እንዲሆን መጠየቁን ተከትሎ ነው ድምጻቸውን ያሰሙት። ለ129 የምክር ቤት አባላት በተላከው ደብዳቤ መሰረት፣ በአንድ የምክር ቤቱ አባል የቀረበውን ይሄንኑ አጸያፊ ተግባር ህጋዊ እንዳይደረግ ጠይቀዋል። በደብዳቤያቸው፣ ይሄ ህግ የሰው ልጅን ሞራላዊነት አሽቀንጥሮ መጣል ነው፣ እንደ ሃገር አለን የምንለውን የሰው ልጆች ዋጋ የሚያሳጣን ነው ብለዋል። ህጉ የሚጸድቅ ከሆነ ስኮትላንድ ስነምግባር የሌለባት፣ ምክር ቤታችንም ለሰው ልጆች ዋጋ የሌለው አዳራሽ መሆኑ ነው ሲሉ አሳስበዋል። በእገዛ ራስን ማጥፋት ማለት የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ የሌለው መሆኑን ማሳያ ነው። ዘፍጥረት ላይ #እግዚአብሔር በአምሳያው የሰውን ልጆች መፍጠሩ፣ ሁሉም የሰው #ልጆች በእግዚአብሔር እንደሚወደድ ማሳያ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ አለው ብለዋል። ይሄንን ደብዳቤ የላኩት ቄስ አንድሪው ዶውኒ እና ቄስ ቦብ አክሮይድ የዩናይትድ ፍሪ ቸርች ኦፍ ስኮትላንድ አገልጋዮች ናቸው። ሃገራችን ስኮትላንድ ሰዎች ራሳቸውን ማጥፋት የማያስቡባት መሆን አለባት ብለዋል። ምናልባት በመሰል ስሜት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ማህበረሰባችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቅርና እንክብካቤ ማሳየት አለበት ብለዋል። ስኮትላንድ የ1517ቱ ተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ያገዙት ጆን ኖክስ ትውልድ ሃገር መሆኗ ይታወሳል።
Показать все...
👍 12🕊 2🔥 1😭 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአፍሪካ ወንጌላዊያን ማህበር በአዲስ አበባ ስብሰባውን አካሄደ። ማህበሩ ባካሄደው ስብሰባው የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተጽኖ የሚያደርሱ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት፣ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ማህበሩ በአፍሪካ የሚገኙ ከ250 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናትን ያቀፈ ነው። በስብሰባው የአፍሪካ ህብረት በ2063 ሊያሳካ ካቀዳቸው ግቦች መካከል ጤናማ ዜጋ መፍጠር እና ተሸጋጋሪ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ማድረግን እንደሚያግዝ በመድረኩ ተነስቷል። አፍሪካን የበለጸገችና ሰላማዊ ለማድረግ እንደሚሰራም የአፍሪካ ወንጌላዊያን ማህበር ገልጿል።
Показать все...
👍 13 5🔥 1🥰 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#እንኳን #ደስ አለህ #ወጣቱ ወንድማገኝ የመላዉ አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ጉባኤ የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ ናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘዉ በ12ኛው የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ወጣቶችን በመወከል የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል:: The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ደስታ እየገለፅን #መልካም የአገልግሎት #ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን። Wondmagegn Udessa Bidire 🙏🙏🙏
Показать все...
👍 26👏 6 3🥰 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ኑ አብረን እናመስንግን #እግዚአብሔር ድል ሰጥቶናልና #50 የድል ዓመታት የመሠረተ ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን የመዘምራን ቡድን "ቢጫ ለባሾቹ" የምስረታ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል በድምቀት እያከበሩ ነው። በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እየተከናወነ በሚገኘው የምስጋና ፕሮግራም የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል። የመዘምራን ኳየሩ ዝማሬዎቹን ለእግዚአብሔር ክብር ፤ ለህዝቡም በረከት እንዲያቀርብ ከተመሠረተበት ከ1966ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ ውስጥ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያዎች ፤ በባህር ማዶ በየኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አጥቢያዎች ሲያገለግሉ እንደቆዩ መድርረኩ ተጠቅሷል። The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለዘጋባ በስፍራው በመገኘት እየተከታተለን ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
Показать все...
👍 12 7🕊 2🔥 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
"... ማን ያውራ ? የነበረ ...." የባሊ አቦው ልጅ የሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ተማሪው የመጀመሪያ የጰንጠቆስጠ ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ምስረታ ውስጥ የነበሩ ባህር ተሻግረው ቤተክርስቲያን በመትከል እና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ላይ በትጋት የሰሩ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከ60 ዓመት በላይ በማገልገል ባለውለታ የሆኑት ፓስተር ዶክተር ዘለቀ አለሙ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል። በትዳር ከ46 ዓመታት በላይ ተሻግረዋል በምዕራቡ አለም ያላቸው ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሊገዙ እየተሰናዱ እና "ግሬስ" በተሰኘ ሴንተር የሰው ልጆች በሙሉ በክርስቶስ የተደረገልን ምንድነው የሚለውን እንዲረዱ ለመስራት እና ለመስበክ እና ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እቅድ እንደነበራቸው በአንድው ወቅት The Christian News - የክርስቲያን ዜና ጋር #የክርስቲያን እንግዳ ሆነው ድንቅ ቆይታ ባደረግንበት ጊዜ አጫውተውን ነበር። "... ማን ያውራ ? የነበረ ..." እንዲሉ የኢትዮጵያ ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር መተረክ ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ መጋቢ ዘለቀ አለሙ (ዶ/ር) ነው። "ሕይወቴ እና ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር በኢትዮጵያ" በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ቀድመው አስተያየት ከሰጡ ሰዎች መካከል መጋቢ በቀለ ወልደ ኪዳን አስተያየታቸው ሰጥተዋ ነበር። በቻናላችን ከ2ዓመት በፊት ያደረግንላቸውን ቃለ መጠይቅ ሊንኩን በመጫን እንድትመለከቱ ግንዣችን ነው። https://youtu.be/1FHp-jLOZJI?si=Fn1MqoGRvgaFq30H
Показать все...
6👍 2😭 2🔥 1🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ታላቁ #የወንጌል #አርበኛ #ወደ #ጌታ ተሰበሰቡ መጋቢ ሰለሞን ጂኖሎ የሻሸመኔ አጥቢያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መሪ መጋቢ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል። በወንጌል ላልተደረሱ አካባቢዎች ወንጌል የማድረስ ሸክም ሲሰሩ ቆይተዋል። በእንዲህ ሁኔታ በመሰጠት የሚያገለግሉ አባት ማጣት እጅግ ልብን የሚሰብር ዜና ቢሆንም ወዳገለገለው ጌታ ተሰብስቦአልና እንጽናናለን። መጋቢ ሰለሞም የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በመሆንም ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል። ጌታ ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
Показать все...
👍 21😭 13🕊 2 1🥰 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቤተክርስቲያን ምክር አልሰማ ብላችሁ የባንክ ደብተር ይዛችሁ ወደ ሐሰተኞች የምትነጉዱ #ሥራ_ፈቶች ሆይ “በጸሎት ሒሳብ ላይ የሚጨመር ቁጥር የለም” ብሏችኃል አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት (ዋልታ ቲቪ) ያለ ሥራ የሚገኝ በረከት የለም::ያለ አንተ ሥራ የሚገኘው ደህንነት ወይም በክርስቶስ የሚገኝ የዘላለም ሕይወት ብቻ ነው::
Показать все...
👍 50😭 3 2👏 2🔥 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ጅማ ክርስቲያን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖ ካምፓስ የቀድሞ የ#ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት (ኪቶ ፋሚሉ) አባል የነበሩ ተማሪዎች መልካም ግንኙነት ሊያስቀጥል የሚችል ክርስቲያን ኔትወርኪንግ ኢቨንት ተካሄደ። #ይህ ለሁለተኛ #ጊዜ የተዘጋጀው ፕሮግራም በዋናነት ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ወጥተው በተለያዩ የግል የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ተማሪዎችን ግንኙነት ማስቀጠል #እና የተሰማሩበትን የቢዝነስ ዘርፍ አስተዋውቀው #መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም አቤኔዜር ማቴዎስ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል። አቤኒዘር አክሎ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ግንኙነቱ ሲቀጥል አይታይም ይህን ክፍተት ለመቀነስ ያሰበ መልካም ግንኙነት እንደሆነ ተናግሯል። ይህ ሕብረት በቀጣይ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ውጪ የሚገኙ ሕብረትን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ወጣት አቤኔዜር አክሎ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል። ክርስቲያን #ዜና ያናገራቸው በፕሮግራሙ #ላይ የሚሰሩትን የተለያዩ ስራዎችን ይዘው የቀረቡ የቀድሞ ተማሪዎች ይህ የህብረት ፕሮግራም ከሌሎች ጋር የመተዋወቅን እና የቢዝነስ ስራ በጋራ ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነግረውናል። The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዘገባውን አዘጋጀን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በክርስቲያን ዜና የዮቲዩብ ቻናል ይዘን እንመለሳለን።
Показать все...
👍 18 2👏 1🙏 1