cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ከሰለፎች መንደር

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 http://t.me/keselefoch_mender አስተያየት ካለወት በዚህ ያድርሱን 👇👇👇 @UmuYusufBot

Больше
Рекламные посты
324
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የጁመዓ ኹጥባ (ምክር) ርዕስ "በዲን ላይ መፅናት" በሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን ሃፊዞሁሏህ በባህር ዳር መስጅደል ቡኻሪ ሚያዚያ ‐ 06 ‐ 2015 #መጠን_6.03mb #እርዝመት_26min የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Показать все...
06_08_2015,_በዲን_ላይ_መፅናት,_በሸይኽ_ሐሰን_ገላው.mp36.03 MB
#አዲስ_ሙሓዶራ ~–➻➝➻➝➻➝➧ ክፍል፡- 1⃣ ርዕስ፦➘➘➘ ➧ « ኢስላሚዊ ጋብቻ እና ተያያዥ ነጥቦች » በሚል ርዕስ 🎙 በሸይኽ ዐብዱልሃሚድ ያሲን አል-ለተሞ ሃፊዘሁሏህ ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል፡- ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ➡️ ኢስልምና በየትኛውም ዘርፍ የተሟላ እና ሰፊ አስተምህሮት ያለው ስለመሆኑ፣ ➡️ እስልምና ከሌሎች ሀይማኖቶች በ3 ነገሮች የሚለይ ስለመሆኑ፣ ➡️ ትክክለኛው ኢስላም ሙሉ ተውሒድ ስለመሆኑ ፣ ➡️ እስልምና ምንም ጉድለት የለለበት ሀይማኖት ስለመሆኑ፣ ➡️ ተዉሒድ/ኢማን ሙስሊሞች ከየትኛውም ቦታ እንዲገናኙ፣እንዲፈቃቀዱ፣ አደራ እንዲባባሉ ትልቅ ምክናየት ስለመሆኑ ፣ ➡️ ጋብቻ አንዱ የኢማን ክፍል ስለመሆኑ፣ ➡️ የአላህን ብቸኝነትና አምልኮት ለእርሱ ብቻ የሚገባ መሆኑን የምንማርበት ስለመሆኑ፣ ➡️ ጋብቻ የልብ መርጊያዉዴታ እና እዝነትን በተጋቢዎች መካከል የሚያመጣ ስለመሆኑ ➡️ የትዳርን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ !!!!፣ 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 🌷በዉዱ ወንድማችን እና በኡስታዛችን ኡስታዝ ዓብዱልቃድር ሀሰን ሃፊዘሁሏህ እና በእህታችን ሙኒራ ሻኪር ኒካህ ፕሮግራም ላይ የተደረገ ሙሓደራ።🌷 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 🎁 بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير. اليوم يوم الأحد شوال ١٠/ ١٠ / ١٤٤٤ 🕌በአዳማ ሰለፍዮች መስጂድ " ኢብኑ ተይሚያ መስጂድ" 🗓 እሁድ ሚያዚያ 22/2015    ➴➘➷ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ t.me/abufewuzanabduselam t.me/abufewuzanabduselam
Показать все...
ኢስላማዊ ጋብቻ እና ተያያዥ ነጥቦች.mp32.00 MB
👉 የረመዳን ግማሽ ሰዎች አላህ ያዘዛቸውን ሰርተው ሳይጨርሱ ወደ አላህ እንቃረባለን እያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን ያመጣሉ ። በእስልምና ዲን ወደ አላህ እቃረብበታለሁ ተብሎ የሚሰራ ማንኛውም ስራ ከቁርኣንና ሐዲስ መረጃ ሊኖረው ይገባል ካልሆ ስራው ወደባለቤቱ ተመላሽ ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ። በአብዛኛው በእስልምና ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን አላህን በመገዛትና ወደርሱ በመቃረብ ስም የሚያመጡት ራፊዳዎችና ሱፍዮች ናቸው ። እነዚህ አካላት ካመጡዋቸው ቁጥር ስፍር የሌላቸው አዳዲስ ፈጠራዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የቀብርና የሙታን መንፈስ አምልኮ ፈጠራ ነው ። ይህ ከእስልምና የሚያወጣና የዘላለማዊ ጀሀነም ባልተቤት የሚያደርግ የኩፍር ተግባር ነው ። ታዲያ እነዚህ በኢስላም ስም ሙስሊሙን የሚያከፍሩ አካላት እነዚህን የኩፍር ተግባራት የተለያየ ስም በመስጠት እንጂ ፊት ለፊት ይዘው አይመጡም ። ለቀብርና ለሙታን መንፈስ አምልኮት ከሚሰጡዋቸው ስሞች አንዱ ረመዳን ግማሽ ( نصف رمضان ) የሚል ነው ። ከዚህ የሚፈልጉት በረመዳን 15 የአምዋት ( ጀምዑ መይት) ቡና በሚል ወደ ሙታኖች ደም በማፍሰስ ለመቃረብ የሚታረድ እርድ ነው ። ይህ ተግባር ( ደም በማፍሰስ ) ትልቅ የአምልኮ ክፍል ሲሆን ለአላህ ከሆነ በጣም ትልቅ ዒባዳ ነው ። ነገር ግን ሸሪዓ ባላዘዘው መልኩ ጊዜ ገድቦ ከተደረገ ለአላህ ተብሎም ቢሆን ቢዳዓ ነው ። ከአላህ ውጪ ላለ አካል ከሆነ ግን ከእስልምና የሚያወጣ ኩፍር ነው ። አምዋት በየትኛውም ወርና ቀን ቡና አያስፈልጋቸውም ሱስም የለባቸውም ። ነገር ግን ደካሞችን በእምነታቸው መፈተን የሚፈልጉ የኢስላም ጠላቶች የህፃን ፀጉር ሽበት የሚያስበቅልን የኩፍር ተግባር ቀለል አድርገው ስም ቀይረው ሙስሊሙን ይግቱታል ። ረመዳን ግማሽን ከሌሎች ቀናቶች በተለየ መልኩ የሚደረግ ዒባዳ የለውም ። በመሆኑም የረመዳን ግማሽ በሚል ወደ ሙታን ለመቃረብ የሚደረገው እርድም ሆነ ሌሎች የትኞቹም ተግባራት እስልምናችንን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ። አንድ ሰው በዚህ ቀን አጥቼ ነው እንጂ ለአምዋት አርድ ነበር ወይም ቅርጫ እገባ ነበር ብሎ ኑፍሮ ቢቀቅል አርዶ ወደ ሙታን እንደተቃረበ ሰው ነው ። አዳዲስ ፈጠራ ከማምጣታችን በፊት የታዘዝነውን ሰርተን እንጨርስ ። አላህ ለሚወደውና ለሚፈቅደው ይወፍቀን ። https://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

የረመዷን ምክር 03 በኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ #መጠን_5.88_mb #እርዝመት_25min #1444_ሒ. የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Показать все...
03,_የረመዷን_ምክር,_በኡስታዝ_ዩሱፍ_አህመድ.mp35.88 MB
የቃጥባሬ መንዙማ በሚል ርእስ በ26/6/2015 በቃጥባሪ መንደር የተደረገ ሙሐደራ https://t.me/bahruteka
Показать все...
የቃጥባሬ መንዙማ.mp39.34 MB
#سورة_الكهف #بصوت:عبد الله الخلف. "ሀያዕ ከ ኢማን ነዉ ይህ ምክሬ ላንቺ ነው!" ውዷ እህቴ ሆይ ተሸፈኚ በሀያዕሽም ንግስት ሁኚ •┈┈•◈◉❒{💎}❒◉◈•┈┈• 【ምክር ለሙስሊሟ እህቴ➧ 👇 ሊንኩን ሼር ያርጉ https://t.me/joinchat/AAAAAFdt3svRi8IOt5es0A
Показать все...
018.mp334.40 MB
👉 ጥቂት ስለ ዐረብ ሀገር ያሉ እህቶች ዐረብ ሀገር ስላሉ እህቶች ሲታሰብ ብዙ ሀሳቦች እየተገፈታተሩ እኔ ካልወጣሁ ይላሉ ። በመጀመሪያ ደረጃ ኢስላም ሴት ልጅ ያለ መሕረም ( ዘመድ የሆነ ወንድ ) መንገደኛ መሆን እንደማትችል ያስቀምጣል ። መንገደኛ ማለት ሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ አንድ ሰው ቤተሰቡን ተሰናብቶ ክ/ሀገር ወይም ወደ ውጪ ልሄድ ነው ብሎ የሚዘጋጅበትና ከቤተሰብ ተለይቶ የሚሄድበት መንገድ ማለት ነው ። ስለሆነም ሴት ልጅ ለብቻዋ በዚህ መልኩ ቤተሰብዋን ተሰናብታ መንገደኛ መሆን አትችልም ። ይህ መብትን መንፈግ ሳይሆን እሷን ከመጠበቅ ነው የሚቆጠረው ። ይሁን እንጂ አብዛኛዎች እህቶቻችን ለእስልምና ያላቸው ግንዛቤ በቂ ካለመሆኑ የተነሳ ይህንን ህግ ይጥሳሉ ። ወደ ውጪ ሀገር በተለይ ዐረብ ሀገር የሚሄዱት የድሀ ቤተሰብ ልጆች ናቸው ። ቤተሰቡም ልጄን አሳድጌ ለመልካም ትዳር ማብቃት አለብኝ ሳይሆን መች ቶሎ አድጋ ዐረብ ሀገር ሄዳ ህይወቴን በቀየረችልኝ ነው የሚለው ። በተለይ ጎረቤት አካባቢ ዐረብ ሀገር ሄዳ ትንሽ ለውጥ እንዲታይ ያደረገች ካለች ጉጉቱ ይጨምራል ። ይህን ሀሳብ ይዘው ወደ ዐረብ ሀገር የሚሄዱት እህቶች በጣም ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር አብዛኞቹ ከወራቶች በኋላ የሄዱበትን አላማ ይረሱታል ። ከላይ እንዳልኩት አብዛኞቹ የድሀ ቤተሰብ ልጆች ሲሆኑ በተለይ ከገጠሩ የሀገራችን ክፍል ይበዛሉ ። ማለትም ምንም አይነት የዲን ግንዛቤ የሌላቸው ይበዛሉ ማለት ነው ። ዐረብ ሀገር እንደሚታወቀው አንድ የሀበሻ ወንድ ቤት ተከራይቶ ከ20 – 30 የሚሆኑ ሴቶችን ይሰበስባል ። ማለት ሴቶቹ እረፍት ሲወጡ ወይም ስራ ሲፈቱ ማረፍያ እንዲሆናቸው ራሳቸው ቤት መከራየት ስለማይችሉ በዚህ መልኩ ይሰበሰባሉ ። አብዛኛው ጊዜ ወንዶቹ ከሴቶቹ በየወሩ ለቤት ኪራይ በሚል የሚቀበሉት ብር ስራ እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል ። እቤት ይቀመጣሉ ማለት ነው ። ከዛ ለሴቶቹ የእረፍት ጊዜ ፕሮግራም ይወጣል በየሳምንቱ እስከ አምስት ሴቶች እረፍት ይወጣሉ ቤቱ ይቀወጣል ። ሁለት ቀን እባካችሁን እንዝናና እያሉ ያላቸውን እያወዳደሙ ቆይተው ለወንዱ ለሳምንት የሚሆነውን ምግብ ሰርረው ፍሪጅ አስገብተው ይሄዳሉ ። የሳምንቱ ተረኞች ልክ እነዚሁ እያለ ይቀጥላል ። በዚህ መሀል አላህን የማይፈሩ ወንዶች ከመረጡት ጋር እንደፈለጉት ይሆናሉ ። ይህ የአብዛኛው ዐረብ ሀገር ያሉ ሴቶች ታሪክ ሲሆን የተወሰኑ በጣም ጨዋ አላማቸውን የማይረሱ እረፍት የማያበዙ ምናልባትም ከትክክለኛ መሕረማቸው ጋር እረፍታቸውን በስርኣትና በፕሮግራም የሚያሳልፉ አሉ ። የእነዚህ ቁጥር ከመጀመሪያው ጋር ሲነፃፀር በጣም ትንሽ ነው ። ሌሎቹና በጣም አናሳዎቹ ደግሞ ወደ ዐረብ ሀገር ከሄዱ በኋላ የዲን ግንዛቤ አግኝተው በሚገርም መልኩ በዲን ስም የሚነግዱ ኢኽዋንና ሙመዪዓ ሙሪድነት ሰለባ ሆነው የሰሩበትን የሚገብሩ ሲሆን ከዚህ በማይተናነስ መልኩ በኦን ላየን እናስተምራለን ለሚሉ ወጠምሻ በሰለፍያ ስም ለሚነግዱ የሚገብሩም ቀላል አይደሉም ። በኦን ላይን ላይ እናስተምራለን የምትሉ በምትበሉት ገንዘብ አላህ ፊት መጠየቃችሁን አስታውሱ እናንተን በተለይ ያልኩት ሰለፍዮች ናቸው ብለው ስለሚያምኗችሁ ነው ። በኦን ላየን ማስተማር አይቻልም ማለቴ አይደለም ። ነገር ግን የሚያስከፍሉትና ለማስተማር ቃል የሚገቡት ከገቡት ቃል ምንያህሉ እንደሚያስተምሩ እነርሱና አላህ ያውቁታል ። ሌሎች እህቶች አሉ ደሞ ኸይር ስራ ከተባለ ለነገ የማይሉ ለራሳቸውም ይሁን ለቤተሰብ የሚል የማያውቁ እነዚህ እህቶች በአላህ መንገድ ላይ ባወጡት ነገር እንዳይፀፀቱ ያስፈራል ። ሌሎች ደግሞ አፈር ግጠው እየሰሩ ለባል ወይም ወንድም ያገኙትን ሁሉ ወደ ሀገር ቁም ነገር ላይ ይውላል ብለው እየላኩ ነገር ግን ባልሰሩበት የሚዝናኑ አላህን የማይፈሩ ወይም የራሳቸውን ህይወት ቀይረው አላውቅሽም የሚሉ ቤተሰቦች ያሉዋቸውም አሉ ። ባጠቃላይ ዐረብ ሀገር ያሉትን እህቶች በተለያየ መንገድ የሚበዘብዙ በጣም ብዙ ናቸው ። እነዚህ እህቶች እድሜያቸው እየሄደ ትዳር ይዘው ልጅ ሳይወልዱ እያለፈባቸው እጃቸው ባዶ ሆኖ ሀገር መግባት እየከበዳቸው በፀፀት እሳት መንደድ ይጀምራሉ ። የተወሰኑ እዛ ሆነው ያላቸውን ለወንድም ወይም እህት እንዲሁም እንጋባለን ላሉዋቸው ወይም ለሱሰኛ ባለቤታቸው ሲልኩ የነበሩና እናርፋለን ብለው ሲመጡ ያ እረፍት አጥተው ተቃጥለው የሰበሰቡትና የላኩት ገንዘብ መና ቀርቶ ለዚያራ ለመሄድ የታክሲ ሲያጡ ተመልሰው የሚሄዱ አሉ !!!። ይህ በጣም ከብዙ አሳዛኝ ህይወታቸው ጥቂቱ ነው ። ለማንኛውም እነዚህ እህቶች የህይወታቸውን አቅጣጫ ቶሎ ለማስተካከል ወስነው ከአላህ እርዳታና እገዛን ጠይቀው ወደራሳቸው ሊመለሱ ይገባል ። ራስ በሰሩት ስህተት አላህን ማማረር ወንጀል ነውና ይጠንቀቁ ። አላህ ለኛም ለእነርሱም መልካሙን ይምረጥልን ። https://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

እነሞር ወረዳ ጉንችሬ ሀይ እስኩል ተጀምሮ እየተዛመተ ያለው ህገ – መንግስቱን የተቃረነ ስልጣንን ለግል አመለካከት ማስፈፀሚያ ያደረገ የአክራሪ አፄያዊያን አስተሳሰብን ያነገበ አካሄድ አራማጅ አመራር ኒቃብ ለብሶ ትምህርት ቤት መምጣት ወንጀል ነው ብሎ ታዳጊ እምነቷ ያዘዛትን ኒቃብ የለበሰሽ ሴት ልጅ እስር ቤት አጉሯል ። ህግ የለም እኛ የፈለግነው ነው የሚሆነው ብለው ኒቃብ የለበሱ ሴቶች ከትምህርት ቤት ይውጡ ካልሆ መማርም ማስተማርም አይቻልም ብለው መምህር እየደበደቡ ፣ የተፃፈውን እያጠፉ ፣ ክፍል ውስጥ እየዘመሩ ፣ ለፀሎት ሄደን እስክንመጣ ትምህርት እንዳይጀመር ብለው የሚያስጠነቅቁ አክራሪ ኦርቶዶክሳዊያንን እንዲያስቆሙ እባካችሁን ሲባሉ አቤት ያላሉ የፀጥታ ሀይሎች እስከመጨረሻው በትእግስት መሄድ የነበረባቸው ግን ማድረግ ካልቻሉ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር በተፈጠረ ፀብ ምክንያት ቤት ለቤት እያሰሱ ማጎር የበቀል መወጣጫ ማድረግ ስራቸው አደረጉት ። ይህ ተግባር ስርአቱን የሚመራው የበላይ አካል አይቶ እልባት ሊሰጠው ይገባል ካልሆነ በተቃራኒ አጋጣሚዎችን እየተጠቀመ ሙስሊሙን ወጣት ለጥፋት የሚዳርገውን የኢኽዋን አንጃ ወጣቱን መጠቀሚያ አድርጎ አሳዛኝ ክስተት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል ። የአሁኑ ስርኣት መሪ የሆኑት ዶ/ አብይ አሕመድ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አባት እንዲህ ሲሉ ጥያቄ ጠይቁዋቸው እርሶ እላይ ነው ያሉት ታች የሚሰራውን እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ ? የሰጡት መልስ በጣም ደስ የሚል ነበር ። መልሱ ምን መሰላችሁ አባት ሆይ ከየት መጥቼ ነው እላይ የወጣሁት ከታች እኮ ነው ። ስጋት አይግባዎት አውቀዋለሁ የሚል ነበር ። https://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

አጭር መልዕክት (12) "ሩቃን የሚመለከቱ ሶስት ተግሳፆች" 1ኛ, ለሩቃ አድራጊዎች 2ተኛ, ለሩቃ አስደራጊ ቤተሰቦች 3ተኛ, ሩቃ ለምታስቀሩ ሴቶች በሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ ጥር 19–2015 EC በኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ የተደረገውን የጁመዓ ኹጥባ ለማጠናከር ያስተላለፉት የ7 ደቂቃ መልእክት። የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Показать все...
ሩቃን_የሚመለከቱ_ሶስት_ተግሳፆች,_በሸይኽ_ሐሰን_ገላው_19_05_2015.mp31.66 MB
አዲስ ሙሓዶራ ርዕስ – "የነብያትና የሰለፎችን ታሪክ ማወቅ ያለው ፋይዳ" በወንድም አቡበክር ዩሱፍ ሃፊዞሁሏህ ጥር ‐ 14 ‐ 2015 በባ/ዳር ዑመሩል`ፋሩቅ መስጅድ የተሠጠ ሙሓዶራ #መጠን_11.29mb #እርዝመት_49min የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Показать все...
የነብያትና_የሰለፎችን_ታሪክ_ማወቅ_ያለው_ፋይዳ,_በወንድም_አቡበክር_ዩሱፍ,_14_05_2015.mp311.29 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.