cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

FAVOUR OF GOD official channel

you are the first to get the favour of Lord. join this channel.Blessed🙏

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
179
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Repost from ናዝራዊ Tube
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንደ ተናገረው ተነስቷል! መቃብሩ ባዶ ነው። እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! @nazrawi_tube
Показать все...
Repost from ናዝራዊ Tube
Фото недоступноПоказать в Telegram
"ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለመወደዴ ማስረጃው ከእልፍ አእላፋት ምስክሮች በላይ ገዝፎ ቆሟል። መድኅኔ ፍቅሩን ለመግለጥ በመስቀል ላይ በደሙ ቀለም ጽፎ ደብዳቤውን (ክቡር እሱነቱን) በችንካር ላይ ለጥፎታል (1ዮሐ. 3፥16)። . ዓለሙን የወደደው ቸሩ እግዚአብሔር የአልማዝ ፈርጥ ሳይኾን ሕይወቱን በልጁ ሰጠን። እኔ ችንካር እርሱ ፍቅር ኾነ። በወጋሁት እጁ አቀፈኝ። ባፈሰስሁት ደሙ ከኀጢአቴ ዐጥቦ አነጻኝ። ያቈሰልሁት ዐመፀኛው ችንካር እኔ ብኾንም፥ በቍስሉ ግን አከመኝ። እናንተንም በፍቅሩ ያክማችኋልና ወደ እርሱ፥ ኑ።" ከ "የዱባ ጥጋብ፥ ገጽ 410፥ የተወሰደ @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Показать все...
Repost from ናዝራዊ Tube
Фото недоступноПоказать в Telegram
ክብርን እንደ ሸማ የተጎናጸፈ እርሱ፣ ዕርቃኑን በመስቀል ላይ ተንጠለጠለ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Repost from ናዝራዊ Tube
ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።" ( ኢሳ. 53:7) ለዕርድ እንደሚነዳ በግ፣ ያለምንም ተቃውሞ ለአሰቃዮቹ የጭከና ፈቃድ ራሱን ሙሉ ለሙሉ አሳልፎ በመስጠት፣ ክርስቶስ ስለ በደላችን በመስቀል ላይ ተቸነከረ። በግ መታረድ ሲጀምር ባለው ኀይል ሁሉ ለማምልጥ ይታገላል እንጂ በፈቃድኝነት ራሱ አይሰጥም። ጌታችን ግን በፍጹም መታዘዝ ካህንና የመስዋዕቱ በግ በመሆን፣ በሞቱ ከእግዚአብሔርና እርስ በእርስ አሳታረቀን። ክርስቶስ በአካል ብቻ ሳይሆን በክፉ ቃላት ውስጡ ተጐድቷል፤ ተከድቷል፤ ስሙ ጠፍቷል፤ ብቸኛ ሆኗል፤ "“ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!" ያለው ያው ሕዝብ፣ ለስቅለት ሞት አሳልፎ ሰጥቶታል። ከተሸከመው ኀጢአታችን የተነሣ ወኪላችን በመሆን የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ በእርሱ ላይ አርፎአል። በእግዚአብሔር የድነት ዕቅድ ውስጥ፣ መስቀሉ ደግሞ መካከለኛ ነው። በመስቀሉ ላይ፣ የእግዚአብሔርም ፍጹም ፍትሕና ፍጹም ፍቅር ተገናኙ። ኀጢአት ያመጣብንና ልንቀበለው የተገባውን የእግዚአብሔር ቁጣና የሞት ፍርድ፣ ክርስቶስ ቤዛ በመሆን ወሰደልን። ኀጢአታችንን ተሸክመ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ ወሰደለን። ኀጢአት የገፈፈንን የእግዚአብሔር ክብር፣ ክርስቶስ ክብር አጥቶ መለሰለን። ቅዱስ ስሙ ለዘላላም የተባረከ ይሁን! ክርስቶስን ከዚሁ የመስቀሉ የዋጆ ሥራ ለማስተጓጐል፣ ከካህናት አለቆችና ከነገሥታት ጀርባ በመሆን በማንነቱና በመጣበት ዐላማ ላይ የመጨረሻውን የሥነ-ልቦና ጦርነት ያወጀው ሰይጣን ነበር። ይኸው የቀደመው ጠላት ነበር፣ ከአርባ ቀናት ጾምና ጸሎት በኋላ ዝሎና ደክሞ የነበረውን ክርስቶስን በምድረ በዳ የፈተነው። ከጴጥሮስ ጀርባ ሆኖ የክርስቶስን የመስቀል ሞት የተቃወመው፣ ይኸው የቀደመው ጠላት ነበር። ክርስቶስም፣ “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን” (ማቴ 16:23) በማለት በጽናት ተቃውሞታል። "ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን። "በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ይል ስለ ነበር እስቲ ከወደደው አሁን ያድነው!” (ማቴ 27:42-43) የሚለውን ፈታኝ ጥያቄ በፍጹም ትዕግሥትና ዝምታ ያሳለፈው፣ ከፊቱ ያለውን የእግዚአብሔርም ዘላለማዊ የድነት ዐላማ በማሰብ ነበር። ይህ የሕማም ሰው፣ ስለራሱ ማንነት፣ ስለንጽሕናውና ስለ መብቱ አልተሟገትም። መከራው ሁሉ ኢ-ፍትሐዊ ነበር፤ ሆኖም እኛን ለማዳን እስከ መስቀል ሞት ድረስ የታዘዘ ሆነ። ዝም አለ። በኋላም፣ ዐይኑ የበራለትም ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦ “እርሱም ኀጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ” (1ጴጥ 2:22-23)። የዋጀን ዝምታውም ነው -- ያለፍትሕ በትዕግሥት የተቀበለው መከራ! በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር ሳይቆጥር፥ ራሱን በፈቃዱ ባዶ የማድረጉ ጫፍ በፍጹም ዝምታውና ትዕግሥቱ ተገልጧል። የሥላሴ አካል ሆኖ ሳለ፣ ዐቅም እንደሌለው ዝም አለ። ፍጡር ጲላጦስ በአምላክ ላይ ያልተገደበ ስልጣን አንዳለው ሲናገር፣ አምላክ ዝም አለ! ኢሳይያስም በመገረም “እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።” አለ። ክርስቶስ ባሳለፈው መከራ ውስጥ፣ ትልቁ የመታገሡ ጉልበት ያረፈው፣ “በጽድቅ ለሚፈርደው [ራሱን] አሳልፎ” ለእግዚአብሔር በመስጥት ላይ ነበር። ይኽም በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ የነበረውን፣ ፍጹም መሰጠት ያሳየናል። ይኽ የሕማም ሰው፣ ስለ እኛ ድነት ዝምታን መረጠ! እርሱ “የሚስብ ውበት ወይም ግርማ አልነበረውም፤ እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም። በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም። በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤. . . በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን . . . እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው። ስለ እኛ ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ኀጢአት ተመቶ . . . ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ . . በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ . . . የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።" (ኢሳ. 53) ወሰን የሌለው ፍጹም ፍቅር! ምላሻችን ምን ይሆን? ይህ ፍቅር የተራበ ትውልድ፣ ይህን የክርስቶስ ፍቅር በእኛ ውስጥ ያይ ይሆን? አቤቱ ቅዱስ አባት ሆይ፤ የመስቀሉ ፍቅር እንደገና ያድሰን። አሜን! ____ ዶ/ር ግርማ በቀለ @nazrawi_tube @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram