cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Больше
Рекламные посты
13 591
Подписчики
Нет данных24 часа
+1217 дней
+62830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
ሀ/ አሥራት
ለ/ ምፅዋት
ሐ/ መስጠት
መ/ ማካፈል
✝✝ #መንፈሳዊ ጥያቄ ✝✝ ------------------------------------ 1️⃣ "ሚካኤል" ማለት ምን ማለት ነው?
Показать все...
እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ
ሰው አምላክ ሆነ
አምላክ ሰው ሆነ
ማን እንደ እግዚአብሔር
ሚካኤል ስለው  ስሙን ✞ ሚካኤል  ስለው ስሙን ስጠራ የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ አዛኝ ነው በእውነት ፍፁም አዛኝ የሚጠብቀኝ የሚያፅናናኝ / 2/ ካለቆች ጋራ ህዝቡን የመራ የሚመላለስ በዚያ ተራራ ባህሩም ሸሸ ከማደሪያው የጌታ መልአክ ሲያናውጠው    ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ፅፏል/2/      /አዝ = = = = = ከባዱን ጋራ ሚዳ ሆኖኛል የወይኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል አልናወጥም ከቶም አልፈራም የጌታ መልአክ ነው ከእኔ ጋራ    ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ፅፏል/2/      /አዝ = = = = = ትቢተኛውን አሸንፎታል ዳቢሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል ታላቅ ፀጥታ በሰማይ ሆነ እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ    ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ፅፏል/2/      /አዝ = = = = = ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሽ የሚቃወሙኝ አጥብቀው ሸሹ ታላቁ መልአክ  ከፊት ቀደመ ታሪክ ተሰራ እንባችን ታበሰ    ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ፅፏል/2/ 👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።   ╔✞═════●◉❖◉●════✞╗        ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ❖ @enamsgn @enamsgn ❖        ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ╚✞═════●◉❖◉●════​✞╝ ✍ ወድሰኒ
Показать все...
ሚካኤል ስለዉ.mp36.25 MB
3👍 1🥰 1
Repost from ወድሰኒ ​​
​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል! እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ። 👉 በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡ ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡ በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡ ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡ ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡ ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
Показать все...
👍 5 1🔥 1
📍 ሚካኤል_ይበልጣል_ክብሩ ሚካኤል ይበልጣል ክብሩ ከመላእክት(2) ዘወትርይቆማል ባምላክ ፊት (2) ሊያሰጠንምህረት ሚካኤል  ጠላት ተረማምዶ    >>    ቅጥራችንን ሳይወርስ    >>   ስፈር በዙሪያችን    >>   ደጃችን እንዳይፈርስ     >>   ምግባር የጎደለው     >>   ባዶ ጽዋችንን     >>   ቅድስናን ሞልተህ     >>   ውሰድ ለአምላካችን         /አዝ = = = = = ሚካኤል  በምስጋና ጅረት   >>     ነፍሳችን ትወሰድ   >>     ክብር ከተሞላ    >>    ከቅኔያት መንገድ    >>    ለየን አምላካችን    >>     እንስገድ ለክብሩ    >>    ውዳሴ ነውና    >>    የእግዚአብሔር  ሀገሩ         /አዝ = = = = = ሚካኤል  ለምህረት ረቧል   >>     ክንፍህ በላያችን   >>     በረከትን አዝለው   >>     ከላይ ከአምላካችን   >>     ከአርያም ጠፈር   >>      የቆሙት እግሮችህ   >>      የድል ዜና ይዘው   >>      ይምጡ ለልጆችህ         /አዝ = = = = = ሚካኤል  እንግዳ አይደለንም    >>     የልኡል በጎች ነን    >>     የለመለመው መስክ    >>     ከላይ የተሰጠን    >>     ጠላት እንዳይጥለን    >>     ከዕርስታችን ነቅሎ    >>     ያሳየን ታምርህ    >>     ክሳችንን ነቅሎ 👉ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ: #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።    ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗        ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞    ❖ @mezmuredawit  ❖    ❖ @mezmuredawit  ❖    ❖ @mezmuredawit  ❖         ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞   ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Показать все...
- Mahtot Tube - _ _ c_YDIJJC6EA.m4a8.86 MB
👍 3 1
ድረስ ሚካኤል ድረስ ሚካኤል አፅናኝ /2/ ተስፋ እንዳል ቆርጥ እርዳኝ የቤትህ አገልጋይ ባለሟል ነኝ ድረስ ሚካኤል በግራም በቀኝ    "           "     ፈታኜ መብዛቱ    "           "     ስምህን ስጠራ    "           "     ሁሉም ሆነ ከንቱ    "           "     ብንገዳገድ እንኳን    "           "     የሚደግፈኝ    "           "    የማከብረው መልአከ    "           "    ጎኔ ቆመልኝ          /አዝ ===== ድረስ ሚካኤል የግብፅ አስማተኞች    "            "     በፊቴ ሲቆሙ    "            "      አድነኝ ሚካኤል    "            "     ስልህ ተገረሙ    "            "    እንደ አፎሚያ    "            "    ስዕልህን ባሳያቸው    "            "     በዙሪያዬ የቆሙት    "            "     ዳግም አጣኋቸው      /አዝ ===== ድረስ ሚካኤል ተመኖርያው ስፍራ   "            "      ከእዮር ከራማ   "            "      በረረ መጣልኝ   "            "      ሀዘኔን ሲሰማ   "            "     ምስጋና ይድረሰው   "            "      የአምላክ ባለሟል   "            "      ከደንቃራ ነገር   "            "       ሰወረኝ እኔን መላከ ሰላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗ ✢    ✥ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖                 ✥   ✢    ╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Показать все...
ድረስ ሚካኤል .mp33.48 MB
👍 1 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
Показать все...
👍 2
ቆየት ያሉ ዝማሬዎች
አዳዲስ ዝማሬዎች
የንስሐ መዝሙሮች
የቸብቸቦ መዝሙሮች
ሁሉንም በአንድ ላይ
🎚 መንፈሳዊ ᴡᴀᴠᴇ Ғᴏʟᴅᴇʀ መግባት የምትፈልጉ ቻናላችሁ ከ 5ᴋ በላይ የሆናችሁ ! FOLDER LINK 👇 https://t.me/addlist/gDkv99HtoPg0Mjc8 አናግሩን ➛ @Dink_boy
Показать все...
👍 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.