cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈

Рекламные посты
13 494
Подписчики
+12124 часа
+8597 дней
+3 24430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ዐሥራ ሦስት የአብነት ደቀ መዛሙርት ዲቁና ተቀበሉ | ጃንደረባው ሚድያ | ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.| አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጃን እስጢፋኖስ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዳር የአብነት ትምህርት ያስተማራቸውንና መሥፈርቱን ያሟሉ ዐሥራ ሦስት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ አንብሮተ ዕድ ማዕረገ ዲቁናን ተቀብለዋል:: የኢጃት ቦርድ ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት "ኢጃት ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በጃን ማዕተብ ከሰባ በላይ ንዑሰ ክርስቲያንን ለምሥጢረ ጥምቀት ፣ ብዙኃንን በጃን ዮሐንስ ለምሥጢረ ንስሓና ቁርባን ፣ በጃን ቃና ዘገሊላ ደግሞ ለምሥጢረ ተክሊል ያበቃ ሲሆን አሁን ደግሞ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ለምሥጢረ ክህነት አብቅቶአል" ብለዋል:: "ዲያቆናቱ በአግባቡ የተማሩና ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ናቸው" ያሉት የጃን እስጢፋኖስ ሰብሳቢ መምህር ኤፍሬም ሲሳይ ሲሆኑ "ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት ትምህርት ሳይኖራቸው ወደ ኢጃት መጥተው በአግባቡ ተምረው ለዚህ በመብቃታቸው እጅግ ደስ ብሎናል:: ትምህርት ሳይጨርሱ ወዴትም እንዳይሔዱ በማስገደድም በአበው ልማድ መሬት ላይ እየተኙ በሌሊት እንዲማሩና ከአብነት ትምህርቱ ጋር መሠረታዊ ነገረ ሃይማኖትም እንዲማሩ ተደርጓል" ብለዋል:: በማያያዝም "በቅርቡ ሱባኤ እስጢፋኖስ የተሰኘ የዲያቆናት ብቻ ሱባኤ ጉባኤ ለማካሔድም ዝግጅታችንን ጨርሰዋል ብለዋል" ዲያቆናቱን አስተምረው ለዚህ ካበቁ መምህራን መካከል አንዱ የሆኑት መምህር ኃይለ ኢየሱስ ተሻለ በበኩላቸው "ወደ አገልግሎት ለመግባት በአግባቡ ደጅ ጸንተውና የአገልግሎቱን ምንነት ተረድተው ለዚህ መብቃታቸው ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ ለማገልገል ያስችላቸዋል:: ለዚህ ደርሰው ማየታችን ለኢጃት ትልቅ ደስታ ነው" ብለዋል::
Показать все...
5👍 1😘 1
✞ ድንቅ አድርጎልኛል ✞ ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ (፪) አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ (፪)             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ ድንቅ አድርጎልኛል ረክሼ ሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል እንዲ ለወደደኝ             አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показать все...
🙏 3👍 2 2
🧡 ሼር 🧡
✝️ በታላቅ ሥልጣን ተነሳ ✝️ እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት የኔታ #አባ_ገብረኪዳን_ግርማ https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1
Показать все...
4
✞ ሞት ይደንግጥ ✞ ሞት ይደንግጥ የአንተን ስም ሰምቶ ይሰንጠቅ ቀላዩ በግርማ ተረትቶ ቁጣውም ጸጥ ይበል ይራቅ አለማመን አሸናፊ ጌታ አንተ ብቻ ግነን(፪) ስምህ ላላመኑት የሚያፍገመግም ነው ሞትና ጨለማን ረትቶ የሰቀለው ድንጋያችንን ሰብረህ ጥለኸዋልና ድል መንሳቱ የለም ተሸንፏልና(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ሞትን እንቅልፍ አርገህ ቀይረህልናል እረፍት የምናልፈው ድልድያችን ሆኗል ትንሳኤህ ሰበረው መቃብሩን ሁሉ ቢሞቱ ያው ናቸው ያመኑ በሙሉ(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አለን በእምነት የምንወርሰው ስምህን ተሸክመን ነፍሱን ለአንተ የሚያኖር አያጣትምና ልባችንን ሰጠን ቀድሰው ግባና(፪)      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የአንተ ስም ሲሰማ ፈታኙ ደንብሯል ጌርጌሴኖን ያለው ሌጌዎን ተሰዷል ስንቱን አሳረፍከው ከከሳሹ እጆች አይደፍርም ከእንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጆች(፪)                   መዝሙር|      ዘማሪት| ፋንቱ ወልዴ "..ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።"                 ኢሳ ፳፭፥፰ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показать все...
👍 2 2
🧡 ሼር 🧡
✝️ ሲጨንቃችሁ እንዲህ በሉ ✝️ እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት የኔታ #አባ_ገብረኪዳን_ግርማ https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1 https://t.me/aba_gebre_kidan1
Показать все...
3
✝ ዕለተ አርብ እንኳን ለዕለተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳተ ብሉይ ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
➡️ ከትንሳኤ ሳምንት ቀናት ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን አንድም ነፍሳት በመባል ትታወቃለች::
➡️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:-
¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት ¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት ¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት ¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል::
✝️ ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :-
¤በመጸነሱ ተጸንሳ ¤በመወለዱ ተወልዳ ¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ ¤በጥምቀቱ ተጠምቃ ¤በትምሕርቱ ጸንታ ¤በደሙ ተቀድሳ ¤በትንሣኤው ከብራ ¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ ¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች:: ➡️ ድንገት የተመሠረተች ሳትሆን ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና የታሠበች: በዓለመ መላእክት የተወጠነች ናት:: በአማን ጐልታ: ግዘፍ ነስታ የተመሠረተችው ግን በደመ ክርስቶስ ተቀድሳ: በትንሳኤው ከብራ: ንጽሕትና ጽሪት ባደረጋት ጊዜ ነው:: መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን ሕልውና አይኖራትም ነበርና ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትከበራለች::
✝ ነፍሳት ✝
➡️ በብሉይ ኪዳን የነበሩና ለ5,500 ዓመታት በሲዖል የተጋዙ ሰዎችን ያመለክታል:: እነርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ በዓመተ ኩነኔ የነበሩ ሰዋች ሲሆኑ ደመ ክርስቶስ ቀድሷቸው: የትንሳኤው ብርሃን ደርሷቸው ወደ ገነት ስለ ገቡ በዚሁ ቀን ይታሠባሉ::
✝️ በእውነት አብያተክርስቲያናትን ቸሩ ይጠብቅልን በቸርነቱ ይማረን። እግዚአብሔር ከአባቶች ነፍስና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን::
Показать все...
🥰 4👍 2 1
✞ ለልደትሽ ምስጋና ይገባል ✞ ለልደትሽ ምስጋና ይገባል ለዓለም መዳን ምክንያት ሆነሻል ልደትሽም የእኛም ልደት ነው ባንች እኮ ነው ፀሐይ ያገኘነው[፪]      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► በሊባኖስ ሰማን አዲስ ዜና ንጽሕት ዘር ተወልዳለችና የዓለም ስቃይ ሰቆቃ ሊያበቃ ተወለደች እንደ ፀሐይ ደምቃ      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ለዚህ ክብር ይገባል እልልታ በልደትሽ አይሆንም ዝምታ የአንቺ ልደት ለዓለም ደስታ ነው አንቺ ምስራቅ ልጅሽም ፀሐይ ነው      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ብርሃን ሆነ በሊባኖስ ዛሬ በልደትሽ በመላዕክት ዝማሬ አይቋረጥ ምስጋና ካ'ፋችን በሊባኖስ ይሰማ ዜማችን      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ስለ ክብር ክብር አለን እኛ ከሊባኖስ ነይልን ወደኛ ከአብ ሕሊና ቀድሞዎን የታሰብሽ ትውልድ ሁሉ ብጽዕ የሚልሽ             መዝሙር| ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показать все...
3👍 1🙏 1
🧡 ሼር 🧡