cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Noor Islamic Reminders

Be in this world like a stranger or one who is passing through

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሰላት ከሰገዱ ቡኋላ መስገጃዎ ላይ መፅናት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉን? የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሰላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለ እና ውዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዱለታል። "አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት።" ይላሉ።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል) 👉 ኢብኑ በጣል(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እጅግ ብዙ ወንጀል ያለበት ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦ መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓእና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሰላት ከሰገደ ቡኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀም።"  
Показать все...
✍ምላስ ላይ ቀላል ሚዛን ላይ ከባድ በአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ሁለት የዚክር ቃላቶችን ላስታውስዎ ሰብሐነላህ ወቢሐምዲህ እና ሰብሐነላህ አልዐዚም አላህ ፍፁማዊ ምስጋና የሚገባው ነው፡፡ የላቀ ለሆነው አላህ ጥራ ይገባው። @Nesiha_Nur_Nejashi
Показать все...
👀 ይህን ያውቁ ኖሯል❓❕ 🔎 በቬነስ በሚባለው ፕላኔት ላይ አንድ ቀን ለማለቅ በመሬት ላይ ከአንድ አመት በላይ ይፈጃል . 🔎በአሜሪካ ውስጥ በየዓመቱ ከ 2 ቢሊዮን በላይ እርሳሶች ✏ ይመረታሉ ፡፡ እነዚህ እርሳሶች ጫፍ ለጫፍ ቢያያዙ መሬትን 🌍 ዘጠኝ ጊዜ ይዞራሉ ፡፡ አማካይ እርሳስ 35 ማይል ርዝመት ያለው መስመር ይስላል ወይም በግምት 50,000 የእንግሊዝኛ ቃላትን ይጽፋል። @Nesiha_Nur_Nejashi
Показать все...
#ጥያቄ? ከ 7ቱ ሰማያት በላይ አላህ( ሱብሀነሁ ወተአላ) ነብዩን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የዳረው የነብዩ ባለቤት ማን ናት?Anonymous voting
  • ሰውደት ቢንት ዙመዓ (ረዲየላሁ ዐንሃ)
  • ኡሙ ሐቢባ ረምላ ቢንት አቢ ሱፍያን(ረዲየላሁ ዐንሃ)
  • አኢሻ ቢንት አቢበክር አስ ሲዲቅ(ረዲየላሁ ዐንሃ)
  • ማሪያተል ቂብጢያ(ረዲየላሁ ዐንሃ)
  • ዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረዲየላሁ ዐንሃ)
0 votes
«السلام عليكم ورحمة الله وبركاتة ጁሙዓ ቀን ላይ ዱዓእ ተቀባይነት እንዳለው ነቢያችን ዐለይሂስሰላቱ ወስሰላም ተናግረዋል፤ በዕለቱ ዱዓእ ሙስተጃብ ይሆናል ተብሎ ይበልጥ የሚከጀለው ከዓስር አንስቶ ጸሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ከቻልን ከዐሱር እስከ መግሪብ ሰላት ድረስ  ኢዕቲካፍ ነይተን መስጂድ በመግባት ካልቻልን ቤታችን ውስጥ ሰአቱን በቂርአት፣በሰለዋት፣በዚክር እያሳለፍን ወደመጨረሻው ሰአት ደግሞ ሀገራችን አላህ ሰላም እንዲያደርግልን፣ለራሳችን እና ሀጃ ላለባቸው ሙስሊም  ወንድም እህቶቻችን የዲን የዱኒያ ሓጃችንን እንዲያሳካልን አላህን ከልባችን ብንማፀን በአላህ ፍቃድ ተጠቃሚዎቸ  እንሆናለን። በተጨማሪም ይህንን  መልእክት ሼር ብናደርገው ደግሞ በኛ ሰበብ ምናልባትም የብዙ ሰው ሀጃ ሊስተካከል ይችላል! وبالله التوفيق!« ©: ኡስታዝ ጀማል ያሲን
Показать все...
ዑመር ብን አልኸጣብ رضي الله عنه እንዲህ አለ:- «እናንተ የተዋረዳችሁ፣ ትንሽም የሆናችሁ፣ የተናቃችሁም የሆናችሁ ሰዎች ነበራችሁ ነገር ግን አሏህ በኢስላም የበላይ አደረጋችሁ ከኢስላም ውጪ የበላይነትን ብትፈልጉ አሏህ ያዋርዳችኀል።» (አልዙሁድ አልኢማም ኢብን ማሊክ) @Ethio_Suna_Media @Ethio_Suna_Media
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ዶ/ር ዩሱፍ አልቀረዷዊ በ96 ዓመታቸው ዛሬ ወደ አኺራ አቅንተዋል።አላህ በምህረቱ ይመልከታቸው።ጀነቱል ፊርደውስንም ይለግሳቸው። ዶ/ር ዩሱፍ አልቀረዷዊ ከ120 በላይ መጽሐፍትን ጽፈው በማበርከት፣ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዓለም ዓቀፍ የቀጥታ ተመልካች ይከታተላቸው በነበረው «አሸሪዓ ወልሀያት» ዝግጅት እና በሙስሊሞች መብት ጉዳይ ላይ በግልጽ በመናገር እና የዓለም ሙስሊም ዑለሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነው በነበራቸው አስተዋጽኦ በዘመናችን በዓለም ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖዋቸውን ማሳረፍ ችለዋል።መልካም ልፋታቸውንም ይቀበላቸው::ማረፊያቸውንም በጀነት ያድርግላቸው። @Nediha_Nur_Nejashi
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِمْ عَلَىْ نَبِينَا مُحَمَّدْ أكثروا من الصلاة على النبي في ليلة الجمعة ويومها 🍃
Показать все...
ከደጋጎች መካከል አንዱ ፊቱ ሁልጊዜ ለምን በደስታ የተሞላ (በሻሻ) እንደሆነ ሚስጥሩን ንገረን ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም «ጉዳዬ ሁሉ በአላህ እጅ ሆኖ ሳለ ለማዘን አፍራለሁ!» ሲል መለሰ። «ፈታ ባለ ፊት ወንድምህን መገናኘት ሰደቃ ነው!» ብለዋልና ረሱሉል ሁዳ፤ ፊታችን ፈገግታ የተሞላበት ይሁን።
Показать все...
*ከኢስላማዊ ማንነቶች ሶስቱ*:— *من أهم مكارم الأخلاق* ———————— አቢ ሁረይራ ረዲየላሁ አንሁ ባወሩት ሀዲስ ነብያችን ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ "በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው *መልካም ይናገር* ወይም ዝም ይበል: በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው *ለጎረቤቱ ደግ ይሁን* ያክብር : በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው *ለእንግዳው ደግ ይሁን* ያክብር ።" ቡካሪና ሙስሊም ዘግበውታል ። عن أبي هُريرةَ رَضِي اللهُ عَنْهُ، أنَّ رسولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قالَ: {مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ، وَمَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيُكْرِمْ جَارَهُ، وَمَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيُكْرِمْ ضَيْفَهُ}. رواه البخاريُّ ومسلمٌ. ★ከሀዲሱ አስተምሮት ውስጥ: — እምነት(ዐቂዳ) እና ስነምግባር(አኽላቅ) የማይነጣጠሉ ሀይማኖታዊ ማንነታችን ናቸው ። ★ ከመናገርህ በፊት አስብ መልካሙን ተናገር መጥፎውን ሆድህ ይቻለው ★ መልካም የሆነን ነገር መናገር እየቻልክ ዝም አትበል ተናገር መልካም ንግግር ሰደቃ ነውና ★ጎረቤትን ማክበር ማለት መልካሙን ሁሉ ለሱ መመኘትና አቅም በፈቀደው መጠን መለገስ ፣ ማገዝ ነው ★ጎረቤት ማለት :— በቤት፣ በሱቅ፣ በቢሮ፣ በታክሲ፣ በመቀመጫ፣ በጉዞ፣ አብሮ ያለ የተጎራበት ሁሉ ማለት ነው ። ★ ለእንግዳ ደግ መሆን ማለት ከተቻለ ከወትሮው ለየት ባለ መስተንግዶ መቀበል ካልሆነ ያለምንም መጨናነቅ ቤት ባፈረው ነገር ማስተናገድ ነው ★እንግዳን ቢያንስ ለ24 ሰዓት ቢበዛ ለሶስት ቀናት ማስተናገድ የታዘዝንበት ሲሆን ከሶስት ቀን በላይ በፈቃደኛነት ማስተናገድ የተወደደ ነው ። ★★★እነዚህን ሶስት ተግባራት ሀይማኖት ፣ ዘር ፣ ብሄር ፣ ዜግነት ፣ ሳንለይ ለሁሉ ሰው ልናደርጋቸው የሚገቡ ተግባራት ናቸው ። አላህ የተግባር ሰው ያድርገን ። @Nesiha_Nur_Nejashi
Показать все...