cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Больше
Рекламные посты
69 341
Подписчики
+624 часа
+1657 дней
+1 08530 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
https://youtu.be/pEeacVCz1Sg?si=I53HRv77HpHnUtNP
6 86310Loading...
02
ጥያቄ፡- ሰላም ዶክተር፡፡ በአንተ ማሕበራዊ መድረኮች በነጻ ስለምናገኛቸው ትምህርች ላመሰግንህ እፈልጋለሁ፡፡ መጠየቅ የምፈልገው ግን፣ በጣም አስቸጋሪ ሕይወት የነበራት አንድ ጓደኛዬ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሳገኛት በጣም ተለውጣ እና ሕይወቷን በስርአት እየመራች አገኘኋትና ምን እንደተፈጠረ ስጠይቃት ከአንተ ጋር የግል ሜንቶርሺፕ እንደወሰደች ነገረችኝ፡፡ ሜንቶርሺፕ ምን ማለት እንደሆነ ስጠይቃት ጋን ማስረዳት አልቻችም፡፡ ሁኔታው ትኩረቴን የሳበው እኔም መለወጥ ስለምፈልግ ነው፡፡ የተለያዩ የማነቃቂያ ስልጠናዎችን ወስጄ ግን እስካሁን ያው ነኝ፡፡ በሜንቶርሺፕና በማነቃቂያ ስልጠኛዎች መካከል ልዩነት አለ? ልዩነታቸውን ብታስረዳኝ፡፡ መልስ፡- በነጻ በማቀርበው የማሕበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በመጠቀም ላይ ስላላችሁ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በምችለውና ጊዜው በፈቀደልኝ ሁሉ ይህንን ማድረጌን እቀጥላለሁ፡፡ በክፍያ የግል ምክር፣ Coaching እና mentorship ላልሺው፣ እሱን የሚፈልጉ ሰዎች inbox በማድረግ ፍላጎታቸውን በመግለጽ አገልግሎቱን እያገኙ እንደሆነ ላሳውቅሽ እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን በማድረግና ቀጠሮ በማስያዝ ላለባችሁ ጥያቄ፣ ተከታታይ የ Coaching እና mentorship ፍላጎት መልስ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ የማነቃቂያ ስጠና እወስዳለሁ ስላልሺው፣ ማነቃቂያ ማለት ያው እንደ ስሙ ማነቃቂያ ነው፡፡ ያነቃቃሻል፣ ማለትም “ትችያለሽ፣ ተነሺ፣ ስሪ ሃብታም ትሆኛለሽ . . .” ይልና ያቃሻል እንጂ መንገዱን አያመላክትሽም፡፡ ይህ ሂደት የራሱ የሆነ ጥቅም ቢኖረውም ዘላቂ ውጤት ግን አያመጣም፡፡ ብዙ ሰዎች እንዲዘህ አይነቱን ዝግጅት ይካፈሉና ማነቃቂያው የሰጣቸው እንድርድረት ሲደክም እደገና ሊነቃቁ ይዳ፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ ከዚህ ሂደት ባለፈ ሁኔታ ለውጥን ከፈለግሽ የሚከተሉትን አሰራሮች መገንዘብና መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ማሰልጠን የአሰልጣኝነት ሂደት ሰልጣኙ አንድን ክህሎት እስከሚያዳብር ድረስ እና ወደ አንድ የብቃት ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ የሚደረግ የሁለት ሰዎች ግንኙነት ነው፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ የራእይ ጉዳይ ሊካተት ወይም ላይካተት ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የአሰልጣኝ ድርሻ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሰልጣኝን አንድ የክህሎት ደረጃ እንዲደርስ ማለማመድ ነው፡፡ ስሆነም፣ ያሰለጥናል፣ ስልጠናው ግቡን መምታቱን ያረጋግጣል፣ በተገቢው ሁኔታ በመሰልጠን ብቃቱን ያዳበረውን ሰው ያሳልፋል፣ በብቃት ያልጨረሰውን ሰው ደግሞ የራሱን ጉዞ እንዲዲከተል ይለቀዋል፡፡ የአሰልጣኝ ገደቡ እዚህ ድረስ ነው፡፡ 2. ማማከር የማማከር ሂደት የሚነካው አንድ ሰው ባጋጠመው ሁኔታ ዙሪያ ወይም ወደፊት መቀጠል በሚያስፈልገው ነገር ላይ ጥበብን የማካፈልንና ምሪትን የመስጠትን ሁኔታ ነው፡፡ በዚህም ግንኙነት ውስጥ የራእይ ጉዳይ ሊካተት ወይም ላይካተት ይችላል፡፡ ሆኖም፣ በምክር ፈላጊው አነሳሽነት ወይም በመካሪው ሃላፊነት የተሰማው እርምጃ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ የጥበብና የምክር መካፈልን ያደርጋል፡፡ ይህ የምክር ተግባር በአንድ ጊዜ ግንኙነት ሊከሰት ሲችል አንዳድ ጊዜ ደግሞ የጥቂት ቀናትንና ሳምንታት ሂደት ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለሆነም፣ መካሪው ምክረ-ሃሳቡን ይለግሳል፣ ተመካሪውም ምክሩን ተግባራዊ ለማድረግ መንገዱን ይቀጥላል፡፡ 3. ማስተማር የአስተማሪ-ተማሪ ግንኙነት እንደ ስልጠና ከአንድ ክህሎት ጋር የተያያዘ ሊሆን ቢችልም ከዚያ የሚለይበት ሁኔታም ሊያቅፍ ይችላል፡፡ አስተማሪው ለተማሪው አንድን ርእስ ወይም ጽንሰ-ሃሳብ ከማስጨበጥ አንጻር ተገቢውን እውቀት ያካፍለዋል፡፡ ይህ ጽንሰ-ሃሳብ ከአንድ ራእይ ጋር ሊዛመድም ላይዛመድም ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን አንድ የአእምሮ እውቀት ከማስጨበጥ፣ አንድን ጥበብ ከማካፈል ወይም አንድን ሞያዊ ክህሎት ከማዳበር ጋር ይገናኛል፡፡ ስለሆነም፣ አንድ አስተማሪ የአሰራሩ ሂደት ለመማር ብቁ ነው ብሎ በፊቱ ያመጣለትን ሰው በማስተማርና በመፈተንና የብቃት ማረጋገጫን በመስጠት ያሳልፋል፡፡ 4. “ኮች” ማድረግ የኮች ድርሻ በአብዛኛው የአሰልጣኝነትን ተግባር ያቀፈ ሲሆን፣ ከዚያ ለየት የሚለው አሰልጣኝ ሰልጣኙ አንድ ክህሎት ደረጃ ከደረሰለት በኋላ ያንን ክህሎት መጠቀም በሚፈልግበት መስክ እንዲጠቀም ሲተወው፣ ኮች ግን አንድ የስኬት ግብ ወይም ጥግ ላይ እስከሚያደርስ ድረስ ይሰራል፡፡ ልክ እንደ ማሰልጠን፣ ማማከርና ማስተማር፣ የኮችነት ሂደትም ምንም እንኳን አንድ ግብ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ከአንድ ራእይ ጋር የተገናኘ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ 5. ሜንቶር ማድረግ በጥቅሉ ሲገለጽ የሜንቶርነት ሂደትና አሰራር ከላይ የተዘረዘሩትን አራት ገጽታዎች ያቀፈ ነው፡፡ ሜንቶር ያሰለጥናል፣ ያማክራል፣ ያስተምራል እንዲሁም ኮች ያደርጋል፡፡ ትክክለኛ ሜንቶር ለአንድ ዓላማ አጠገቡ ያስጠጋውን ሰው የሕይወት አቅጣጫ መስመር የማስያዝ አቅም አለው፡፡ አመለካከቱን፣ ባህሪይውን፣ ዲሲፕሊኑንና ከዚያም አልፎ ራእዩን ማካፈል አንጻር ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ ስለዚህ ሜንቶር ከላይ የተዘረዘሩትን አራቱን ሂደቶች ያጠቃልላል፣ እነዚህ አራቱ ሂደቶች ግን ሜንቶርነትን አያጠቃልሉም፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
9 78531Loading...
03
ጥያቄ፡- ሰላም ዶክተር፡፡ በአንተ ማሕበራዊ መድረኮች በነጻ ስለምናገኛቸው ትምህርች ላመሰግንህ እፈልጋለሁ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ሕይወት የነበራት አንድ ጓደኛዬ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሳገኛት በጣም ተለውጣ አገኘኋትና ምን እንደተፈጠረ ስጠይቃት ከአንተ ጋር የግል ሜንቶርሺፕ እንደወሰደች ነገረችኝ፡፡ ሜንቶርሺፕ ምን ማለት እንደሆነ ስጠይቃት ጋን ማስረዳት አልቻችም፡፡
8 3132Loading...
04
በፍጹም አታቁም! “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡ • “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡” • “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?” • “ይህ ነገር ወደፊት አላራምድ አለኝ፡፡” • “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡” • “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?” በእዚህና በመሰል ስሜቶች ከጀመርከው ነገር እንዳትገታ ከፈለክ “በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡- • ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡ • መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡ • ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡ • በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡ • መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
9 60372Loading...
05
በ Zoom ሊሰጥ የታቀደው የስድስት ሳምንት ስልጠና ባለፈው ሰኞ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡ የመጀመሪያውን ሳምንት (ክፍል አንድ) ትምህርት ጀምረናል፡፡ ምናልባት ለመሳተፍ ፈልጋችሁ የተዘናጋችሁና ሳትመዘገቡ የመጀመሪያው ክፍል ያመለጣችሁ ካላችሁ ለጥቂት ሰዎች ብቻ አንድ እድል እንሰጣለን፡፡ በእዚህ ሁለት ቀናት ቀድሞ ጥያቄ ላቀረቡና ለሚመዘገቡ አምስት ሰዎች ያመለጣቸውን ክፍለ-ጊዜ የማካካሻ ክፍለ-ጊዜ እንደምሰጥ አሳውቃለሁ፡፡ በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ጥያቄያችሁን ለህሊና በመላክና መስፈርቱን በሟላት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ @Helinakeb
10 8158Loading...
06
ችግር ሲታየን! የሚከፈለን ለፈታነው ችግር ነው! ችግር ስናይ ሁለቱ ምርጫዎቻችን 1. መነጫነጭ፣ መካሰስ፣ መወቃቀስ፣ አሉታዊ ወሬን ማራባት 2. እንደተልእኳችን ማየት፣ መፍትሄ መፈለግ፣ ማበርከት የሁለተኛው መንገድ ጥቅም 1. ለችግሩ መፍትሄ በማምጣታችን ምክንያት ይህ ነው የማይባል እርካታ ይሰጠናል፡፡ 2. ለፈታነው ችግር የገንዘብ ክፍያ እገኛለን፡፡ 3. የስነ-ልቦና ጤንነት እናገኛለን፡፡ ለተግባራዊ ማብራሪያ ከታች ያለውን የ YouTube ሊንክ በመጫን ትምህርቱን ይከታተሉ! https://youtu.be/QDZ73X37fnQ
10 25318Loading...
07
የጠበቅነውና የሆነው ነገር ሊለያይ! በአንድ ነገር ላይ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ስሜታችንንና አንዳንዴም ገንዘባችንን አውጥተን፣ ሰርተንና ገንብተን የጠበቅነው ውጤት ሌላ ያገኘነው ውጤት ግን ሌላ ሲሆን ግር መሰኘታችን አይቀርም፡፡ ሆኖም፣ አንድን ነገር ጠብቀን የምንፈልገውና የምንጠባበቀው ውጤት ሳይሆን ሲቀር ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሸ ወሳኝ ነው፡፡ ለማንኛውም ማየት የሚገቡን ሁኔታዎች . . . 1. ምናልባት የተሳሰተና መጀመር የሌለብንን ነገር ጀምረን ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት ያለን አማራጭ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ የተጀመረውን የተሳሳተ ነገር በማቆም፣ ትክክለኛ ነገር የመጀመር ውሳኔ መወሰንና የአቅጣጫ ለውጥ ማድረገ ነው፡፡ 2. ምናልባት ትክክለኛውን ነገር ጀምረን የተጠቀምነው ስልት ግን የተሳሳተ ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት የአደራረግ ስልታችንን የማረምና የተለየ ስልት የመጠቀምን አማራጭ መከተል የግድ ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ማንበብ ካለብን ማንበብ፣ መሰልጠን ካለብን መሰልጠን፣ ባለሞያ ማማከር ካለብን ደግሞ ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡ 3. ምናልባት የተጀመረው ነገርም ሆነ የተጠቀምንበት ስልት ትክክለኛው ሆነው ሳለ የተጠባበቅነው ውጤት እውነታውን ያላገናዘበ ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት ከአንድ ነገር የምንጠባበቀው ውጤት ከልክ ያለፈና ከእውነታ ውጪ የመሆኑን ሁኔታ ልክና ገደብ ማስያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ካላስተካከል ሁል ጊዜ ተስፋ እንደቆረጥን እንኖራለን፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
10 48851Loading...
08
የዓላማና የተስፋ ግንኙነት በአንድ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታራሚዎች በቂ የሆነና የተሟላ የምግብ አቅርቦት ነበራቸው፡፡ ከተወሰነ የማረሚያ ቤት ቆይታቸው በኋላ እርስ በርሳቸው ስለተላመዱ በተለያዩ ጨዋታዎች እየተደሰቱና አንዳንድ ሞያ ነክ ነገሮችንም እየሰሩ መረጋጋት ጀምረዋል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁሉንም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተጫጫናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተስፈኛ ሆነው የመቆየት አቅማቸውንም አጡ፡፡ የሆነው ነገር ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሲነሱ በማረሚያ ቤቱ ግቢ አንድ ጥግ ላይ የተከመሩ አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ነበሩና እነዚህን ጆንያዎች ካሉበት በማንሳት ወደሌላው የማረሚያ ቤቱ ግቢ ጥግ እንዲወስዱና እንዲከምሯቸው ተነገራቸው፡፡ ሁሉም ታራሚዎች በመነሳሳት ያንን ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ ከዚያም ወደማምሻው ላይ ጠዋት ወስደው የከመሩትን የጆንያ አሸዋ ክምር ወደ ነበረበት እንዲመልሱ ታዘዙና ይህ ስራ በየቀኑ እንደሚቀጥል ተነገራቸው፡፡ እነዚህ ታራሚች በተወካያቸው በኩል አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ወዲያና ወዲህ የሚመላለሱበት ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ምንም ዓላማ የሌለው ተግባር እንደሆነና አርፈው እንዲታዘዙ ተነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ስሜታቸው በጣም የወረደው፡፡ ምንም ዓላማ የሌለውን ተግባር ሲደጋግሙ መኖር ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ምናልባት ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የሚጫጫነን የመኖራችንን ዓላማና ትርጉም እንዲሁም በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች ለምን እንደምናደርጋቸው ዓላማቸውን በሚገባ ስላላወቅነው ይሆን? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12 19964Loading...
09
በአንድ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ! አንድን የምታውቁትን ነገር እንደገና ላስታውሳችሁ፡፡ በአለም ላይ አሁን እናንተ በማለፍ ላይ ባላችሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ፣ በማለፍ ላይ ያሉና ወደፊትም የሚያልፉ ሰዎች እልፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ይህ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲቀብራቸው፣ ሌሎች ደግሞ በእርግጥም ያልፉታል፡፡ ለዚህ ልዩነት መነሻ የሚሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ የመቻላቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእነዚህ ሰዎች መካከል ያለው ዋና ልዩነት፣ በዚያው ተውጠው የቀሩት ሰዎች ከሚያልፉበት ሁኔታ የተነሳ በመደናገጥ ወደፊት መገስገስን በመተው በመቆማቸው ምክንያት ሲሆን፣ እነዚያ ዘልቀው የሄዱትና በአሸናፊነት የወጡት ደግሞ በሚያልፉበት ሁኔታ ውስጥ በፍጹም ሳይቆሙ ወደፊት በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት ነው፡፡ በአንድ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ፣ በእርግጥም እለፉ እንጂ እንዳተቆሙ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
11 75450Loading...
10
የልጅነት ልምምዴ ጣጣ! “የቤተሰቡ ብቸኛ ሴት ልጅ ሆኜ ነው ያደኩት፡፡ በልጅነቴ ያሳለፍኳቸው ደስ የሚያሰኙ ብዙ ልምምዶች ቢኖሩኝም እስካሁን ትዝታው በፍጹም ያልደከመና ትናንትና የሆነ እስከሚመስለኝ ድረስ ትዝ የሚለኝ አንድ ሁኔታ አለ፡፡ ገና የአምስት ዓመት ልጅ እያለሁ አንድ ቀን አባቴ አዲስ ልብስ ገዛልኝና በጣም ከመደሰቴ የተነሳ ወዲያውኑ ልብሱን ለብሼ ላሳየው አባቴ ተቀምጦ ቲቪ ሲመለከት ወደነበረበት ወደ ሳሎን ቤት መጣሁ፡፡ አባቴም፣ “ዋው! በጣም የሚያምር ልብስ ነው፣ ነገር ግን ውፍረትሽን ትንሽ አወጣው” ብሎ የተናገረኝ ንግግር እስካሁን ውስጤ ቀርቷል፡፡ አሁን የ25 አመት ወጣት ነኝ፡፡ ይህ የአባቴ ንግግር በራሴ ላይ ካመጣብኝ የአመለካከት ቀውስ ጋር እየታገልኩኝ እንደምኖር ሲሰማኝ የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚያተኩሩት የማያምረው የእኔነቴ ክፍል ላይ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ምንም አይነት ልብስ ብገዛ የልብሱን ውበት እኔ ያበላሸሁት ነው የሚመስለኝ፡፡ የምለብሰው ልብስም ሆነ የማደርጋቸው ነገሮች የእኔን አስቀያሚነት የሚያጎሉ እንደሆነም ይሰማኛል፡፡ ስዎች ሳይገፉኝ የገፉኝ ሳይነቅፉኝ የነቀፉኝ፣ ሳያገልሉኝ ያገለሉኝ . . . ይመስለኛል”፡፡ የዚህች ወጣት ታሪክ የተለያየ ቅርጽና ቀለም ይያዝ እንጂ ብዙ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች የሚታገሉበትን ሁኔታን አመልካች ነው፡፡ አያችሁ፣ እድሜያችን ከሰባት ዓመት በታች በነበረበት ጊዜ አመለካከታችንን ገና ቀርጸን ያልጨረስንበት እድሜ (formative age) ላይ በመሆናችን ምክንያት የሚነገረንን ነገር በሙሉ እንደወረደ የመውሰድ ዝንባሌ አለን፡፡ በሌላ አገላለጽ አንድ ነገር ሲነገረን፣ “ይህ ሰው እንደዚህ ያለኝ ከእኔ የተነሳ ብቻ ሳይሆን ከራሱም የግል አመለካከት አንጻር ነው” በማለት በምክንያታዊነት (rationalize አድርገን) የማሰብ የአእምሮ ክፍላችን ስላልዳበረ ማንነታችን የተነገረውን ሁሉ እንደ እውነት ተቀብሎ ነው የምናድገው፡፡ ይህ ውስጠ-ህሊናችን የገባውና የተቀበልነው “እውነታ” መሰል "ምልከታ" በወደፊቱ የራስ-በራስ እይታችን ላይ ይህ ነው የማይባል ጫናን የማስከተል አቅም አለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ . . . 1. ከራሳችሁ ጋርም ሆነ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት አንጻር የምታስቧቸው ሃሳቦች ትክክል እንዳልሆኑ እያወቃችሁ እንኳን ማቆም ካቃታችሁ . . . 2. ከራሳችሁ ጋርም ሆነ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት አንጻር የምታንጸባርቋቸው ስሜታዊ ሁኔታዎች ትክክል እንዳልሆኑ እየገባችሁና እየተጸጸታችሁ ደጋግማችሁ የምታደርጓቸው ከሆነ . . . 3. “መቀየር እኮ እፈልጋለሁ ግን አልቻልኩም” የምትሏቸው፣ የፍቅር ግንኙታችሁን፣ ትዳራችሁን፣ ጓደኝነታችሁን ወይም ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን የሚያበላሹ ባህሪዎችና ዝንባሌዎች ካሏችሁ . . . ወደኋላ መለስ በማለት የልጅነት ልምምዳችሁን በማሰብና ምናልባት በአንድ ልምምድ ተጽእኖ ስር የመሆናችሁን ሁኔታ እንድታጣሩ ትመከራላችሁ፡፡ ይህንን የለውጥ መንገድ ለመጀመር ደግሞ፣ ጸሎት የማድረጋችሁ አስፈላጊነት ሳይዘነጋ፣ ስለሁኔታችሁ በማንበብ፣ ምክርን በመውሰድና ሆን ብሎ (intentionally) በማሰብ የለውጥ መንገድን መጀመር ይኖርባችኋል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
15 11352Loading...
11
የልጅነት ልምምዴ ጣጣ!
13 5656Loading...
12
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ? (በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡) 1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣ 2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣ 3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣ 4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣ 5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣ ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ በቴሌግራም inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
16 00722Loading...
13
ኳሱ ነው ወይስ መሬቱ!? አንድን ኳስ የምታነጥሩበት (የምታንጠባጥቡበት) መሬት ድንጋያማ (ኮረኮንች) ከሆነ በእጃች ላይ ያለውን ኳስ ምንም ያህል በጥንቃቄ ብታነጥሩትም ኳሱ ወደየት አቅጣጫ ነጥሮ ሊሄድ እንደሚችል እርግጠኛ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ የዚህ ውጤት መንስኤ ኳሱ ሳይሆን መሬቱ ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ፣ መሬቱ ምንም ያህል ለጥ ያለ፣ ውኃ ልኩን የጠበቀና የለሰለሰ ቢሆንም በእጃችሁ ያለው ኳስ ጠማማ ከሆነ ኳሱን ስታነጥሩት፣ አሁንም ቢሆን ኳሱ ወደየት አቅጣጫ ነጥሮ ሊሄድ እንደሚችል እርግጠኛ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ የዚህኛው ተመሳሳይ ውጤት ደግሞ መንስኤ መሬቱ ሳይሆን ኳሱ ነው፡፡ ኳሱ የራሳችንን፣ መሬቱ ደግሞ የአካባቢችንን ሁኔታ ጠቋሚ ናቸው፡፡ ይህ ምሳሌ፣ የስሜታችን ጉዳይ በየቀኑ (አንዳንዴም በየሰዓቱ) የሚለዋወጥበትን ሁለት መንስኤዎች ጠቋሚ ስለሆነ በጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባው እንደሆነ እናስባለን፡፡ ልክ እንደዚያ ኳስ ስሜታችን አንዴ ወደዚህ አንዴ ደግሞ ወደዚያ የሚዋዥቅበት አንዱ ምክንያት የተዛባ የግል አመለካከትና የስነ-ልቦና ሁኔታ ውስጥ ስላለን ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ስሜታችንን የመግዛት፣ የማረጋጋትና ካለበት ቀውስ የማውጣት ስራ ይጠበቅብናል፡፡ በተቃራኒው፣ ልክ እንደዚያ ኳስ ስሜታችን አንዴ ወደዚህ አንዴ ደግሞ ወደዚያ የሚዋዥቅበት ሌላኛው ምክንያት የአካባቢያችን አስቸጋሪነትና ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ፣ ዙሪያችን በስሜታችን ላይ አጉል ተጽእኖ የሚያስከትል ያልጠበቅነውን ሁኔታ ሲፈጥርብን ያንን ለማለፍ የሚያስችል የስሜት ብቃትና ጽንአት ይዘን መዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ስሜታችን ላይ እንስራ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623
15 97561Loading...
14

10Loading...
15

9818Loading...
16
Hello all ! የግል ሕይወታችንን ራእይ በማወቅና በመኖር ዙሪያ የምሰጠው የZoom ስልጠና ሊሰጥ ሶስት ቀን ብቻ ነው የቀረው፡፡ ለመሳተፍ አስባችሁ የተዘናጋችሁ ከዚህ በታች ባለው የቴልግራም አድራሻ ህሊናን ኮንታክት በማድረግ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ ላስታውሳችሁ፡፡ @helinakeb የተመዘገባችሁ በእለቱ እንገናኝ!
18 86820Loading...
17
ጽንአት!!! “አንድ ሰው የሚያልቅለት ሲሸነፍ አይደለም፤ የሚያልቅለት በበቃኝ ሲያቆም ነው” - Richard M. Nixon በሕወትህ በአንድ ባመንክበትና ትክክል በሆነ ዓላማ እስከመጨረሻው ከመጽናት ውጪ ምንም ቁም ነገር ልታከናውን አትችልም፡፡ ዛሬ ይህንና ያንን እየጀመርክ እስከጥጉ ሳታደርሳቸው ነገ ደግሞ ወደሌላ ነገር ዘወር የማለት ለማድ ካለህ በተቻለህ ፍጥነት ይህንን ዘይቤ መቀየር እንዳለብህ ትመከራለህ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን የጀመርነውን ነገር እስከጥጉ የማንወስድበት ዋነኛ ምክንያት ስንወድቅ ወይም ያልተሳካልን ሲመስለን ነው፡፡ ሆኖም፣ ውድቀት፣ አለመሳካት፣ እንቅፋትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በማንኛውም አንድን መልካም አላማ ይዞ በሚራመድ ሰው ሕይወት ውስጥ የማይቀሩ ሂደቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም፣ አንደኛችንን ውድቀትን አያያዝ ብልሃት ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡ ሲወድቁ መነሳት በጽንአቱ የታወቀ ሰው ለወደቀበት ለእያንዳንዱ ክስተት መነሳትን አስመዝግቦ ወደ ፊት የሚራመድ ሰው ነው፡፡ መሳሳት፣ መውደቅ፣ መክሰር፣ ግብን አለመምታትና የመሳሰሉት ብዙዎችን ኃያላን የጣሉ ሁኔታዎች ለእሱ የእድገት ምክንያቶች እንጂ የተስፋ መቁረጥ ምንጮች አይደሉም፡፡ ውድቀትን እንደ አንድ ብቸኛ ክስተት ማየት ወድቀው የሚቀሩ ሰዎች ሲወድቁ ውዳቂ ነኝ ብለው የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡ በተቃራኒው ስኬታማ ሰዎች አንድ ውድቀት የእነሱን ማንነት እንዲወስን አይፈቅዱም፡፡ ውድቀትን እንደ አንድ ብቸኛ ክስተትና እንደ ትምህርት እድል ነው የሚቆጥሩት፡፡ አደራረግን መቀየር ስኬታማ ሰዎች ነገሮችን በአንድ መልኩ ሞክረው አያቆሙም፡፡ ያልተሳካበትን መንገድ በመተው ሁኔታውን በሌላ መልኩ ይቀርቡታል፡፡ ለማከናወን በአይነ-ህሊናቸው ላዩት ነገር አንዱ መንገድ ካልተሳካ ሌላ መንገድ እንዳለው ጽኑ እምነት አላቸው፡፡ ሃላፊነትን መውሰድ ተሸናፊ ሰዎች ለተከሰተው ስህተት የሚወቀስ ሰው ይፈልጋሉ፡፡ በአንጻሩ ስኬታማ ሰዎች ለሰሩት ስህተት ሃላፊነትን የሚወስዱና የተሻለ መንገድን ለመፈለግ የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡ አንዱ ሌሎችን በመውቀስ ሲረካና ሲያቆም፣ ሌላኛው ሃላፊነትን በመውሰድ መፍትሄ በማግኘት ይረካል፤ ወደ ፊትም ዘልቆ ይሄዳል፡፡ በውስጥ ላይ ማተኮር አሸናፊ ሰዎች ወሳኙ ነገር በዙሪያቸው የተከናወነው ሳይሆን በውስጣቸው የተከናወነው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በእነርሱ ዙሪያም ሆነ በእነርሱ ላይ የሆነው ነገር ውስጣቸውን እስካልነካው ድረስ ምንም እንደማይሆኑ ያውቃሉ፡፡ የደረሰባቸው ማንኛውም አስከፊ ሁኔታ በውስጣቸው ያለውን ጽኑ እምነት ካልነካውና ትክክለኛውን ምላሽ መስጠትን ከለመዱ ወደግብ የመድረሳቸው አሸናፊነት ዘላቂነት ይኖረዋል፡፡ በርታ !!! በርቺ !!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
21 950127Loading...
18
ጽንአት!!!
17 2688Loading...
19
https://vm.tiktok.com/ZMMcyp8tp/
19 5187Loading...
20
ሌሎችን ከማነቃቃታችን በፊት! በፈረንጆቹ በ1930 ዎቹ ውስጥ አንድ ልጅ ካለበት የስኳር ሱስ የተነሳ ብዙ ስላስቸገራት እናቱ ይህንንም ባህሪውን ለማስቆም ብዙ ከሞከረች በኋላ ተስፋ ቆረጠች፡፡ በመጨረሻ ጋንዲ (Mahatma Gandhi) ጋር ብወስደው ካለው ታዋቂነትና ተሰሚነት የተነሳ ይመክረውና ተጽእኖ ያደርግበታል ብላ ስላመነች በጠራራ ጸሐይ ብዙ መንገድ ተጉዛ ወሰደችው፡፡ በብዙ መከራ ጋንዲን ካገኘችው በኋላ ጥያቄዋን አቀረበች፡፡ “ልጄ ብዙ ስኳር ይበላል፡፡ ለጤንነቱ ጥሩ ስላልሆነ እባክህ አስቁመው” አለችው፡፡ ጋንዲም በሚገባ ካደመጣት በኋላ፣ “ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመለሱ” በማለት መልሶ አሰናበታት፡፡ ብዙ መንገድ ስለመጣች በጣም አዘነች፡፡ ሆኖም፣ የልጇ መለወጥ ነገር ግድ ስለሚላት ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመልሳ ብዙ መንገድ አቋርጣ መጣች፡፡ ልክ ሲያገኙት ጋንዲ ለልጁ እንዲህ አለው፣ “ሁለተኛ ስኳር እንዳትበላ፣ ለጤንነትህ ጥሩ አይደለም”፡፡ ልጁም፣ “እሺ” ብሎ በመታዘዝ ደግሞ ስኳር እንደማይበላ ቃል ገባለት፡፡ የልጁ እናት እጅግ ተበሳጨችና፣ “መጀመሪያ ስንመጣ ይህችን አጭር ምክር ነግረኸው መፍትሄ መስጠት ስትችል ለምን አስለፋኸን” አለችው፡፡ ጋንዲም፣ “ከሁለት ሳምንታት በፊት እኔ ራሴ ብዙ ስኳር የመብላት ችግር ነበረብኝ፡፡ ምክሬ ጉልበት እንዲኖረው ስኳር የመብላት ልማዴን ለመቀነስና ልኩን ለማስያዝ ጊዜን ፈልጌ ነው” አላት፡፡ ሰዎችን ከማሰልጠናችን በፊት እኛ የመሰልጠናችን ጉዳይ! . . . ሰዎችን በአንድ ጎዳና እደሄዱ ከማነሳሳታችን በፊት እኛ ያንን ጎዳና ለመጀመር የመነሳሳታችን ጉዳይ! . . . ሰዎችን “ትችላላችሁ” ከማለታችን በፊት እኛ ቢያንስ ሙከራ የማድረጋችን ጉዳይ! . . . እጅግ አስፈላጊና ለመልእክታችን የተጽእኖ ጉልበት የሚጨምር ጉዳይ መሆኑ ዛሬ ይታሰብበት፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ መካሪ፣ ሜንቶር፣ አሰልጣኝና አነቃቂ ሰው ስትፈልጉ በቅድሚያ በመንገዱ ያለፈበትን ሰው ፈልጋችሁ ማግኘታችሁን እርግጠኞች ሁኑ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
17 69352Loading...
21
ሌሎችን ከማነቃቃታችን በፊት!
15 2486Loading...
22
እውነተኛ ሕይወት ሲመዘን! አንድ አሜሪካዊ ነጋዴ በአንዲት የሜክሲኮ የወደብ ከተማ ዳር ቆሞ ሳለ አንዲት ትንሽ ጀልባ አንድ አሳ አጥማጅ ይዛ ወደ ወደቡ ተጠጋች፡፡ በጀልባ ውስጥ አንድ የሜክሲኮ ተወላጅ አሳ አጥማጅ ያጠመዳቸው ቁጥራቸው ከመጠን ያለፈ ትናንሽ አሳዎች አሉ፡፡ አሜሪካዊው ሜክሲኮአዊውን ስለአሳ ማጥመድ ችሎታው ካደነቀው በኋላ አንድን ጥያቄ አቀረበለት፣ “እነዚህን አሳዎች ለማጥመድ ስንት ጊዜ ፈጀብህ?” “በጣም አጭር ጊዜ” ብሎ መለሰ፣ ሜክሲኮአዊው፡፡ አሜሪካዊው፣ “ይህንን ያህል አሳ በአጭር ጊዜ ማጥመድ ከቻልክ ለምን ቀኑን ሙሉ ውለህ ብዙ አሳ ለማጥመድ አትሞክርም” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሜክሲኮአዊው፣ “አሁን በምሰራበት ሁኔታ ለቤተሰቤ በቂ አቅርቦትን ይዤ እገባለሁ” ብሎ መለሰ፡፡ አሜሪካዊው ጥያቄውን በመቀጠል፣ “በቀረህ ጊዜ ምን ታደርጋለህ?” አለው፡፡ ሜክሲኮአዊው ገበሬ፣ “ጠዋት በቂ እረፍት እወስዳለሁ፣ በቂ አሳ ካጠመድኩ በኋላ ልጆቼ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከእነሱ ጋር እጫወታለሁ፣ ከዚያም ከባለቤቴ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ እንወስዳለን፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ እልና ከጓደኞቼ ጋር ሻይ እየጠጣን ጊታሬን መታ መታ አደርጋለሁ፤ ቀኔ በእነዚህ ሁኔታዎች ሙሉ ነው”፡፡ አሜሪካዊው በመገረምና በማሾፍ፣ “እኔ የታዋቂው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ተመራቂ ነኝ፡፡ ልምከርህ! ከጠዋት እስከማታ አሳ ማጥመድ አለብህ፡፡ ከዚያም ተለቅ ያለ ጀልባ መግዛት ትችላለህ፡፡ ከዚያ በአሳ ጠመዳ የምታሳልፈውን ጊዜህን ትንሽ ጨመር በማድረግ በርካታ ጀልባዎችን ትገዛለህ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙ ጀልባዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ዋና አከፋፋይ መሆን ትጀምርና ለአሳ ጠመዳ በምትወስደው ጊዜህ ላይ ጥቂት ጨመር በማድረግ የራስህን ፋብሪካ ትከፍታለህ፡፡ ከዚያም ከዚህች መንደር ትወጣና ወደ ሜክሲኮ ዋና ከተማ ትገባለህ፣ ከዚያ ወደ ሎስ አንጀለስ፣ ቀስ በቀስም የአለም የገበያ ማእከል ወደሆነችው ወደ ኒውዮርክ በመግባት ታላቅ ሰውና ሚሊየነር ትሆናለህ፡፡” ሜክሲኮአዊው በመገረም፣ “ይህ የምትለው ጉዳይ ስንት ጊዜ ይፈጃል?” አለው፡፡ አሜሪካዊውም፣ “ከ20 እስከ 25 ዓመታት ይፈጃል” አለው፡፡ ሜክሲኮአዊውም መልሶ፣ “ከ25 ዓመታት በኋላ እዚያ ደረጃ ከደረስኩ በኋላስ?” አለው በፍጥነት፡፡ አሜሪካዊው በመሳቅ፣ “ያን ጊዜማ የሚያጓጓ ነገር ውስጥ ትገባለህ፡፡ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቀህ ይህንን የገነባኸውን ንግድ ለሕዝብ በማቅረብ አክሲዮን ትሸጥና ብዙ ቢልየን ብር በማግኘት እጅግ ባለጠጋ ትሆናለህ፡፡” አሁንም ሜክሲኮአዊው መልሶ፣ “በቢልየን የሚቆጠር ብር ካገኘሁ በኋላስ” አለው፡፡ “ከዚያማ ጡረታ ትወጣና ወደነበርክበት የባህር ወደብ ከተማ ትመለሳለህ፡፡ አሁን እንደምታደርገው ጠዋት በቂ እረፍት ትወስዳለህ፣ በቂ አሳ ካጠመድ በኋላ ከልጅ ልጆችህ ጋር ትጫወታለህ፣ ከዚያም ከባለቤትህ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ ትወስዳለህ፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ ትልና ከጓደኞች ጋር ሻይ እየጠጣህ ጊታርህን መታ መታ ታደርጋለህ”፡፡ ሜክሲኮአዊው ተገረመ፡፡ በሃሳቡ፣ “አሁን የምኖረውን የተረጋጋ የሕይወት ሁኔታ ከ25 ዓመታት ልፋት በኋላ ለማግኘት ምን አስሮጠኝ” ብሎ በማሰብና በአሜሪካዊው ሃሳብ ስቆ መንገዱን ቀጠለ፡፡ 1. ራሳችንን መመዘን ያለብን በሕይወት ዘመናችን ውስጥ ባሉት ዓመታት ሳይሆን በዓመታቶቻችን ውስጥ ባለው ጣፋጭ ሕይወት ነው፡፡ 2. ስኬታችን መመዘን ያለብን በገነባነው ቤት ግዝፈት ሳይሆን በቤቱ ውስጥ በሚኖረው በፍቅር የተገነባ ቤተሰብ ነው፡፡ 3. አቅጣጫችንን መመዘን ያለብን እኛ በነዳነው መኪና አይነት ሳይሆን እኛን በነዳን ራእይ ምንነት ነው፡፡ ስራ፣ ገንዘብ፣ ታዋቂነት፣ ውበት፣ ስልጣን፣ እውቀትና የመሳሰሉት ቁሳቁስ-ነክ ነገሮች ሰላምና ፍቅር የሞላበትን ቤተሰባዊ ሕይወት እንድንኖር ካላደረጉን ከንቱ ናቸው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
20 346138Loading...
23
እውነተኛ ሕይወት ሲመዘን!
16 2105Loading...
24
ሕይወታችሁን ለማስተካከል ወይም ለማበላሸት አንድ ነገር በቂ ነው! አዎን! አንድ ነገር በቂ ነው! ካልተጠነቀቅን አንድ የተሳሳተ ነገር እድሜ ልካችንን የሚከተል መዘዝ ይዞ ይመጣል፡፡ 1. አንድ “የተሳሳተ” ሰው • በብዙ ብልጽግና መኖር ስትችሉ በድህነት፣ በጤንነት መኖር ስትችሉ በበሽታ፣ በደስታ መኖር ስትችሉ በኃዘንና በቁዘማ እንድትኖሩ ሊደርጋችሁ ይችላል፡፡ የምትመርጡትን ሰው በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ 2. አንድ የተሳሳተ አመለካከት • የምታስተናግዱትን ሃሳብ፣ አመለካከትና ፍልፍና በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ 3. አንድ የተሳሳተ ውሳኔ • ሰው የሚኖረው ምርጫና ውሳኔውን ስለሆነና በተሳሳተ ምርጫችሁ ምክንያት የልተጻፈላችሁን ታሪክ ልትኖሩ ስለምትችሉ የምትመርጡትንና የምትወስኑትን ነገር በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ 4. አንድ የተሳሳተ ልምምድ • በጓደኛ ተጽእኖ፣ በ“ልሞክረው” እና በመሳሰሉት መንገዶች የምትገቡባቸውና የምትለማመዷቸው ነገሮች እድሜ ልክ የማይለቅ ልምምድ ውስጥ ይከታሉ፡፡ ለመፍትሄ ሃሳቦች ከዚህ በታች ያለውን የYouTube Link በመጫን ሙሉውን ሃሳብ ይከታተሉ https://youtu.be/WoLQdo_0dsA
20 482107Loading...
25
https://youtu.be/uDVUXq0L3Yw?si=JgJe50Mcjv1-BEej
16 25219Loading...
26
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!
15 3149Loading...
27
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! አንድ ሃብታም ጎብኚ ወደ አንዲት ሃገር ከተጓዘ በኋላ ከከተማ ራቅ ወዳለ ስፍራ ለጉብኝት ሄደ፡፡ በዚያም አንድን እጅግ በጣም ደሃ የሆነ አስጎብኚ ቀጠረውና አካባቢውን እያሳየው ሲጓዙ ሳለ ጎብኚው አንድ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀው አይነት ዛፍ ተመለከተ፡፡ በነገሩ ተገረመና ውስጡ ምን እንደሆነ ለማወቅ ለጉዞ የያዘውን አነስተኛ መጥረቢያ አንስቶ ዛፉን እቆርጣለሁ ብሎ ተሳስቶ ጣቱን ቆርጦ ጣለው፡፡ ይህ ባለጠጋ ጎብኚ በስቃይ ሲጮህ አስጎብኚው፣ “አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው” እያለ በመደጋገም ሲነግረው እጅግ ተበሳጨና አጠገባቸው የሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገፍትሮ ጥሎት ሄደ፡፡ ይህ ጎብኚ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ጸጉረ ልውጥ ሰው ሲያገኙ ቀቅለው የሚበሉ ጎሳዎች አገኙት፡፡ የሚበላ ሰው በማግኘታቸው የተደሰቱት እነዚህ ሰዎች ጥፍር ካሰሩት በኋላ እንደልማዳቸው እሳታቸውን አንድደውና መቀቀያውን ጥደው በዙሪያው ከጨፈሩ በኋላ ጎብኚውን መቀቀያው ውስጥ ሊጨምሩት ሲሉ በድንገት የተቆረጠውን ጣቱን ተመለከቱ፡፡ በእምነታቸው መሰረት እንደዚህ አይነት ሰው መብላት ክልክል ስለሆነ ሃሳባቸውን ቀይረው እንዲሄድ ለቀቁት፡፡ ይህ ጎብኚ የነበረበት የፍርሀት መንቀጥቀጥ ረገብ ሲልለት መጀመሪያ ትዝ ያለው በንዴት ገደል ውስጥ ገፍቶ የጣለው አስጎብኚው ነበረና ሄዶ ጎትቶ በማውጣት ይቅርታን ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ አሁንም እንደተለመደው፣ “ችግር የለውም፣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” የሚል ነበር፡፡ ጎብኚው ይህንን መልስ በድጋሚ በመስማቱ፣ ምን ለማለት እንደፈለገ ጠየቀው፡፡ የአስጎብኚው መልስ እንደዚህ የሚል ነበር፡- “አንዱ ጣትህ በመቆረጡ ምክንያት በእነዚህ ሰዎች ከመበላት ዳንክ ስለዚህ አንዱ ጣትህ መቆረጡ ጥሩ ልምምድ ባይሆንም የኋላ ኋላ ግን ለበጎ ሆነ፡፡ አንተ ደግሞ እኔን በንዴት ገደል ውስጥ መክተትህ ምንም ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ያንን በማድረግህ ምክንያት እዚሁ ባልቀርና አብሬህ ብጓዝ ኖሮ አንተን ትተው እኔን ይበሉኝ ነበረ፡፡ ይህም ለበጎ ሆነ”፡፡ ካጠፋ በኋላ የሚመለስና ይቅርታ የሚጠይቅ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! ይቅርታ ሲጠየቅ መለስ ብሎ ይቅር የሚል ጨዋ ማንነት ላለው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በሁሉም ነገር በፈጣሪው ላይ ያለውን እምነት ለማይተው ሰው ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! በአሁኑ ወቅት የምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለበጎ እንዲለወጥላችሁ ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
18 428162Loading...
28
ችግር ሲታየን! በምንም አይነት ሕብረተሰብ ውስጥ ብንኖርም፣ በዚያ ሕብረተሰብ መካከል አንድ ችግር ወይም ክፍተት ሲታየን ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሽ በሁለት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያውና ፈጽሞ የማይመከረው፣ መነጫነጭ፣ ስህተተኛውን ፈልጎ መክሰስ፣ ሰውን መውቀስ፣ አሉታዊ ወሬን ማራባትና የመሳሰሉት አይነት መንገድ ነው፡፡ ይህ ዝንባሌና ልምምድ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለእኛ ለራሳችን እጅግ አክሳሪና ጤና-ቢስ ነው፡፡ ሁለተኛውና የሚመከረው፣ ችግሩ ለእኛ ስለታየን እንደቤት ስራችንና እንደተልእኳችን ማየት፣ በታየን ነገር ላይ አንዳንድ የመፍትሄ መንገዶችን መፈለግና የማበርከት መንገድ ነው፡፡ ይህ ዝንባሌና ልምምድ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለእኛ ለራሳችን ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው፡፡ 1. ለችግሩ መፍትሄ በማምጣታችን ምክንያት ይህ ነው የማይባል እርካታ ይሰጠናል፡፡ በሕብረተሱ መካከል ጤናማ እና ሚዛናዊ በራስ መተማመን ያላቸው ሰዎች በየጊዘው የሚያዩትን ችግር ለመፍታት ራሳቸው የሚያቀርቡ ሰዎች ናቸው፡፡ 2. ለፈታነው ችግር የገንዘብ ክፍያ እገኛለን፡፡ በዙሪያችን ብንመለከት ሰዎች የገቢ ምንጭን የሚያገኙት ለሚቱት ችግር ነው፡፡ የሰዎችን ችግር ስናቃልልላቸው ሰዎቹ ደስ ብሏቸው ገንዘብን ይከፍሉናል፡፡ 3. የስነ-ልቦና ጤንነት እናገኛለን፡፡ የሚያዩት ችግር ይዘው ከሚነጫነጩ ይልቅ መፍትሄ ለማምጣሰ የሚሰሩ ሰዎች አዎንታዊ አመለካከት ስለሚዳብሩ ጤናማ ማንነት ይኖራቸዋል፡፡ እድሉ አያምልጣችሁ! • እኛ ያለን ነገር የሌላቸው ሰዎች መብዛት - እኛ ያለንን የመስጠት ታላቅ እድል ነው! • እኛ ያየነውን ነገር ያላዩ ሰዎች መብዛት - እኛ ያየነውን የማሳየት ታላቅ እድል ነው! • እኛ የገባን ያልገባቸው ሰዎች መብዛት - እኛ የገባንን የማስረዳት ታላቅ እድል ነው፡፡ • እኛ የምናውቀውን የማያውቅ ሰዎች መብዛት - እኛ የምናውቀውን የማሳወቅ ታላቅ እድል ነው! • እኛ የምንችለውን የማይችሉ ሰዎች መብዛት - እኛ የምንችለውን እንዲችሉ የማሰለጠን ታላቅ እድል ነው! ሰዎችን ለውጡ! ሃሳብ ሽጡ! መፍትሄን አምጡ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
21 46063Loading...
29
ችግር ሲታየን!
16 1568Loading...
30
ችግር ሲታየን! https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
1600Loading...
31
https://vm.tiktok.com/ZMMW39wB7/
19 3617Loading...
32
ምን አደርግ ነበር? አንድ ጊዜ ቆም በሉና ሃሳባችሁን ከሶስት እስክ አምስት አመት መለስ በማድረግ ራሳችሁን ይህንን ጥያቄ ጠይቁት፡- አሁን የማውቀውን ነገር ያን ጊዜ ባውቅ ኖሮ ወይም አሁን የገባኝ ነገር ያን ጊዜ ገብቶኝ ቢሆን ኖሮ ምን አደርግ ነበር? ምንስ እለውጥ ነበር? በሉ ጊዜው አልረፈደም ዛሬ አስቡ፣ አቅዱ እና አድርጉት! ዛሬ ለለውጥ ተነሱ! ምናልባት ያን ጊዜ ማድረግና መለወጥ ትችሉ የነበረው ነገር አሁ በፍጹም እድሉ እንደገና የማይመጣ ስለሆነ አልፎበታል ካላችሁ፣ ዛሬ እጃችሁ ካለው ነገር አንጻር በመነሳት ምን ማድረግና ምን መለወጥ እንደምትችሉ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡ ቢያንሰ ቢያንስ ይህንን የሕይወት ዘይቤ መጀመርና ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ መልካም ቅዳሜ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
18 01859Loading...
33
ይህ የስጠና ማስታወቂያ በZoom የሚሰጥ ሲሆን በተለይም ከሃገር ቤት ውጪ ለምትኖሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ በፖተሩ ላይ ባለው የቴሌግራም አድራሻ ማለትም @Helinakeb የመመዝገብ ፍላጎታችሁ ገልጻችሁ inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ በሃገር ውስጥ ላላችሁ አዲስ አበባ በአካል የሚሰጥ ስልጠና በመዘጋጀት ላይ ስለሆነ ማስታወቂያውን እስክንለቅ ታገሱን፡፡ በሃገር ውስጥ የምትኖሩና የሰዓቱን ልዩነት አጣጥማችሁ የ Zoom ስልጠናውን መሳተፍ ከፈለጋችሁ በ @Helinakeb ፍላጎታችሁ ገልጻችሁ inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
17 5649Loading...
34

35
የስልጠና እድል! With Dr. Eyob Mamo ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡ ራእይ . . . • የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . . • ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . . • ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . . . . . ብቸኛው መንገድ! በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
10Loading...
36

15 0139Loading...
37
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡ በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡ ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡ አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን? መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች … • ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡ • ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ • አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡ እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
19 465150Loading...
38
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”
16 05125Loading...
39
ስሜታዊውና ምክንያታዊው ስሜታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት የሚሰጥ ድንገተኛ ምላሽ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ምላሽ ውጤት ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ በተቃራኒው ምክንያታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት በቂ ጊዜ ወስዶ፣ ውጤቱን አውጥቶና አውርዶ ውጤቱን ከጅማሬ አይቶ ምላሽ መስጠት ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ ስታስብ መነሻህ ስሜታዊነት ይሁን ወይስ አእምሮህ ያሰበበትና አጥጋቢ ምክንያት ያለው ተግባር ለይተህ የማወቅን ልምምድ አዳብር፡፡ ይህንን መለማመድ ዘወትር በስሜት እየተነዳህ ውሳኔና እርምጃ ውስጥ ከመግባትና ውጤቱ አፍራሽ ከሆነ ሁኔታ ይጠብቅሃል፡፡ ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት ለነበረህ ገጠመኝ የሰጠኸውን ምላሽ አስብና ያንን ምላሽ የሰጠህበትን መነሻ አሳብ አጢነው፡፡ “ያነሳሳኝ ስሜት ነው ወይስ አእምሮዬን ተጠቅሜ በቂ ምክንያት አግኝቼ ነው?” የሚል የማስታወሻ ጽሑፎችን በመጻፍ ልዩነቱን ማየት ትችላለህ፡፡ እንዲህ አይነት ልምምዶችን በመደጋገም በማድረግ ስሜታዊ ልማዶችህን ቀስ በቀስ ልትቀርፋቸው ትችላለህ፡፡ አንዲት ደቂቃ በመታገስ የእለቱን የጋለ ስሜት ማሳለፍ ሲችሉ የመጣላቸውን የስሜት ንዝረት በማስተናገድ የሌላውንና የራሳቸውን ታሪክ ያበላሹ ሰዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡ በየእለት የሰው ለሰው ግንኙነት መካከል በሚነሱ ነገሮች ሁሉ የሚፈነዱና ቁጣ ቁጣ የሚላቸው ሰዎች፣ በትዳርና በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ በስሜት በተናገሩት ንግግር ከተቆሳሰሉ በኋላ ለመወያየት የሚሞክሩ ሰዎች፣ በማሕበራዊውና በሃገር ደረጃ አንድን ነገር ገና ከመስማታቸው ስለሁኔታው በሚገባ ሳያጠኑና የምክንያታዊነት ሂደት ሳይከተሉ ለጥፋት የሚነሳሱ ሰዎች ምክንያታዊ ሳይሆኑ ስሜታዊ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያታዊነት የበሳሎች መንገድ ነው፡፡ ምክንያታዊነት የአዋቂዎች ምርጫ ነው፡፡ ምክንያታዊነት ሚዛናዊ በራስ የመተማመን ደረጃ የደረሱና ከፍ ያሉ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ ስሜታዊነት ጠባብነት ነው፡፡ ስሜታዊነት አርቆ ማሰብ ያለመቻል ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የመሸነፍና አቅም የማጣት ምልክት ነው፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ከስሜታዊነት ወደ ምክንያታዊነት የመሸጋገርን ጉዞ እንድትጀምርና የግልህን፣ የቤተሰብህንና የሕብረተሰቡን ሕይወት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የምትሰራ ብልህ ሰው እንድትሆን ላበረታታህ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
21 307109Loading...
40
ስሜታዊውና ምክንያታዊው
15 82710Loading...
Показать все...

👍 41
ጥያቄ፡- ሰላም ዶክተር፡፡ በአንተ ማሕበራዊ መድረኮች በነጻ ስለምናገኛቸው ትምህርች ላመሰግንህ እፈልጋለሁ፡፡ መጠየቅ የምፈልገው ግን፣ በጣም አስቸጋሪ ሕይወት የነበራት አንድ ጓደኛዬ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሳገኛት በጣም ተለውጣ እና ሕይወቷን በስርአት እየመራች አገኘኋትና ምን እንደተፈጠረ ስጠይቃት ከአንተ ጋር የግል ሜንቶርሺፕ እንደወሰደች ነገረችኝ፡፡ ሜንቶርሺፕ ምን ማለት እንደሆነ ስጠይቃት ጋን ማስረዳት አልቻችም፡፡ ሁኔታው ትኩረቴን የሳበው እኔም መለወጥ ስለምፈልግ ነው፡፡ የተለያዩ የማነቃቂያ ስልጠናዎችን ወስጄ ግን እስካሁን ያው ነኝ፡፡ በሜንቶርሺፕና በማነቃቂያ ስልጠኛዎች መካከል ልዩነት አለ? ልዩነታቸውን ብታስረዳኝ፡፡ መልስ፡- በነጻ በማቀርበው የማሕበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በመጠቀም ላይ ስላላችሁ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በምችለውና ጊዜው በፈቀደልኝ ሁሉ ይህንን ማድረጌን እቀጥላለሁ፡፡ በክፍያ የግል ምክር፣ Coaching እና mentorship ላልሺው፣ እሱን የሚፈልጉ ሰዎች inbox በማድረግ ፍላጎታቸውን በመግለጽ አገልግሎቱን እያገኙ እንደሆነ ላሳውቅሽ እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን በማድረግና ቀጠሮ በማስያዝ ላለባችሁ ጥያቄ፣ ተከታታይ የ Coaching እና mentorship ፍላጎት መልስ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ የማነቃቂያ ስጠና እወስዳለሁ ስላልሺው፣ ማነቃቂያ ማለት ያው እንደ ስሙ ማነቃቂያ ነው፡፡ ያነቃቃሻል፣ ማለትም “ትችያለሽ፣ ተነሺ፣ ስሪ ሃብታም ትሆኛለሽ . . .” ይልና ያቃሻል እንጂ መንገዱን አያመላክትሽም፡፡ ይህ ሂደት የራሱ የሆነ ጥቅም ቢኖረውም ዘላቂ ውጤት ግን አያመጣም፡፡ ብዙ ሰዎች እንዲዘህ አይነቱን ዝግጅት ይካፈሉና ማነቃቂያው የሰጣቸው እንድርድረት ሲደክም እደገና ሊነቃቁ ይዳ፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ ከዚህ ሂደት ባለፈ ሁኔታ ለውጥን ከፈለግሽ የሚከተሉትን አሰራሮች መገንዘብና መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ማሰልጠን የአሰልጣኝነት ሂደት ሰልጣኙ አንድን ክህሎት እስከሚያዳብር ድረስ እና ወደ አንድ የብቃት ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ የሚደረግ የሁለት ሰዎች ግንኙነት ነው፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ የራእይ ጉዳይ ሊካተት ወይም ላይካተት ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የአሰልጣኝ ድርሻ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሰልጣኝን አንድ የክህሎት ደረጃ እንዲደርስ ማለማመድ ነው፡፡ ስሆነም፣ ያሰለጥናል፣ ስልጠናው ግቡን መምታቱን ያረጋግጣል፣ በተገቢው ሁኔታ በመሰልጠን ብቃቱን ያዳበረውን ሰው ያሳልፋል፣ በብቃት ያልጨረሰውን ሰው ደግሞ የራሱን ጉዞ እንዲዲከተል ይለቀዋል፡፡ የአሰልጣኝ ገደቡ እዚህ ድረስ ነው፡፡ 2. ማማከር የማማከር ሂደት የሚነካው አንድ ሰው ባጋጠመው ሁኔታ ዙሪያ ወይም ወደፊት መቀጠል በሚያስፈልገው ነገር ላይ ጥበብን የማካፈልንና ምሪትን የመስጠትን ሁኔታ ነው፡፡ በዚህም ግንኙነት ውስጥ የራእይ ጉዳይ ሊካተት ወይም ላይካተት ይችላል፡፡ ሆኖም፣ በምክር ፈላጊው አነሳሽነት ወይም በመካሪው ሃላፊነት የተሰማው እርምጃ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ የጥበብና የምክር መካፈልን ያደርጋል፡፡ ይህ የምክር ተግባር በአንድ ጊዜ ግንኙነት ሊከሰት ሲችል አንዳድ ጊዜ ደግሞ የጥቂት ቀናትንና ሳምንታት ሂደት ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለሆነም፣ መካሪው ምክረ-ሃሳቡን ይለግሳል፣ ተመካሪውም ምክሩን ተግባራዊ ለማድረግ መንገዱን ይቀጥላል፡፡ 3. ማስተማር የአስተማሪ-ተማሪ ግንኙነት እንደ ስልጠና ከአንድ ክህሎት ጋር የተያያዘ ሊሆን ቢችልም ከዚያ የሚለይበት ሁኔታም ሊያቅፍ ይችላል፡፡ አስተማሪው ለተማሪው አንድን ርእስ ወይም ጽንሰ-ሃሳብ ከማስጨበጥ አንጻር ተገቢውን እውቀት ያካፍለዋል፡፡ ይህ ጽንሰ-ሃሳብ ከአንድ ራእይ ጋር ሊዛመድም ላይዛመድም ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን አንድ የአእምሮ እውቀት ከማስጨበጥ፣ አንድን ጥበብ ከማካፈል ወይም አንድን ሞያዊ ክህሎት ከማዳበር ጋር ይገናኛል፡፡ ስለሆነም፣ አንድ አስተማሪ የአሰራሩ ሂደት ለመማር ብቁ ነው ብሎ በፊቱ ያመጣለትን ሰው በማስተማርና በመፈተንና የብቃት ማረጋገጫን በመስጠት ያሳልፋል፡፡ 4. “ኮች” ማድረግ የኮች ድርሻ በአብዛኛው የአሰልጣኝነትን ተግባር ያቀፈ ሲሆን፣ ከዚያ ለየት የሚለው አሰልጣኝ ሰልጣኙ አንድ ክህሎት ደረጃ ከደረሰለት በኋላ ያንን ክህሎት መጠቀም በሚፈልግበት መስክ እንዲጠቀም ሲተወው፣ ኮች ግን አንድ የስኬት ግብ ወይም ጥግ ላይ እስከሚያደርስ ድረስ ይሰራል፡፡ ልክ እንደ ማሰልጠን፣ ማማከርና ማስተማር፣ የኮችነት ሂደትም ምንም እንኳን አንድ ግብ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ከአንድ ራእይ ጋር የተገናኘ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ 5. ሜንቶር ማድረግ በጥቅሉ ሲገለጽ የሜንቶርነት ሂደትና አሰራር ከላይ የተዘረዘሩትን አራት ገጽታዎች ያቀፈ ነው፡፡ ሜንቶር ያሰለጥናል፣ ያማክራል፣ ያስተምራል እንዲሁም ኮች ያደርጋል፡፡ ትክክለኛ ሜንቶር ለአንድ ዓላማ አጠገቡ ያስጠጋውን ሰው የሕይወት አቅጣጫ መስመር የማስያዝ አቅም አለው፡፡ አመለካከቱን፣ ባህሪይውን፣ ዲሲፕሊኑንና ከዚያም አልፎ ራእዩን ማካፈል አንጻር ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ ስለዚህ ሜንቶር ከላይ የተዘረዘሩትን አራቱን ሂደቶች ያጠቃልላል፣ እነዚህ አራቱ ሂደቶች ግን ሜንቶርነትን አያጠቃልሉም፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 134 25😱 4🤩 3😁 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጥያቄ፡- ሰላም ዶክተር፡፡ በአንተ ማሕበራዊ መድረኮች በነጻ ስለምናገኛቸው ትምህርች ላመሰግንህ እፈልጋለሁ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ሕይወት የነበራት አንድ ጓደኛዬ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሳገኛት በጣም ተለውጣ አገኘኋትና ምን እንደተፈጠረ ስጠይቃት ከአንተ ጋር የግል ሜንቶርሺፕ እንደወሰደች ነገረችኝ፡፡ ሜንቶርሺፕ ምን ማለት እንደሆነ ስጠይቃት ጋን ማስረዳት አልቻችም፡፡
Показать все...
👍 25
Фото недоступноПоказать в Telegram
በፍጹም አታቁም! “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡ • “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡” • “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?” • “ይህ ነገር ወደፊት አላራምድ አለኝ፡፡” • “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡” • “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?” በእዚህና በመሰል ስሜቶች ከጀመርከው ነገር እንዳትገታ ከፈለክ “በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡- • ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡ • መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡ • ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡ • በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡ • መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
👍 121 49
Фото недоступноПоказать в Telegram
በ Zoom ሊሰጥ የታቀደው የስድስት ሳምንት ስልጠና ባለፈው ሰኞ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡ የመጀመሪያውን ሳምንት (ክፍል አንድ) ትምህርት ጀምረናል፡፡ ምናልባት ለመሳተፍ ፈልጋችሁ የተዘናጋችሁና ሳትመዘገቡ የመጀመሪያው ክፍል ያመለጣችሁ ካላችሁ ለጥቂት ሰዎች ብቻ አንድ እድል እንሰጣለን፡፡ በእዚህ ሁለት ቀናት ቀድሞ ጥያቄ ላቀረቡና ለሚመዘገቡ አምስት ሰዎች ያመለጣቸውን ክፍለ-ጊዜ የማካካሻ ክፍለ-ጊዜ እንደምሰጥ አሳውቃለሁ፡፡ በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ጥያቄያችሁን ለህሊና በመላክና መስፈርቱን በሟላት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ @Helinakeb
Показать все...
👍 53 15
ችግር ሲታየን! የሚከፈለን ለፈታነው ችግር ነው! ችግር ስናይ ሁለቱ ምርጫዎቻችን 1. መነጫነጭ፣ መካሰስ፣ መወቃቀስ፣ አሉታዊ ወሬን ማራባት 2. እንደተልእኳችን ማየት፣ መፍትሄ መፈለግ፣ ማበርከት የሁለተኛው መንገድ ጥቅም 1. ለችግሩ መፍትሄ በማምጣታችን ምክንያት ይህ ነው የማይባል እርካታ ይሰጠናል፡፡ 2. ለፈታነው ችግር የገንዘብ ክፍያ እገኛለን፡፡ 3. የስነ-ልቦና ጤንነት እናገኛለን፡፡ ለተግባራዊ ማብራሪያ ከታች ያለውን የ YouTube ሊንክ በመጫን ትምህርቱን ይከታተሉ! https://youtu.be/QDZ73X37fnQ
Показать все...
ችግር ሲታየን ምን እናደርጋለን? || Dr. Eyob Mamo || የሚከፈለን ለፈታነው ችግር ነው! || በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

1. ችግር ሲታየን! የሚከፈለን ለፈታነው ችግር ነው! ችግር ስናይ ሁለቱ ምርጫዎቻችን 1. መነጫነጭ፣ መካሰስ፣ መወቃቀስ፣ አሉታዊ ወሬን ማራባት 2. እንደተልእኳችን ማየት፣ መፍትሄ መፈለግ፣ ማበርከት የሁለተኛው መንገድ ጥቅም 1. ለችግሩ መፍትሄ በማምጣታችን ምክንያት ይህ ነው የማይባል እርካታ ይሰጠናል፡፡ 2. ለፈታነው ችግር የገንዘብ ክፍያ እገኛለን፡፡ 3. የስነ-ልቦና ጤንነት እናገኛለን፡፡ እድሉ አያምልጣችሁ! • እኛ ያለን ነገር የሌላቸው ሰዎች መብዛት - እኛ ያለንን የመስጠት ታላቅ እድል ነው! • እኛ ያየነውን ነገር ያላዩ ሰዎች መብዛት - እኛ ያየነውን የማሳየት ታላቅ እድል ነው! • እኛ የገባን ያልገባቸው ሰዎች መብዛት - እኛ የገባንን የማስረዳት ታላቅ እድል ነው፡፡ • እኛ የምናውቀውን የማያውቅ ሰዎች መብዛት - እኛ የምናውቀውን የማሳወቅ ታላቅ እድል ነው! • እኛ የምንችለውን የማይችሉ ሰዎች መብዛት - እኛ የምንችለውን እንዲችሉ የማሰለጠን ታላቅ እድል ነው! #solution #growth #inovation

👍 45 10🔥 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የጠበቅነውና የሆነው ነገር ሊለያይ! በአንድ ነገር ላይ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ስሜታችንንና አንዳንዴም ገንዘባችንን አውጥተን፣ ሰርተንና ገንብተን የጠበቅነው ውጤት ሌላ ያገኘነው ውጤት ግን ሌላ ሲሆን ግር መሰኘታችን አይቀርም፡፡ ሆኖም፣ አንድን ነገር ጠብቀን የምንፈልገውና የምንጠባበቀው ውጤት ሳይሆን ሲቀር ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሸ ወሳኝ ነው፡፡ ለማንኛውም ማየት የሚገቡን ሁኔታዎች . . . 1. ምናልባት የተሳሰተና መጀመር የሌለብንን ነገር ጀምረን ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት ያለን አማራጭ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ የተጀመረውን የተሳሳተ ነገር በማቆም፣ ትክክለኛ ነገር የመጀመር ውሳኔ መወሰንና የአቅጣጫ ለውጥ ማድረገ ነው፡፡ 2. ምናልባት ትክክለኛውን ነገር ጀምረን የተጠቀምነው ስልት ግን የተሳሳተ ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት የአደራረግ ስልታችንን የማረምና የተለየ ስልት የመጠቀምን አማራጭ መከተል የግድ ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ማንበብ ካለብን ማንበብ፣ መሰልጠን ካለብን መሰልጠን፣ ባለሞያ ማማከር ካለብን ደግሞ ማማከር አስፈላጊ ነው፡፡ 3. ምናልባት የተጀመረው ነገርም ሆነ የተጠቀምንበት ስልት ትክክለኛው ሆነው ሳለ የተጠባበቅነው ውጤት እውነታውን ያላገናዘበ ይሆናል ሁኔታው ይህ እንደሆነ ከደረስንበት ከአንድ ነገር የምንጠባበቀው ውጤት ከልክ ያለፈና ከእውነታ ውጪ የመሆኑን ሁኔታ ልክና ገደብ ማስያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ካላስተካከል ሁል ጊዜ ተስፋ እንደቆረጥን እንኖራለን፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
96👍 55🔥 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዓላማና የተስፋ ግንኙነት በአንድ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታራሚዎች በቂ የሆነና የተሟላ የምግብ አቅርቦት ነበራቸው፡፡ ከተወሰነ የማረሚያ ቤት ቆይታቸው በኋላ እርስ በርሳቸው ስለተላመዱ በተለያዩ ጨዋታዎች እየተደሰቱና አንዳንድ ሞያ ነክ ነገሮችንም እየሰሩ መረጋጋት ጀምረዋል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁሉንም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተጫጫናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተስፈኛ ሆነው የመቆየት አቅማቸውንም አጡ፡፡ የሆነው ነገር ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሲነሱ በማረሚያ ቤቱ ግቢ አንድ ጥግ ላይ የተከመሩ አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ነበሩና እነዚህን ጆንያዎች ካሉበት በማንሳት ወደሌላው የማረሚያ ቤቱ ግቢ ጥግ እንዲወስዱና እንዲከምሯቸው ተነገራቸው፡፡ ሁሉም ታራሚዎች በመነሳሳት ያንን ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ ከዚያም ወደማምሻው ላይ ጠዋት ወስደው የከመሩትን የጆንያ አሸዋ ክምር ወደ ነበረበት እንዲመልሱ ታዘዙና ይህ ስራ በየቀኑ እንደሚቀጥል ተነገራቸው፡፡ እነዚህ ታራሚች በተወካያቸው በኩል አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ወዲያና ወዲህ የሚመላለሱበት ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ምንም ዓላማ የሌለው ተግባር እንደሆነና አርፈው እንዲታዘዙ ተነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ስሜታቸው በጣም የወረደው፡፡ ምንም ዓላማ የሌለውን ተግባር ሲደጋግሙ መኖር ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ምናልባት ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የሚጫጫነን የመኖራችንን ዓላማና ትርጉም እንዲሁም በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች ለምን እንደምናደርጋቸው ዓላማቸውን በሚገባ ስላላወቅነው ይሆን? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
👍 201 73🔥 10🎉 1
Repost from Dr. Eyob Mamo
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአንድ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ! አንድን የምታውቁትን ነገር እንደገና ላስታውሳችሁ፡፡ በአለም ላይ አሁን እናንተ በማለፍ ላይ ባላችሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ፣ በማለፍ ላይ ያሉና ወደፊትም የሚያልፉ ሰዎች እልፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ይህ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲቀብራቸው፣ ሌሎች ደግሞ በእርግጥም ያልፉታል፡፡ ለዚህ ልዩነት መነሻ የሚሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ የመቻላቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእነዚህ ሰዎች መካከል ያለው ዋና ልዩነት፣ በዚያው ተውጠው የቀሩት ሰዎች ከሚያልፉበት ሁኔታ የተነሳ በመደናገጥ ወደፊት መገስገስን በመተው በመቆማቸው ምክንያት ሲሆን፣ እነዚያ ዘልቀው የሄዱትና በአሸናፊነት የወጡት ደግሞ በሚያልፉበት ሁኔታ ውስጥ በፍጹም ሳይቆሙ ወደፊት በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት ነው፡፡ በአንድ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ፣ በእርግጥም እለፉ እንጂ እንዳተቆሙ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
👍 133 59🔥 16😢 5🤩 1
የልጅነት ልምምዴ ጣጣ! “የቤተሰቡ ብቸኛ ሴት ልጅ ሆኜ ነው ያደኩት፡፡ በልጅነቴ ያሳለፍኳቸው ደስ የሚያሰኙ ብዙ ልምምዶች ቢኖሩኝም እስካሁን ትዝታው በፍጹም ያልደከመና ትናንትና የሆነ እስከሚመስለኝ ድረስ ትዝ የሚለኝ አንድ ሁኔታ አለ፡፡ ገና የአምስት ዓመት ልጅ እያለሁ አንድ ቀን አባቴ አዲስ ልብስ ገዛልኝና በጣም ከመደሰቴ የተነሳ ወዲያውኑ ልብሱን ለብሼ ላሳየው አባቴ ተቀምጦ ቲቪ ሲመለከት ወደነበረበት ወደ ሳሎን ቤት መጣሁ፡፡ አባቴም፣ “ዋው! በጣም የሚያምር ልብስ ነው፣ ነገር ግን ውፍረትሽን ትንሽ አወጣው” ብሎ የተናገረኝ ንግግር እስካሁን ውስጤ ቀርቷል፡፡ አሁን የ25 አመት ወጣት ነኝ፡፡ ይህ የአባቴ ንግግር በራሴ ላይ ካመጣብኝ የአመለካከት ቀውስ ጋር እየታገልኩኝ እንደምኖር ሲሰማኝ የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚያተኩሩት የማያምረው የእኔነቴ ክፍል ላይ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ምንም አይነት ልብስ ብገዛ የልብሱን ውበት እኔ ያበላሸሁት ነው የሚመስለኝ፡፡ የምለብሰው ልብስም ሆነ የማደርጋቸው ነገሮች የእኔን አስቀያሚነት የሚያጎሉ እንደሆነም ይሰማኛል፡፡ ስዎች ሳይገፉኝ የገፉኝ ሳይነቅፉኝ የነቀፉኝ፣ ሳያገልሉኝ ያገለሉኝ . . . ይመስለኛል”፡፡ የዚህች ወጣት ታሪክ የተለያየ ቅርጽና ቀለም ይያዝ እንጂ ብዙ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች የሚታገሉበትን ሁኔታን አመልካች ነው፡፡ አያችሁ፣ እድሜያችን ከሰባት ዓመት በታች በነበረበት ጊዜ አመለካከታችንን ገና ቀርጸን ያልጨረስንበት እድሜ (formative age) ላይ በመሆናችን ምክንያት የሚነገረንን ነገር በሙሉ እንደወረደ የመውሰድ ዝንባሌ አለን፡፡ በሌላ አገላለጽ አንድ ነገር ሲነገረን፣ “ይህ ሰው እንደዚህ ያለኝ ከእኔ የተነሳ ብቻ ሳይሆን ከራሱም የግል አመለካከት አንጻር ነው” በማለት በምክንያታዊነት (rationalize አድርገን) የማሰብ የአእምሮ ክፍላችን ስላልዳበረ ማንነታችን የተነገረውን ሁሉ እንደ እውነት ተቀብሎ ነው የምናድገው፡፡ ይህ ውስጠ-ህሊናችን የገባውና የተቀበልነው “እውነታ” መሰል "ምልከታ" በወደፊቱ የራስ-በራስ እይታችን ላይ ይህ ነው የማይባል ጫናን የማስከተል አቅም አለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ . . . 1. ከራሳችሁ ጋርም ሆነ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት አንጻር የምታስቧቸው ሃሳቦች ትክክል እንዳልሆኑ እያወቃችሁ እንኳን ማቆም ካቃታችሁ . . . 2. ከራሳችሁ ጋርም ሆነ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙነት አንጻር የምታንጸባርቋቸው ስሜታዊ ሁኔታዎች ትክክል እንዳልሆኑ እየገባችሁና እየተጸጸታችሁ ደጋግማችሁ የምታደርጓቸው ከሆነ . . . 3. “መቀየር እኮ እፈልጋለሁ ግን አልቻልኩም” የምትሏቸው፣ የፍቅር ግንኙታችሁን፣ ትዳራችሁን፣ ጓደኝነታችሁን ወይም ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን የሚያበላሹ ባህሪዎችና ዝንባሌዎች ካሏችሁ . . . ወደኋላ መለስ በማለት የልጅነት ልምምዳችሁን በማሰብና ምናልባት በአንድ ልምምድ ተጽእኖ ስር የመሆናችሁን ሁኔታ እንድታጣሩ ትመከራላችሁ፡፡ ይህንን የለውጥ መንገድ ለመጀመር ደግሞ፣ ጸሎት የማድረጋችሁ አስፈላጊነት ሳይዘነጋ፣ ስለሁኔታችሁ በማንበብ፣ ምክርን በመውሰድና ሆን ብሎ (intentionally) በማሰብ የለውጥ መንገድን መጀመር ይኖርባችኋል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 176 69🔥 14😁 2