cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Muktarovich Ousmanova

Ethiopia forever

Больше
Рекламные посты
63 595
Подписчики
+724 часа
+127 дней
-36530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አሜሪካ እየተናገረች ነው፦ "አሸናፊ በሌለበት ሁኔታ የቀጠለው ጦርነት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ካተረፈው ችግርና ጉዳት ባለፈ ይህ ነው የሚባል ውጤት አላመጣም። ስለዚህም አሁን ጊዜው የውይይት ነው። " በኢትዮጵያ የአሜሪካ አንባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ
Показать все...
የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር በጥይት ተመቱ፡፡ ***** የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ከሰአት በኋላ በሀንድሎቫ ከተማ በተተኮሰባቸው ጥይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቁሰላቸውን የስሎቫኪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከጥቃቱ ጋ በተያያዘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንም የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ገልጸዋል፡፡
Показать все...
ሰላም የሃገሬ ልጆች በያላችሁበት ሰላም ይብዛላችሁ። ዶክተር ሀብታሙ እባላለሁ። ኦሮምኛን በራሴ መንገድ ተምሬ መንገዴን ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ለማሳየት የሚረዳ Riqicha/ሪቂቻ የተሰኘ መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ። Riqicha/ሪቂቻ ለአፋን ኦሮሞ ጀማሪወች የቋንቋውን ህግ እና አጠቃቀም በአማርኛ:በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ በቀላሉ ግን በጥልቀት ለማስተማር የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉን እንዴት እና ለምን እንዳዘጋጀሁት ማወቅ ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ይችን ዘገባ ተመልከቱ፡ (https://www.press.et/?p=87024) • Riqicha/ሪቂቻ መጽሐፍ አዲስ አበባ ውስጥ የተወሰኑ መጽሐፍት ቤቶች ውስጥ ይገኛል። • የመጽሐፉን ትምህርቶች ከዚህ በታች ባሉት የማህበራዊ ትስስር ገጾች መከታተል ትችላላችሁ። 1. Telegram Chanel Link: t.me/riqichaOromooGrammar 2. you tube Chanel Link: https://youtube.com/@doctorhabtamug.jenberei?feature=share8 ኑ ኦሮምኛን አብረን እንማር! Koottaa Afaan Oromoo waliin haa barannu!
Показать все...
በብልፅግና ፓርቲ እና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት #ለሶስተኛ ግዜ በመቐለ ከተማ ተካሄደ በብልፅግና ፓርቲ እና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት ለሶስተኛ ግዜ በመቐለ ከተማ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7/2016 ተካሂዷል:: በውይይቱም ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመረውን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ ከመከሩ በኃላ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል:: በመጀመርያ አጀንዳነት የተለየውን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ሁለቱም ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት በመስማማት ፤ በመጨረሻም :- 1. በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት በማካሄድ፣ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከጀመርነው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ደርሰዋል:: 2. ማናቸውንም ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ ሁለቱም አካላት የበኩላቸውን ፓለቲካዊ ድርሻ ለመወጣትና በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል:: በተያያዘም የሚኖሩ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉ እና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ደርሰዋል :: 3. ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማምያዎች በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር ተስማምተዋል:: 4. የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፓለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መስማማት ላይ ደርሰዋል:: በቀጣይም በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት በመስማማት የእለቱን ውይይት አጠናቋል::
Показать все...
ሃሰተኛ ዩቲዩበሮችን መያዙ ቀጥሏል፣ ህፃናትን አርጃለሁ በማለት ቪዲዮ የሰራችው ተያዘች። #FastMereja በዩቲዩብ ሃሰተኛ ታሪኮች እውነተኛ በማስመሰል ከሰሩት መካከል ይህቺ "ገነት ግርማ" ትባላለች ሺ ህፃናትን አርጃለው ይኼኛው አንድ ሺ አንደኛዬ ነው ብላ ቪዲዮዎችን የሰራችው በውጪ ቋንቋዎችም እስኪተረጎም ያበቃችው በቅን ልቦች ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በተሰራ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ውላ በአሁን ሰዓት በየካ ፖሊስ መምሪያ እንደምትገኝ ቅን ልቦች ለፋስት መረጃ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል። ፋስት መረጃ
Показать все...
ቦሌ ብራስ እጅግ ታዋቂ የእናቶች ሆስፒታል ነው። የሀገር ሀብት ነው። ሀብትን ለኮሪደር አፍርሶ፣ ሌላ ሀብት አፍስሶ ሌላ ህንፃ መገንባት ምን ይባላል?
Показать все...
በትምህርት ተቋማት በሚቀጠለው 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ተገለጸ በሚቀጠለው ዓመት 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስቴርና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው በተገመገመበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር ተገምግሟል። የበጀት ስሚ መርሀ ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሁኑን ጠቁመው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
Показать все...
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ 📌 https://t.me/sellphone2777 📞  0929008292 📩 inbox @bina27 📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
Показать все...
አምባሳደር ማይክ ሀመርና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በአሜሪካን ኤምባሲ ተወያይተዋል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር እና የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ ጉዳይ የተወያዩት በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት የፖለቲካ ምህዳሩ እያደር መጥበብ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ሰላም ላይ ያላቸው ሚና የመሳሰሉትን መክረዋል
Показать все...
ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል። የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መቃጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል። ዘገባው የ Capital ጋዜጣ
Показать все...