cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

RAFA

LONG TERM THINKER PROBLEM SOLVER

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
184
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

✍ ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት📚 የማንበብ ያህል ነው ፡፡ ⚠️ ጨርሳችሁ ካላነበባችሁ አጀምሩት⚠️ ምክር ለወዳጅ : 👉👉🏾 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። : 👉🏾👉🏾 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። : 👉🏾👉🏾 የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። : 👉🏾👉🏾 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ። : 👉🏾👉🏾 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ። : 👉🏾👉🏾 ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። : 👉🏾👉🏾 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ። : 👉🏾👉🏾 ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ። : 👉🏾👉🏾 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ። : 👉🏾👉🏾 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። : 👉🏾👉🏾 በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ። : 👉🏾👉🏾 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ። : 👉🏾👉🏾 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! : 👉🏾👉🏾 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ። : 👉🏾👉🏾 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ። : 👉🏾👉🏾 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ። : 👉🏾👉🏾 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ። : 👉🏾👉🏾 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ። : 👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ። : 👉🏾👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። : 👉🏾👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። : 👉🏾👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ። : 👉🏾👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Показать все...
ውስጥህ ነው ወሳኙ ! ውጪ ያለው ውጤትህ የውስጥህ ንግግር ነጸብራቅ ነው ። ሰዎች ይጠሉኛል የሚለውን ሀሳብህን ካላቆምክ ሰዎች አንተን መጥላታቸውን ይቀጥላሉ ፤ በየሄድኩበት ክፉ ሰዎች ያጋጥሙኛል የሚለውን ሀሳብህን ማቆም ካልቻልክ ከተማው በክፉ ሰዎች መወረሩን ይቀጥላል ። ጥሩ ተመኝ ጥሩ እንድታገኝ ! በሰዎች ለመወደድ ብዙ ዋጋ እንከፍላለን፤ ሰዎች ደግሞ አይን የሚጥሉት ወይ አጥብቀው የሚወዱት ጠንካራ የሆነ ሰውን ነው። ማንም ደካማን አይወደውም፤ እንዲሁ የሚወድህ ፈጣሪ ብቻ ነው። ወዳጄ ጠንካራ መሆን ከፈለክ ራስህን አክብረው፣ ራስህን ከነ ድክመትህ ውደደው እና የህይወትህን ትልቁን አላማ እወቀው እሱ ላይ አተኩር ከዛ ሰዎሰዎይች አንተ ላይ ያተኩራሉ፤ እሱኮ ጠንካራ ነው አላማ አለው ብለው ይወዱሀል፤ ሳታስበው ድንቅ ማንነት ገነባህ ማለት ነው! የትኛውም ገንዘብ ቢተጣጠፍ ወይ ቢጨማድ ወይ ቢረገጥ ዋጋው እንደማይቀንስ እኛም በከባድ ፈተና ብንፈተን ከባድ ውጣ ውረዶች ቢገጥሙንም ዋጋችን መቼም እንደማይቀንስ መርሳት የለብንም!
Показать все...
ይሄ ሰው እብድ ነው፡፡ ( አብርሃም ሙሉ ሰው) እቤተክርስቲያን አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ሶላቱን ሰገደ እመስኪድ ፊት ቆሞ ፣ በትምህርተ መስቀል ፣ ተሳለመ ሄደ ምንድነው ይሄ ሰው ፣ ሃይማኖት እምነቱ ? በ'ሱ ልብ አንድ ሆነው ፣ ያፀኑት ሁለቱ እሳት እና ውሃን ውሃ እና እሳትን ፣ የያዘ አደባልቆ ምን የሚሉት ጥበብ ፣ ከማን ዘንዳ አውቆ ከአማኞች ተራ፣ ተለየ እርቆ ? ... የኔ መንገድ ብቻ ፣የጽድቅ እየተባለ ይሄ ሰው እንዴት ነው ፣ ከሁሉም ተስማምቶ፣ መከተል የቻለ ? ሁለት እግር ያለው ፣ ሁለት ዛፍ ካልወጣ አንደኛውን መምረጥ ፣ ሆኖ እድል እጣ ወይም ሁሉን መተው ፣ አማራጭ እያለው ለሁሉም የሚከብድ፣ ለብቻው ሚቀለው ወላሂ ! ማርያምን ! ፣ ይሄ ሰው እብድ ነው ፡፡
Показать все...
ብ.ል.ግ.ና ፓርቲ " ጣፋጯን ሲጋራ እናጭስ በጋራ" በጠዋት ከተነሳው ዛሬ አምስት አመቴ ሆነኝ ማለት ነው፡፡ በዚ ለሊት 'ምሄድበት አለኝ አደራ እንዳላረፍድ ቀስቅሱኝ' ያላቸው ሰው ያለ ይመስል በሁለት ትላልቅ ማደንቆሪያ ሬድዮ ከመቀስቀስ አልፎ ልትፈርስ አንድ ሀሙስ የቀራትን ጎጆአችንን ሊያፈርሱት ሲሞክሩ አንዲት አዛውንት አሮጊት ቀድሞውኑም የተከፈተ በራቸውን ከፍተው ወጡ፡፡ "ኧረ ስለፈጠራቹ ፤ ኧረ በጉልበታችሁ አምላክ ፤ ቆይ እስኪ ንገሩኝ እኛ ምርጫ በመጣ ቁጥር ጭቃ ማዘጋጀት አለብን እንዴ?" ወገባቸውን ይዘው ሹፌሩን ይገላምጡት ጀመር፡፡ " እንዴ ማዘርዬ የምርጫ ካርዶን ነው እንጂ የምን ጭቃ ነው ሚያዘጋጁት?" ሹፌሩ መለሰ፡፡ " እናንተ የቦረቦራቹትን ጆሮዬንም ግርግዳዬንም ልደፍንበት ነዋ" አሉት የንዴት ፊት እያሳዩት፡፡ ሹፌሩም ምንም ሳይመስለው ፈገግ ብሎ የሬድዮኑን ድምፅ ከፍ አደረገው፡፡ "ሰላም ሰላም ሰላም ፤ ስዶች ነን ብ.ል.ግ.ናን ይምረጡ ፤ ፓርቲአችን በብዙዎች ዘንድ የሚወደደውን 'ሲጋራን' ምልክት አድርጓል፡፡ ብ.ል.ግ.ናን ቢመርጡ ሲጋራን የማናደርስበት ክልል አይኖርም፡፡ ምን እሱን ብቻ ከሲጋራ ጋር እጅና ጓንት የሆኑትን አሽሽ ፤ ጋንጃና ጫትን እንደ እድሜአችሁ ተደራሽ እናደርጋለን፡፡ አሮጊቶች ያለከልካይ ሰው እንዲዘለዝሉ ወይንም እንዲያሙ ተግተን እንደምንሰራ በ ስድ ስም ቃል እንገባለን፡፡ እኛን አምነው ስልጣን ላይ ቢሾሙን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ አምስት አመት ሙሉ ያለስራ ተኝቶ የሚቅም ትውልድ እናፈራለን፡፡ አላማችን ሳንባ የሌለው ትውልድ ማፍራት ነው ፡፡ ብ.ል.ግ.ናዎች ነን !! " በሂወቴ እንደዛሬ ምርጫ እንደ ነፃነት የናፈቀኝ ጊዜ የለም፡፡ እኔም የዜግነት ግዴታዬን ለወጣ ብዬ አሰብኩና ከሱቅ ሲጋራ ገዛውና ወደ ሹፌሩ ጠጋ ብዬ "ተመርጣችሁ በነፃ አብረን እስከምንጨስና እስከምናጨስ አሁን እኔ የገዛውልህን አጭስ" ብዬው መርሀቸውን ጮክ ብዬ እየተናገርኩ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ #Beki "ጣፋጯን ሲጋራ እናጭስ በጋራ" ቤካ ስም አይጠቅስም😜 ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
Показать все...
ልማድ አንተ ማለት የየቀን ልማድህ ውጤት ነህ ፤ በየቀኑ የምታደርገው ልማድህ ያንተን ህይወት ይወስነዋል ምን ስታደርግ ነው የምትውለው ?አሁን ያለህን ውጤት የወሰነው የውጪው ሁኔታ ሳይሆን ያንተ ውሎ ነው ስታደርግ የምትውለው ምንድን ነው?
Показать все...
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው! አንተ መጥፎ ገጠመኝ ብለህ ያዘንክበት ጉዳይ ምን መልካም ነገር ይዞልህ እንደሚመጣ አታውቅም፤ ይሄኔ ከስንቱ አምልጠሀል ወዳጄ!
Показать все...
ደስተኛ መሆን ማለት አሁን ያለህበትን መቀበል ከዛ እያንዳንዱን ቅፅበት ማጣጣም ነው። ለማን ብለሀ ነው ስላለፈው የምትናደደው? ስለሚመጣው የምትጨነቀው? ወዳጄ ስለ ነገ አላማ ይኑርህ በተረፈ ዛሬን አጣጥመው፤ ከዚህ ውጪ ካደረክ ነፋስ እየተከተልክ ነው!
Показать все...
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን #ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን #ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን #አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና #ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል #እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል @beteafework 💚 @Kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Показать все...
✝ ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቀለሜ ቤተሰቦች 🙌🏾 እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። ✝በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🍁••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @BF_RAFA1
Показать все...
ድንግል_ማርያም_ብዬ_ሊቀ_መዘምራን_ኪነጥበብ_@DNZEMA_ዜማ_ቅዱስ_ያሬድ.mp32.20 MB