2 387
Подписчики
+424 часа
+677 дней
+35730 дней
Архив постов
#እንኳን_ደስ_አለን🏆
የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር የሆኑት አቤል ዘገየ በምርጥ የኢኖቬሽን ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድረው አሸናፊና ተሸላሚ በመሆን የኮሌጁን ብሎም የአስተዳደሩን ስም በኩራት አስጠርተዋል።
አሰልጣኝ መምህሩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በተለይም በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል "Initiating the resumption of industry extension service through stakeholder engagement" በሚል አርዕስት አቅርቦ በመወዳደር ነው አሸናፊ መሆን የቻለው።
ይህም በኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት መልካም አጋጣሚን በመጠቀም ለዘርፉ እሴትን በመጨመርና የማህበረሰብን ችግሮች ለመፍታትና አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ተግባራዊ በማድረግ ለተመረጠ የተሻለ የኢኖቬሽን ፕሮጀክት እውቅናና ማበረታቻ ለመስጠት በማሰብ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰርተው ከቀረቡ አስራ ሁለት ፕሮጀክቶች በቀዳሚነት ተመርጦ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶለታል፤
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመዘገው ውጤት የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህር አቤል ዘገየ ምርጥ የተሻለ የኢኖቬሽን ፕሮጀክት በመባል በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ በመሆንህ እንኳን ደስ አለህ! እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ግንቦት 4/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
የ1444ኛው ሂጅራ የረመዳን ወር ፆምን አስመልክቶ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር እና ሰራተኞች በጋራ የአፍጥር ስነ ስርዓት አካሄዱ።
የረመዳን ፆም 29 ቀን በሆነው በትላንትናው ምሽት የኮሌጃችን አመራሮች እና ሰራተኞች የታደሙበት ደማቅ የአፍጥር መረሃ ግብር በማድረግ አብሮነታቸውን አሳይተዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
#መልካም_የትንሳኤ_በዓል
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
ለኢትዮ ጣሊያን የአይ.ሲ.ቲ አሰልጣኝ መምህራን የክህሎት ክፍተት ስልጠና ተሰጠ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስልጠና በተከታታይ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል የዚሁ አካል የሆነ ለኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአይ.ሲ.ቲ ትምህርት ክፍል አሰልጣኝ መምህራን window server 2008 ላይ መስጠት ተቸሏል፤
የዊንዶውስ ሰርቨር 2008 በዋናነት ዊንዶውስ ሰርቨር 2008 R2 የሰርቨር ቨርችዋልን ለመስራት ዋና አቅሞችን ይሰጣል ፣ይህም አንድ ድርጅት ፊዚካል ሰርቨሮችን ወደ ጥቂት ሆስት ሰርቨር ስርዓቶች የማዋሃድ አቅም በመስጠት አጠቃላይ የአይቲ ኦፕሬሽን ወጪን በመቀነስ ፋይዳው ከፍ ያለ ይሆናል፤
በዚህም በትምህርት ክፍሉ ከስልጠናው ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና ለሰልጣኞች ለመስጠት፤ መምህራኑን በተሻለ ቴ/ጂ ስልጠና እንዲሰጡና እነርሱም የተሻለ ቴ/ጂ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ በማስቻል ለሚሰሩ ተያያዥ ስራዎች አስፈላጊነቱ ከፍ ያለ መሆኑንና ስልጠናውም ከመምህራኑ ጥያቄ በመነሳት የተሰጠ በመሆኑ ትምህርትና ስልጠናን በተሻለ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል እንደሚሆን በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ተናግረዋል፡፡
የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ከመጋቢት 22 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአስተዳደሩ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር በሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ/የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ 2015 ዓ.ም የክህሎት ውድድር ላይ በክላስተር ደረጃ የተደረገውን ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደርን ለመወከል በክልል ደረጃ የተደረገውን የመጨረሻ ውድድራቸውን አካሂደዋል።
በክልል ደረጃ በተካሄደው ውድድርም ኮሌጃችን የተወከለባቸው ሰባት የሙያ ዘርፎች ሲሆኑ እነሱም:-
1,በኤሌትሪካል/ኤሌክትሮኒክስ
2, በማኑፋክቸሪንግ
3, በአውቶሞቲቭ
4,በኮንስትራክሽን
5,በውድ ዎርክ
6,በአይ.ሲ.ቲ
7,በሆቴልና ቱሪዝም የሙያ ዘርፎች ናቸው።
በውድድሩ ከሁለቱ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው የሚሳተፉም ይሆናል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 28/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመጋቢት 22 ጀምሮ በክላስተር ደረጃ ባካሄደው የ2015 ዓ.ም የክህሎት ውድድር የተሳተፉ አስልጣኝ መምህራን እና ሰልጣኝ ተማሪዎች በውድድሩ ያስመዘገቡት ውጤት።
