cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሐመረ ኖኅ ሰንበት ት/ቤት

ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዓለም ገና ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ እና ድንግል ማርያም ወ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም የሐመረ ኖኅ ሰንበት ት/ቤት ቻናል ነው፡፡ "ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኻችሁ እፅፍላችሁ ዘንድ ግድ ኾነብኝ::" የይሁዳ.መ ፩-፫

Больше
Рекламные посты
353
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
-530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከክፋ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ፤ አንተ ወታቦተ መቅደስከ። Arise, O LORD, into thy rest; thou, and the ark of thy strength. መዝሙረ ዳዊት ፻፴፩(፻፴፪):፰ | PSALMS 131(132):8
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
🟢 🟡 🔴 ~ ነሐሴ 7 || ጽንሰታ (ቁጽረታ) ለእግዝእትነ ማርያም - የድኅነት መነሻ ቀን፨ ****************************** የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት ቅድስት ሐና የተወለደችው በቤተ ልሔም ይሁዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢያቄም የሚባል ሰው አግብታ ትኖር ነበር፡፡ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ሐና መካን ስለነበረች ልጅ መውለድ አልቻሉም፡፡ በዚህም ለበርካታ ዓመት ሲያዝኑና አምላካቸውን ሲማጸኑ ኖሩ፡፡ በዚህም መካከል ስዕለትን ተሳሉ፤ ፈጣሪ ልጅ ቢሰጣቸው ለቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደሚሰጡም ቃል ገቡ፡፡ አንድ ቀን ሁለቱም የእግዚአብሔር መልአክ በራእይ ተገልጦ የተባረከ ልጅ እንደሚሰጣቸው ነገራቸው፡፡ እጅግም ደስ ተሰኙ፤ በነሐሴ ሰባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች፤ ሁለቱ ጻድቃን የእግዚአብሔር ሰዎቸም በግንቦት አንድ ቀን እንደ ፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅን ወለዱ፡፡ እስከ ሦሰት ዓመት ድረስም በቤት ካሳደጓት በኋላ ስዕለታቸውን አስበው ለቤተ ከርስቲያን ሰጧት፡፡ እመቤታችንም በቤተ መቅድስ ለዘጠኝ ዓመት ኖራለች፤ ከዚያም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመወለድ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንዳበሠራትና ለጻድቁ ዮሴፍ እንዲጠብቃት እንደሰጠች ቅዱሳት መጻሕፈት ይነግሩናል፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት ከሁላችንም ጋር ይኑር፤ አሜን!
Показать все...
እግዚአብሔር አምላክም ኃዘናቸውን ሰምቶ ሐምሌ ፴ እሷ ለእርሱ ግምጃ ሲያስታጥቁት መቋሚያው አፍርታ ፍጥረት ፍሬዋን ሲመገቡ፣ እሱ ለእሷ ነጭ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በቀኝ ጆርዋ ገብታ በማኅፀንዋ ስታድር ራዕይ  አሳያቸው። እነርሱም ሄደው ለመፈክረ ሕልም/ ሕልም ተርጓሚ/ ነገሩት፤ ሕልም ተርጓሚውም የከበረች ልጅ ትወላዳለችሁ” ሲል ተረጎመላቸው። እያቄም እና ሐናም ሕልማቸው እንዲፈጸምላቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት እየጠየቁ ኖሩ፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምን እና ሣራን የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሐና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነችውን እና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር የነበረችው እመቤታችን ድንግል ማርያም በነሐሴ ሰባት ቀን  ተፀነሰች፡፡ ሐና በእርጅናዋ ጊዜ መፅነሷን የሰሙት ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርሙው፤ እየመጡ ጠይየቋት፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም በተሰነፀች ጊዜ ተአምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳባን ልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መፅነሷን ለማረጋገጥ መሕፀን ዳሰሰቻት፡፡ በአድናቆትም ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ በሌላ ጊዜም የአጎቷ ልጅ ሳምናስ በሕመም ምክንያት ይሞትና ሐና ትወደው ስለነበር አስክሬኑ በተቀመጠበት አልጋ ዙሪያ ስታለቅስ ድንገት ጥላዋ ቢያርፍበት የሞተው ተነሥቶ ሐና የአምላክ እናት የምትሆን እመቤታችንን እንደምትወልድና በዚህም ሐና እጅግ የከበረችና ምስጋና የሚገባት መሆኗን መሰከረ፡፡ ለዓለም ሁሉ የድኅነት መገኛ የሆነች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነሐሴ ሰባት የተባረከች እንደመሆኗ መላው ክርስቲያን በዓሏን ሊያከብር ይገባል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ  ልጅሽ ወዳጅሽ ይቅርታውን፣ ቸርነቱን፣ ምሕረቱን በእኛ ላይ ያሳድርብን ዘንድ ለምኝልን፡ አሜን!! ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ነሐሴ እና መዝግበ ታሪክ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፅንሰታ ለማርያም የብሕንሳ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ  በቅዳሴ ማርያም ላይ የእመቤታችንን የፅንሰቷን ነገር "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተጺነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ:- ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ" በማለት ተናግሯል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመወለዷ በፊት የአባቷ እና የእናቷ ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ በኢየሩሳሌም አገር የሚኖሩ ኢያቄምና ሐና የተባሉ በጣም ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡  ልጅ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ እግዚአብሔር እየሄዱ እግዚአብሔር አምላክ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መባ ይዘውም ሒደው ለሊቀ ካህናት ሮቤል ሲሰጡት እረሱምሊቀ ካህኑ እንኳ ሳይቀር “እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መባችሁን አልቀበልም” ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል። በሊቀ ካህናቱ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀምጠው ሳለ  ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክተው “ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?” ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡ እንዲሁም ”ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው‘ እያሉ ያቃልሉት ነበርና በዚህም እያዘኑ እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ይኅን በሰሙ ጊዜ “ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ” ስለትን ተሳሉ፡፡
Показать все...
✝ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘእለተ ሐሙስ https://t.me/zikirekdusn
Показать все...