ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 537 подписчиков, занимая 8 326 место в категории Технологии и приложения и 2 176 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 537 подписчиков.

Согласно последним данным от 04 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 26, а за последние 24 часа — -7, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 26.64%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 15.41% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 139 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 395 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 05 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 537
Подписчики
-724 часа
-77 дней
+2630 день
Архив постов
photo content

photo content

photo content

በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃው ሳይፈስ ስኬታማ ጥገና ተከናወነ …….//……… በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃው ሳይፈስ ከ18 ሜትር ጥልቀት በላይ ወደ ውሃ ውስጥ በመግባት ስኬታማ ጥገና መከናወኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሳ ገለጹ፡፡ ግድቡ ላይ 1.5 ሜትር ክበት ስንጥቅ በመኖሩ ግድቡ ውሃ የማስረግ ችግር ገጥሞት እንደነበር የገለፁት አቶ ደሳለኝ በዘመነ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ውሃው ሳይፈስ ጥገናውን በማከናውን ችግሩን መቅረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ የቻይናው ሲጂጂሲ ኩባንያ የጥገና ሥራውን ያከናወነ ሲሆን ሌሎች ታዋቂ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ውሃው ካልፈሰሰ መጠገን አንችልም ያሉትን ሲጂጂሲ ውሃው ሳይፈስ በመጠገን ለኃይል ማመንጫው በቂ የውሃ ክምችት እንዲኖር አስችሏል፡፡ በተጨማሪም የደለል ማስወገጃ እና መቆጣጠሪያ አሸንዳ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረ ሲሆን ጥገና ተከናውኖለት ወደ ሥራ ለማስገባት የሙከራ እና የፍተሻ ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ ደሳለኝ ገለፃ ለዚህ ጥገና አጋዥ የሆኑ የመቆጣጠሪያ ሰሌዳ እና የሞተር ፓምፕ ገጠማ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በጥገና ሥራው ላይ 31 ያህል ቻይናውያን የተሳተፉ ሲሆን የጣቢያው ሠራተኞችም በሥራው ላይ በመሳተፍ ጠቃሚ እውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውንም ነው አቶ ደሳለኝ የገለፁት፡፡ የኃይል መቆጣጠሪያው ሥርዓት ተበላሽቶ ለቁጥጥር አስቸጋሪ እንደነበርና በራስ የሰው ኃይል ከኮምፒውተር ሞደፊኬሽን በመስራት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለመጠባበቂያ ጀነሬተር ማስቀመጫ የሚያገለግል ቤት መገንባቱንም ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡ ሥራ አስኪያጁ እንደተናገሩት ከጥገና ሥራዎች ባሻገር ለሠራተኞች ምቹ ከባቢ ለመፍጠር የመኖሪያና የቢሮ አካባቢዎችን የማፅዳትና የማስዋብ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ ሠራተኞች በትርፍ ጊዜያቸው ራሳቸውን እንዲያዝናኑ የማዘወተሪያ ሥፍራዎችን የማደስና የዋይ ፋይ ኔትወርክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አቶ ደሳለኝ አብራርተዋል፡፡ በ1996 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጊቤ አንድ የውሀ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 184 ሜጋ ዋት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content

photo content

photo content

photo content

ዘርፉን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ እየተሰራ ነው ……//…… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ የሥራ ክፍል የሥራ ዘርፉን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድርግ የአቅም ግንባታ ሥራ ፕሮጀክት ቀረጾ ወደ ትግበራ መግባቱን የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውድነህ የማነ ገለጹ፡፡ አቶ ውድነህ እንደ ገለጹት በተቋም ደረጃ የተሰጠውን ተልዕኮ እና የሥራ ዘርፉ ከኃይል ሽያጭ በተጨማሪ በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በማድረግ አንድ የገቢ አማራጭ ለማድረግ በተቋም ደረጃ የተያዘውን ስትራቴጂክ እቅድ ለማሳካት ሥር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ የአቅም ግንባታ ስራዎች ፕሮጀክት ቀርጾ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የብድር ድጋፍ የሚከናወነው ይህን ፕሮጀክት በዘርፉ በርካታ ልምድ ያለው ኤሌክትሮ አማካሪ (ELC Electro-consult) የተባለ የኢጣሊያን ኩባንያ ጋር ውል በመፈራረም ከጥቅምት 16 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ስራ መገባቱን ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡ በሰራ ዘርፉ ያሉት ስድስት ዳሬክተሮች እና ሁለት ማናጀሮች በዋናነት የሚመሩት እና የስራ ዘርፉ ሰራተኞች ተሳታፊ የሚሆኑበት የአቅም ግንባታ ስራው የሚከተሉት አራት ዋና ዋና አላማዎች እንዳሉት አቶ ውድነህ የገለጹ ሲሆን እነርሱም ፡- 1ኛ አሁን ያለውን የክፍሉን አሰራር ስርአትና አወቃቀር አለማቀፍና ተወዳዳሪ ከሆኑ የአማካሪ ድርጅቶች ጋር ንፅፅር በማድረግ ያለውን ክፍተት መለየትና ፤ ክፍተቱን ለመሙላት የሚያስችል ስራዎችን ማለትም የቢዝነስ ፕሮሰስ ዲዛይን፤ ፖሊሲ ፤ ፕሮሲጀር፤ ፎርም፥ ቴምፕሌት ፤ መመሪያና ማኑዋል መዘጋጀት፡፡ 2ኛ የክፍሉን ሰራተኞች አቅም ለመጨመር የሚያስችሉ ስልጠናዎች መስጠት ሲሆን፤ በዚህ ረገድ ሁሉንም የስራ ክፍሎች የሚያከናውናቸውን ስራዎች ሊያግዙ የሚችሉ ሰፋ ያሉ ስልጠናዎች ከመስጠት በተጨማሪ ለክፍሉ የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በተደራጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሰልጠን እንዲቻል የስልጠና ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀት፡፡ 3ኛ የውሃ ኃይል ማመንጫ፣ የፀሃ ኃይል ማመንጫና፤ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በተመለከተ የአለማቀፍ አበዳሪዎችና ማዕቀፍ(framework) ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ጥናትና ዲዛይንሰ ሰራዎችን ለማገዝ የሚያስችሉ የዲዛይንና አናላሲስ ሶፈትዌር ግዢን ማከናወን ፡፡ 4ኛ ክፍሉን በቀጣይ በዘርፉ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት ለመጨመር የሚያስቸሉ ስራዎችን በማከናወን የክፍሉን የቢዝነስ ሞዴል መቅረፅ፤ ወደ ማማከር ገበያ ለመግባት የሚያስችል የማርኬቲንግ ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀት፤ እንዲሁም የቢዝነስ ቀጣይነትና አስተማማኝነትን የሚያረጋግጥ እቅድ ማዘጋጀት መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ የአቅም ግንባታ ስራዎቹን በ14 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት የ1,518,160.00 የአሜሪካ ዶላር እና የ11,215,586.00 የኢትዮጵያ ብር የፋይናስ ወጪ በጀት ተይዞለታል፡፡ ሁሉም የሚመለከታቸው ሰራተኞች ፕሮጀክቱን በንቃት በመሳተፍ በቀጣይ ለሚጠበቅባቸው ትልቅ ኃላፊነት እራሳቸውን ከወዲሁ ማዘጋጀት እንደ ሚጠበቅባቸው ኃለፊው አስገንዝበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content

ተቋሙ የ2014 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ገመገመ ………..////……….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ ሥራ አመራር የተቋሙን የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡ ከጥቅምት 9 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በተደረገው ግምገማ የስራ ክፍሎች በሩብ ዓመቱ ያከናወኗቸውን ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከኦፕሬሽን ስራዎች አኳያ በኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች በኩል የኦፕሬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ጥገና ሥራዎች በሩብ ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም እንደነበራቸው በግምገማው ላይ ተጠቅሷል፡፡ በግንባታ ላይ የሚገኙት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ የኮይሻ፣ የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ፣ የአይሻ የንፋሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት ግንባታቸው በመከናወን ላይ ነው፡፡ ቀሪ ሥራዎችን ከተቀመጠላቸው ጊዜ አንፃር ተጣጥመው እንዲሰሩ አቅጣጫ የተሰጠባቸው ሲሆን በትራንሰሚሽን ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን ያሉ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ መርሐ ግብር መሰረት እየተከናወኑ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በፀጥታ ችግርና በኮሮና በሽታ ምክንያት ለማከናወን አለመቻሉን በወይይቱ ላይ ተነስተዋል፡፡ ሦስት ቀናትን በፈጀው የሩብ ዓመት ግምገማ ላይ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ በተሰሩ የኢነርጂ ሀብት ልማትና የመነሻ ዲዛይን ስራዎች፣ የጀነሬሽን፣ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ቦታ መረጣ፣ ቅየሳና ተያያዥ ስራ እንዲሁም በግል አልሚዎች የሚገነቡ IPP/PPP የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ስራዎችን ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከከፋይናንስ ስራዎች አኳያ የኃይል ሽያጭና ሌሎች ገቢዎችን በመሰብሰብ ገቢ የማሳደግ፣ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ወጪን የመቀነስ፣ እና ካፒታል የማሳደግ ስራዎች የተከናወኑ መሆኑንና በንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት በግምገማው ላይ ተነስተዋል፡፡ ከሰው ሃብት ስራዎች አኳያ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የስራ አፈጻጸም ምዘና ሰርዓት የሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ አግባብነት፣ የሰው ኃብት መረጃ ማሟላትና ማደራጀት፣ የአደረጃጀትና የአሰራር ስርዓት ማሻሻያዎች፣ እንዲሁም የስራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በግምገማው ማጠቃለያ እንደገለፁት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዝግጅት ጊዜ ቢሆንም የተመዘገበው አፈፃፀም ተቋማዊ ዕቅዱን ለማስፈፀም በሚያስችል መስመር ላይ እየሄድን እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ተቋሞ ዘመናዊ አሰራርን ለመተግበር ያስችል ዘንድ የኮርፖሬት ሰርቪስ አስተሳሰብ ከማምጣት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን እና ሥራን በERP /SAP/ ሲስተም ለመስራት እየተደረገ ያለውን ጥረትም የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው በሩብ ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ሥራዎች ትኩረት ተሰጥባቸው በሁለተኛ ሩብ ዓመት ውስጥ ተካተው መከናወን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡ ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ የሲሚንቶ እና ብረታ ብረት ግብዓት አቅርቦት አለመሟላት፣ የፀጥታ ችግር መኖር፣ በፕሮጀክት የግንባታ ስራዎች ላይ እንደችግር የተነሱ ጉዳዮች ሲሆኑ በቀጣይ የታዩ ጉድለቶችን በማረም ሥራን የተሳለጠ ለማድረግ የስራ ተነሳሽነት መፍጠር እንደሚገባ ገልፀው አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ መድረኮችን በመፍጠር መስራት እንደሚገባ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content

photo content

photo content

ጣቢያው አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ እየሠጠ ነው -------//------- ከአዲስ አበባ በ319 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ክልል በሀላባ ከተማ የሚገኘው የሀላባ ባለ 230/132/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ ኃይል እየሠጠ ይገኛል፡፡ የጣቢያው ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ገበየሁ እንደገለፁት በ1982 ዓ.ም. ከሶዶ1 በ132 ኪ.ቮ. መስመር ኃይል በመቀበል ለሀላባ እና ለአካባቢው በ15 ኪ.ቮ. ኃይል በመስጠት በይፋ ሥራ የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ይሁንና በ2007 ዓ.ም. ማከፋፈያ ጣቢያው በተደረገለት የአቅም ማሣደግ ሥራ ኃይል የመቀበል አቅሙን ወደ 230 ኪ.ቮ ለማድረስ መቻሉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከአቅም ማሳደግ ሥራው በኋላ ማከፋፈያ ጣቢያው ሁለት ባለ 132 ኪ ቮ. እና አራት ባለ 15 ኪ.ቮ መስመሮች እንዲኖረው መደረጉን አንስተዋል፡፡በዚህም ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረለት ተናግረዋል፡፡ ከሆሳዕና በ230 ኪ ቮ. እና ከወላይታ ሶዶ በ132 ኪ.ቮ መስመር የሚቀበለውን ኃይል ባሉት አራት ባለ 15 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች ሀላበ ከተማ እና ዱራሜ ወረዳ ጨምሮ በአካበቢው ለሚገኙ አካባቢዎች እና በ132 ኪ ቮ. ለሻሸመኔ ማከፈፈያ ጣቢያ ኃይል እየሰጠ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content

photo content

photo content

በጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ዩኒት ሶስትን በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ….//…. በጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙ አራት ዩኒቶች መካከል ዪኒት ሶስትን በ15 ቀናት ውስጥ በሙሉ አቅም ኃይል እንዲያመነጭ ለማስቻል የጥገና ሥራ እያከናወኑ መሆኑን የጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተስፋ ተናግረዋል፡፡አጠቃላይ የጥገና ሥራውም 95 በመቶ ደርሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጠባብ ጫፍ (Nozzle) እና የውሃ መቆጣጠሪያ (Control valve) ገጠማ ሥራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራና የፍተሻ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ እንደ አቶ አሸናፊ ገለፃ ለዩኒት 3 የተደረገለት የጥገና አገልግሎት ሲያመነጭ ከነበረው 25 ሜጋ ዋት ወደ 105 ሜጋ ዋት ከፍ እንዲል ያስችለዋል፡፡ የጥገና ሥራው በራስ ኃይል መከናወኑ የተቋሙ ሠራተኞች የጥገና ክህሎት አቅም እያደገ መምጣቱን ያሳያል ያሉት ኃላፊው የጀርመኑ ቮይት ኩባንያ ለባለሙያዎች በኦንላይን ሥልጠና በመስጠት ማገዙን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ የጥገና ሥራ ላይ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙም አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለዪነት 3 የሚያገለግል የቀለበት ብረት ሥራ በራስ አቅም የተሰራ ሲሆን ይህም ወጪ ሊደረግ የነበረን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ማዳን ተችሏል፡፡ ከሶስት ወራት በፊት ዩኒት አንድን በመጠገን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉንም ነው አቶ አሸናፊ ያስታወቁት፡፡ አጠቃላይ የጣቢያውን ሥርዓት ለማዘመን ከጀርመኑ ቮይት ኩባንያ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውንና ይህም የጣቢያውን ሙሉ አቅም ለመጠቀም ይረዳል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የአየር ማስተንፈሻ አካል፤ ትራንስፎርመር፣ አሸንዳ እና የማቀዝቀዣ ስርዓት ባለፉት ሶስት ወራት ጥገና ተከናውኖላቸዋል፡፡ ጣቢያው ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ብሔር ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ክልል፣በየም ልዩ ወረዳ ይገኛል፡፡ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም Facebook (https://www.facebook.com/Ethioelectric) Log in or sign up to view See posts, photos and more on Facebook.

photo content
+3

EEP Communication - Статистика и аналитика Telegram-канала @eepcommuication