ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 567 подписчиков, занимая 8 356 место в категории Технологии и приложения и 2 162 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 567 подписчиков.

Согласно последним данным от 24 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 24, а за последние 24 часа — 19, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.91%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 15.83% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 035 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 465 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 8.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 25 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 567
Подписчики
+1924 часа
+197 дней
+2430 день
Архив постов
photo content
+9

የፈተና የውጤት ማስታወቂያ ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሹፌር-3ኛ ጂ1 የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎ
+1
የፈተና የውጤት ማስታወቂያ ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሹፌር-3ኛ ጂ1 የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል ከተ.ቁ 1 እስከ 6 ያላችሁ በመንገድ ትራንስፖርት ህግና ደንብ በሚፈቅደው አግባብ መሰረት በተሰጠው የተግባር ፈተና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በዋናው መ/ቤት ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው የሰራተኛ ምደባ ቢሮ የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምድ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

ባለፉት ሦስት ወራት ተቋሙ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አግኝቷል ........///....... የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ያቀረቡት በተቋሙ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ትንተና መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ልደት ዘሪሁን እንደገለፁት ለመደበኛና ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ 110 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል። ባለፉት ሦስት ወራት ተቋሙ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለውጭ ሀገር እና ለዳታ ማይኒንግ ከቀረበ ኃይል 59 ነጥብ 42 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ነው የጠቀሱት። እንደ ወ/ሮ ልደት ገለፃ የተለያዩ ንብረቶችን በማስወገድና ተቋሙ የማይጠቀሞባቸውን ቤቶች በማከራየት በሩብ ዓመቱ ከ33 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል። በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከኃይል ሽያጭ ያገኘው ገቢ ከዕቅዱ አንፃር የ13 በመቶ ብልጫ እንዳለው የጠቀሱት ወ/ሮ ልደት የተመዘገበው የኃይል ሽያጭ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ36 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ነው የገለፁት። በበጀት ዓመቱ ከ7 ሺህ 200 ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያላቸው የአምስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል። ተቋሙ በሩብ ዓመቱ 6 ሺህ 501 ጊጋ ዋት ሰዓት በማመንጨት ከዕቅዱ 17 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ ያለው ኃይል ማምረቱን አመልክተዋል። ከሰው ኃይል አቅም ግንባታ አንፃር ከ2 ሺህ ለሚልቁ የተቋሙ ሠራተኞች ሙያዊ እና የአመራር ክህሎት ስልጠና መሰጠቱንም ነው ያስታወቁት። በሩብ ዓመቱ የለገጣፎ- ኮምቦልቻ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ሁለተኛ የመስመር ዝርጋታን በተቋሙ የራስ ኃይል የግንባታ መምሪያ እንዲከናወን በመደረጉ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ በ15፣ 33፣ 45 እና 66 ኪሎ ቮልት መስመሮች ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር  ከ12 ሺህ 500 ጊዜያት በላይ የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ነው ወ/ሮ ልደት የተናገሩት። በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ለተቋሙ የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር የሰራተኞች ክበብ የሚውል 258 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን ጠቁመዋል። በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀገሬ ውሒብ እንደገለፁት  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለ ተቋም ነው። በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማደጉን፣ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን እና የኃይል ሽያጭ ዕድገት ማሳየቱን እንዲሁም የተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት ሒሳብ ተዘግቶ ለኦዲት መሰጠቱን በጥንካሬ አንስተዋል። የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከጊዜና ከበጀት አንፃር ትኩረት እንዲደረግበት፣ የውጭ ሀገር ብድር ክፍያ እና የውጭ ሀገር የኃይል ሽያጭ የገቢ አሰባሰብ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ወ/ሮ ሀገሬ አሳስበዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአድሚንስትሬሽን ኦፊሰር 1ኛ እና በፋይናንስ አድሚንስትሬሽን ኦፊሰር 1ኛ የስራ መደቦች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ሰራ
+2
የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአድሚንስትሬሽን ኦፊሰር 1ኛ እና በፋይናንስ አድሚንስትሬሽን ኦፊሰር 1ኛ የስራ መደቦች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች መካከል በአድሚንስትሬሸን ኦፊሰር 1ኛ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 እና በፋይናንስ አድሚንስትሬሽን ኦፊሰር 1ኛ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 ስማችሁ የተገለጸው ከህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የሰው ኃይል ምደባ ቢሮ በመገኘት የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ሂደት እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በቃሊቲ 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ፤ በቡታጅራ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና በገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመሮች ላይ የጥገና ሥራ ይከናወናል፡፡ በተጨማሪም የለገጣፎ -ኮምቦልቻ 2ኛ መስመርን ኢነርጃይዝ የማድረግ ሥራ ይሠራል፡፡ ስለሆነም በተጠቀሰው ዕለት በቃሊቲ 2 የማከፋፈያ ጣቢያ በሚከናወነው የጥገና ሥራ በሃና ማርያም፣ በብሔረ ፅጌ፣ በአዲስ ጎማ ፋብሪካ፣ በሳሪስ፣ በቦሌ ቡልቡላ፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ፣ በአዲስ ሰፈር፣ በኦሳካ ብረታብረት ፋብሪካ አካባቢ ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ድረስ፤ እንዲሁም በቡታጅራ የማከፋፈያ ጣቢያ በሚከናወነው ጥገና በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በቡኢ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ኃይል ተቋርጦ ይቆያል፡፡ በገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሚከናወነው የጥገና ሥራ ደግሞ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በፊቼ ከተማና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ዕለት እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም የለገጣፎ -ኮምቦልቻ 2ኛ መስመርን ኢነርጃይዝ የማድረግ ሥራ ስለሚከናወን ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ጠዋት 1፡00 ሰዓት ድረስ በደብረብርሃን ከተማ፣ በሲኖ ብረታ ብረት ፋብሪካ እና በለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ኤሌክትሪክ ተቋርጦ የሚቆይ በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ጣቢያዎቹ ከ72 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል አምርተዋል ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ ሁለትና ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ72 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማምረታቸውን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌታቸው አበበ እንደተናገሩት በሩብ ዓመቱ በአዋሽ ሁለት 24 ነጥብ 6 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ታቅዶ 17 ነጥብ 65 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማምረት የዕቅዱን 71 ነጥብ 73 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ በአዋሽ ሦስት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ደግሞ 56 ነጥብ 32 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ታቅዶ 55 ነጥብ 25 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማምረት የ98 ነጥብ 11 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ የአዋሽ ሁለት አፈጻጸሙ ዝቅ ሊል የቻለው ዓመታዊ ጥገና በሚከናወንበት ጊዜ በተርባይን ቤሪንግ ቫይብሬሽን ላይ የተከናወነው ጥገና ከታቀደው በላይ ጊዜ በመውሰዱ እና የክረምቱ የውሃ መጠን በማነሱ እንደሆነ ጠቁመዋል። የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸም ከዕቅዱ ዝቅ ያለ ቢሆንም በአዋሽ ሦስት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተመረተው ኃይል ግን ካለፈው ሁለት በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው የኃይል ምርት የ 6 በመቶ ብልጫ ያለው ነው ብለዋል። ጣቢያዎቹ ከዕድሚያቸው አኳያ የመልሶ ግንባታ ሥራ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው የታቀደውን ኃይል ለማማረት የሚያስችሉ የጥገና ሥራዎችን በማከናወን ውጤታማ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። የአዋሽ ሁለት እና ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እያንዳንዳቸው 32 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ችግሮችን በምክክር በመፍታት ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል .........///......... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሥራ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ። ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች የተሰጠውን ሥልጠና በንግግር የከፈቱት በተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ ጌታቸው እንደገለፁት ለሚፈጠሩ ችግሮች ወቅታዊ መፍትሔ ለመስጠት ምክክር የማይተካ ሚና ይኖረዋል። የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው ጤናማ የሆነ ምክክር በማድረግ ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር እንደሚያስችልም ጠቁመዋል። "የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር ለምርታማነት" በሚል ርዕስ ሥልጠናውን የሠጡት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማህበራዊ ምክክር ባለሙያ አቶ ጌታቸው ታምሩ እንደተናገሩት  ሥልጠናው በቀጣይ በተቋሙ የሚካሄዱ ምክክሮች ውጤታማ እንዲሆኑ በግብዓትነት ያግዛል። ምክክሩ አሰሪውና ሠራተኛው በተቋሙ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ምርታማነትን ማዕከል ያደረገ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲፈጠር ያስችላል ብለዋል። እንደ ባለሙያው ገለፃ በምክክር ሂደቱ ላይ አሰሪ፣ ሠራተኛ እና መንግስት የሁለትዮሽና የሦሰትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰዋል። የምክክር ሂደቱ "ከክርክር ወደ ምክክር፣ ከምክክር ደግሞ ወደ ምርታማነት" ለመሸጋገር ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ምክክሩ የተቋም ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን  ለማሳደግ፣ ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ፣ የሥራ ባህል ለውጥ ለማምጣት፣ የአሰሪና ሠራተኛን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር እንዲሁም የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመለየትና መፍትሔዎቻቸውን ለማመላከት እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመረጃና ዕውቀት አስተዳደር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ከበደ እና የተቋሙ መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ፀሐፊ አቶ ኃይሉ ወልዴ በበኩላቸው ምክክሩ ሠራተኛው ለተቋሙ ምርታማነት ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በውይይት በመለየት ለችግሮቹ የመፍትሔ አማራጮቹን ለማስቀመጥ ይረዳል ብለዋል። በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ ሠራተኞቸ እና የሥራ መሪዎች በየሥራ ክፍላቸው የሚካሄዱ ምክክሮችን በበላይነት እንደሚመሩ አስታውቀው ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆንም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። በዕለቱ በምክክር ሂደቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። የተቋማትን ምርታማነት ለማሳደግ "የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር ለምርታማነት" የሚል ስትራቴጅ ተቀርጾ እየተሰራ ሲሆን ምክክሩም ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ. ም እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ➡️ Link 1 ➡️ Link 2 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌ
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ➡️ Link 1 ➡️ Link 2 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የማመንጫ ጣቢያውን ደህንነት ለመጠበቅ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ደህንነት ለመጠበቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ጥሪ አቀረቡ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ በቀለ እንደገለጹት ከወሰን አለመከበር እና ከስርቆት ጋር ተያይዞ የማመንጫ ጣቢያው ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል። የጣቢያው ውሃው የሚተኛበት ቦታ ወይም ከሰዎች እና እንስሳት ንክኪ ነጻ እንዲሆን የተከለለውን አካባቢ በማለፍ የግድቡ ውሃ በሚቀንስበት በበጋ ወራት የእርሻ ሥራ መበራከቱ የግድቡን ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም ጣቢያው በደለል እንዲሞላ ከማድረጉም በላይ የግብርና ተረፈ ምረቱ ወደ ጣቢያው እየገባ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቴዎድሮስ እንቅስቃሴው ውሃ ወደ ጣቢያው እንዳያልፍ እያደረገ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ቴዎድሮስ ገለፃ የግብርና ተረፈ ምርቱና ገለባው ወደ ጣቢያው የማቀዝቀዣ ማሽኖች በመግባት እንዳይሰሩ ከማድረግ ባለፈ የሚፈጠረው ሙቀት ዕቃዎቹን እስከ ማቅለጥ መድረሱን ተናግረዋል። በዚህ የተነሳ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ ከሦስት ቀን በላይ እንዲቆም ማድረጉን እና የኦፕሬሽን ሥራ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ገልጸዋል። ከዚህም ሌላ ከኃይል ማመንጫ ቤቱ እስከ ውሃ መቀበያው ወይም ኢንቴክ ያለው የመሬት ውስጥ መስመር እና ስዊች ያርዱንና ማመንጫ ቤቱን የሚያገናኙ መስመሮች ላይ የሚፈጸመው ስርቆትም ለጣቢያው ፈተና መሆናቸውን ተናግረዋል። የአካባቢው አባገዳ የሆኑት ሐጂ እንድሪስ ሐጂ ጉራሪ በበኩላቸው ማመንጫ ጣቢያው ለአካባቢው ማህበረሰብ የልማት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል። የማመንጫ ጣቢያው መኖር ከተሞች እንዲስፋፉ፣ የመብራትና ውሃ አቅርቦት እንዲኖር፣ በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት እንዲከፈት በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አንስተዋል። በመሆኑም የማመንጫ ጣቢያውን ወሰን አልፎ ከማረስ እና ከስርቆት ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን አባ ገዳ ሐጂ እንድሪስ ገልጸዋል። ከሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን የማመንጫ ጣቢያው ደህንነት ላይ ስጋት የደቀኑ ችግሮችን ለመፍታት መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ሁለተኛው ምዕራፍ የሳፕ ቴክኖሎጂ በይፋ መተግበር ጀመረ ………///……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የተቋም ሀብት ዕቅድ ሥርዓት - ERP የሚያዘምነው የሳፕ ቴክኖጂ ሁለተኛ ምዕራፍ በተጠናቀቁ አስራ አንድ ሞጁሎች ዛሬ በይፋ መተግበር ጀምሯል፡፡ የተጠናቀቁን የአሰራር ሞጁሎች በይፋ ሥራ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ ተቋሙን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ወደተሻለ ዲጂታል አሰራር ለማሸጋገር እተሰራ ነው፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሳፕ ትግበራ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን መሙላት እና ለአሰራር ምቹ ያልሆኑትን ማስተካከል በቀጣም በትኩረት እርምት መውሰድ እንደሚገባ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሳስበዋል፡፡ የተቋሙ የሞደርናዜሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ገነቱ ደሳለኝ እንደተናገሩት ሁለተኛው ምዕራፍ ከፋይናንስ፣ ከንብረት አስተዳደር፣ ከቅጥርና ሰው ሀብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ከሚኖሩት 22 ሞጁሎች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ወደ ተግባር የሚገቡት 11 ሞጆሎች ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 11 ሞጁሎች ጥቃቅን ማስተካከያ ተደርጎላቸው በቅርቡ ወደ ትግበራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ ገነቱ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቺፍ ኦፊሰር አቶ ጌትነት ታደሰን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ኃፊዎች ስለ ሞጁሎች ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ ኃለፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ ሞጁሎቹ ሙሉ በሙሉ ሲተገበሩ ጠንካራ የሀብት ቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት፣ የተቋሙን ወጭ ለመቀነስና ሥራን ለማቀላጠፍ እና መረጃዎችን ለማጥራት እንዲሁም በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችንና አሰራሮችን ለማዘመን ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የሚከናወኑት የአካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቶች የፕሮጀክቶችን ተቀባይነት ከፍ ያደርጋል ……….///………… የኃይል መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከመተግበራቸው በፊት የሚከናወኑ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቶች በፕሮጀክቶች ትግበራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ እያገዘ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋቀሳ ተሰማ እንደገለጹት ፕሮጀክቶች የሚገኙበትን አካባቢና የአካባቢውን የማህበረሰብ ደህንነት ለመጠበቅና ከለላ ለመስጠት ፕሮጀክቶች ከመተግበራቸው በፊት የአካባቢና ማህበረሰባዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቶች ይከናወናሉ፡፡ ጥናቶቹ በሀገሪቱ ያሉ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎችን እንዲሁም የአበዳሪ ተቋማትን ፖሊሲና አሰራር መሰረት በማድረግ እንደሚከናወኑም ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ዋቀሳ ገለፃ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናቶች ከፕሮጀክት ትግበራ ጋር ተያይዞ በአካባቢውና በማህብረሰቡ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ ጥናቶቹ በፕሮጀክት ትግበራ ጊዜ ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮቹ እንደ ጉዳት ዓይነት እና መጠን በዕቅድ ላይ የተመሰረተ የመፍትሔ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያግዛል ብለዋል። እየተከናወኑ ያሉ ጥናቶች ማህበረሰቡ በፕሮጀክቶች ዕቅድና አተገባበር ላይ እምነት እንዲኖረው በማድረግ የፕሮጀክቶችን ተቀባይነት እና አፈፃፀምን ከማሳደጉም ባለፈ በቀጣይ ለሚታቀዱ ሥራዎች በግብዓትነት እያገዘ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የጥናት ሥራው ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላትን እና ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በቅንጅት እንደሚከናወን ተወካዩ አመልክተዋል፡፡ በጥናቱ የተገኙ ውጤቶች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲደረጉ ፕሮጀክቱን ለሚተገብረው ቢሮ ሰነዱ እንደሚሰጥና ቢሯቸውም በአፈጻጸሙ ላይ ክትትል እንደሚያደረግ አስታውቀዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት የ19 የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና 11 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ጥናት ለማከናወን መታቀዱን አቶ ዋቀሳ ጠቁመዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ቡድኑ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል ..........///........ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሀምበርቾ አቻውን አንድ ለባዶ አሸንፏል። ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማህሌት ምትኩ በ30ኛው ደቂቃ የኢትዮ-ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል አስቆጥራለች። ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፍፁም የጨዋታ የበላይነት ባሳየበት በዚህ ጨዋታ የአማካኝ ቦታ ተጫዋችዋ ዙፋን ደፈርሻ የጨዋታው ኮከብ በመሆን ሽልማት ተበርክቶላታል። ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ5ኛ ሳምንት መርሃግብር ከባህርዳር ከነማ ጋር በመጪው ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም  ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም