ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
613
Подписчики
+124 часа
-17 дней
-1030 дней
Архив постов
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ሰኔ ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታችን_ለቅድስት #ድንግል_ማርያም_በኬልቄዶን_አውራጃ_በቂሣርያ አገር ያለ ዕንጨት ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች #የመጀመሪዋ_ቤተ_ክርስቲያኗ በተወደደ ልጅዋ እጅ #ለታነፀችበት_ለሕንጸተ ቤተ ክርስትያን_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረን።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_እግ_ነግ_ዜማ፦ "አመ የሐንፃ #እግዚአብሔር_ለጽዮን ወይኄድሳ ለኢየሩሳሌም #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምስለ #መላእክቲ_ ዖዳ በደሙ ቀደሳ በዕፀ መስቀሉ ዐተባ"። ትርጉም፦ #እግዚአብሔር_ጽዮን ባነጻት (በሰራት)ና #ኢየሩሳሌምንም በሚያድሳት ጊዜ #ኢየሱስ_ክርስቶስ #ከመላእክቱ_ጋር_ዞራት በደሙም ቀደሳት (አመሰገናት) በዕፀ (በዕንጨት) መስቀሉም ባረካት። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ በዚች ቀን #በኬልቄዶን_አውራጃ_በቂሣርያ አገር #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን_ያለ_ዕንጨት_ያለ_ጭቃና_ውኃ_በሦስት_ደንጊያዎች_በተወደደ_ልጅዋ_እጅ_የታነፀችበት_ነው። ልመናዋ በረከቷም ወንዶችና ሴቶች ባሮቿ ከሆነ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                  ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እማዕምቅ ጸዋዕኩከ እግዚኦ። እግዚኦ ስምዐኒ ቃልየ። ወይኩን ዕዝንከ ዘያፀምዕ ቃለ ስእለትየ"። መዝ 129፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ወይም ማቴ 13፥44-ፍ.ም።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ግሩም ምክሩ እምዕጓለ እመሕያው። ዘይሬስያ ለባሕር የብሰ። ወበተከዚ የኃልፋ በእግር"። መዝ 65፥5-6 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ4፥24-38። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 14፥29-34፣ 2ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 13፥38-44። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን በዓል፣ ነቢዩ ኤልያስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ ከዚህ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሌሊት በሥጋው ላይ እሳትን አነደዱ እሳቱም በላዩ እየነደደ ምንም ምን አልነካውም ወስደውም በገበያ ውስጥ ጣሉት ከዚያም አንሥተው በባሕር ውስጥ ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ ደሴቱ ወደብ ዳር ደረሰ እናቱም ጠብቃው ነበርና ወስዳ ገነዘችው ለጥቂት ወራትም በቤቷ ውስጥ ሸሸገችው። ❤ ከዚህም በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅና ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በሐዲስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ብሶይ_አኖብ፦ የስሙ ትርጓሜውም የጠራ ወርቅ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ ከድምያጥ አውራጃ ስሟ ባኖስ ከሚባል አገር ከአቅራብ መኰንን ከቆጵርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ ከከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ልጆች ወገን ነበር በዚህም ቅዱስ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። ቅዱሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊቱ ታመነ። ❤ ወደ እንዴናውም ወሰዱት በመኰንኑ አርያኖስ ፊት ቁሞ በጌታችን ታመነ አርያኖስም በእርሱ ላይ ተቆጣ "ለአማልክትም ሠዋ" አለው። አልታዘዘለትም ሥቃዩንም አልፈራም መኰንኑም ወስዶ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ ወደሚገድሉበት ቦታም ሊወስዱት አወጡት ብዙ ሕዝብም ይከተሉት ነበር እነሆ ከዚያም የአርያኖስ መኰንን አንበሶች ነበሩ። የሚጠብቃቸውም ሰው ነበር እነርሱም በብረት ሰንሰለት ታሥረው ነበር ከእነርሱም አንዱ አንበሳ የብረት ሰንሰለቱን በጥሶ ሩጦ ወደ ቅዱስ ደረሰ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱሱን በአንበሳው ጀርባ ላይ አወጣውና ዐይነ ፀሐይ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሰው በረረበት ቅዱሱ ግን ዐይኑን ሸፍኖ ስለ ነበር ውዴት እንዳለ አላወቀም በዚያም ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ብሶይ አኖብ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 19 ስንክሳር።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለጻድቃን_እለ_በቋዓት"። ትርጉም፦ በቋዓት ያሉ ለኾኑ #ጻድቃን_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን ላይ።                                                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 1፥1-8፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20 እና የሐዋ ሥራ 19፥11-18። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥8-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ወይም የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ሰኔ ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን #ለሰማዕቱ_ሐዲስ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፣ #ለአባ_ብሶይ_አኖብ ሰማዕትነት ለተቀበሉት #ለዕረፍታቸው_በዓልና_ለአምስት_ጭፍሮች እሊህም #ለአርሶፎኒስ_ለጴጥሮስ_ለአስኪርዮን #ለአርጌንዮስ_ለቢልፍዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከደብረ_ቋዓት ቅዱሳን አባቶቻችን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አምስቱ_ጭፍሮች፦ እሊህም ስማቸው አርሶፎኒስ፣ ጴጥሮስ፣ አስኪርዮስ፣ አርጌንዮስና ቢልፍዮስ ነው። በዲዮስጲልዮስ ቅጽር ውስጥ ይኖሩ ነበር። መኰንኑም ለጣዖታት እንዲሠው በአስገደዳቸው ጊዜ "እኛስ የንጉሣችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ እንፈጽማለን ለእርሱም እንሰዋለን" አሉት መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ በአንድ ቤት ውስጥም እንዲዘጉባቸውና እስከ ሁለት ቀን ያህል ውኃ እንዳይሰጧቸው አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ እንዲያመጧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ "ለአማልክት ሠዉ" አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል "እኛስ ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ እንሠዋለን ለረከሱ አጋንንትን ግን አንሠዋም" አሉት። አንገታቸውንም አሥረው ወደ ሌላ አገር ይወስዱአቸው ዘንድ አዘዘ። አርጌንዮስም ወንድሞቹን "እኔ እውነትን እነግራችኋለሁ የእግዚአብሔር መልአክ አምስታችንንም በስማችን ሲጠራን ሸምቼዋለሁና" አላቸው። ❤ ዳክስ ወደሚባል መኰንንም በአደረሷቸው ጊዜ መኰንኑ አስቀድሞ አርሶፎኒስን ወስዶ "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ በአለውም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው በከተማ ውስጥ እንዲጎትቱትና እንዲአዞሩት አዘዘ። በመለሱትም ጊዜ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ፊቱን እንዲአጠወልጉት አዘዘ ሁለተኛም እስከ ሚጨነቅ ድረስ በሠረገላ ውስጥ አሥረው ቊልቊል ሰቀሉት ሃይማኖቱንም ጠብቆ ክብር ይግባውና ለጌታችን ነፍሱ ሰጠ። ❤ ሁለተኛም ጴጥሮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ትእዛዙንም ባልተቀበለው ጊዜ እንዲአሠቃዩትና እንጨት ተክለው ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሁለተኛም ምድሩን ቆፍረው ከትከሻው በታች ቀብረው በቅሎዎችን በላዩ እንዲነዱበት አዘዘ ይህንንም እግዚአብሔር እየረዳው ታገሠ ከጉድጓድም በአወጡት ጊዜ ከሥቃዩ ብዛት የተነሣ ሥጋው ጠወለገ መናገርም ተሣነው በግንድ ውስጥም አሥረው ጣሉት። ❤ ከዚህም በኋላ አርጌንዮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ያለ መብልና መጠጥም በተበሳ ግንድ ውስጥ አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት። ❤ ዳግመኛም አስኪርዮንን አቀረቡት ዳክስም "ለራስህ እዘን በክፉ አሟሟትም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እንዲሰነጥቁት አዘዘ ወታደሮችም ተረከቡትና በጽኑ ሥቃይ አሠቃዩት በትዕግሥቱም በአሸነፋቸው ጊዜ ለመኰንኑ ነገሩት በረኃብና በጽም ይሞት ዘንድ በግንድ ውስጥ አሥረው በባዶ ቤት እንዲዘጉበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። ❤ ደግመው ዲያቆን ቢፍዮስን አቀረቡት መኰንን ዳክስሞ "እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው ባልሰማውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ ሥጋውን ሠነጣጥቀው በከተማው አደባባይ ጎተቱት እንጨት ተክለውም ቊልቊል ሰቀሉት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ ከሃይማኖቱም ባልተናወጸ ጊዜ በረኃብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስጥ አሥረው በላዩ መዝጊያ ሠርተው ዘጉበት። በየዕለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ሆነው ይጎበኙት ነበር ጳሔን የተባለው የሰኔ ወር በባተ በሠላሳ ጴጥሮስ ነፍሱን ሰጠ። እርሱንም አውጥተው ደጁን በሌሎቹ ላይ ዘጉ። ❤ የከበረ አርጌንዮስም ከአምስት ቀን በኋላ ዐረፈ እርሱን አውጥተው በቀሩት ላይ ደጁን ዘጉ። ብፁዕ አስኪርዮንም ከዐሥራ ሁለት ቀን በኋላ ዐረፈ። እርሱንም አውጥተው በቅዱስ ቢልፍዮስ ላይ ደጃፍ ሠርተው ዘጉበት እርሱም የሚያርፍባት ቀን ስትደርስ ወንድሞቼ ታገሡኝ በዚች ሌሊት እወጣለሁና አላቸው። ከዐሥራ ዘጠኝ ቀን በኋላ በዚያች ልሊት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ገድለኞች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ሰማዕቱ_ሐዲስ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስላም ነበር ከግብጽ ደቡብ ድምራ ከሚባል አገር ክርስቲያን ሴት አግብቶ ከእርሷም ሦስት ልጆችን ወለደ ከሦስቱም አንዱ ይህ ቅዱስ ነው። ከእናቱም ጋራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔድ ነበር ቅዱስ ቁርባንንም ይቀበል ዘንድ እናቱን ለመናት እርሷም ማንም የክርስትናን ጥምቀት ሳይጠመቅና ንጹሕ ሳይሆን ቁርባን ሊቀበል አይችልም አለችው። ❤ ከዚህም በኋላም ከተረፈ መሥዋዕቱ ሰጠችው በጎረሳትም ጊዜ ጣዕሟ በአፉ ውስጥ እንደ ማር ሆነ "የዚች የቁራሿ ጣዕም በአፌ ውስጥ እንዲህ የሆነ የዋናው የቁርባኑ ኅብስት ጣዕም ምን ያህል ይሆን" ብሎ በልቡ አሰበ ከዚች ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ። ❤ በአደገም ጊዜ ክርስቲያን ሴት አገባ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ መፈለጉንም ነገራት እርሷም ወደሌላ አገር ሒዶ የክርስትናን ጥምቀት እንዲጠመቅ መከረችው እርሱም ወደ ሌላ አገር ሒዶ ተጠመቀ ስሙንም ለውጦ ጊዮርጊስ ተባለ። እስላሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ከዚያም አምልጦ ሳፍጥ ወደሚባል አገር ሸሸ በዚያም ሦስት ዓመት ኖረ። ወሬውም በተገለጠ ጊዜ ቀጡር ወደ ሚባል አገር ሒዶ የልዳዊው ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ ኖረ። ❤ ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ድምራ ተመለሰ እስላሞችም ሰሙ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት የመኰንኑም ሚስት ክርስቲያን ነበረች ለመኰንኑም "አታሠቃየው" አለችው መኰንኑም አሥሮ በወህኒ ቤት ዘጋበት። እስላሞችም ተሰብሰቡ የወህኒ ቤቱንም ደጅ ሰብረው ታላቅ ግርፋት ገረፉት አካላቱም ቈራርጠው በሕይወትና በሞት መካከል ጣሉት። ሲነጋም ክርስቲያኖች የሞተ መስሏቸዋልና ሊቀብሩት መጡ ነገር ግን በሕይወት አገኙት። ❤ ከዚህም በኋላ እስላሞች ተሰብስበው "ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኛ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተን እንገድልሃለን" አሉት የመዛሕዝም ልጅ የከበረ ጊዮርጊስም "ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም የፈለጋችሁትን አድርጉ" አላቸው። እጅግም ተቆጡ በመርከብ ምሰሶ ላይም ሰቅለው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት መኰንኑም ከስቅላት አውርደው በእሥር ቤት እንዲአሥሩት አዘዘ እንደዚሁም አደረጉ። ሚስቱም ታጽናናውና እንዲታገሥ ታደርገው ነበር ሰይጣንም እንዳያስተውና የደከመበትን ዋጋ እንዳያጣ በልቡ ወደ ክርስቶስ ያስብ ዘንድ ትመክረው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና አረጋጋው አበረታታውም ከሰማዕታትም ጋራ እንደ ተቈጠረ በማግሥቱም ራሱን በሰይፍ እንደሚቆርጡት ነገረው። በነጋም ጊዜ እስላሞች ወደ መኰንኑ ተሰብስበው ጊዮርጊስን ይሰጣቸው ዘንድ ፈለጉ መኰንኑም የወደዱትን ያደርጉበት ዘንድ እንዲሰጧቸው አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ ከእሥር ቤት አወጡት ድምራ በምትባል አገር በከበረ የመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ሰኔ 19 ቀን ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

❤ አባ ጰላሞንም እየጸለየ ቃሉ ወዳመለከተው ወደ አባ ለትጹን በዓት ደረሰ፡፡ አባ ጰላሞንም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀብሎ ሰላምታ ሰጠው፡፡ ወደ ተራራውም ወጥተው ከጸለዩ በኋላ ተቀምጡ፡፡ አባ ጰላሞንም የመረረ ልቅሶን እያለቀሰ ሰይጣን በፈተናው እንደጣለው ለአባ ለትጹን ይነግረው ጀመረ፡፡ እንዲህም አለው፡- "በአንዲት ዕለት የእጅ ሥራዬን ለመሸጥ በግብፅ ገበያ መንገድ ስጓዝ ሰይጣን መጥቶ ልቤን አዘነጋት፤ መድኃኒት የሚሆነኝን የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እጠራ ዘንድ አልተወኝም፡፡ ዳግመኛም እንደ ንጉሥ ከተማ የታነፀች ውኃዎችና ተክሎች መልካም ዛፎችም ያሏት ከተማን አሳየኝ፡፡ የእጅ ሥራዬንም ልሸጥ ሳስብ ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት ሙቶ በምታዝን ሴት አምሳል ታየኝ፡፡ "የእጅ ሥራህን እኔ እገዛሃለሁ" ብለኝ ወደ አዳራሽ አስገባችኝ፡፡ እንቅቦቹንም ከላዬ አውርዳ አኖረች፣ እግሮቼንም አጠበች፣ አሽከሮቿንም ምግብ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘቻቸው፡፡ ከእርሷ ጋርም እበላ ዘንድ ብዙ ማለደችኝ፣ በልተን ጠጥተን ሰከርን፡፡ ስንጨዋወትም አሽከሮቿ ሁሉም ወጡና ሁለታችን ብቻችንን ቀረን፡፡ ያንጊዜም ልቤ በዝሙት እሳት ተቃጠለ፡፡ እግዚአብሔርንም መላእክቶቹንም ቢሆን አላሰብኩም በእርግጥ ከእርሷ ጋር እንደሚተኛ ሆንኩ፡፡ ❤ ከዚህ በኋላ በነቃሁ ጊዜ ብመለከት ምንም ነገር አላገኘሁም፡፡ ሴትም ቤትም ማዕድም አትክልትም ቢሆን አላገኘሁም፡፡ ነገር ግን ራሴን ከተራራው በታች አገኘሁት፡፡ ምንም እንዳልበላና እንዳልጠጣም ሰው ሆንኩ፡፡ እጅግም አለቀስኩ፡፡ ሰይጣንም በሩቁ ቆሞ "መጻተኛ ጰላሞን ሆይ ወዮልህ እንደወፍ ላጠምድህ በአንተ ላይ በርትቻለሁና…" እያለ ሲዘብትብኝ አየሁት፡፡ ነገሩንም ሰምቼ በመስቀል ምልክት በላዩ አማተብኩ፣ ከእኔም ሸሸ፡፡ "አሁንም አባቴ ለትጹን ሆይ በደሌን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንልኝ በቅድስናህ ተማፅኛለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ አባ ጰላሞንም "አይዞህ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር እንደሚልህ አምናሁ" ብሎ አጽናናው፡፡ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ጸለየ፡፡ ወደ እነርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- "የታመናችሁ አገልጋዮቼ አትፍሩ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በእናንተ ላይ አይበረታታም፡፡ ጰላሞንም የሠራውን ኃጢአት በራሱ በሰይጣን ላይ አደረግሁ፣ የጰላሞንን ኃጢአት ብቻ አይደለም ነገር ግን የሚፈትናቸውን ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን በሰይጣን በራሱ ላይ እመልሳለሁ"፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አባ ጰላሞን ከአባ ለትጹን በረከትን ተቀብሎ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ በዓቱ ሄደ፡፡ ተጋድሎውንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፡- የሰኔ 17 ስንክሳር።                                              ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ኀይልየኒ ወዝክርየኒ እግዚአብሔር። ወውእቱ ኮነኒ መድኃንየ። ቃለ ትፍሥሕት ውስተ አብያቲሆሙ ለጻድቃን"። መዝ 117፥14። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 17፥5-11።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አኮ ከመዝ ኃጥአንሰ አኮ ከመዝ። ዳዕሙ ከመ መሬት ዘይግሕፎ ነፋስ እምገጸ ምድር። ወበእንተዝ ኢይትነሥኡ ረሲዓን እምደይን"። መዝ 1፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥1-10፣ ያዕ 5፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-49። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ገሪማ ከሞት የተሰወሩበት በዓል፣ ለአባ ለትጹን፣ የአባ ጰላሞን የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ አባት እናቱን በዝሙት አስረግዞ ፅንሱንም መርዝ አጠጥቶ በማኅፀኗ የገደለውን ርጉም ሰው ከዘላለማዊው ሥቃይና ኩነኔ ለታደጉት #ለአባ_ለትጹንና ፍፁም መናኒ ለሆነ ለመጻተኛ ከሰው ጋር ተነጋግሮ ለማያውቀውና በተራራ ላይ ብቻውን በገድል ተጠምዶ ሲኖር የጌታችንን መከራ እያሰበ ቀንና ሌሊት ያለቅስ ለነበረው ለባሕታዊ #አባ_ጰላሞን ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕታት #ከነአኮራን፣ #ከበርተሎሜዎስ፣ #ከእለስክንድርያ፣ #ከእለስክንድሮስ፣ #ከዮሴፍና_ከጻድቂቱ_አርሴማ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤#አባ_ለትጹን፦ ይህም አባት ከብህንሳ አገር ነበር ጎልማሳ በነበረ ጊዜም "ነፍሱን ስለ እኔ የጣላትም ያገኛታል ለዘላለም ሕይወትንም ይጠብቃታል" የሚለውን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የሕያው ንጉሥን ቃል ሰማ ወዲያውኑ ልቡ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ዘላለማዊ ተድላ እንደ እሳት ነደደ። ቅዱስ ቁርባንንም ተቀብሎ እስዋሕት ወደ ሚባል ገዳም ሔደ በጾም በጸሎትና በስግደት ታላቅ ተጋድሎን ያለ ማቋረጥ ይጋደል ጀመር ሰባት ሰባት ቀንም ይጾም ነበር። ❤ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና የምንኲስና ልብስን ዘንድ ወደ አባ ኤስድሮስ እንዲሔድ አዘዘው እርሱም መልአኩ እንዳዘዘው ሔደ አባ ኤስድሮስም በልብሱና በአስኬማው ላይ አርባ ቀኖች ጸለየ ከዚያም በኋላ ልብሱንና አስኬማውን አለበሰው በገድል መጠመድን ጨመረ። ❤ ከዚያም መምህሩንም አስፈቅዶ ወጥቶ ብቻውን መጋደል ጀመረ፡፡ በአቅራቢያውም አንድ ገዳም ነበረና አንድ ቀን አበ ምኔቱ ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው፡፡ መነኰሳትም ዙሪያውን ከበውት ሲያለቅሱት አገኛቸው፡፡ እንዲሁም የሰይጣን ሠራዊትም አበ ምኔቱን ከበውት ደስ ሲሰኙ አያቸውና ደንግጦ "አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድነው?" ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው፡፡ እርሱም መነኰሳቱን ከእርሱ እንዲርቁ ካደረገ በኋላ የሠራውን በደሉን እንዲህ ብሎ ነገረው "እኔ ካሁን በፊት ማንም ያልሠራውን ኃጢአት ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ፡፡ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር ሄድኩ፡፡ "ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል" ብዬ በድፍረት በቁርባን ላይ የምቀድስ ሆንኩ፡፡ ለጠላሁትም በቁርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ እሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል፡፡ ከእናቴም ጋራ ዓሥር ጊዜ ተኝቻለሁ፣ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆዷ ውስጥ ገደልኩት፡፡ ኃጢአቴ ብዙ ነውና ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፡፡ ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና" ብሎ ለአባ ለትጹን ነገረው፡፡ ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ፤ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲያሠቃዩዋት አባ ለትጹን ተመለከታት፡፡ ❤ በዚህም አባ ለትጹን የመረረ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ለትጹን "ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" የሚለውን የቅዱስ ወንጌልን ቃል አስቦ ስለዚያ ኃጥእ ሰው ነፍስ ወደ ጌታችን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊያሠቃያት ጀመረ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መትቶ አስነሣውና እንዲህ አለው "ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ነፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና፡፡ እግዚአብሔር እውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም"፡፡ ❤ አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደሆነ እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም፡፡ ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን መጥቶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠና ከባሕሩ ውስጥ አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ ሚካኤልን አዘዘው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም አባ ለትጹንን ከባሕሩ አውጥቶ ከሞት አድኖ ቤታችን ፊት አቆመው፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንም "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለሆነ በደሉም ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ሰው ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ?" አለው፡፡ አባ ለትጹንም "መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ግን የእኔንም ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት" ብሎ ጌታችንን ለመነው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት፡፡ ጌታችንም በከበሩ እጆቹ ዳሰሳትና እንዳልተፈጠረች አደረጋት፡፡ ወዲያውም "ይህቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን" አለ፡፡ አባ ለትጹንም ስለይቅርታውና ስለቸርነቱ ገናናነት መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን አባ ለትጹንን "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ በእውነት እነግርሃለሁ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ በስምህ መባ ለሚያስገባ ወይም የተራበ ለሚያበላ የተጠማ ለሚያጠጣ የተራቆተ ለሚያለብስ ገድልህን ለሚጽፍ እኔ የሁሉንም ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፣ ስማቸውንም በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ፣ በጎ ዋጋቸውንም እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልኪዳን ሰጥቶት ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ አባ ለትጹንም እጅግ ደስ ብሎት ወደ በዓቱ በመመለስ ብዙ ከተጋደለ በኋላ ገድሉን ፈጽሞ ሰኔ 17 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ለትጹን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትጉር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ባሕታዊ_አባ_ጰላሞን፦ ከተጋድሎው የተነሣ ሰይጣን እስከ ደከመ ድረስ በተራራ ላይ እግዚአብሔርን እያገለገለ በገድል ተጠምዶ ሲኖር ቀንና ሌሊት ያለቅስ ነበር፡፡ ከሰው ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ ሰይጣን የሚያስቅ ነገርንና ጨዋታን እያመጣበት ይፈትነው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጰላሞን የጌታችንን መከራ እያሰበ ይተክዝ ያለቅስ ነበር፡፡ ሰይጣንም በዚህ ተቆጥቶ አንበሳ ሚዳቋን እንደሚያድን አባ ጰላሞንን ያድነው ነበር፡፡ በአንዲት ቀንም አባ ጰላሞን የእጅ ሥራውን ሊሸጥ ተነሠቶ ወደ ገበያ ሲጓዝ ሰይጣን ጎዳናውን አሳተው፣ ልቡንም መሰጠው እንጂ የሚያደርገውን ያውቅ ዘንድ አልተወውም፡፡ ❤ ከሰባት ቀኖች በኋላ አባ ጰላሞን ከረኀብና ከውኃ ጥም የተነሣ ከመሬት ላይ ወደቀ፤ ለሞትም የደረሰ ሆነ፡፡ ሰውን ወዳድ የሆነ ጌታችንም እንዲጠፋ አልተወውምና ሰይጣንን ከእርሱ አርቆ አሳደደው፡፡ አባ ጰላሞን በእርሱ ላይ የሆነውን ባወቀ ጊዜ ወደ ጌታን ጮኸ፡፡ ወዲያውም "ጰላሞን ሆይ አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በአንተ ላይ ክፉ ሊሠራ አይልችም፡፡ ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ደቡብ ጥቂት ተጓዝ በዚያም በተራራው አጠገብ የሚኖር ስሙ ለትጹን የሚባል ሽማግሌ ጻድቅ ሰው ታገኛለህ፣ እርሱ ስለ ስሜ ብዙ መከራ የተቀበለ ነው፡፡ ያደረከውንም ሁሉ ሰይጣንም እንዴት እንዳሳተህ ንገረው፣ እርሱ ኃጢአትህ እስኪሠረይ ስለ አንተ ይጸልያልና" የሚል ቃልን ሰማ፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ_ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ይስሐቅ ባደረጉት ተአምር ስማቸው #አባ_ገሪማ_ለተባሉት ከዚህ ዓለም #ከሞት_ለተሰወሩበት_ዓመታዊ_መታሰቢያ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ይስሐቅ_አባ_ገሪማ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ የሮም ንጉሥ ነበር ስሙም መስፍንያኖስ ይባላል። የንግሥት እናቱ ስምም ሰፍንግያ ነው እርሷም መካን ስለሆነች በእናቱ በቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ከማላጅነት በመማፀን ወደ እግዚአብሔር እየለመነች ኖረች። ከዚህ በኋላ ይህን የተባረከ ልጅ ተቀበለች ስሙንም ይስሐቅ ብላ ጠራችው። ጥቂት በከደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት አስተምረው ዲቁና አሾሙት። ❤ አባቱ በሞተ ጊዜ የሮም ሰዎች በአባቱ ዙፋን ላይ አነገሡት እየፈረደና በቅን እየገዛ ሰባት ዓመት ኖረ። በዋሻ የሚኖረው አባ ጰንጠሌዎንም በሰማ ጊዜ እንዲህ ብሎ ወደርሱ ላከ "ልጄ ይስሐቅ ሆይ ሙታኖቻቸውን ይቀብሩ ዘንድ ሙታኖችን ተዋቸው አንተ ግን ክብር ይግባውና የክርስቶስን የማያልፍ መንግሥት ትሻ ዘንድ ወደ እኔ ና" አባ ገሪማም መልእክቱ ደርሶት በሰማ ጊዜ መንግሥቱን ትቶ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ያንጊዜም ጌታ የላከው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጠለት ብርሃናውያን በሆኑ ክንፎቹም ተሸክሞ የዐሥር ወር የሚሆነውን መንገድ በሦስት ሰዓት አደረሰው በአባ ጰንጠሌዎንም ደጅ አቆመው ይህም በኢትዮጵያ ንጉሥ በእልአሚድ ዘመን ነበር። ❤ አባ ጰንጠሌዎንም ቅዱስ ይስሐቅን በአየው ጊዜ ደስ ብሎት አቅፎ ሳመው ወደ በዓቱም አስገብቶ የምንኲስና ልብስን አለበሰው። ይስሐቅም በጾም በጸሎትና በስግደት ተጠምዶ ቆዳው ከዐፅሙ እስከሚጣበቅ ሲጋደል ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ መደራ ወደተባለ ቦታ ሔደ በዚያም ድንቅና ተአምር እየአደረገ በሽተኞችን በመፈወስና አጋንንትን በማስወጣት ብዙ ዘመን ኖረ። በአንዲት ዕለትም በጥዋት ሥንዴ ዘራ በሠርክም መሥዋትን አሳረገ። በማግሥቱም በግራር ዛፍ ላይ በሮችን አውጥቶ የሥንዴውን ነዶ አበራየ ሰባ ሰባት የእንቅብ መስፈሪያም ሆነ። ሁለተኛም የወይን አረግ በአለት ላይ ተከለ ወዲያውም በቀለች አበበችና አፈራች በእርሷም መሥዋዕትን አሳረገ። አንዲት ቀንም ሲጽፍ መሸና ፀሐይ ሊጠልቅ ተቃረበ በቦታውም እንዲቆም አዘዘው ጽሕፈቱንም እስቲጨርስ ቆመ። ምራቁንም ትፍ ባለበት ዘንድ ጠበል ፈልቆ እስከ ዛሬ ለበሽተኞች ፈውስ ሆኖ ይኖራል። ❤ በአንዲት ዕለትም ሰዎች ወደ አባ ጰንጠሌዎን መጥተው "ቀሲስ ይስሐቅ እኮ ከበላ በኋላ የቁርባን ቅዳሴ ቀደሰ" ብለው ነገሩት አባ ጰንጠሌዎንም ወደርሱ ሒዶ "ልጄ ይስሐቅ ሆይ ምሥጢር ስለ አለኝ ከአጠገባችን ሰዎችን አስገልል" አለው ይስሐቅም "ሰዎችን ተውና ዕንጨቶችና ድንጋዮችም ይገለሉ" አለ። ወዲያውኑም ዕንጨቶችና ድንጋዮች አንድ ምራፍ ያህል ሸሹ። አባ ጰንጠሌዎንም "ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ" አለ ስለዚህም ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ገሪማ ተባለ። ❤ መልካም ተጋድሎንና የቀና አካሔዱን በፈፀመ ጊዜ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት "ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያው ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍና ለሚያጽፍ፣ ለሚያነበውና ለሚተረጉመው ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ዳግመኛም "የተራበውን ላበላ፣ የተጠማውንም ላጠጣ እኔ የሕይወት እንጀራን እመግበዋለሁ የድኅነት ጽዋንም አጠጣዋለሁ" አለው። በቤተ ክርስቲያንህም በማኅሌት ያመሰገነውንና የፀለየውን እኔ የመላእክትን ምስጋና አሰማዋለሁ የተራቆተውንም ለሚያለብስ የብልህ እጅ ያልሠራው የብርሃን ግምጃን አለብሰዋለሁ ነፍሱም ከሥጋው በምትለይ ጊዜ የጨለማ መላእክት አይቀርቡትም። የብርሃን መላእክትም በዙሪያው አቆማቸዋለሁ። በስምህም ቤተ ክርስቲያን ለሠራ በሰማያት አርባ ሰባት የብርሃን ቦታዎችን እኔ እሰጠዋለ፣ ለቤተ ክርስቲያንህ መባ የሚሰጠውንም እኔ በመንግሥቴ እቀበለዋለሁ፣ ቦታህን የሚያከብረውንም እኔ በመንግሥቴ አከብረዋለሁ፣ ጠላቶች አጋንንትን ረግጦ የሚገዛበትንም እሰጠዋለሁ"። ❤ አባ ገሪማም "ይህን ታላቅ ሀብት በቸርነትህ ብዛት የሰጠኸኝ አቤቱ ስምህ ይክበር ይመስገን ግን ጌታዬ ሆይ መታሰቢያዬን ላደረገ፣ ገድሎንም ለጻፈ እስከ ስንት ትውልድ ትምርልኛለህ" አለ። መድኃኒታችንም "እስከ ዐሥራ ሁለት ትውልድ እምርዋለሁ" አለው አባ ገሪማም መድኃኒታችንን "ልጆች ባይኖሩትስ ምን ታደርግለታለህ" አለው። መድኃኒታችንም "ዐሥራ ሁለት ዕጽፍ ክብር እሰጠዋለሁ" ብሎ መለሰለት። ❤ ዳግመኛም "የሞት ጥላ እንደማያገኝህ ታላቅ የምሥራች እነግርሃለሁ" አለው ይህንንም ተናግሮ ሰላምታ ሰጥቶት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ቅዱስ አባ ገሪማም በልቡ ደስ ተሰኘ ወዲያውኑም ሰኔ 17 ቀን በብርሃን ሠረገላ ተነጥቆ ብሔረ ሕያዋን ገባ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም አባ ገሪማ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 17 ስንክሳር።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ሰኔ ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን #የእግዚአብሔር_መልአክ_ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦለት #ሕፃኑንና_እናቱንም_ይዞ_ወደ #እስራኤል_አገር_እንዲመለስ_ላአዘዘበት_ዕለትና #መልካም_ሽምግልና_ላለለው ስም አጠራሩ ለከበረ በገዳም ለሚኖርና በገድል ለተጠመደ #ለስልሳ_ዓመት ብቻው ሰው ሳያይ ለኖረ አባት ለላይኛው ግብጽ ሰው #ለአባ_አቡናፍር_ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #የአባ_አቡናፍርን_ገድል ከተናገረ #ከአባ_በፍኑትዮስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_አቡናፍር፦ የዚህም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቊጥሩ ከገዳማውያን ነውና። አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ። ❤ በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጒሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያት ጸለየ ከዚህም በኋላ "አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" አለው ይህንንም በማለት ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት። ❤ ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ። ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ በዚያ በረሀ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው። አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኰሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ "እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን?" አልኳቸው እነርሱም "አወን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው" አሉኝ። ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ። ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳምውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚች ምንጭ እጠጣለሁ በዚች በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም" አለኝ። ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው። ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገብን። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ። ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው። ❤ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ። ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ የከበሩ ገዳማውያን በአባ አቡናፍርና በአባ በፍኑትዮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 16 ስንክሳር።                                                 ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወአዝማድየኒ ቀብፁኒ ወተናከሩኒ። ወተኀየሉኒ እለ የኀሥሥዋ ለነፍስየ። ወእለኒ ይፈቅዱ ሕማምየ ነበቡ ከንቶ። መዝ37፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ማር 3፥20-ፍ.ም።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 6፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥10-15 እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ሰኔ_፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሰማይ_ጭፍራ ለተባለ #ለቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ ክርስቲያን_መርዩጥ በተባለ አገር #ለከበረችበት_ለቅዳሴ_ቤቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤት፦ ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበሸ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጒድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋራ አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ለንሡም የቊስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ ከዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አላት። ከእንቅልፍም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ስሟም መርዩጥ ተባለች። ❤ እግዚአብሔር ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቊጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ሰኔ 15 ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ15 ስንክሳር።                                                   ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ"። መዝ 88፥19። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 7፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥44-51። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ የቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚናስ የቅዳሴ ቤት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤ ❤ እንኳን ለሐዋርያት ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ የላይ ቤት የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ ፫ "#ዘምሩ_ለእግዚአብሔር_ጻድቃን እስመ ተንሥአ #ክርስቶስ_እሙታን (ዘምሩ)፤ በህየ ሠበረ ኆኃተ ብርት ወበህየ አውፅአ ዘቀዳሚ ልሕኵቶ (ዘምሩ)፤ አርአዮ #ለቶማስ_ርግዘተ_ገቦሁ_ወለእንድርያስ_ቅንዋተ እደዊሁ (ዘምሩ)፤ ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት በ፵ ዕለት #ምስለ_መላእክት_ዘምሩ_ለእግዚአብሔር ጻድቃኑ ወግነዩ ለዝክረ ቅድሳቱ"፡፡ ትርጉም፦ ጻድቃን ሆይ! #ለእግዚአብሔር_ዘምሩ፤ #ክርስቶስ_ከሙታን ተነሥቷልና በዚያ የብረትን ደጅ ሰበረ፤ የቀደመውን ማሰሮውን (ዕዳ ደብዳቤውን) አወጣ፤ #ለቅዱስ_ቶማስ_የተወጋውን ጎኑን፤ #ለቅዱስ_እንድርያስ_የእጆቹን_ችንካሮች_እሳየው፤ በዐርባ ቀን ወደ ሰማያት ዐረገ፤ ጻድቃን ከመላእክት ጋራ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፣ ለቅድስናው መታሰቢያ ተገዙ።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የታች_ቤት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ግበሩ በዓለክሙ በትፍሥሕት ዮም በዛቲ ዕለት ሰንበተ ክርስቲያን (ግበሩ) ዘሐመ ወሞተ ሲኦለ ወሪዶ ፈትሐ ሙቁሐነ (ግበሩ) ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት #ተኰነኑ_ሎቱ_መላእክት ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ #ተዝካረ_ትንሣኤሁ_ለመድኀኒነ፡፡ ትርጉም፦ ዛሬ በዚህች በሰንበተ ክርስቲያን ቀን በዓላችሁን በደስታ አድርጉ፤ መከራ የተቀበለ፤ የሞተው #ጌታ_ወደ_ሲኦል ወርዶ እስረኞችን ፈታ፤ በክብር በምስጋና ወደ ሰማያት ዐረገ፤ #መላእክት_ሁላቸው_ተገዙለት! #የመድኀኒታችን_የትንሣኤው መታሰቢያ ደስታ ደስታ ደስታ ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወበመንፈስ አዚዝ አጽንዐኒ። ከመ እምሀሮሙ ለኀጥአን ፍኖተከ። ወረሢዓን ይትመየጡ ኀቤከ"። መዝ 50፥12-13 ወይም 50፥11፥12 የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 1፥1-15 ወይም 1ኛ ቆሮ 14፥1-27፣ 2ኛ ጴጥ 1፥1-12 ወይም 1ኛ ዮሐ 4፥1-9 እና የሐዋ ሥራ 8፥14-25 ወይም 10፥44፥51። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 16፥1-17 ወይም ዮሐ 15፥17-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ። መልካም ዕለተ ሰንበትና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤             ❤ #ሰኔ ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን #ለከበረ_መልአክ_ለሐዲስ_የምሥራች ነጋሪ ለሆነ #ለመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል (በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ሠሩላቸው)፣ ለኄኖስ ልጅ #ለቅዱስ_ቃይናን_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ_በዐልና #ለኢየሩሳሌም_ኤጲስቆጶስ_ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከሰማዕቱ #ከቅዱስ_አቡላግ፣ #ከሁለት_መቶ_ሰማዕታትና ስለ እውነት ከሰደደ ከአባታችን #ከቅዱስ_ማትያንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤#በዚችም_ዕለት_ለከበረ_መልአክ_አዲስ_የምሥራች_ነጋሪ_ለሆነ_የመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ገብርኤል_በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ሠሩላቸው። ❤ ይህ የከበረ መልአክ የእራኤል ልጆች ከሰይጣን እጅ ስለመዳናቸውና ከምርኮም ስለ መመለሳቸው ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር በሚጸልይና በሚማልድ ጊዜ አስቀድሞ የተገለጠለትና ስለ ድኅነታቸውና ስለ ቤተ መቅደስም መታነፅ የነገረው ነውና። ዳግመኛም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መምጣትና መገደል ስለ ቤተ መቅደስም መፍረስ ከዚያም በኋላ ስለ ሐሳዊ መሲሕ መምጣት ነገረው። ❤ ለመድኅን መምጣትም በሱባዔ የወሰናቸው ዘመናት በተፈጸሙ ጊዜ ይህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ቅድስት ድንግል ወደ እመቤታችን ማርያም መጣ ዓለምን ስለ ማዳን የእግዚአብሔር ልጅ ከርሷ ሰው ስለመሆኑ ነገራት። ❤ ስለዚህም የበዓላቶቹን መታሰቢያ እንድናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን። እኛም ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ያድነን ዘንድ ለመንግሥቱም የተዘጋጀን ያደርገን ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ እኛ እንለምነው። ልዕልና ችሎታም ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የዚህም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ቃይናን፦ ቃይናንም መቶ ሰብዓ ዓመት ኖረ መላልዔልንም ወለደው መላልዔልንም ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ ሴቶች ልጆችና ወንዶችም ወለደ። ቅዱስ ቃይናን መላ ዘመኑ ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ነው ከዚያም በኋላ ዐረፈ። የቅዱስ ቃይናን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ አባ ኢላርዮንና በታላቁ አባ ኤስድሮስ ገዳም በታናሽነቱ መነኰሰ ከአባ ኤጲፋንዮስ ጋራም በገድል በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የደግነቱ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜናም በቦታው ሁሉ ተሰማ። ከዚህም በኋላ ኤጲፋንዮስ በቆጵሮስ አገር ኤጲቆጶስነት ከተሾመ በኋላ እርሱን መርጠው በኢየሩሳሌም ኤጲስቆስነት ሾሙት። ❤ ይህ አባት በሹመት በነበረ ጊዜ ሰይጣን በገንዘብ ፍቅርና በዚህ ዓለም ክብር አሳተው ብዙ ገንዘብ ሰብስቦ ለማዕዱ የሚመገብበት የወርቅና የብር ሣህን አሠርቶ ነበርና ለድኆችና ለምስኪኖችም መራራትን ተወ፤ ምንም የእንጀራ ቁራሽ አይሰጣቸውም ነበር። ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በሰማ ጊዜ የቀድሞውን ተጋድሎውንና የዓለም መናኒነቱን ፍቅሩንም አስታውሶ እጅግ አዘነ ከቀድሞ ጀምሮ በመንፈስ ወንድሙና ወዳጁ ነበርና። ❤ ስለዚህም ብፁዕ ኤጲፋንዮስ ከቆጵሮሰሰ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አባ ዮሐንስ መጣ አባ ዮሐንስን በጥበብ ከስሕተት ያድነው ዘንድም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ባለበት ቤተ መቅደስ ለመስገድ እንደመጣ አገኘው። በተገናኙም ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን ወደ ቤቱ አስገብቶ ማዕድ አዘጋጀለት በማዕድም ላይ ከብርና ከወርቅ የተሠራ ሣህኖችን አኖረ አባ ኤጲፋንዮስም በልቡ አዘነ ለድኆችና ለምስኪኖች ርኄራኄ እንደሌለውም አየ። ❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወጥቶ በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት በአንዱ አደረ። ምክንያትም አዘጋጀ ይህም እንዲህ ነው ወደ አባ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከ "ወንድሜ ሆይ ከቆጵሮስ አገር ሽማግሎችና የሕዝቡ መምህራን ወደ እኔ መጥተዋልና በእነርሱ ፊት ታከብረኝ ዘንድ ከወርቅና ከብር የተሠሩ የማዕድ ዕቃዎችን ይመገቡባቸው ዘንድ እንድትልክልኝ እሻለሁ" እርሱም ላከለት። ያን ጊዜም አባ ኤጲፋንዮስ ዕቃዎቹን ወስዶ ሸጣቸው ዋጋቸውንም ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወታቸው። ❤ ከዚህም በኋላ በተገናኙ ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን "የላክሁልህን የማዕድ ዕቃዎቼን መልስ" አለው እርሱም "እሺ" አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ነገረው አባ አረጲፋንዮስም "እሺ" አለው። በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ካለበት ቤተ መቅደስ ሲወጣ አገኘው ያን ጊዜም ያዘውና "ገንዘቤን እስምትሰጠኝ አልለቅህም" አለው አባ ኤጲፋንዮስም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያን ጊዜም የአባ ዮሐንስ ዐይኖቹ ታወሩ። ያን ጊዜም ይቅር ብሎት ዐይኖቹን ይገልጥለት ዘንድ እያለቀሰ ወደ አባ ኤጲፋንዮስ ማለደ እርሱም መጸጸቱን አይቶ አንዲቱን ዐይኑን ገለጠለት እንዲህም አለው "ነፍስህን ታስብ ዘንድ አንዲቷ ዐይንህ ዕውርት እንደሆነች ትቶልሃል"። ገሠጸውም እንሆ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀድሞ ድካምህን ብርታትህንና ተጋድሎህን አስቦ ራራልህ ከስሕተትም አዳነህ" አለው። ❤ "የማዕድ ዕቃዎችንም እኔ እንደሸጥኳቸውና ስለ አንተ ለድኆችና ለምክኪኖች እንደ መጸወትኳቸው ዕወቅ አንተ በገንዘብ ፍቅር መጠመድህንና የቀድሞውን መልካም ሥራህን መተውህን ብሰማ ነው እንጂ ከቆጵሮስ ወደ ኢየሩሳሌም አልመጣም ነበር"። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ቅዱስ ዮሐንስ ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆነ በርኅራኀረም መንገድ ሔደ ያለውንም ጥሪቱን ሁሉ ሰጠ ምንም አላስቀረም ልብሶቹንም ለተራቆቱ ሰጠ በሞተ ጊዜ አንድ አላድ ከዚያም በታች ከእርሱ ዘንድ እስከ አልተገኘ ድረስ ሰጠ። ❤ ጌታችንም የመፈውስ ሀብትን ሰጠው ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከተቀደሰ ዘይት እየቀባ ፊታቸውንም አዳኝ በሆነ መስቀል ምልክት እያማተበ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ አዳናቸው። መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ ክብር ይግባውና ጌታችንን አገልግሎ ሰኔ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 13 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለገብርኤል_በእደዊሁ_ዘተአሥሩ። መላእክተ ሰማይ ጌጋየ በትውልደ ሰብእ ዘገብሩ። ለዝንቱ መልአክ በእንተ ዕበዩ ወክብሩ። በብሔረ ግብጽ መምህራን ሥርዓት አንበሩ። በዛቲ ዕለት ይትገበር ተዝካሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_13።                      

ለትልልቆች ነው የሚገባው፣ ትዕግሥት አድርግ…" ሲሉት እርሱም "…ለእኔ የሚሻለኝን ዐውቃለሁ" ብሎ መለሰ። እነርሱም በመልሱ ተገርመው አመነኰሱትና ማትያስ የሚል ስም ሰጡት። ❤ ከዚህም በኋላ አቡነ ማትያስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው በጾም በጸሎት ተወስነው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እየተቀበሉ ማገልገል ጀመሩ። በዚኸም ጊዜ ሰይጣን በሥጋቸው ፈተናቸው። እርሳቸውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው "ኦ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበላት፣ ግደለኝ፤ እንዴት ከተወለድኹ ጀምሮ እስከዛሬ ፍጹም የማላውቀው መጥፎ ሀሳብ ከሚመጣብኝ ሞት ይሻለኛል፣ ግደለኝ.. እያሉ ሲጸልዩ የክብር ባለቤት ጌታችን በአካል ተገልጦላቸው በመለኮታዊ እጆቹ ዳስሶ ፈጽሞ አዳናቸው። ❤ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አቡነ ማትያስ ከአንድ መነኵሴ ጋር ለገዳሙ ማኅበር ምግብ ለማዘጋጀት ወደ በረሓ እንደደረሱ የሚጠጡት ውኃ ሲያጡ አባታችን ማትያስ ጸሎት ካደረሱ በኋላ በበትራቸው መሬትን ባርከው እንደ ሊቀ ነቢያትሙሴ ውኃ አፈለቁ። እነርሱም የማኅበሩን ምግብ ይዘው ሲመለሱ በመንገድ ላይ ሽፍቶች አግኝተዋቸው ምግቡን ወሰዱባቸው፤ አባታችንም ጸሎት ቢያደርጉ ወዲያው እነዚያ ሽፍቶች ታመው ወደቁ። ከዚያም ሽፍቶቹ "እናንት የአምላክ ሰዎች ሆይ! እባካችሁ ይቅር በሉን፣ የወሰድንባችሁንም እንኩ ውሰዱ፣ እኛንም እርዱን…" እያሉ ለመኗቸው። አባታችንም ምራቃቸውን እንትፍ ብለው በትእምርተ መስቀል አማትበው በእርሱ ዳበሷቸውና ሽፍቶቹ ዳኑ። ❤ ዳግመኛም በአንደኛው ቀን መነኰሳቱ ሁሉም ሥራ ጨርሰው ተኝተው ሳለ አቡነ ማትያስ ግን ደከመኝ ሳይሉ መቶ ሃምሳውንም መዝሙረ ዳዊት ሲደግሙ አደሩ እግዚአብሔርም መላእክቱን ልኮ አንድ ፈረስ ሰጣቸው። አባታችንም በዚህ ተደስተው ለኹለተኛ ጊዜ መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት ሲደግሞ አሁንም ለኹለተኛ ጊዜ ፈረስ ተላከላቸው። ከእርሳቸውም ጋር የነበሩት መነኰሳት ምን እንደተፈጠረ ሳያውቁ ተኝተው አደሩ። አቡነ ማትያስን መላእክት ወደ ሰማያት አውጥተዋቸው በገነት ተድላ ያሉ ጻድቃንን አሳይተው ዳግመኛም የኀጥአንን ፍዳና መከራ አሳዩዋቸው። አባታችንም የኀጥአንን መከራ አይተው አዝነው ደንግጠው አለቀሱ። በዚህም ጊዜ "የተመረጥህ ማትያስ ሆይ! አትፍራ፣ እነዚህ ሕጌን የማያከብሩ ትእዛዜን ያፈረሱ ናቸው፣ በተድላ ገነት ያየኻቸውም ጻድቃን ናቸው" የሚል ቃል አጽናናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ምድር ተመልሰው በመጡ ጊዜ አበ ምኔቱ አባ ተወልደ ምድኅን ዐርፈው በእርሳቸው መንበር አባ ፊቅጦር ተተኩ፤ ከአባ ፊቅጦርም በኋላ አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት መሠረት አቡነ ማትያስን መርጠው ለመሾም ተስማሙ ነገር ግን አባታችን ማትያስ ሹመቱን እምቢ ሲሉ እጅና እግራቸውን አሥረው በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው። ❤ አቡነ ማትያስም ወደ ሰማያት ወጥተው የጻድቃንን ደስታና የኀጥአንን ፍዳ መከራ ከተመለከቱና ወደምድር ተመልሰው ከመጡ በኋላ መነኰሳቱን ሁሉ ሰብስበው ሕግንና ሥርዓትን ተግብረው ይኖሩ ዘንድ ስለነገሯቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዳንድ ክፉዎች ወደ ንጉሡ ዘንድ ሔደው በብዙ ነገር በሐሰት ከሰሷቸው። ንጉሡም የተነገረው ሁሉ እውነት መስሎት አባታችንን ከሥልጣን አወረዳቸውና አሳደዳቸው። አቡነ ማትያስም ከገዳሙ ወጥተው ሲሔዱ "ከአንተ ከአባታችን አንለይም ብለው 230 መነኰሳት አብረዋቸው ሔዱ። ከዚህም በኋላ "ትኹል ጎዳዕ፣ ጨዓት፣ ቃቕብዳ፣ ኣቄታብ፣ ወኪ፣ ምድረ ባሕር" ወደተባሉ የተለያዩ | ቦታዎች ሔደው በተጋድሎ ኖሩ። በየበረሓውም ሲጓዙ ልጆቻቸው ውኃ ሲጠማቸው አባታችን መሬትን ባርከው ውኃ አፍልቀው አጠጧቸው። አባታችንም በምድረ ባሕር ሣሉ እህል ሳይቀምሱ በአንዲት ዋሻ ለኹለት ሳምንት ከቆዩ በኋላ በዚኸች ቦታ ላይ በሞት ማረፍ ፈለጉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ "ለአንተ የምትሆን ምድር አዘጋጅቼልሃለሁና ወደልጆችህ ተመለስ" አላቸው። ❤ አባታችን ዳግመኛም ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ወደ ዓንደቕ ከዚያም ወደ ዒላ ሔደው ለ66 ቀናት ከቆዩ በኋላ ደብረ ብርሃን ደረሱ። አባታችንም ይኸችን ቦታ "እግዚአብሔር የሰጠን ገዳማችን ናት" አሉ። ቦታዋንም ደብረ በረከት ብለው ሰየሟት። ❤ የዕረፍታቸውም ጊዜ ሲደርስ ልጆቻቸውን ሰብስበው በቃለ እግዚአብሔር አጽናንተው "በሥጋ ብለያችሁም በመንፈስ ግን ከመካከላችሁ አልለያችሁምና አትፍሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፣ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስንና የአቡነ አብሳዲን ሥርዓት ጠብቁ…" ብለው ከመከሯቸው በኋላ በእርሳቸው ቦታ ዮሐንስን ሾመውላቸው ከጌታችን ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ሰኔ 13 ቀን በሰላም ዐረፉ። ❤ አቡነ ማትያስም ካረፉ በኋላ ለልጆቻቸው በአካለ ነፍስ እየተገለጡ አጽናንተዋቸዋል ። ከማረፋቸውም በፊት "አስቀድመው .....ከእናንተ ውስጥ የሚማረኩ አሉ፣ ነገር ግን እኔ አድናችኋለሁ" ብለዋቸው ስለነበር ትንቢታቸው ደርሶ ኹለቱ መነኰሳት ተማረኩ ነገር ግን በአባታችን ጸሎት ወደ ገዳማቸው ተመለሱ። ዳግመኛም ከመነኰሳቱ ውስጥ ሰባቱን ዐረማውያን ማረኳቸው፣ ንብረታቸውንም ወስደው ኹለቱን ገድለው፣ አምስቱን በባሕር ውስጥ ጣሏቸው፤ በዚኸም ጊዜ አባታችን ማትያስ በአካለ ነፍስ መጥተው "ልጆቼ አይዟችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አወጣችኋለሁ፣ ባሕሩንም በእሳት አቃጥለዋለሁ" ብለው ካወጧቸው በኋላ ባሕሩን በእሳት አቃጥለውታል። ከአቡነ ማትያስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤               ❤ #ሰኔ_፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ በበትራቸው መሬትን ባርከው እንደ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ውኃ ላፈለቁት ዳግመኛም በባሕር የተጣሉ ልጆቻቸውን ባሕሩን በተአምራት አቃጥለው ልጆቻቸውን ላዳኑት በኤርትራ አገር የሚገኘውን "ደብረ ብርሃን ወደብረ በረከት ወደብረ ሰማዕት" ገዳም ለመሰረቱት #ለአቡነ_ማትያስ_ዘምራራ ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ማትያስ (#ማይታን)፦ አባታቸው በዚህ ዓለም ሀብትና ንብረት ያፈራ ቢሆኑም በመጀመሪያ የክርስትና እምነትን ግን አልተቀበለም ነበር። ሀብቱንም የሚያወርሰው ልጅ ስላልነበረው በዚህ ይጨነቅ ነበር። የአቡነ ማትያስም እናት "…ክርስቲያን ሴቶች እኮ ወደ እግዚአብሔር ለምነው ልጅ ያገኛሉ፣ እኛም ወደ እግዚአብሔር እንለምንና ልጅ ካገኘን ለእግዚአብሔር ይሆናል" በማለት ለባሏ ነገረችው። እነርሱም ከተመካከሩ በኋላ "ልጅ ካገኘን እኛም ክርስቲያን እንሆናለን" ብለው ስዕለት ተሳሉ። ለቤተ ክርስቲያንም ዕጣን ሰጥተው ካህኑን "እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጠን ጸልይልን" አሉት። ❤ እመቤታችንንም በጸሎት ሲማጸኗት ቆይተው እግዚአብሔር ስዕለታቸውንና ጸሎታቸውን ተቀብሎ ልጅ ሰጣቸውና እጅግ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርንና እመቤታችንን አመሰገኑ። ከዚህም በኋላ ወላጆቻቸው አምነው ተጠመቁና ስማቸው አብርሃም እና ኂሩተ ማርያም ሲባሉ የሕፃኑም ስም ድኁነ እግዚእ ተባለ። አብርሃምና ኂሩተ ማርያምም ፍጹም ክርስቲያኖች ከሆኑ በኋላ እግዚአብሔር በበረከት ጎበኛቸውና ሌሎች ፈቃደ እግዚእ፣ ባርያ እግዚእ፣ ንዋየ እግዚእ፣ ደጋፊነ እግዚእ እና ጥሪተ እግዚእ የሚባሉ አምስት ልጆችን ወለዱ። ስለዚህም አቡነ ማትያስ በ14 መ/ክ/ዘ ጽልማ ታኺታ በሚባል ቦታ ተወለዱ። እርሳቸውም በመጀመሪያ ስማቸው ጥሪተ እግዚእ ተብለው እንደ ቅዱስ ዳዊት የመጨረሻ ልጅ ሆነው በእረኝነት ወላጆቻቸውን ያገለግሉ ነበር። ❤ ጥሪተ እግዚእ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከእርሱ ጋር በግ የሚጠብቁ ጓደኞቹ ከሰው ማሳ እሽት ሰርቀው አምጥተው "ና ከእኛ ጋር ብላ" አሉት። እርሱ ግን የሌላን ሰው እህል አልበላም ብሎ እምቢ አለ፤ ለእናቱም ሲነገራት እናቱ ተደስታ አቅፋ ሳመችው። ጓደኞቹም በሌላ ጊዜ እንዲሁ የተሰረቀ እያመጡ ይበላ ዘንድ ቢፈታተኑትም እርሱ ግን እሺ አይላቸውም ነበር። በዚኸም ነገር ይህ ታናሽ ብላቴና ጥሪተ እግዚእ ኢትዮጵያዊውን ታላቅ ጻድቅ አቡነ ሀብተ ማርያምን መሰላቸው። ከዕለታትም በአንደኛው ዕለት አባታቸን ሀብተ ማርያም በጐችን ሲጠብቁ ሌሎች እረኞች በአመጻ ከሰው ሰርቀው ቆርጠው ያመጡትን እሸት "ና እንብላ" አሏቸው። አባታችን ግን "ከየት እንዳመጣቸሁት ምንም ስለማላውቅ አልበላም" አሏቸው። እረኞቹም ሀብተ ማርምን በቁጣ ዐይን እያዩአቸው ተቀምጠው ሲበሉ አባታችን "የማንችለው ዝናብ መጥቷልና ተነሡ በፍጥነት ወደቤታችን እንሂድ" አሏቸው። እረኞቹም "ሠማዩ ብራ ነው ምንም ደመና የለውም፤ ነፋስም አይነፍስም። እኛ የማናየው አንተ ብቻ የምታየው ምን ነገር አለ?" እያሉ በአባታችን ላይ ተዘባበቱባቸው። አባታችን ግን በጎቻቸውን እያስሮጡ በፍጥነት ወደ ቤታቸው ሔዱ፤ ወዲያውም በጣም ኃይለኛ ዝናብ ዘነበ፤ የጥፋት ውኃው በላያቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ እነዚያን እረኞች ከቦታቸው አልተነቃነቁም ነበርና በጥፋቱ ውኃ አለቁ። በዚያችም ሌሊት አቡነ ሀብተ ማርያን ከሰማይ ሦስት ጊዜ "ሀብተ ማርያም ሀብተ ማርያም" የሚል ድምፅ ጠራቸው። አባታችንም እንደ ሳሙኤል "ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር" ሲሉ ጌታችን አናገራቸው። ❤ ከዚህ በኋላ "ለሚሰሙ ለመረጥኳቸው ቃሌን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔም ጋር በምሥጢር በባለሟልነት ትነጋገር ዘንድ መርጨሃለሁ" አላቸው። ከጥቂት ቀንም በኋላ አባታችን ዳግመኛ በጐችን እየጠበቁ ሳሉ አንድ አመጸኛ መጣና በትራቸውን በኃይል ነጥቆ ወሰደባቸው። አቡነ ሀብተ ማርያምም "በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ እቋቋምህ ዘንድ ኃይል የለኝምና በትሬን መልስልኝ" ቢሉት የትዕቢትን ቃል ተናገራቸው። አባታችንም "እምቢ ካልክስ እሺ የእግዚአብሔርን ኃይል ታያለህ" አሉት። ወዲያም ያ አመጸኛ ላዩ ታች ታቹ ላይ፣ ግራው ቀኝ ቀኙ ግራ ሆኖ በአየር ላይ ተሰቅሎ ዋለና እየጮኸ አባታችንን ለመናቸው። አባታችንም "የቀጣህ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ባሉት ጊዜ ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ። በዚያ የነበሩና ይህንን ተአምር ያዩ እረኞችም እጅግ ፈርተው ሔደው ለወላጆቻቸው ያዩትን ተናገሩ። የሀገሩ ሰዎችም "ቀድሞ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያለ ሲጸልይ ሲሰግድ አይተነዋል፣ አሁንም ጠላቱን በነፋስ የሚቀጣ ይህ ልጅ ወደፊት ምን ይሆን!" እያሉ አደነቁ። ወላጆቻቸውም ይህን በሰሙ ጊዜ በግ ጠባቂነቱን አስተዋቸውና ሃየማኖትን ይማሩ ዘንድ ወስደው ለመምህር ሰጧቸው። ❤ ወደ ጥሪተ እግዚእ ዜና ገድል እንመለስና እርሱም ከአመጸኞች ጋር ባለመተባበር ፈሪሃ እግዚአብሔርን ገንዘብ አደረገ። መንፈስ ቅዱስ በእናቱ ማሕፀን ሳለ እንደነቢዩ ኤርምያስ መርጦታልና በዋዛ ፈዛዛም ከእነርሱ ጋር አይተባበርም ነበር። ፊደልን እንኳን ሳይማር መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት መጻሕፍትን ዐወቀ፣ ትእዛዛትንም ሁሉ ጠበቀ። አባቱ አብርሃምም ዳግመኛ በጎችን መጠበቅ ትቶ ከብቶችን እንዲጠብቅ ስላዘዘው ሕፃኑም በኅብረት የማንንም ከብት ሳይለይ ይጠብቅ ነበር። ❤ በዚህም ወቅት ፈቃደ እግዚእ የተባለው ወንድማቸው ዓለምን ንቆ ገዳም ገብቶ ስለመነኰሰ ወንድሞቹ ሔደው ለአባታቸው ነገሩት፤ አባታቸውም "የእኛ ፈቃድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አላቸው። እርሱም ከነልጆቹ እንደሚመነኵስ ራእይ አይቶ ልጆቹን ጠርቶ "ልጆቼ ሆይ! እኛም እንደ ፈቃደ እግዚእ እንመነኵስ ዘንድ አለን" ሲላቸው ልጆቹም "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን፣ ስሙ በእኛ በባሪያዎቹ ይክበር ይመስገን" አሉ። ❤ ከዚህም በኋላ አራቱ የአብርሃም ልጆች ታኺታ የምትባለውን ቦታ ትተው ወንድማቸው ወደመነኰሰበት ገዳም ለማየት ሲሔዱ ታናሹ ጥሪተ እግዚእም አብሮ ለመሔድ ተነሣ። እነርሱም "መንገዱ ሩቅ ነው አንተ ትንሽ ልጅ ነህ ከዚሁ ቆይ" ብለው ትተውት ቢሔዱም እርሱ ግን ከኋላ ከኋላቸው እየተከተላቸው ሲሔድ እንዲመለስ ያባርሩት ነበር። ከዚያም ሕርሻ የሚባል ቦታ ላይ ሲደርሱ ጥሪተ እግዚእን "ንብረትና ስንቅ እየጠበቅህ ከዚህ ቆየን እኛ ማሳችንን አይተን እንመለሳለን",ብለው ትተውት ሔዱ። እርሱም በዚህ ጊዜ በደብረ ማርያም ያሉ መነኰሳትን ተመለከተና የሚጠብቀውን ንብረትና ስንቅ ትቶ መነኰሳቱን ተከትሎ ወደ ገዳም ሲገባ ወንድሙን ፈቃደ እግዚእን በዚሁ ገዳም ውስጥ አገኘው። ፈቃደ እግዚእ እና መነኰሳቱም ከየት እንደመጣ እየጠየቁት አቅፈው ሳሙት። ጥሪተ እግዚእም አመጣጡን ነገራቸው። ❤ ወንድሞቹም ከሔዱበት ሲመለሱ ጥሪተ እግዚእን ስላጡት እያዘኑ ሳለ የገዳሙ አንድ መነኵሴ ሕፃኑ ወደ ገዳም እንደገባና ከታላቅ ወንድሙ ጋር እንደተገናኘ ነገሯቸው። ወንድሞቹም ወደ ገዳሙ ገብተው አበ ምኔቱን አባ ተወልደ መድኅንን አግኝተው ተባረኩ። አበ ምኔቱም ከወንድሞቻቸው ጋር አገናኛቸውና እያለቀሱ ተሳሳሙ። ከዚያም ወንድሞቹ ወጥተው ወደ ማሳቸው ሲሔዱ ሕፃኑ ጥሪተ እግዚእ ግን በገዳም ቀረ። በዚያም መመንኰስ እንደሚፈልግ ሲናገር መነኰሳቱ "ልጄ ሆይ! ይህ ለአንተ ይከብድሃል ምንኵስና