ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
613
Подписчики
+124 часа
-37 дней
-1130 дней
Архив постов
                           ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለቢካቦስ_ዘኮኖሙ_ተበያጼ። ለተስዓቱ ወኃምስቱ ሰማዕታተ ክርስቶስ እንበለ ግጋፄ። ጣዖታተ ይዝልፍ ወንጉሠ ዐማፄ። ለዝ ጥቡዕ ኢመጽኦ ድንጋፄ። እስከ መተሩ ሥጋሁ በማሕፄ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_የነሐሴ_10።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በማኅበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር። ወለአምላክነ በአንቅዕተ እስራኤል። ህየ ብንያም ወሬዛ በኃይሉ"። መዝ 67፥26-27። የሚነበበው ወንጌል ማር 11፥23-27።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ። ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ"። መዝ 73፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ነሐሴ ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳ #ለማኅበረ_በኵር_መታሰቢያ_በዓል፣ በእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት #በቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መግሥት ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_መጥራ ለዕረፍት በዓል፣ በከሀዲ መክስምያኖስ እጅ ሰማዕት ለሆነ #ለቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ ለዕረፍት በዓል፣ እስሙናይን ከሚባል አገር ለሆኑ ለከበሩ #ለቅዱሳን_ከቢካቦስና_ዮሐንስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ_ጋር_ሰማዕትነት_ከተቀበሉ_ከሠላሳ_ሺህ_ማኅበርተኞቹ_ሰማዕታት፣ ከቅዱሳን #ከቢካቦስና_ዮሐንስ_ከእነርሱ_ጋር_ሰማዕትነት ከተቀበሉ #ከዘጠና_አምስት_ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ በዚህችም ቀን #የማኅበረ_በኲር_በዓልን እንዲከበር የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓት ሠሩ እነዚህም #ከአቤል_ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲሁም እስከ ምጽአት #ስለጽድቅ_ደማቸውን_ስለሚያፈሱ እና ደስተኞች ስለ ሆኑት #አዕላፍ_መላእክትም_ሁሉ። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መጥራ፦ ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው። ❤ የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም "የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኋቸው" አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው። ❤ ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ መጥራ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ፦ ይህም ቅዱስ በንጉሥ መክስምያኖስ ፊት በአቆሙት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ" አለው። የከበረ ሐርስጥፎሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ"። ንጉሡም ተቆጥቶ ሥጋው ተቆራርጦ በምድር ላይ እስቲወድቅ በበትር ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት ጣሉት በላህያቸውም እንዲአስቱት ሁለት ሴቶችን ንጉሡ ወደርሱ ላከ ቅዱሱ ግን የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራቸው የዛሬ የሆነ የዚህንም ዓለም ኃላፊነት አስገነዘባቸው ወደ መክስምያኖስም በተመለሱ ጊዜ "እንዴት አደረጋችሁ" አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት "በከበረ ሐርስጥፎሮስ አምላክ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ እኛ እናምናለን" ንጉሡም ሰምቶ አንዲቱን በዕንጨት ላይ ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ሁለተኛዋን በአንገቷ ደንጊያ አንጠልጥለው ቊልቊል እንዲሰቅሏት አዘዘና ምስክርነታቸውን እንዲህ ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ ዕንጨቶችን ሰብስበው በማንደጃው ውስጥ አድርገው አነደዱ የከበረ ሐርስጥፎሮስን እጅና እግሩ እንደ ታሠረ ከውስጡ ጨመሩት ያን ጊዜም "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" አለ እሳቱ ከቶ ምንም አልነካውም። ሕዝቡም ይህን አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ዐሥር ሺህ ያህል ሰዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ ሁለተኛም የብረት ሠሌዳዎችን በእሳት አግለው አመጡ ቅዱሱንም በላያቸው በአስተኙት ጊዜ ምንም ምን የነካው የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰዎችና አርባ ሕፃናት አምነው ምስክር ሁነው ሞቱ። ❤ ንጉሥ መክስምያኖስም አይቶ እጅግ ተቆጣ የቅዱስ ሐርስጥፎሮስንም ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።ከንጉሡም ዘንድ በወጣ ጊዜ ጸሎትን አደረገ ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ ከዚህም በኋላ ምስክርነቱን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ቢካቦስና_ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ቢካቦስ ክርስቲያን ሲሆን በሥውር ወታደር ሆነ። አንጥያኮስ ለሚባል መኰንንም ስለ ዮሐንስና ስለ ኤጲስቆጶስ አባ አክሎግ ከተርሴስ አገር ስለ ናሕር ስለ አባ ፊልጶስም እነርሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው። ❤ መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ "እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን?" አላቸው "እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" አሉት። መኰንኑም "ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ" አላቸው። ቅዱሳኑም እንዲህ ብለው መለሱለት "እኛስ ለረከሱና ለተናቁ አማልክት አንሠዋም ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከጌታችን ኢየሱስ በቀር"። መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ምስክርነታቸውንም እስከፈጸሙ ድረስ አሠቃያቸው። ❤ ቅዱስ ቢካቦስን ግን ከአሠቃየው በኋላ አሠረውና ከመንኰራኲር ውስጥ ጨመረው ዘቅዝቆም ሰቀለው ሕዋሳቱንም ቆራረጠው ጌታችንም ያስታግሠውና ያበረታው ነበር ያለ ጉዳትም ጤናማ አድርጎ አስነሳው። ❤ ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ከብዙዎች ሰማዕታት ጋራ ላከው በመርከብም ውስጥ እህልና ውኃ ሳይቀምሱ ሃያ ስድስት ቀኖች ኖሩ። በርሙን ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይተው በምሳር ቆረጡት የምስክርነቱንም ተጋድሎ ፈጸመ መንግሥተ ሰማያትም አክሊልን ተቀበለ። ❤ ከሀገረ በርሙን ሹማምንቶችም አንድ ባለ ጸጋ ሰው መጥቶ የቅዱስ ቢካቦስን ሥጋ ወስዶ በአማሩ ልብሶች ገነዘው ወደ አገሩ እስሙናይንም ላከው። በመከራውም ወራት ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ ከእርሱም ጋራ የተገደሉ ዘጠና አምስት ሰዎች ናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ለቅዱሱ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ቢካቦስና ዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 10 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_እብል_ኪያክሙ_ማኅበረ። እምነቢያት ቅድመ ወእምወንጌላውን አኅረ። ፍሡሐን አእላፍ #እለተሳተፍክሙ_በኲረ። #ጽዮንሃ በጺሐክሙ ሀገረ። በጸሎትክሙ ቅድስት ዝክሩነ ወትረ"።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ነሐሴ ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን #ለአባታች_ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል (በዚች ቀን አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ ከሰማይ የወረደውን የቊርባን ኅብስት ተቀብለው ያቀበሉበት ነው ብሎ ገድላቸው ይናገራል)ና ስጥኑፍ ከሚባል አገር ለሆኑ ለሰማዕቱ ለካህኑ #አባ_ኦር ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጲላጦስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ ስጥኑፍ ከሚባል አገር የሆነ የከበረ #ቄስ_አባ_ኦሪ፦ ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት። ❤ ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው እርሱም "ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም" ብሎ እምቢ አለው። መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ኦሪ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 9 ስንክሳር።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-24፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ለሚስቱ #ቅድስት_ለሰሎሜ ለሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም፣ #አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር_አስዮና_ስሙና #መርካሎት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_አሞን ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ሚስቱ_ሰሎሜ ሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም_አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር፣ #አስዮና_ስሙና_መርካሎስ፦ ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት። ❤ የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው። ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኰል እንዲገባ አደረጉት። ❤ በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእሊም ቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ"። መዝ 57፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥24-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 7፥12-26። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከሰባቱ ከዋክብትን አንዱ ለሆኑት ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ በመሔድ ታላቁ ገዳም ደጋ እስጢፋኖስን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና፡- ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ "ዓቃቤ ሰዓት" እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ❤ ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ❤ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ "ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ" ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ "ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት (ገንፎ)" ብለው በመናገር ምላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ❤ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ❤ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከአቡነ ኂሩተ አምላክ ረድኤት በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለሐዋርያት_አለቃ_ለቅዱስ_ጴጥሮስ የሕያው እግዚብሔር ልጅ ብሎ ለመሰከረበትና ሥልጣነ ክህነት (የመንግሥተ ሰማያትን ምክፈቻ ቊልፍ) ለተቀበለበት በዐልና እግዚአብሔር ለሚወድ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለቅዱስ_ናዖድ_ለዕረፍት በዐል (8ሺህ ዘመን አታሳየኝ ብሎ ሲፀልዩ 8ሺህ ሳይገባ 1500ዓ.ም ያረፉት)፣ ለራኄል ልጅ #ለቅዱስ_ዮሴፍ ልደትና ለእስክድርያ ሃያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጢሞቴዎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን #የሐዋርያት_አለቃ_የከበረ_ሐዋርያ_ቅዱስ_ጴጥሮስ በዓል ነው። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና። ❤ በከበረ ወንጌል እንተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊሊጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል" ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኵላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን። ❤ ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ሰለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጪ አወጣቸው። ከእርሷቸውም ኤልያስ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ። ቅዱስ ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ "ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ" አላቸው። ስዚህም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጪ አወጣቸው። ❤ እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ "ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ" በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ በእውነት ምስክ ሆነ። ❤ ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት፣ የኤጲስቆጶሳት፣ የቀሳውስትና ዲያቆናት ሹመት ተሰጠ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለሁላችን ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ጢሞቴዎስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ለእስክንድርያ ሃያ ስድስተኛ ነው። ይህም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መርጦት ተጋዳይ የነበረ አባ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ ከዐረፈ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ። ❤ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል ንጉሥ መርቅያን በእስክንድርያ አገር ሌላ መናፍቅ ሊቀ ጳጳሳት ሾሞ አባት ጢሞቴዎስን አስቀድሞ አባ የዲዮስቆሮስ ተሰዶባት ወደ ነበረች ደሴተ ጋግራ አጋዘው። መርቅያንም ከሞተ በኋላ የእስክንድርያ ሰዎች ተነስተው መርቅያን የሾመውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት አባ የዲዮስቆሮስ እንደ አዘዘ አባ ጢሞቴዎስ መልሰው ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ የመርቅያን ልጅ ሊዮን ነገሠ ያን ጊዜ አባ ጢሞቴዎስ ሁለተኛ ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ዐሥር ዓመት ኖረ ሊዮን እስከ ሞተ ድረስ ከእርሱም ኋላ ዘይኑን ነገሰ። ያን ጊዜም አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበረ ሲመቱ በታላቅ ክብር መለሰው ሕዝቡንም እያስተማራቸውና እየመከራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ኖረ። ❤ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ መንበር ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ እግዘብሔርንም አገልግሎ ነሐሴ 7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለጴጥሮስ_ሥዩም። ላዕለ ሐዋርያት ኄራን ካህናተ ኵሉ ዓለም። ሶበ ለክርስቶስ አምኖ ከመ ወልደ አምላክ ዮም። ኢከሠተ ለከ ይቤሎ ዘሥጋ ወደም። እንበለ አቡየ ዘሀሎ እምቅድም"።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለዮሴፍ_ዘተሠይጠ_ወኮነ_ገብረ ወተሞቅሐ ሠለስተ ዓመተ"። ትርጉም፦ በወንድሞቹ ተሸጦ አገልጋይ ለኾነ፤ ሦስት ዓመታት ለታሰረ ለዮሴፍ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 7።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት #ድንግል_ማርያም_ለፅንሰቷ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                                                     ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእት አለቃ #ቅዱስ_ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ #ጻድቅ_ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን_ፅንሰቷን ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው። ❤ ይህም ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤልም ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደረጉ ስለትን ተሳሉ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎች ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላቸውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች። ❤ በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት አመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ በቅዱስ ኢያቄምና በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ለምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ"። መዝ 86፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1፥1-17።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13 ወይም መዝ 84፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 9፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 2፥6-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የእመቤታችን የፅንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ጌታችን_ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ላወጣላት #ከ36_ቅዱሳት_አንስት አንዷ ለሆነችው ለእናታች #ለቅድስት_መግደላዊት_ማርያም_ለዕረፍት በዐል መታሰቢያና #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነች ለከበረች #ለቅድስት_ኢየሉጣ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሲኖዳ_ረድእ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዊፃ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                        ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም፦ ይችም ቅድስት ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች። ❤ በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም "እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል" አላቸው ። ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት "ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው" አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው። ❤ ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች። ❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በቅድስት መግደላዊት ማርያም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር የሆነች #ቅድስት_ኢየሉጣ፦ ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብ ወረሰች ከታጋዮችንም አንዱ በግፍ ተነስቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿን ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት። ❤ ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት። በልቧም እንዲህ አለች "የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም"። ❤ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች "እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ"። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም ነሐሴ 6 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ❤ ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የአባ_ሲኖዳ_ረድእ_ቅዱስ_አባ_ዊፃ፦ እርሱም ከእግዚአብሔር ብዙ ምሥጢራትን የሰማ የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደ አየና እደንሰማ የጻፈ ነው። መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ እግዚአብሔርም አገልግሎ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም ዐረፈ። እግዚአብሔር በአባ ዊፃ ጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 6 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለኢየሉጣ_እንበይነ_ምግባር_ሠናይ። በውስተ እቶን ዘእብዋእ በውዴተ ብእሲ እኩይ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_ነሐሴ 6።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን"። መዝ 44፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥10-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓሣ ከሰማይ ለሚዘንብላቸው ለመናኔ መንግሥት #አቡነ_ኢዮስያስ_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #መናኔ_መንግሥት_አቡነ_ኢዮስያስ፡- ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጥር 6 ቀን ሲወለዱ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በመመነን በመጀመሪያ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ገቡ፡፡ አቡነ ኢዮስያስ በሐይቅ ገዳም ለ14 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኰሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አጠናቀው ተምረዋል፡፡ በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ትግራይ ደብረ በንኰል ገዳም ሄዱ፡፡ በደብረ በንኰልም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ መነኰሱ፡፡ ቆብ የተቀበሉት ግን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡ ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩአቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ወደ አዱዋ አውራጃ ዛሬ በስማቸው ወደተጠራው ገዳም ሄደው በቦታው ላይ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ገዳሙንም ከገደሙት በኋላ በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ ያፈለቁት ጠበል በፈዋሽነቱ የታወቀ ነው፡፡ በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ነሐሴ 6 ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ በየዓመቱ ነሐሴ 6 ቀን በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡ ❤ አቡነ ኢዮስያስን ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን ቢያስቸግሯቸው ጻድቁም በጸሎት ቢያመለክቱ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ የንብ መንጋ መጥቶ አረማውያኑን አንጥፍቶላቸዋል፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡ ❤ ጻድቁን እንደ ረድእ ሆኖ የሚያገለግላቸው አንበሳ ነበራቸው፡፡ ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የሰየመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከአቡነ ኢዮስያስ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ነሐሴ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮያዊው_ጻድቅ በኤርትራ አገር በሐማሴን አውራጃ ከአስመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ አስደናቂ ገዳም #ዘደብረ_ቢዘን ለመሰረቱት እንደ ሐዋርያው #ቅዱስ_ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ለነበሩት ለአንዳዴ ባሕር ለአባታችን #ለአቡነ_ፊልጶስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ፊልጶስ_ዘደብረ_ቢዘን፦ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ የተመረጡና እንደተወለዱ ነው ሰማንያ አንዱን የብሉይ መጻሕፍትን አጠናቀው ያወቁት ናቸው፡፡ በ12 ዓመታቸውም ለመመንኰስና ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን "አሰናብቺኝ" በማለት ጠይቀዋል፡፡ ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘውና ደብረ ጸራቢ ወደሚባለው ገዳም ገቡ፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስም የምንኵስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ ከባድ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢመክሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኵስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነገሯቸው፡፡ ከብዙ ፈተናም በኋላ አመነኰሷቸው፡፡ ❤ በገዳሙም እንጨት እየለቀሙና እየፈለጡ፣ ውኃ እየቀዱ፣ የክርስቶስን ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ በጾምና ጸሎት ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ነገራቸውና ሽሬ አደያቦ ወደሚባለው ስፍራ ሄዱ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገሩ ዞረው ሰበኩ፡፡ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእርሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡ 16 ደጋግ መነኰሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ፡፡ ይኸውም በኤርትራ ክፍለ ሀገር በሐማሴን አውራጃ ከአሥመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው አስደናቂው ገዳም ነው፡፡ ❤ ጻድቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባሕር በተአምራት ያቃጠሉት አባት ናቸው፡፡ በንጉሡ በዐፄ ዳዊት ዘመን ሰንበትን አንድ ብቻ ናት እያሉ በአንደኛዋ ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ጻድቁ አቡነ ፊልጶስ ይህን ሰምተው አንዲት ሰንበት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው፡፡ ከግብፅ የመጡት ጳጳስም ቀደም ብሎ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሁንም ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ ዐፄ ዳዊት አከራክረዋቸው ጳጳሱም በክርክሩ ተረቱ፡፡ ክፉዎችም በአቡነ ፊሊጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው፡፡ በአቁማዳ ጠቅልለው ሐይቅ ባሕር ውስጥ ጣሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባሕር በእሳት ተቃጥሎ ጽድቃቸውን መስክሮላቸዋል፡፡ ❤ ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባሕር ዳርቻ ላይ የተቃጠለው ድንጋይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ በወቅቱ የንጉሡ ሚስት በዋናተኛ አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አስወጣቻቸው፡፡ እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው፡፡ ወዲያውም "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው አለመግባባትና ክፉዎችም በባሕር ውስጥ ስለጣሏቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያው ታርቀዋል፡፡ በዘመናቸውም ርኃብ ስለነተሳ ጻድቁን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማክረዋቸዋል፡፡ አቡነ ፊልጶስም "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው መከሯቸው፡፡ ❤ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም በአቡን ፊልጶስ ምክር መሰረት ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዐሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዓሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊልጶስ ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል። ከአባታችን አቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱስ ከሚለው መጽሐፍ።                           ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለፊልጶስ_እንተ_ክህለ_ያዕዱ። ለዘጸውዖ ብእሲ ለውኂዘ ክረምት እምነ ሞገዱ። ወእምኔሁ አብ እለ መንፈስ ተወልዱ። እንዘ ይዜንው ኃይሎ ወምግባረ ጽድቁ ይንዕዱ። ስሙዓቲሁ ወጽአ ለዓለም በዐውዱ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_5።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ነሐሴ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን #እህቱን_ቅድስት_ማርያን ከዘማዊነት ሕይወት ወደ ጽድቅ ሕይወት ለመራት ለታላቁ ተጋዳይ ለሌለው #ለአባ_አብርሃም_ለዕረፍት_በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ ወታደር #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለዕረፍት_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ አብርሃም እህት ከቅድስት ማርያ ከመታሰቢያዋ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_አብርሃም፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ባለጸጎች ናቸው በተግሣጽና ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት ። በአደገ ጊዜም ያለ ፈቃዱ አጋቡት እግዚአብሔርም ወደሚፈቅደው ይመራው ዘንድ ሲለምን ኖረ። በሰባተኛውም ቀን በዐልጋው ላይ ሳለ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሳሥቶት ከጫጉላ ቤቱ ወጣ ብርሃን እየመራው ሒዶ ባዶ ቤት አግኝቶ በውስጡ ገብቶ ኖረ ምግቡን ከሚቀበልባት ከጥቂት መስኮት በቀር መዝጊያ ሠርቶ ደጁን ዘጋ። ❤ ዓለምን ከተወ በዓሥረኛው ዓመት አባትና እናቱ ብዙ ጥሪት ትተውለት ሞቱ እርሱ ግን ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ በጾምና በጸሎት ተወስኖ እየተጋደለ ኖረ ከአንድ ዐጽፍና ሰሌን በቀር ምንም ምን ጥሪት አላኖረም እንዲህም ሆኖ ዐሥር ዓመት ተጋደለ። ❤ እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አየ በአንዲት አገርም አረማውያን ነበሩ ከታናሾቻቸው እስከ ታላላቆቻቸው ወደ ሃይማኖት ሊመልሳቸው የሚችል የሌለ። በአንዲት ቀንም አባ አብርሃምን ጳጳሱ አሰበው ብርታቱንና ብልህነቱንም አይቶ ቄስ እንዲሆንና እነዚያን አረማውያን እንዲመልሳቸው አስገደደው በግድ አስጨንቆም ቅስና ሾመው ። ወደዚያም ቦታ ደርሶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ እነዚያን አረማውያን እርሱን ፈጣሪያቸውን ወደ ማወቅ ይመልሳቸው ዘንድ በውስጧ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ❤ በአነዲት ቀንም ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ገባ ያን ጊዜ ጣዖታቱን ከመቀመጫቸው ጣላቸው የአገር ሰዎችም በአዩ ጊዜ ቁጣን ተመልተው አብዝተው ደበደቡትና ከአገር አበረሩት በጥዋትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲጸልይ አገኙት። ሁለተኛም በገመድ አሥረው ወደ ከተማው ውጭ ጐትተው በላዩም አፈር ቆልለው እንዳይሞት ጥቂት መተንፈሻ ትተው አልፈው ከዚያ ሔዱ። በእግዚአብሔርም ኃያል ተነሥቶ ሔደ ስለ መመለሳቸውም ሲጸልይ አገኙት በእንዲህ ያለ ሥራም እየተጋደለ ዐሥር ዓመት ኖረ። ❤ የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ልባቸውን መለሰ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከታናናሾች እስከ ታላላቆች ድረስ ሁሉንም አጠመቃቸው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትም ጸኑ። ❤ ከዚህም በኋላ በሃይማኖታቸው መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ከንቱ ውዳሴ እንዳያመጣበት ፈርቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አገሪቱንም በመስቀል ምልክት አማተበባትና ማንም ሳያውቅ ወጥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ ። ❤ ሰይጣንም በሚያስፈራው በብዙ ሥራ ይፈታተነው ነበር ቅዱሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኃይል አሸነፈው። ጽኑ በሆነ ተጋድሎም ኖረ ያለ ዕንባም ሰዓት አላለፈችውም በጥርሶቹም አልሳቀም በከንፈሮቹም ፈገግ አላለም ስጋውን ቅባት አልነካውም ስጋውንና ደሙን ከሚቀበልበት ጊዜ በቀር ፊቱንና እግሩን አልታጠበም ። ❤ እናትና አባቱ በስድስት ዓመቷ ትተዋት የሞቱ እኅት ነበረችው ስሟም ማርያ ይባላል ዘመዶቿም ወደ አብርሃም አምጥተዋት ፈሪሀ እግዚአብሔር ሃያ ዓመት ሆናት ድረስ ትሕትናንም እያስተማራት በእርሱ ዘንድ አደገች። ❤ ከዚህም በኋላ ሰይጣን ቀንቶባት ከአንድ መነኩሴ ጋር አፋቀራት ድንግልናዋንም አጠፉች ልብሷንና አስኬማዋን ለውጣ ወደ ሌላ አገር ሔደች። አባ አብርሃምም በዚያች ሌሊት ታላቅ ከይሲ ርግቢቱን ሲውጣትና ጥቂት ቆይቶ ከእግሩ በታች ሲተፋት ራእይን አየ። በማግሥቱም ማርያ ከቦታዋ ታጣች አባ አብረሃምም ደነገጠ ወደ እግዚአብሔርም ከብዙ ዕንባ ጋር ጸለየ እርሷን ያገናኘው ዘንድ። ከጥቂት ወራትም በኋላ እኅቱ ያለችበትን አባ አብርሃም ሰማ ሰዎችም እንዳያውቁት የምንኵስናውን ልብስ ለውጦ ፊቱንም ተከናንቦ የወታደር ልብስ ለብሶ በፈረስ ተቀምጦ ወዳአለችበት አገር ሔደ ከዚያም ደርሶ ማርያ ወዳለችበት ገባ የመሸተኛንም ልብስ ለብሳ በአያት ጊዜ እጅግ አዘነ ነገር ግን እንዳትሸሸው እንድታውቀው አልሆነም። ❤ ከዚህም በኋላ ለሚያገለግላት አሽከር ከማርያ ጋር የሚደሰትበት መብልና መጠጥ እንዲያዘጋጅ የወርቅ ዲናር ሰጠው ለርካሽ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ይመስላት ዘንድ። ከራት በኋላም ወደ ውስጠኛው ቤት አስገባት በሩንም ዘጋ እጇንም ይዞ ራሱን ገለጠላት በአወቀችውም ጊዜ ደንግጣ እንደ በድን ሆነች "ልጄ ሆይ አይዞሽ ከእግዚአብሔር በቀር ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ የለም ነገር ግን ወደ ንስሐ ተመለሺ ወደቦታሽም ገብተሽ የቀድሞ ሥርዓትሽን ያዢ" አላት እርሷም እሺ አለች። ❤ በነጋም ጊዜም ወስዶ በፈረሱ አስቀመጣትና ደስ እያለው ተመለሰ እኅቱን ከሰይጣን እጅ ማርኳልና ወደቦታውም በደረሰ ጊዜ የቤቷን ደጅ ዘግቶላት ማቅ በመልበስ እየተጸጸተች የተጋድሎንም ሥራ እየተማረች በብርታቷና በተጋድሎዋ ያዩ ሁሉ እስቲአደንቁ ጸንታ ኖረች ። ❤ እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ ሰው እጆች ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ አጋንንትን በማስወጣት በሽተኞችን በማዳን ከአንዲት ዓመትም በኋላ የማርያን ንስሓዋን አይቶ በሰባ ዘመኑ የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ነሐሴ 5 ቀን ዐረፈ። ❤ ማርያ እኅቱም ከለቅሶ ጋር ትርኅምትን በማብዛት ቀንና ሌሊት እየተጋደለች ሌሎች አምስት ዓመታትን ኖረች ከዚያም በኋላ ዐረፈች ያዩዋትም በፊቷ ውስጥ ሰለአለው ብርሃን እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አብርሃም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ❤ ተጋዳይ ወታደር የሆነ ቅዱስ ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው እርሱም በከሀዲ በዑልያኖስ ሠራዊት ውስጥ ወታደር ሆነ። ንጉሡም ከባልንጀሮቹ ወታደሮች ጋራ ላከው የክርስቲያን ወገኖችንም በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዛቸው። ❤ እርሱም ለባልንጀሮች ጭፍሮች ክርስቲያኖችን እጅግ እንደሚጠላቸውና እንደሚጣላቸው ይገልጽላቸዋል በጭልታም ገብቶ በጎ ነገርን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል ያጽናናቸዋልም። ሁል ጊዜም ይጸልያል ይጾማል ይመጸውታልም የቅዱሳንንም አኗኗር ኖረ ምስጉን እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላምዐአረፈ። ለእርሱም ለጌታ ምስጋና ይሁን። የቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 5 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ። መዝ 17፥43-44። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 12-10-17፣ 1ኛ ዮሐ 5፥14-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 15፥1-13። የሚነበቡ ወንጌል 15፥1-11 የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።                                                   

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                ❤ #ነሐሴ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ከዳዊት_ዘር_ለሆነ ለአካዝ ልጅ ንስሃ በመግባቱ በእድሜ ላይ 15 ዓመት ለተጨመረለት #ለንጉሥ_ቅዱስ_ሕዝቅያስና እንደ በግ የጸጉር ልብስ ለብሶ በበረሃ ለሚኖር ሰማዕቱ #ቅዱስ_መርምኅናምን ላሳመነና እህቱን ሣራንም ከለምፅዋ ላነፃት ለአባታችን #አባ_ማቴዎስ_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ዳዊትና_ወንድሞቹና ከግብጽ ደቡብ ስንካር ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ #ከቅዱስ_ፊልጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                   ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_ንጉሥ_ሕዝቅያስ፦ ይህ ንጉሥ ከዳዊት ዘር የአካዝ ልጅ ነው። ከጻድቁ ንጉሥ ከዳዊት በኋላ እንደ ሕዝቅያስ ያለ በእስራኤል ውስጥ አልተሾመም ከዚህ ጻድቅ ንጉሥ በቀር ሁሉም ጣዖትን አምልከዋልና መሠዊያም ሠርተዋልና። ❤ እርሱም በነገሠ ጊዜ ጣዖታትን ሰበረ መሠዊያቸውንም አፈረሰ ከነሐስ የተሠራውንም እባብ ቆራረጠ የእስራኤል ልጆች አምልከውት ነበርና እግዚአብሔርም ዘመነ መንግሥቱን እጅግ አሳመለት በጎ ነገርንም ሁሉ ሰጠው። ❤ ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዘመን የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በዘመኑ እንደርሱ ያለ የሌለ ኃይለኛ ብርቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ የፈሩትና የታዘዙለት ነው። ሕዝቅያስም ከእርሱ ግርማ የተነሣ ፈርቶ አገሩን እንዳያጠፋ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ላከለት ሰናክሬምም ደስ ብሎት ምንም ምን አልተቀበለም በእርሱ ላይና በልዑል እግዚአብሔር ላይ ተቆጥቶ "እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ አይችልም " በማለት የስድብ ቃል ላከ እንጂ። ❤ ሁለተኛም በልዑል ስም ላይ ስድብና ቊጣ የተጻፈበትን ደብዳቤ ላከ ሕዝቅያስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ ለበሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ "አቤቱ የእስራኤል አምላክ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ አንተም ብቻህን ዓለም መንግሥታት ላይ ንጉሥ የሆንክ አንተም ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ልመናዬን አድምጥ። ዐይኖችህን ገልጠህ ተመልከት ሕያው እግዚአብሔር አንተን እያቃለለ ሰናክሬም የላከውን ቃሉን ስማ"። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም የተናገረውን እንዲነግሩትና ስለርሱና ስለ ሕዝቡ ይጸልይ ዘንድ ወደ ኢሳይያስ መልእክተኞችን ላከ። ኢሳይያስም ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልብህን አጽና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደርሱ ያለ ያልተማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ ሊሠራ እግዚአብሔር አለውና"። ❤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ የለኪሶም ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አገኙ የተረፉትም ከንጉሣቸው ጋራ ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ። ሰናክሬምም ሊጸልይ ወደ ጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ልጆቹ አድራማሌክና ሶርሶር በሰይፍ መትተው ገደሉት። ሕዝቅያስም ከሰናክሬም እጅ ድኖ የተመሰገነ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ❤ በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ ለሞትም ደረሰ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስም ወደርሱ መጥቶ "እግዚአብሔር እንዲህ አለ ትሞታለህ እንጂ አትድንም ቤትህን ሥራ" አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ እያመሰገነውም እንዲህ አለ "አቤቱ በቀና ልቡና በዕውነት ሥራ በፊትህ ጸንቼ እንደኖርኩ ፈቃድህንም እንደፈጸምሁ አስብ" ብሎ ሕዝቅያስ ፈጽሞ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰ። ❤ ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ዐፀድ ደረሰ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው "ሒደህ ለወገኖቼ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ያባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በለው። ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ እስከ ሦስት ቀንም ወደ እግዚአብሔር ቤት ትመጣለህ። በዘመኖችህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይቺንም አገር ስለ እኔና ስለ ባላሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ"። ❤ ሕዝቅያስም ኢሳይያስን እንዲህ አለው "እግዚአብሔር እንደሚያድነኝ እስከ ሦስት ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመውጣቴ ምልክት ምንድ ነው"። ኢሳይያስም እንዲህ አለው "የተናገረውን ቃል ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምልክቱ ይህ ነው አነሆ ጥላው ወደ ዐሥረኛው እርከን ይወርዳል። ወደ ዐሥረኛው እርከን ቢመለስ ምልክቱ ይህ ነው"። ሕዝያስም "እንዲህ አይደለም የጥላው ወደ ዐሥረኛ እርከ መመለስ ቀላል ነው። መመለስስ ከሆነ ፀሐይ ወደ ዐሥረኛው እርከን ይመለስ" አለ። ኢሳያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፀሐይም ዐሥሩን እርከን ተመለሰ። ❤ ሕዝቅያስንም የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና። በመንበረ መንግሥቱም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነግሦ ኖረ። እግዚአብሔርን አገልግሎ ነሐሴ 4 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በንጉሥ ቅዱስ ሕዝቅያስ በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን እንደ በግ የደጒር ልብስ ለብሶ በበረሃ የሚኖር #አባ_ማቴዎስ ዐረፈ። እርሱም መርኅናምን ያሳመነው ሣራንም ከለምፅዋ ያነፃት ነው። የአባ ማቴዎስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 4 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለሕዝቅያስ_ዘጸለየ_በሕቁ። ዘተወሰከ ዘመኑ ወፈድፈደ እምኊልቁ። እመኒ ሶቤሃ ተዐየርዋ ለድድቁ። በእደ መልአክ ሠራዊት ፋርስ ኀልቁ። ወለመልኮሙ ቀተልዎ ደቁ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_4።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኀ ይትኀሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"። መዝ 20፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 12፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 5፥6-12 እና የሐዋ ሥራ 17፥23-28። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 14፥31-35። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።