cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሞዐ ተዋሕዶ / Mo'aa Tawaahido / MOA Orthodox

ይህ ገጽ የቤተክርስቲያንን 7ቱን ጥያቄዎች ምላሽ ለማስገኘት መረጃና ውይይት የሚተላለፍበት ነው። የሞዐ ተዋሕዶ መወያያ:- @Defend_Orthodoxy_EOTC_Discussion የሞዐ ተዋሕዶ ቻናል፡ @Moa_Tewahido

Больше
108 761
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

👆🏾👆🏾👆🏾👆🏾 ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ከላይ የተለጠፈውን ዜና አድምጠን ለአፍታ ራሳችንን እንመርምር? ይህን መዕራፍ አንብበን ስንጨርስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንጠይቅ? የት እንደቆምን እናስብ። እኛ ክርስቲያኖች ነን ስንል ምን እንደሆንን፥ በምን አይነት የቤተ መንግሥትና የቤተከ ክህነት እረኞች እንደምንመራ እናስብ፥ ከላይ የሰማችሁትን ተማሪዎችን በአውቶብስ ጭኖ ወታደር ካፕም እሰገብቶ የሚደፍር የአብይ አህምድ አሊን ሠራዊት እናስብ፥ ሠራዊቱ የሠለጠነበትን መንገድ እናስብ፥ ሠራዊቱ ይህን አድርጎ በዚህ አገር መኖር መቻሉን በማሰብ ሕዝብ ምን አይነት ስነ ልቦና ውስጥ እንደሚገኝም እናስብ። በመጨረሻም በራሳችን ላይ ምን መሆን አንደሚገባን፥ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስን። ምርጫችን በዘላለም ሕይወትና በዘላለም ሞት መካከል ብቻ ነውና አስበን እንወስን!! ( ፩) በአሕዛብ ስንኳ የሌለ ዝሙት፥ አገር አንዲጠብቅ እረኛ በተባለ መንግሥት የራስን ልጅ አፍኖ በካፕም ውስጥ በቡድን መድፈር የፈቀደ ሕሊና፥ መንግሥታዊ ሥርዓት፥ ይሀን ተሸክሞ የሚኖር ሕዝብ ምን አይንእ የሞራል ደረጃ ላዑእ ነው? (፪) ይህንን ነውር የሚሠሩትን የማያስወግድ መንግሥት፥ ቤተ እምነት ምን አይነት ደረጃ ላይ ይገኛል? (፫) ይህን ድርጊት የማያወግዝና በዘምታ “እየተመካከርን ነው፥ በጥበብ ቤተ ክእስቲያንን እያሻገርን ነው፥ ሕንጻ እየሠራን ነው ወአተ” የሚሉ ጳጳሳትና መነኮሳት፥ ካህናትና የሰበካ ጉባዔ መሪዎች “እምነት” በመጽሐፍት የተጻፈልንና እንከተለዋለን የምንለው የሐዋርያት ቀዳሚት እምነት ናት? (፬) ጥቂት አርⶄ ሊጡን ያቦካዋልና አዲስ ሊጥ ሁኑ የተባለውን የጌታን ትምህርት ወዴት ጥለነው ነው በመላው አገሪቱ የሰፈነውን መንግሥታዊና ቤተክህነታዊ ሁለንተናዊ ሙስና (የሞራል ውድቀት፥ የቁስ ስስትና ሌብነት፥ ዝሙት፥ ዘረኝነት፥ ማኅበራዊ መፋረስ) አገሩ ሁሉ በአዛባዊ እርⶄ ሲቦካ እረኞች ተስማምተው የሚኖሩት? እኛም በዝምታ የተዋጥነው? (፭) በዓላቶቻችን በቅንነትና በእውነት ቂጣ የሚደረጉና በእርግጠኝነት ከአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አለመሆኑን ልናረጋግጥ እንችላለን? ወይስ እስከነ ሁለንተናዊ ሙስናችን በከበሮ፥ በያሬዳዊ ዜማ፥ በሞንታርቦ፥ በጧፍ ብርሃን፥ በአብለጭላጪ ልብስ ውስጥ የተሰወረ አሕዛባዊነት ነው? (፮)ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። ብሎ ቅዱሱ የመንፈስ ቅዱስ ማኅደር ቅዱስ ጳውሎስ ትዕዛዝ የተቀበልን እኛ አንዴት ከሴሰኛ ምንግሥትና ቤእምነት ጋር እንደዚህ ተባበርን? (፯) ከዚህ ዓለም ሳትወጡ የዓለምን ርኩሰትና ሴሰኝነት ተዋጉት፥ መስክሩበት (ቁጥር 10) ተብለን እንዴት ልጆቻችንን በጅምላ የሚደፈር የጦር ሠራዊት አሠልጥኖ የሚመራ የአብይ አህምድ አሊ አይነት በግብሩ ሰይጣንን የሚሰቀና ሰው አገራችንን አንዲመራ ፈቀድንለት? (፰) የውጨውስ አሕዛቢ ርኩሰት ከቁጥጥራችን ውጭ ሆኗል፥ በትምህርትና በተግሣጽ የማይመለስ መንግሥታዊ ሥርዓት ሆኗን፥ መፍትሔው በጦር መሣሪያና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ብቻ የሚወጡት ነው ብንል ስንኳ፥ የጥመቀት ልጆች በቤኣችንና በሠራዊቱ ውስጥ ሴት ደፋሪና ነፍ ገዳይ ሲሆኑ መናገርና መከላከል ለምን ተሳነን? ======================================================= ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥1 በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና። 2 እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። 3-4 እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ 5 መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው። 6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን? 7 እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ 8 ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም። 9 ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። 10 በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን፥ ወይም ገንዘብን የሚመኙትን ነጣቂዎችንም፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩትን አላልሁም፤ ይህስ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር። 11 አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። 12 በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? 13 በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።
Показать все...
👍 9
የአብይ አህምድ አሊ ሠራዊት ሴት ተማሪዎችን በአውቶብስ ጭኖ በካምፕ ውስጥ አስገድዶ ደፈራቸው አደረ!! በፀጥታ አመራሮች ልዩ ስብሰባ የቦምብ ፍንዳታ!ተማሪዎች በወታደራዊ ካምፕ ምን ተደረጉ!16 July 2024 https://youtube.com/watch?v=h0kACO5X2bw&si=UIfCLdRka7OMzUjl
Показать все...
በፀጥታ አመራሮች ልዩ ስብሰባ የቦምብ ፍንዳታ!ተማሪዎች በወታደራዊ ካምፕ ምን ተደረጉ!16 July 2024

በፀጥታ አመራሮች ልዩ ስብሰባ የቦምብ ፍንዳታ!/ተማሪዎች በወታደራዊ ካምፕ ምን ተደረጉ!?/ክምር ድንጋይ.! ደምቢያ.! ወልዲያ.! ቡሬ.! Ethio News_ኢትዮ ኒውስ ቻናል 2@ethionewschannel2 [email protected]

https://t.me/beletekassa

ጳጳሳትን ሳይቀር የዋጠው አዲሱ ክርስቲያኖች ያላስተዋሉት ኑፋቄ ኦርቶዶክሳዊነትና የፖለቲካው ትክክለኝነት ( ዘመናዊ ሥዝም ኑፋቄ ነው) ፋንታሁን ዋቄ ህዳር 2013 ኦርቶዶክሳዊነትና የሰይጣን መንግሥት ከሚለው መጽሐፍ መግቢያ ተወስዶ ተስፋፍቶ የተጻፈ ይህ ኑፋቄ ስነኳንስ ሕዝባዊውን ጳጳሳትን፥ መነኮሳትን፥ ካህናትን፥ የባህል መሪዎችን፥ ሙፍቲዎችንና ዑስታዞችን፥ ሰባኪያነ ወንጌል ሁሉ የበከለ የፍትሕ፥ የእውነት፥ የሰብአዊነትና የማኅበረሰብ አጠቃላይ አጥፊ ሆኖ ተከስቷል። የፖለቲካ መሪዎች፥ የሲቪልና የቢሮክራሲ ባለሚያዎች፥ በአንድ የሥራ ጽ/ቤት ውስጥ ያሉ ተዋረዳዊ ግኑኝነት ያላቸው ሠራተኞች ሳይቀር የሚነጋገሩት ፖለቲካዊ ትክክለኝነትን ታሳቢ አድርገው ነው። ሐሰትና እውነት፥ ፍትሕና ግፈኝነት፥ ሰብአዊነትና አራዊትነት፥ እኩል በዓለአገራዊነት፥ ክብረ-ሰብእ የመሳሰሉት ወሳኝ የመኖር ትርጉም መሠረታዊ እሤቶች ሁሉ ዋጋ አጥተዋል። በዚህ ጉዞ መእመናንና ዜጎችም በየበኩላቸው በተክርስቲያንን ትተው የሚያስደስቱትን ጳጳስ ቆሞስ፥ ዜገችም የአገራቸውንና የትውልድ ነገር ትተው በወቅቱ ሥልጣን ላይ ያሉትን ለማስደሰት ፖለቲካዊ ትክክለኝነታቸውን ጠብቀው የሚናገሩ፥ የሚያደርጉና ግኑኝነት የሚፈጥሩ ናቸው። ስለ እውነት፥ ስለ ፍትሕ፥ ስለ ክብረ-ሰብእ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያንና አገር፥ ስለ ሕዝብና መጭው ትውልድ ጥቅም የሚናገር የለም። አብዛኛው በፖለቲካዊ ትክክለኝነት እግዚአብሔርን ሳይቀር እንደሚገባ በአምልኮታቸውና በአርአያነት ሊመሰክሩ አልቻሉም። ፖለቲካዊ ትክክለኝት ሲገለጥ፦ የየዘመኑን ፖለቲካ (የየዘመኑ ፖለቲካ መሠረቱ በየዘመኑ የበላይነት የሚጎናጸፍ ነፅሮተ ዓለምና ፍልስፍና ነው) ለመምሰልና ለማስደሰት መናገር እና እግዚአብሔርን ለማስደሰት መኖር በአንድነት አይገኙም። ይጋጫሉ። እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚኖር ኦርቶዶክሳዊያን በእምነታቸው መኖር ከፈቀዱ ከሁሉቱ አንዱን መምረጥ የግድ ይላቸዋል። ፖለቲካዊ ትክክለኝነትና ኦርቶዶክሳዊ ክርስቶሳዊነት አብረው አይገኙም። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 👉🏿 https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com/2024/07/blog-post.html
Показать все...
Fantahun Wakie My daily reality ፋንታሁን ዋቄ የየዕለቱ እውነታዎቼ

Ethiopian, Orthodox, Fantahun

👍 45
Показать все...
የስብከተ ወንጌል ቀን ክብረ በዓል እና የተረሳው ስብከተ ወንጌል! ክፍል #1 ስብከተ ወንጌል እና መዋቅሩ

#ቀሲስ_ንዋይ_ካሳሁን #መር_ፋንታሁን_ዋቄ #ዲን_ሙሉጌታ_ኃይለማርያም #ዮሴፍ_ከተማ #ethiopia #ቤተክርስቲያን #ሲኖዶስ #eotc_one_holy_synod #ሻይ_ቡና #shay_buna #amhara #oromiya #ebc #tigray #somali #afar #fano #addisababaethiopia #amharic #abiyahmedali #ukraine #russia #amharicnews #shay #shorts #amharicmusic #yosef #getachewreda #sergegnawegoch #ሠርገኛ #ወጎች #ሰሎሞን #ሹምዬ #ethiopiannews #gurage #wolega #southafrica #europeanunion #europeanparliament #ofc #gebeyanu #usa #endf #አብይ #አህመድ #አሊ #solomon #shumiye #debretsion #addisababa #shay #buna #wolega #shorts #ola #shene #eritrea #War #invasionofukraine #nama #williamruto #joebiden #antonyblinken #jawarmohammed #mereragudina #demekemekonnen #ብልጽግና #ፓርቲ #prosperity #party #oromiya region #amhara region #wolkait #kenya #abelbirhanu #ebc #ebs #fetadaily #fanatv #artstv #ethioforumኢትዮፎረም #ኢትዮ_ቱንቢ #Ethio_Tunbi_Media

Показать все...
ከማግለል እስከ መወንጀል እና ጥቃቶች! ተጠናክሮ የቀጠለው የኦርቶዶክሳውያን ከሀገራዊ መድረኮች መገለል እና መዘዙ!

#ፋንታሁን_ዋቄ #ሙሉጌታ_ኃይለማርያም #አለማየሁ_ሙላት (ዶ/ር) #ዮሴፍ_ከተማ

"በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ነገረ የምንጠባበቅበት አይደለም።ሁላችንም በገባንና በቻልነው መጠን የየድርሻችንን የምንወጣበት ነወ። ኦርቶዶክሳዊ ሥራ ሱታፌያዊ ነው።ለሆነ አካል የምንሰጠው አይደለም ።የውክልና ክርስትና የለም።ብዙ ነገሮችን በውክልና ማሰራት እንፈልጋለን ፣ክርስትና የውክልና አይደለም ለሆነ አካል(ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ለመዋቅር) ሰጥተን የምንቀመጠው አይደለም።ቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ነው የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ ፣ቀኖናና ትውፊቷን ይቆጣጠራል።በዚህ ውስጥ ግን ሀይማኖቷን፣ሥርዓቷንና ምእመናኗን ለማስጠበቅ የሚሰሩ ስራዎች የተፈቀዱ ናቸው። ዐይናችንን መትከልና መከታተል ያለብን ህልውና፣ድል አድራጊነትና ትንሣኤያችን ላይ ነው።"
Показать все...
3.80 MB
👍 20
Показать все...
የኦፌኮ መንታ ምላስ፣ የጦርነት አዋጅና የሰላም ጥሪ

ትንታኔ

👍 1
👆👆👆መእመናን እጅግ እጅግ የምናለቅስበት ዘመን ላይ ነን። እልቂታችንና ስደታችን፣ ጥቃታችን ሁሉ ለእረኞቹ ምቾት ሆኗል። የኦርቶቶክስ ግልጽ ጠላት የሆነው የመንግሥት መሪ ትዕዛዝን እየተቀበሉ ምንምጰሳያቅማሙና ሳይፈሩ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ሥራ ነው ብለውናል። እኔስ እረኞቹ ክደውናል ብዬ ተከራክሬአለሁ:- https://youtu.be/ROZxWVOL3tg ክፍል 1 https://youtu.be/wP7uHZG5Hak ክፍል 2 https://youtu.be/wP7uHZG5Hak
Показать все...
፪ቱም እረኞች ክደውናል ማለ ትነው? ክፍል ፩ /ፋንታሁን ዋቄ / Fantahun Wakie

ቤተ መንግሥትና ቤተ እምነት ተባብረው የካዱት ዜጋና ምእመን ድርሻው ምንድነው?

👍 3
ሊቀ ጳጳሱ እንዴት እንዲህ አሉ ? // እውነቱ የቱ ጋር ነው? #ethiobeteseb https://youtube.com/watch?v=Bm4K1Pgr_F0&si=J2j6X3hsQZvZ_wHH
Показать все...
ሊቀ ጳጳሱ እንዴት እንዲህ አሉ ? // እውነቱ የቱ ጋር ነው? #ethiobeteseb

ሊቀ ጳጳሱ እንዴት እንዲህ አሉ ? እውነቱ የቱ ጋር ነው? #ethiobeteseb

👍 1
Показать все...
The Mystery of Millions of Missing Amharas: Where Have They Gone?

The Mystery of Millions of Missing Amharas: Where Have They Gone? Be a Member to our channal

https://www.youtube.com/channel/UCeO6Cwa_piOXYazOJwcEhfg/join

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.