cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ማህበረ ፍኖተ ሕይወት(Mahebere Finote Hiwot)

" ...እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፣ ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል፤ ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቀን ዋጋ ይወስዳል (ማቴ 10፤40-42) ” የሚለውን አምላካዊ ቃል መሰረት በማድረግ ማህበራችን መመስረት ቻለ፡፡ ለበለጠ መረጃ: @fmw1987, @ts121212, @Tsita8

Больше
Рекламные посты
399
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
Нет данных30 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
➯ ኢፍትሐዊነት ነገሥት አንቀጽ 24 ሀብታም ወንድ ድሃ ሴትን አላገባም አይበል፣ ሀብታም ሴትም ድሃ ወንድን አላገባም አትበል፤ ባዕል መለኮት ነዳይ ሥጋን ተዋሕዷልና፤ ልዑል መለኮት ትሑት ሥጋን ተዋሕዷልና፤ እንዲያውም ሀብታሙ ወንድ ድሃይቱን ሴት ቢያገባ ሀብታሚቱም ሴት ድሃውን ወንድ ብታገባ ትልቅ ክብር ያገኛሉ፤ የእጮኝነት መሠረቱ ጾታዊ ፍቅር ነው፤ ይህም በመፈላለግ ይገለጣል፤ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የመፈላለግ ስሜት ካለ ሁለቱ ለእጮኝነት መጠያየቅ ይችላሉ፤ ነገር ግን ፍላጎቱ የአንዱ አካል ብቻ ከሆነ እና አንደኛው የማይፈልግ ከሆነ የፈለግሁትን ካላገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ማስቸገር አይገባም፤ ጠይቆ እምቢ ከተባለ ያው ኃፍረቱን ተከናንቦ ሌላ ይፈልግና ይጠይቅ፤ ምንስ ቢሆን እርሱ እየወደዳት እርሷ ባትወደው ወይም እርሷ እየወደደችው እርሱ ባይወዳት ከማትወደው/ከማይወዳት ሰው ጋር ለምን ለመኖር ይመኛል፤ አገባብስ እርሷም እርሱም ተዋደው ሲጋቡ ነው፤ አንድ ጊዜ አንዱ ጓደኛየ አንዷን ልጅ ፈለገና ሂዶ ጠየቃት ከዚያ እምቢ አለችው። ➯ ከዚያ ወረብ ሲያጠና "ኀዲጎ ብእሲቶ (ሚስቱን ትቶ)" የሚለውን ወረብ ደጋግሞ ይወርብ ጀመር መምህራችን ልጅቱ እምቢ እንዳለችው ሰምተው ኖሯል በቃ እሱኛውን ወረብ በትክክል ብለኽዋል ወደቀጣዩ እለፍ አሉት፤ አንድን ወረብ አጥንተህ በደንብ ከያዝከው ከዚያ ቀጣዩን ወረብ ታጠናለህ፤ የየኔታ ንግግር በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የመጀመሪያው ወረቡን ብለኽዋል ወደ ቀጣዩ እለፍ ማለታቸው ነው ሁለተኛው ደግሞ በቃ የመጀመሪያ ጥያቄህን ያቀረብክላት ልጅ እምቢ ካለች ወደቀጣዩ እለፍ ማለት እርሷን ትተህ ሌላ ፈልግ ማለታቸው ነበር፤ ሀብታም ወንድ ሀብታሟን ሴት ድሃ ወንድ  ድሃዋን ሴትም ማግባትም ይችላል፤ ሌላው በእጮኝነት ጊዜ በሐሳብ ያለመስማማት ነገር ካለ ቢለያዩ ኃጢኣት አይሆንም፤ ከተጋቡ በኋላ ግን መለያየት አይቻልም፤ የእጮኝነት ጊዜ ለየብቻቸው ነው መኖር ያለባቸው፤ እጮኛሞች እስካልተጋቡ ድረስ በአንድ ላይ መተኛት በአንድ ላይ ማደር አይገባቸውም።   ➯ አንድ ወንድ አንዲት ሴትን ለማግባት ወይም አንድ ሴት አንድን ወንድ ለማግባት የግድ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች አሉ፤ ከእነዚህም አንዱና ዋናው ሃይማኖት ነው ሴቶች በሃይማኖት የማይመስላችሁን ወንድ አታግቡ፤ ወንዶችም እንዲሁ በሃይማኖት የማትመስላችሁን ሴት አታግቡ፤ ታድያ እንዲህ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ✍️ "ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሷል። ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች" ይላልሳ ምን ማለት ነው? ካልከኝ። 📖1ኛ ቆሮ 7፥14 ➯ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተነገረበትን ምክንያት ማወቅ ሀሳቡን በትክክል እንድንረዳው ያደርገናል፤ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ያለው አሕዛብን አስተምሮ ወደ ክርስትና ሲመልስ ሚስት ክርስቲያን ትሆንና ባል ሳይሆን ይቀራል፤ ባል ክርስቲያን ይሆንና ሚስት ሳትሆን ትቀራለች፤ በዚህ ምክንያት ጠብ እንዳይነሳ ባል ክርስቲያን ከሆነ በጊዜ ሂደት አስተምሮ ክርስቲያን ያደርጋታል በማለት ይህንን ተናገረ፤ ይህንንም የሚያስረዳን ቁጥር 13 ላይ "ሴቲቱም የማያምንና ሚስቲቱን የሚያፈቅር  ከእርሷም ጋር ሊኖር የሚወድ ባል ቢኖራት ባሏን አትፍታ" ይላል፤ የሚያፈቅራት ብሎ የገለጠው የሚወዳት ከሆነ ለእርሷ ሲል ትንሽ ቆይቶ እንደ እርሷ ሃይማኖት ይሆናልና እንዲህ አለ፤ ነገር ግን ተምሮም ተነግሮም ወደ ትክክለኛዋ ሃይማኖት ካልመጣ ልትፈታው እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚሁ ምእራፍ ቁጥር 15 ላይ "የማያምን ግን ቢፈታ ይፍታ" ብሎ ነግሮናል፤ ይህንን መነሻ አድርገው 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በፍትሐ ነገሥታቸው ክርስቲያን ክርስቲያንን ብቻ እንዲያገባ ሥርዐት ሠርተዋል። ➯ ስለዚህ አሁን ላይ አስተምረህ ወደ ሃይማኖት ከመለስክ በኋላ አጭተህ ማግባት ትችላለህ እንጂ ገና ወደ ትክክለኛዋ ሃይማኖት ሳትመጣ እያለች እርሷን አግብቼ ወደ እኔ ሃይማኖት እመልሳታለሁ ግን አትበል፤ ሥለዚህ ባልና ሚስት በሃይማኖት አንድ የሆኑ መሆን አለባቸው፤ በሃይማኖት አንድ ሆነው ከተጋቡ በኋላ ከሁለት አንዱ ሃይማኖቱን ቢቀይርሳ እንዴት ይሆናል የሚል ጥያቄ ከጠየቅከኝ ደግሞ መልሱ "ይፋቱ" ነው፤ ምክንያቱም ✍️ "ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም" ይላልና ነው። 📖ማቴ 10፥37 ➯ ከዚህ ጥቅስ በታች ቁጥር 34 ላይ "ሰይፍን እንጂ ሰላም ለማምጣት አልመጣሁም" ብሏል፤ የዚህ ትርጉሙ በሃይማኖት ምክንያት እናትና አባት ባልና ሚስት ወላጅና ልጅ ቢለያዩ የሚገባ መለያየት መሆኑን ነው፤ ሰይፍ የተባለውም ይህ ነው። ➯ ከዚህ ላይ "ሰላም" ለማምጣት አልማጣሁም ያለው "አንተም በሃይማኖትህ አንቺም በሃይማኖትሽ ተባብለው በአንድ ተስማምቶ መኖርን ነው ሰላም ያለው" ይህ ሰላም ክርስቲያናዊ ሰላም አይደለም፤ ክርስቲያናዊው ሰላም ከክርስቶስ ጋር በመኖር በክርስቶሳዊ ሕይወት በመኖር የሚመጣ ሰላም ነው፤ ይህኛውን ሰላም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐ.14፣27 "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" ብሎናል፤ ስለዚህ በሃይማኖት የማይመስለንን ሰው ማጨት ማግባት አይገባም፤ከተጋባን፤ በኋላ ሃይማኖቱን ቢለውጥ እንኳ መፋታት ይገባል ማለት ነው። ይቀጥላል ........ 📌  አዘጋጅ ®  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ  ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ   ✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች" 📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                             ይቆየን 🕹 ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ፤ የተሳተውን፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ቸሩ መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ያድለን፤ በፀሎታቹ አስቡኝ አትርሱኝ የተለያየ ጽሁፍ ያላቹ፣ መተረክ እንችላለን የምትሉ እና ካርድ በመግዛት ቻናሉንና ግሩፑን በተለያየ አገልግሎት ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። 📩Coment  📥  @Yebiruk ───────────                     Channel  🧲  https://telegram.me/Tewahedo12                     Group 🧲  https://telegram.me/OrtodoxTewahedo12       Facebook Like Page (የፌስቡክ ፔጅ) 🧲   http://facebook.com/Tewahedo12 YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ) 🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw  ───────────
440Loading...
02
➯ ከዚያ በታች ግን ማግባትም ማጋባትም አይቻልም፤ ወንዱም በምቾት ያደገ በአካል የጠነከረ ከሆነ በ18 ዓመቱ ማግባት ይችላል። ከዚያ በታች ግን አይቻልም፤ ወንዱ ወይም ሴቷ በቤተሰብ ሥር የሚተዳደሩ ከሆነ በቤተሰብ ፈቃድ ያጫሉ፤ ነገር ግን ራሳቸውን የቻሉ በአካል የጠነከሩ ከሆኑና በኑሮም በቤተሰቦቻቸው ጥገኛ ያልሆኑ ከሆነ ራሳቸው መርጠው ራሳቸው አጭተው ሽማግሌ አስልከው መጋባት ይችላሉ፤ የእድሜ ጉዳይ መነሻውን ተናገርኩ እንጂ ከዚያ በላይ ከሆኑ ፈቅደው ተፈቃቅደው መጋባት ይችላሉ፤ በእድሜ ወንዱ ሊበልጥ ይችላል፤ ሴቷም ልትበልጥ ትችላለች፤ ነገር ግን እድሜያቸው ተቀራራቢ ቢሆን ይመረጣል። ➯ ይኽውም መረዳዳት የሚለውን በሀሳብም ለመረዳዳት የእድሜ መቀራረብ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፤ ዙሮ ዙሮ ግን በፍትሐ ነገሥቱ እንደምናየው የሴቷ አነስ ቢል የተሻለ ነው፤ ሴት 65 ዓመት ከሆናት በኋላ ማግባት አይገባትም። ➯ ሌላው በእጮኝነት ጊዜ ወደፊት ምን ሠርተው እንዴት ሠርተው ራሳቸውን እንደሚያኖሩ ማሰብ መወያየት ይገባል፤ ሌላው ነገር ደግሞ ለእጮኝነት ለመጠየቅ ሴትም ወንድን መጠየቅ ትችላለች፤ ወንድም ሴትን መጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ከተጠያየቁ በኋላ ሽማግሌ ወደ ቤተሰብ የሚልክ ወንዱ ነው፤ ወንዱ ወደ ሴቷ ቤተሰቦች ነው እንጂ ሴት ወደ ወንድ ቤተሰብ ሽማግሌ ልካ "ላገባው ነው" ማለት አይገባትም፤ ከእጮኝነት በኋላ ጥሎሽ ወይም ማጫ የሚሰጥ ደግሞ ወንድ ነው፤ ይኽውም ለአዳም መላእክት ወርቅ እጣን እና ከርቤ አምጥተው ሰጥተውታል፤ አዳምም ለሔዋን ማጫ አድርጎ ሰጥቷታልና የዚያ ምሳሌ ነው። ➯ የልጆቻችንን ከርስ ብቻ የምንሞላ ከሆንን እያሳደግን ያለነው ሮሆቦት እንጂ ሰው አይደለም፤ ከሮሆቦት የተሻሉ ልጆችን ማሳደግ ከፈለግን የተፈጠሩበትን ዓላማ እንዲያውቁ በስነልቡና ጠንካራ እንዲሆኑ በስነ ምግባር የታነጹ ልጆች እንዲኖሩን ከፈለግን ከልጅነታቸው ጀምረን ነገረ እግዚአብሔርን ሃይማኖትን ልናሳውቃቸው ይገባል፤ እኛ ሆዳቸውን ልብሳቸውን ብቻ እየቻልን አእምሯቸውን ግን በሌላ ሰው ሌላ ትምህርት ካስያዝነው እንደ ስልክ እኛ ቻርጅ እናደርጋለን ሶፍት ዌሩን ሌላ ባዕድ ይሞላዋል ማለት ነው፤ ሲጀምር ቤተክርስቲያን አንድን ልጅ አንዱ ክርስትና እንዲያነሳው ሥርዐት የሠራች የሃይማኖትን ትምህርት ጠንቅቆ እንዲያስተምረው ነው፤ አሁን አሁን ግን ይህ የለም፤ ነገር ግን የትዳር ዋናው ዓላማ የእግዚአብሔርን አምሳል የሆነ ልጅን ማስገኘት ነው። ➯ ስለዚህ ልጆቻችን በመሰረታዊነት ከምግበ ሥጋም ከልብሰ ሥጋም በተጨማሪ የሚያስፈልጋቸው ምግበ ነፍስ ነው፤ ስለዚህ በልጅነታቸው ቤተክርስቲያን እየወሰድን እናቆርባቸዋለን አበ እመ ማለት ሲጀምሩ ደግሞ በቃለ እግዚአብሔር አፋቸውን እናስፈታቸዋለን፤ እንግዲህ በትዳር አማካኝነት ባልና ሚስት የእግዚአብሔር አምሳል የተባለውን ሰው ያስገኛሉ፤ ይህም ትልቅ በረከት ነው። ✍️"...ልጆች ሆይ አብን አውቃችኋላና እጽፍላችኋለሁ" ተብሏል። ሃይማኖትን ማሳወቅ ይገባል። 📖1ኛ ዮሐ 2፥13
360Loading...
03
💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን   ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 ክፍል ሁለት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥               ስለ እጮኝነት......         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  ካለፈው ሳምንት የቀጠለ... 📌 ሌላው ወደ እጮኝነት ከመግባታችን በፊት ለእጮኝነት ያሰብናት ሴት/ወንድ ከአራቱ ዝምድናዎች ውስጥ የሌለች/ለ መሆኑን መረዳት አለብን፤ አራቱ ዝምድናዎች የተባሉም። 1) መንፈሳዊ ዝምድና 2) የአሳዳጊ አባትና እናት ዘመዶች 3) የሥጋ ዝምድና 4) የጋብቻ ዝምድና ➯ የምታጫት ሴት ወይም የምታጪው ወንድ ከእነዚህ ዝምድናዎች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24ን ይመልከቱ። ➯ የሥጋ ዝምድና ማለት የእናትህ እና የአባትህ ዘመዶችን ሁሉ ማግባት አይገባም፤ ይህም ማለት አክስት፣ አጎት አያት ቅድመ አየት እያለ ይቀጥላል፤ ይህም ዝምድና እስከ ሰባት ትውልድ ቀጥሎ በስምንተኛው መጋባት ይቻላል፤ ይህም ማለት ለምሳሌ አንተ እስከ ሰባተኛ የልጅ ልጅ ብታይና ወንድምህም እስከ ሰባተኛ የልጅ ልጅ ቢያይ የመጨረሻው ሰባተኛው የልጅ ልጅህና የወንድምህ ሰባተኛው የልጅ ልጅ መጋባት አይችሉም፤ በስምንተኛው ግን መጋባት ይቻላል ማለት ነው። የሰባት ትውልድ አቆጣጠሩ፦ 1) አንተ ወይም አንቺ 2) እናትህ ወይም አባትህ 3) የእናትህ እናት እና አባት     የአባትህ እናት እና አባት 4) የእናትህ እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት እናትና አባት 5) የእናትህ እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት እናት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት እናትና አባት 6) የእናትህ እናት አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ እናት አባት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ አባት እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ እናት አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት እናት እናት አባትና እናት     የአባትህ እናት እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት አባት እናትና አባት 7) ወንድ ከሆንክ የምታገባት ሴት፣ ሴት ከሆንሽ ደግሞ የምታገቢው ወንድ ትውልዳችሁ ሲቆጠር በሰባቱ ትውልዶች በየትኛውም አቅጣጫ ማለቴ በእናትህ እናት እናት፣ ወይም ባጭሩ ከላይ በጠቀስናቸው ዝርዝሮች ውስጥ እስከ ሰባት ባለው ተመሳሳይ አያት ሊኖራችሁ አይገባም፤ እህት ወንድም፣ አክስት አጎት ወዘተ በላይኛው ይቆጠራል። 🔘 ለምሳሌ ➯ የአጎትህን ልጅ የማታገባበት ምክንያት ስትቆጠር አንድ አንተ አለህ፤ ከዚያ በሁለተኛ አባትህ ወይም እናትህ አሉ፤ ከዚያ በሦስተኛ የእናትህ እናትና አባት ወይም የአባትህ እናት እና አባት አሉ፤ በሦስተኛው አያታችሁ ስለምትገናኙ መጋባት አይቻልም፤ በእንደዚህ ዓይነት አቆጣጠር እስከ ሰባት ባለው በሆነ አያት ወይም ቅድመ አያት የምትገናኙ ከሆነ የሥጋ ዝምድና ስላላችሁ መተጫጨት መጋባት አይገባም። ➯ የክርስትና አባት ወይም እናት ዝምድና ያልነው ደግሞ መንፈሳዊ ዝምድና ይባላል፤ መንፈሳዊ ዝምድና የሚባለው ደግሞ አንተን ክርስትና ያነሳህ ሰውየ ሥጋዊ ዘመዶቹ ሁሉ በመንፈሳዊ ዝምድና የአንተ ዘመዶች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የክርስትና አባትህን ዘመዶች በሙሉ ማግባት አይቻልም ማለት ነው፤ የአሳዳጊ እናት ወይም አባት ዝምድና የተባለው ደግሞ አሳዳጊህ እንደ አባት ወይም እናት ስለሆኑ የአሳዳጊህ ዘመዶች በሙሉ በሥጋ ባይዘመዱህ እንኳ ዘመዶችህ ይሆናሉና ከዚያ አትጋባ ማለት ነው። ➯ የጋብቻ ዝምድና የሚባለው ደግሞ አንተና ሚስትህ በዝሙት ምክንያት ብትፋቱ እና እንደገና ሌላ ሚስት ለማግባት ብትፈልግ በሦስቱም ዝምድናዎች በኩል የሚስትህ ዘመድ ያልሆነች መሆን አለባት ማለት ነው፤ በንሥሓ አባት አንድ የሆኑ ልጆች ከላይ በጠቀስናቸው ዝምድናዎች ካልተዛመዱ በስተቀር መጋባት ይችላሉ፤ ይህ በሐዲስ ኪዳን በፍትሐ ነገሥት የቀረበው ዝምድና ነው፤ የመንፈሳዊ ዝምድና እስከም የለው ብዙ ነው ካለ በኋላ አንድም እንደሥጋዊው ዝምድና እስከ ሰባት ነው ተብሎ ታትቷል፤ ይህም ቤተክርስቲያን ሰውን ለማዛመድ የሄደችበት ርቀት እጹብ እጹብ ብለን እንድናደንቅ ያደርገናል። ➯ የእንጀራ እናትህን/አባትህን ልጅ ምንም እንኳ በእናትም በአባትም ባትገናኙም ማግባት አትችልም፤ ምክንያቱም የጋብቻ ዝምድና ይፈርሳልና ነው፤ በእጮኝነት ጊዜ ሌላው ትልቁ ጉዳይ የእድሜ ጉዳይ ነው፤ ፍትሐ ነገሥት ሴት 12/15 ዓመት ሳይሞላት ወንድ 18/22 ዓመት ሳይሞላው ማግባት አይገባውም ይላል፤ እጮኛ ልያዝ ቢል እንኳ እድሜው ከዚህ ዓመት በታች ከሆነ በቤተሰቡ ፈቃድ እንጂ እርሱ ራሱ መርጦ ማጨት አይችልም፤ ነገር ግን ይላል ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24 ሴቲቱ በምቾት አድጋ በአካል የጠነከረች ከሆነ ቢያንስ በ12 ዓመቷ ታግባ ይላል።
310Loading...
04
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-13-2
330Loading...
05
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-13
450Loading...
06
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን   ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 ክፍል ሁለት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥         ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ሕይወት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  📌 ድንግልናና ቅዱስ ጋብቻ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ 📌 የድንግልና ሕይወት ትርጉምና ዓላማ ❖ ድንግልና ክብረ ሥጋን ፣ ማሕተመ ሥጋንና ማሕተመ ሕሊናን ጠብቆ ከዓለም ርቆ ለመኖር መወሰን ፣ መለየት ፣ መጠበቅ ፣ መጠንቀቅ በሚል ትርጉም ይጠቃለላል፡፡ ❖ የቋንቋው ትርጉም ይህን ይመስላል ሲባልም ፣ ገላጭ ማረጋገጫው ማኅተሙና ምስክሩ የዓላማ ጽናት ነው፡፡ ❖ የድንግልና ሕይወት ትክክለኛ ትርጉም አገኘ የሚባለው ፣ በድንግልና ሕይወት ጸንቶ ለመኖር የወሰነ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ለድንጋሌ ሥጋ መሠረት የሆነውን ድንጋሌ ሕሊናን በጽኑ ዓለት ላይ የመሠረተ መሆኑን እርግጠኛ ሲሆን ነው፡፡ ❖ ድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ሕሊና ልቡና ላይ ከተመሠረተ ፣ ነፋሳት ቢገፉት አይናወፅም ፤ መንገድ ቢረዝምበት ይዘልቃል እንጂ ጉዞው አይሰናከልም፡፡ ❖ የድንጋሌ ሥጋ መሪው ፊት አውራሪው ድንጋሌ ሕሊና ከሆነ ፣ የንጽሐ ሥጋ ልጓሙና ማሕተሙ ንጽሐ ሕሊና ንጽሐ ልቡና መሆኑ ከታወቀ የማሕተመ ሥጋ አዛዡ ናዛዡ ማሕተመ ሕሊና እንደሆነ ከተረጋገጠ የድንግልና ሕይወት ካለምንም ጥርጥር የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ ❖ የድንግልና ሕይወት ዓላማ ለሞት ለኃጢአት ከመገዛት ርቆ ፤ ኅልፈት በማያገኛት ሕይወት አሳርፋ ለማኖር ተዘጋጅታ ያለች የመንግሥተ ሰማይን ርስትን ገንዘብ ለማድረግ ነው፤ መቼም ስለድንግልና ሕይወት ሲነገር የብዙ ደናግላን የቅድስና ሕይወት ማሰብና ማስታወስ ይቻል ይሆናል ፤ ይሁን እንጂ በማንኛውም ክርስቲያን አእምሮ ቀድሞ የሚቀረፀው የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የድንግልና ሕይወት ነው፤ ምክንያቱም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፈጣሪዋን መውለድዋ ፣ ወላዲተ አምላክ ፣ እመ አምላክ ፣ ወላዲተ ቃል ለመባል መብቃትዋ በድንጋሌ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ፣ ድንጋሌ ሥጋን ከድንጋሌ ሕሊና ፤ ንጽሐ ሥጋን ከንጽሐ ልቡና በፍጹምነት አስተባብራ መገኘትዋ ነው፡፡ ❖ ፈጣሪዋን ለድኅነተ ዓለም የወለደች ድንግል ማርያም ቅድመ ወሊድ ድንግል ፤ ጊዜ ወሊድ ድንግል ፤ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናት፤ ድንግል ፍጽምት፥ ድንግል ወእም ያሰኛትም ይኸው ነው፤ ድንግልናዋ ሕፀፅ የሌለበት በመሆኑ ምክሐ ደናግል "የደናግል መመኪያ" ትባላለች፡፡ ❖ ድንግልናዋ ድንጋሌ ሥጋን ከድንጋሌ ሕሊና ያስተባበረ ፍጹም በመሆኑ ድንግል በክልኤ (በ፪ኤ) ትባላለች፡፡ 📖 ኢሳ 7፥24 ፤ 📖 ሉቃ 1፥34-35 📖 ማቴ 1፥18-23 ❖ ድንጋሌ ሕሊናን በፍጹምነት ቢመለከቱት ከባድና ፈታኝ ነው ፤ ሰማያውያን መላእክትን ጭምር የተፈታተነ ሕይወት ነው ፤ ድንጋሌ ሕሊና ዓላማውን ስቶ ፈሩን ለቅቆ ግንቡ ከፈረሰ የድንግልና ሕይወት ከሥር መሠረቱ ይናጋል ፤ መንፈሳዊ ሕይወት ይበላሻል፡፡ ❖ ቅድስና ትርጉም ያጣል ፤ በድንግልና ስም የሚደረገው ጥረት ሁሉ ውጤቱና ትርፉ ከንቱ ልፋት ብቻ ይሆናል፤ አዳምን ከክብሩ ያዋረደ ፤ እግዚአብሔርን ከመሰለ ጌታ ርቆ ገነትን የመሰለች ርስት ተነጥቆ ለግብራተ ዲያብሎስ የዳረገ የድንጋሌ ሕሊና ህፀፅ ነው፡፡ ❖ ቅሩበ እግዚአብሔር ፥ አኃዜ መንጦላዕት ይባል የነበረው ዲያብሎስ ፈጣሪውን ያስካደው፥ ከክብሩ ያዋረደው ፥ ወደ ባሕረ እሳት ያስጣለው "ያስወረወረው" የድንጋሌ ሕሊና ድቀት ነው፡፡ ✍️ "አኅለዮ ለአዳም አምላክና" ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ 📖 3ኛ መቃ 2፥10-17 🔔 ንስሀ ግን የወደቁትን ታነሳለች ቀማኛውን መጽዋች፣ ዘማዊውንም ድንግል ታደርጋለች ይቀጥላል ........ 📌  አዘጋጅ ®  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ 📌ምነጭ ✍️በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ 📚ሕይወተ ወራዙት ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ   ✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች" 📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                             ይቆየን
410Loading...
07
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-07
580Loading...
08
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-07-2
720Loading...
09
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-07-3
930Loading...
10
https://telegra.ph/ዳግም-ትንሣኤ-04-26
1000Loading...
11
ሰላም ውድ የማህበረ ፍኖተ ሕይወት አባላት እንደምን ሰነበታችሁ ወርሃዊ ጉባኤያችን እሁድ 04/09/2016 ዓ•ም ነው። ስለሆነም ሁላችንም በተለመደው ቦታ (ሰንበቴ ቤቱ) እና በተለመደው ሰዓት (6:00) ሌሎች እህት ወንድሞችንም ጭምር በመጋበዝ እንድንገኝ ይሁን። ጉባኤ ስትመጡ ቢያንስ ሌላ አንድ ሰው ይዛችሁ መምጣትን አትርሱ። የእግዚአብሔር ሰላም አይለየን፡፡ አሜን!
1250Loading...
12
https://telegra.ph/ሚስት-እንዴት-እንምረጥ-ትምህርተ-ጋብቻ-12-26
1230Loading...
13
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ግንቦት-05-07-6
1230Loading...
14
https://telegra.ph/የአምላክን-እናት-ልደት-ልደታ-ለማርያም-05-09
1150Loading...
15
https://telegra.ph/ቅዱስ-አልዓዛር-04-22
1100Loading...
16
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-29-8
1070Loading...
17
https://telegra.ph/ኦርቶዶክሳዊ-የጾታ-ትምህርት-12-27
1270Loading...
18
https://telegra.ph/እለተ-ቶማስ-ወይም-አብርሃም-04-21
1010Loading...
19
        ❖ ዋናው ምሥጢር ግን እነዚህ 50 ዕለታት የአዝማነ መንግሥተ ሰማያት (የሰማያዊው ዕረፍት) ምሳሌዎች ናቸው:: ❖ ስለዚህ በእነዚህ ቀናት መጾም መስገድ "መንግስተ ሰማያት ውስጥ ከገቡ በኋላ ድካም መውጣት መውረድ አለ" ያሰኛልና ነው:: ❖ በዚያውም ላይ "ኢታጹርዎሙ ጾረ ክቡደ (ከባድ ሸክም አታሸክሙ)" የተባለ ትእዛዝ አለና ቅዱሳን አበው በጾም የተጐዳ ሰውነት ካልጠገነ ወጥቶ ወርዶ ሠርቶ መብላት ይቸግረዋልና ሰውነታችን እንዲጠገን ይህንን በፈሊጥ ሠርተዋል:: ✍"ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ፤ ወሠራዔ መብልዕ በዸንጠኮስቴ" እያልን አበውን እናከብራለን:: 📚(አርኬ) ❖ ስለዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም : ስግደት ንስሐ ሐዘን ልቅሶ . . . የለም፤ አይፈቀድምም፤ ግን ይህንን ተከትሎ ሃምሳውን ቀን ሙሉ ሆድ እስኪተረተር ከበላን ጉዳቱ ሥጋዊም መንፈሳዊም ይሆናል። ❖"አበው እንደነገሩን "እንደ ልባችሁ ብሉ" ሳይሆን የተባለው "ጦም አትዋሉ" ነው:: 🔘ምሳሌ ❖ በልቶ ጠጥቶ ከሚመጣ ኃጢአት ክፋትና ፈተና ለመጠበቅ ሃምሳውን ቀናት ጥሬ የሚበሉ አሉ። ❖ ጠዋት ተመግበው ከ24 ሰዓት በሁዋላ ጠዋት የሚመገቡ አሉ። ❖ መጥነው ጥቂት በልተው አምላካቸውን የሚያመሰግኑ አሉ:: ❖ ነዳያንን አጥግበው እነርሱ ከነዳያን ትራፊ የሚቀምሱ አሉ:: ❖ እኛም ከእነዚህ መካከል የሚስማማንን መርጠን ልንከውን በተለይ ደግሞ በጸሎት ልንተጋ ይገባል:: ❖ አልያ ብሉ ተብሏል ብለን ያለ ቅጥ ብንበላ ብንጠጣ እኛው ራሳችን የሰይጣን ራት መሆናችን ነውና ልብ እንበል፤ ማስተዋልንም ገንዘብ እናድርግ፤ አምላከ ቅዱሳን ማስተዋሉን ያድለን:: ✍"እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ፤ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፤ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው፤ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፤ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም" 📖ሮሜ 8፥5 ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 ✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ ➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ" ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን 
1051Loading...
20
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል" 📖1ኛ ቆሮ 15÷20 ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ፤ ፍሥሐ ወሰላም።        ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ ለምን በበዓለ ሃምሳ ንስሐ መግባት ይከለከላል ለሚለው መልስ        ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥ ✍ #ከእናተው #ለተጠየቀው #ጥያቄ #የተሰጠ #መልስ #እነሆ ❓በበዓለ ሃምሳ ንስሐ ለምን ተከለከለ ❖ በቅድስት ቤተክርስቲያን ያለበቂ ምክንያት የሚደረግ ያለ ምሥጢርም የሚከወን ምንም ነገር የለም:: ❖ የሃይማኖትን ትምህርት አብዝተን በተማርን ቁጥር የምናውቀው አለማወቃችን ነውና ምንም ያህል ብንማር የአዋቂነት መንፈስም ቢሰማን ከመጠየቅ ወደ ጐን አንበል፤ መጠየቅ ለበጐ እስከሆነ ድረስ ሁሌም መልካም ነው፤ ግን ልብን እያጣመሙ ቢያደርጉት ደግሞ ገደል ይከታል:: ❖ ወደ ጉዳዬ ልመለስና ሁሌ የሚገርመኝ የትውልዱ አመለካከት ነው:: ❖ ጾም ሲመጣ "ለምን . . . አልበዛም? . . ." ዓይነት ቅሬታዎች ይበዛሉ፤ በዓለ ሃምሳ ሲመጣ ደግሞ "እንዴት ይህን ያህል ቀን ይበላል . . ." ባዩ ይከተላል:: ❖ ቤተክርስቲያን ግን ሁሉን የምትለን ለጉዳይ ለምክንያትና ለእኛ ጥቅም ነው::  🔘ለምሳሌ ❖ በዓለ ሃምሳ ድንገት እንደ እንግዳ ደርሶ እንደ ውሃ ፈሶ የመጣ ሥርዓት አይደለም፤ ይልቁኑ ምሳሌ ተመስሎለት በብሉይ ኪዳንም ሲከወን የነበረ እንጂ:: ❖ እንደሚታወቀው እስራኤል ከግብጽ ባርነት በ9 መቅሰፍት በ10ኛ ሞተ በኩር ወጥተው በ11ኛ ስጥመተ ባህር ጠላት ጠፍቶላቸው ወደ ምድረ ርስት ተጉዘዋል:: ❖ ቅዱስና የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከእግዚአብሔር እየተቀበለ ብዙ ሥርዓቶችን ለቤተ እስራኤል አስተምሯል:: ❖ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ ለሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ድኅነት ጥላና ምሳሌዎችም ነበሩ፤ በኦሪት ዘሌዋውያን ላይ ጌታ እንዲህ ይላል ✍". . . ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቁጠሩ፤ እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ ሃምሳ ቀን ቁጠሩ፤ አዲሱንም የእህል ቁርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ"  📖ዘሌ 23፥15 ❖ ይህም "በዓለ ሰዊት (የእሸት በዓል)" የሚባል ሲሆን ከፋሲካ 7 ሱባኤ (49 ቀን) ተቆጥሮ በሰንበት (ቅዳሜ) ማግስት (እሑድ ቀን) በዓለ ሃምሳ ይውላል፤ በዓሉ በግሪክኛው "ዸንጠቆስቴ (Pentecost)" ይባላል፤ "በዓለ ሃምሳ" እንደ ማለት ነው:: ❖ ለዚያም ነው ቅዱስ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በዚህ ቀን መሰጠትን ሊነግረን ሲጀምር "ወአመ ተፈጸመ መዋዕለ ዸንጠኮስቴ . . ." የሚለው::  📖ሐዋ 2፦1 ❖ በዓለ ሃምሳ (50ው ቀናት) በብሉይ "የእሸት በዓል" ቢባሉም ለሐዲስ ኪዳን ግን "የሰዊት (እሸት) መንፈሳዊ" ዕለታት ናቸው:: ❖ ጌታ መድኃኔዓለም ስለ እኛ መከራ ተቀብሎ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ያሉት 50 ቀናት የዕረፍት የተድላ የመንፈሳዊ ሐሴት ቀናት ናቸው፤ በእነዚህ ዕለታት ማዘን ማልቀስ ሙሾ ማውረድ ንስሃ መግባት ወዘተ አይፈቀድም:: ❓ለምን ቢሉ ❖ ለእኛ ካሣ በጌታችን መፈጸሙን የምሰናስብባቸው ቀናት ናቸውና፤ በእነዚህ ዕለታት ብናዝን "አልተካሰልንም" ዋጋ አልተከፈለልንም ያሰኛልና:: ❖ በዚህ ጊዜ መስገድ መጾም "ክርስቶስ በከፈለልን ዋጋ ሳይሆን በራሴ ድካም (ተጋድሎ) ብቻ እድናለሁ" ከማለት ይቆጠራልና:: ❖ ፍስሐ ወሰላም ለእለ አመነ ላመን ሁሉ ደስታና ሰላም ተደረገልን" ተብሎ በነግህ በሠርክ በሚዘመርበት ጊዜ ማዘን . . . ሲጀመር ካለማመን ሲቀጥል ደግሞ "ደስታው አይመለከተኝም" ከማለት ይቆጠራልና:: ❖ ሃምሳውም ቀናት እንደ ዕለተ ሰንበት ይቆጠራሉና፤ መጾምና መስገድ በዓል ያስሽራልና::
780Loading...
21
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-29-7
790Loading...
22
https://telegra.ph/ማዕዶት-04-20
920Loading...
23
ቃለህይወት ያሰማልን አባታችን፥እንኳን አብሮ አደረሰን
1070Loading...
24
Media files
2143Loading...
25
Media files
2313Loading...
26
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ኾኖ ከሙታን ተነሥቷል።ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና።" 1ቆሮ ፰፭÷፳~፳፩ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
1210Loading...
27
"እንደ ተናገረ ተነስቷል "መላው የማኅበረ ፍኖተ ሕይዎት አባላት እንኳን አደረሳችሁ
1060Loading...
28
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥              እለተ ቅዳሜ     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህች በሰሙነ ሕማማት ያለች እለተ ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፤ በዙ ስምም አላት በጥቂቱ እንመልከት 1. ቀዳም ስኡር(የተሻረችው ቅዳሜ) ትባላለች ❖ ምክንያቱም እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በሰንበት እለት የግልም ሆነ የአዋጅ ጾም በፍጹም አይጾምም፤ ውጉዝም ነው፤ ነገር ግን በዚህች የሕማማት ቅዳሜ ይህ ሥርአት ይሻራል ይጾማልም። ❖ ስለዚህ የተሻረችው ቅዳሜ ተባለች፤ በዚህ እለት የሚጾምበት ምክንያት እናቱ እናታችን ድንግል ማርያምና ቅዱሱ ሐዋርያ ዮሐንስ የጌታን ሞት አይተው እስከትንሳኤው ምግብን አልቀመሱም ነበር። ❖ ያን መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ከቻልን ከአርብ ጀምሮ ከከበደን ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ ቀኑን ሙሉና እስከሌሊቱ 9:00 እናከፍላለን እንጾማለን። 2. ለምለም ቅዳሜ ትባላለች ❖ ምክንያቱም በዚህ እለት ጠዋት በቤተክርስቲያን ካህናት ለሕዝበ ምእመናን ለምለም ቀጤማን ያድላሉ፤ ምእመናንም ይህን ቀጤማ በጭንቅላታችን እናስራለን፤ ይህም ምሥጢር ✍"ለኔ ሰላምን ልትሰጠኝ አንተ የእሾህ አክሊል ደፋህ እኔን ልታነግሰኝ አንተ ተንገላታህ የክብር አክሊል ልታረግልኝ የሾህ አክሊል አረክ " ስንል ነው። 3. ቅዱስ ቅዳሜ ትባላለች ❖ ቅዱስ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረታትን ፈጥሮ ጨርሶ ያረፈባትና የቀደሳት ስትሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ስለሰው ልጅ ሲል በቤዛነት ያደረገውን የማዳን ሥራ ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር አረፈ፥ በነፍሱም ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል ለ5500 ዘመናት ሲሰቃዩ የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ ወደ ዘላለም ረፍት ወስዷቸዋልና ይህች እለት ቅዱስ የሆነች ልዩ እለት ትባላለች። እንበለ ደዌ ወሕማም ፤እንበለ ጻማ ወድካም    ዓመ ከመ ዮም ፤ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ             እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ            በፍስሓ ወበሰላም ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ      ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን
1280Loading...
29
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-29-4
1000Loading...
30
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-29
1010Loading...
31
https://telegra.ph/ጌታችን-የደቀ-መዛሙርቱን-እግር-ስለማጠቡ-የሊቃውንት-ትርጓሜ-04-16
1230Loading...
32
https://telegra.ph/ሰሞነ-ሕማማት-ዘእለተ-ረቡዕ-04-15
1000Loading...
33
https://telegra.ph/ሰሙነ-ሕማማት-ዘእለተ-ማክሰኞ-04-14
750Loading...
34
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴: https://telegra.ph/የሰሙነ-ሕማማት-ዘእለተ-ሰኞ-04-13 https://telegra.ph/ሰሙነ-ሕማማት-ዘእለተ-ማክሰኞ-04-14 https://telegra.ph/ሰሞነ-ሕማማት-ዘእለተ-ረቡዕ-04-15
1110Loading...
35
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-29-3
1050Loading...
36
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-25-6
1340Loading...
37
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-25-2
1490Loading...
38
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-18
1310Loading...
39
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘሚያዚያ-04-23
1230Loading...
40
https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-ሚያዝያ-04-18-3
1280Loading...
➯ ኢፍትሐዊነት ነገሥት አንቀጽ 24 ሀብታም ወንድ ድሃ ሴትን አላገባም አይበል፣ ሀብታም ሴትም ድሃ ወንድን አላገባም አትበል፤ ባዕል መለኮት ነዳይ ሥጋን ተዋሕዷልና፤ ልዑል መለኮት ትሑት ሥጋን ተዋሕዷልና፤ እንዲያውም ሀብታሙ ወንድ ድሃይቱን ሴት ቢያገባ ሀብታሚቱም ሴት ድሃውን ወንድ ብታገባ ትልቅ ክብር ያገኛሉ፤ የእጮኝነት መሠረቱ ጾታዊ ፍቅር ነው፤ ይህም በመፈላለግ ይገለጣል፤ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የመፈላለግ ስሜት ካለ ሁለቱ ለእጮኝነት መጠያየቅ ይችላሉ፤ ነገር ግን ፍላጎቱ የአንዱ አካል ብቻ ከሆነ እና አንደኛው የማይፈልግ ከሆነ የፈለግሁትን ካላገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ማስቸገር አይገባም፤ ጠይቆ እምቢ ከተባለ ያው ኃፍረቱን ተከናንቦ ሌላ ይፈልግና ይጠይቅ፤ ምንስ ቢሆን እርሱ እየወደዳት እርሷ ባትወደው ወይም እርሷ እየወደደችው እርሱ ባይወዳት ከማትወደው/ከማይወዳት ሰው ጋር ለምን ለመኖር ይመኛል፤ አገባብስ እርሷም እርሱም ተዋደው ሲጋቡ ነው፤ አንድ ጊዜ አንዱ ጓደኛየ አንዷን ልጅ ፈለገና ሂዶ ጠየቃት ከዚያ እምቢ አለችው። ➯ ከዚያ ወረብ ሲያጠና "ኀዲጎ ብእሲቶ (ሚስቱን ትቶ)" የሚለውን ወረብ ደጋግሞ ይወርብ ጀመር መምህራችን ልጅቱ እምቢ እንዳለችው ሰምተው ኖሯል በቃ እሱኛውን ወረብ በትክክል ብለኽዋል ወደቀጣዩ እለፍ አሉት፤ አንድን ወረብ አጥንተህ በደንብ ከያዝከው ከዚያ ቀጣዩን ወረብ ታጠናለህ፤ የየኔታ ንግግር በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የመጀመሪያው ወረቡን ብለኽዋል ወደ ቀጣዩ እለፍ ማለታቸው ነው ሁለተኛው ደግሞ በቃ የመጀመሪያ ጥያቄህን ያቀረብክላት ልጅ እምቢ ካለች ወደቀጣዩ እለፍ ማለት እርሷን ትተህ ሌላ ፈልግ ማለታቸው ነበር፤ ሀብታም ወንድ ሀብታሟን ሴት ድሃ ወንድ  ድሃዋን ሴትም ማግባትም ይችላል፤ ሌላው በእጮኝነት ጊዜ በሐሳብ ያለመስማማት ነገር ካለ ቢለያዩ ኃጢኣት አይሆንም፤ ከተጋቡ በኋላ ግን መለያየት አይቻልም፤ የእጮኝነት ጊዜ ለየብቻቸው ነው መኖር ያለባቸው፤ እጮኛሞች እስካልተጋቡ ድረስ በአንድ ላይ መተኛት በአንድ ላይ ማደር አይገባቸውም።   ➯ አንድ ወንድ አንዲት ሴትን ለማግባት ወይም አንድ ሴት አንድን ወንድ ለማግባት የግድ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች አሉ፤ ከእነዚህም አንዱና ዋናው ሃይማኖት ነው ሴቶች በሃይማኖት የማይመስላችሁን ወንድ አታግቡ፤ ወንዶችም እንዲሁ በሃይማኖት የማትመስላችሁን ሴት አታግቡ፤ ታድያ እንዲህ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ✍️ "ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሷል። ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች" ይላልሳ ምን ማለት ነው? ካልከኝ። 📖1ኛ ቆሮ 7፥14 ➯ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተነገረበትን ምክንያት ማወቅ ሀሳቡን በትክክል እንድንረዳው ያደርገናል፤ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ያለው አሕዛብን አስተምሮ ወደ ክርስትና ሲመልስ ሚስት ክርስቲያን ትሆንና ባል ሳይሆን ይቀራል፤ ባል ክርስቲያን ይሆንና ሚስት ሳትሆን ትቀራለች፤ በዚህ ምክንያት ጠብ እንዳይነሳ ባል ክርስቲያን ከሆነ በጊዜ ሂደት አስተምሮ ክርስቲያን ያደርጋታል በማለት ይህንን ተናገረ፤ ይህንንም የሚያስረዳን ቁጥር 13 ላይ "ሴቲቱም የማያምንና ሚስቲቱን የሚያፈቅር  ከእርሷም ጋር ሊኖር የሚወድ ባል ቢኖራት ባሏን አትፍታ" ይላል፤ የሚያፈቅራት ብሎ የገለጠው የሚወዳት ከሆነ ለእርሷ ሲል ትንሽ ቆይቶ እንደ እርሷ ሃይማኖት ይሆናልና እንዲህ አለ፤ ነገር ግን ተምሮም ተነግሮም ወደ ትክክለኛዋ ሃይማኖት ካልመጣ ልትፈታው እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚሁ ምእራፍ ቁጥር 15 ላይ "የማያምን ግን ቢፈታ ይፍታ" ብሎ ነግሮናል፤ ይህንን መነሻ አድርገው 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በፍትሐ ነገሥታቸው ክርስቲያን ክርስቲያንን ብቻ እንዲያገባ ሥርዐት ሠርተዋል። ➯ ስለዚህ አሁን ላይ አስተምረህ ወደ ሃይማኖት ከመለስክ በኋላ አጭተህ ማግባት ትችላለህ እንጂ ገና ወደ ትክክለኛዋ ሃይማኖት ሳትመጣ እያለች እርሷን አግብቼ ወደ እኔ ሃይማኖት እመልሳታለሁ ግን አትበል፤ ሥለዚህ ባልና ሚስት በሃይማኖት አንድ የሆኑ መሆን አለባቸው፤ በሃይማኖት አንድ ሆነው ከተጋቡ በኋላ ከሁለት አንዱ ሃይማኖቱን ቢቀይርሳ እንዴት ይሆናል የሚል ጥያቄ ከጠየቅከኝ ደግሞ መልሱ "ይፋቱ" ነው፤ ምክንያቱም ✍️ "ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም" ይላልና ነው። 📖ማቴ 10፥37 ➯ ከዚህ ጥቅስ በታች ቁጥር 34 ላይ "ሰይፍን እንጂ ሰላም ለማምጣት አልመጣሁም" ብሏል፤ የዚህ ትርጉሙ በሃይማኖት ምክንያት እናትና አባት ባልና ሚስት ወላጅና ልጅ ቢለያዩ የሚገባ መለያየት መሆኑን ነው፤ ሰይፍ የተባለውም ይህ ነው። ➯ ከዚህ ላይ "ሰላም" ለማምጣት አልማጣሁም ያለው "አንተም በሃይማኖትህ አንቺም በሃይማኖትሽ ተባብለው በአንድ ተስማምቶ መኖርን ነው ሰላም ያለው" ይህ ሰላም ክርስቲያናዊ ሰላም አይደለም፤ ክርስቲያናዊው ሰላም ከክርስቶስ ጋር በመኖር በክርስቶሳዊ ሕይወት በመኖር የሚመጣ ሰላም ነው፤ ይህኛውን ሰላም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐ.14፣27 "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" ብሎናል፤ ስለዚህ በሃይማኖት የማይመስለንን ሰው ማጨት ማግባት አይገባም፤ከተጋባን፤ በኋላ ሃይማኖቱን ቢለውጥ እንኳ መፋታት ይገባል ማለት ነው። ይቀጥላል ........ 📌  አዘጋጅ ®  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ  ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ   ✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች" 📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                             ይቆየን 🕹 ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ፤ የተሳተውን፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ቸሩ መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ያድለን፤ በፀሎታቹ አስቡኝ አትርሱኝ የተለያየ ጽሁፍ ያላቹ፣ መተረክ እንችላለን የምትሉ እና ካርድ በመግዛት ቻናሉንና ግሩፑን በተለያየ አገልግሎት ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። 📩Coment  📥  @Yebiruk ───────────                     Channel  🧲  https://telegram.me/Tewahedo12                     Group 🧲  https://telegram.me/OrtodoxTewahedo12       Facebook Like Page (የፌስቡክ ፔጅ) 🧲   http://facebook.com/Tewahedo12 YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ) 🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw  ───────────
Показать все...
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

"ሥርዓትን እማር ዘንድ ያስጨነከኝ መልካም ሆነልኝ" መዝ 118 (119) ፥ 71 ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ግሩፑ http://t.me/OrthodoxTewahedo12 ይህ Channel #ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም አ/ጀመረ ለአስተያየት 📥 ➩ @Tewahedo12_bot

➯ ከዚያ በታች ግን ማግባትም ማጋባትም አይቻልም፤ ወንዱም በምቾት ያደገ በአካል የጠነከረ ከሆነ በ18 ዓመቱ ማግባት ይችላል። ከዚያ በታች ግን አይቻልም፤ ወንዱ ወይም ሴቷ በቤተሰብ ሥር የሚተዳደሩ ከሆነ በቤተሰብ ፈቃድ ያጫሉ፤ ነገር ግን ራሳቸውን የቻሉ በአካል የጠነከሩ ከሆኑና በኑሮም በቤተሰቦቻቸው ጥገኛ ያልሆኑ ከሆነ ራሳቸው መርጠው ራሳቸው አጭተው ሽማግሌ አስልከው መጋባት ይችላሉ፤ የእድሜ ጉዳይ መነሻውን ተናገርኩ እንጂ ከዚያ በላይ ከሆኑ ፈቅደው ተፈቃቅደው መጋባት ይችላሉ፤ በእድሜ ወንዱ ሊበልጥ ይችላል፤ ሴቷም ልትበልጥ ትችላለች፤ ነገር ግን እድሜያቸው ተቀራራቢ ቢሆን ይመረጣል። ➯ ይኽውም መረዳዳት የሚለውን በሀሳብም ለመረዳዳት የእድሜ መቀራረብ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፤ ዙሮ ዙሮ ግን በፍትሐ ነገሥቱ እንደምናየው የሴቷ አነስ ቢል የተሻለ ነው፤ ሴት 65 ዓመት ከሆናት በኋላ ማግባት አይገባትም። ➯ ሌላው በእጮኝነት ጊዜ ወደፊት ምን ሠርተው እንዴት ሠርተው ራሳቸውን እንደሚያኖሩ ማሰብ መወያየት ይገባል፤ ሌላው ነገር ደግሞ ለእጮኝነት ለመጠየቅ ሴትም ወንድን መጠየቅ ትችላለች፤ ወንድም ሴትን መጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ከተጠያየቁ በኋላ ሽማግሌ ወደ ቤተሰብ የሚልክ ወንዱ ነው፤ ወንዱ ወደ ሴቷ ቤተሰቦች ነው እንጂ ሴት ወደ ወንድ ቤተሰብ ሽማግሌ ልካ "ላገባው ነው" ማለት አይገባትም፤ ከእጮኝነት በኋላ ጥሎሽ ወይም ማጫ የሚሰጥ ደግሞ ወንድ ነው፤ ይኽውም ለአዳም መላእክት ወርቅ እጣን እና ከርቤ አምጥተው ሰጥተውታል፤ አዳምም ለሔዋን ማጫ አድርጎ ሰጥቷታልና የዚያ ምሳሌ ነው። ➯ የልጆቻችንን ከርስ ብቻ የምንሞላ ከሆንን እያሳደግን ያለነው ሮሆቦት እንጂ ሰው አይደለም፤ ከሮሆቦት የተሻሉ ልጆችን ማሳደግ ከፈለግን የተፈጠሩበትን ዓላማ እንዲያውቁ በስነልቡና ጠንካራ እንዲሆኑ በስነ ምግባር የታነጹ ልጆች እንዲኖሩን ከፈለግን ከልጅነታቸው ጀምረን ነገረ እግዚአብሔርን ሃይማኖትን ልናሳውቃቸው ይገባል፤ እኛ ሆዳቸውን ልብሳቸውን ብቻ እየቻልን አእምሯቸውን ግን በሌላ ሰው ሌላ ትምህርት ካስያዝነው እንደ ስልክ እኛ ቻርጅ እናደርጋለን ሶፍት ዌሩን ሌላ ባዕድ ይሞላዋል ማለት ነው፤ ሲጀምር ቤተክርስቲያን አንድን ልጅ አንዱ ክርስትና እንዲያነሳው ሥርዐት የሠራች የሃይማኖትን ትምህርት ጠንቅቆ እንዲያስተምረው ነው፤ አሁን አሁን ግን ይህ የለም፤ ነገር ግን የትዳር ዋናው ዓላማ የእግዚአብሔርን አምሳል የሆነ ልጅን ማስገኘት ነው። ➯ ስለዚህ ልጆቻችን በመሰረታዊነት ከምግበ ሥጋም ከልብሰ ሥጋም በተጨማሪ የሚያስፈልጋቸው ምግበ ነፍስ ነው፤ ስለዚህ በልጅነታቸው ቤተክርስቲያን እየወሰድን እናቆርባቸዋለን አበ እመ ማለት ሲጀምሩ ደግሞ በቃለ እግዚአብሔር አፋቸውን እናስፈታቸዋለን፤ እንግዲህ በትዳር አማካኝነት ባልና ሚስት የእግዚአብሔር አምሳል የተባለውን ሰው ያስገኛሉ፤ ይህም ትልቅ በረከት ነው። ✍️"...ልጆች ሆይ አብን አውቃችኋላና እጽፍላችኋለሁ" ተብሏል። ሃይማኖትን ማሳወቅ ይገባል። 📖1ኛ ዮሐ 2፥13
Показать все...
💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን   ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 ክፍል ሁለት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥               ስለ እጮኝነት......         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  ካለፈው ሳምንት የቀጠለ... 📌 ሌላው ወደ እጮኝነት ከመግባታችን በፊት ለእጮኝነት ያሰብናት ሴት/ወንድ ከአራቱ ዝምድናዎች ውስጥ የሌለች/ለ መሆኑን መረዳት አለብን፤ አራቱ ዝምድናዎች የተባሉም። 1) መንፈሳዊ ዝምድና 2) የአሳዳጊ አባትና እናት ዘመዶች 3) የሥጋ ዝምድና 4) የጋብቻ ዝምድና ➯ የምታጫት ሴት ወይም የምታጪው ወንድ ከእነዚህ ዝምድናዎች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24ን ይመልከቱ። ➯ የሥጋ ዝምድና ማለት የእናትህ እና የአባትህ ዘመዶችን ሁሉ ማግባት አይገባም፤ ይህም ማለት አክስት፣ አጎት አያት ቅድመ አየት እያለ ይቀጥላል፤ ይህም ዝምድና እስከ ሰባት ትውልድ ቀጥሎ በስምንተኛው መጋባት ይቻላል፤ ይህም ማለት ለምሳሌ አንተ እስከ ሰባተኛ የልጅ ልጅ ብታይና ወንድምህም እስከ ሰባተኛ የልጅ ልጅ ቢያይ የመጨረሻው ሰባተኛው የልጅ ልጅህና የወንድምህ ሰባተኛው የልጅ ልጅ መጋባት አይችሉም፤ በስምንተኛው ግን መጋባት ይቻላል ማለት ነው። የሰባት ትውልድ አቆጣጠሩ፦ 1) አንተ ወይም አንቺ 2) እናትህ ወይም አባትህ 3) የእናትህ እናት እና አባት     የአባትህ እናት እና አባት 4) የእናትህ እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት እናትና አባት 5) የእናትህ እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት እናት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት እናትና አባት 6) የእናትህ እናት አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ እናት አባት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ እናት እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት እናት አባት እናትና አባት     የእናትህ አባት እናት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት እናት አባትና እናት     የእናትህ አባት አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ እናት አባት አባት እናትና አባት     የአባትህ እናት እናት እናት አባትና እናት     የአባትህ እናት እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት አባት እናትና አባት     የአባትህ አባት እናት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት እናት አባትና እናት     የአባትህ አባት አባት አባት እናትና አባት 7) ወንድ ከሆንክ የምታገባት ሴት፣ ሴት ከሆንሽ ደግሞ የምታገቢው ወንድ ትውልዳችሁ ሲቆጠር በሰባቱ ትውልዶች በየትኛውም አቅጣጫ ማለቴ በእናትህ እናት እናት፣ ወይም ባጭሩ ከላይ በጠቀስናቸው ዝርዝሮች ውስጥ እስከ ሰባት ባለው ተመሳሳይ አያት ሊኖራችሁ አይገባም፤ እህት ወንድም፣ አክስት አጎት ወዘተ በላይኛው ይቆጠራል። 🔘 ለምሳሌ ➯ የአጎትህን ልጅ የማታገባበት ምክንያት ስትቆጠር አንድ አንተ አለህ፤ ከዚያ በሁለተኛ አባትህ ወይም እናትህ አሉ፤ ከዚያ በሦስተኛ የእናትህ እናትና አባት ወይም የአባትህ እናት እና አባት አሉ፤ በሦስተኛው አያታችሁ ስለምትገናኙ መጋባት አይቻልም፤ በእንደዚህ ዓይነት አቆጣጠር እስከ ሰባት ባለው በሆነ አያት ወይም ቅድመ አያት የምትገናኙ ከሆነ የሥጋ ዝምድና ስላላችሁ መተጫጨት መጋባት አይገባም። ➯ የክርስትና አባት ወይም እናት ዝምድና ያልነው ደግሞ መንፈሳዊ ዝምድና ይባላል፤ መንፈሳዊ ዝምድና የሚባለው ደግሞ አንተን ክርስትና ያነሳህ ሰውየ ሥጋዊ ዘመዶቹ ሁሉ በመንፈሳዊ ዝምድና የአንተ ዘመዶች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የክርስትና አባትህን ዘመዶች በሙሉ ማግባት አይቻልም ማለት ነው፤ የአሳዳጊ እናት ወይም አባት ዝምድና የተባለው ደግሞ አሳዳጊህ እንደ አባት ወይም እናት ስለሆኑ የአሳዳጊህ ዘመዶች በሙሉ በሥጋ ባይዘመዱህ እንኳ ዘመዶችህ ይሆናሉና ከዚያ አትጋባ ማለት ነው። ➯ የጋብቻ ዝምድና የሚባለው ደግሞ አንተና ሚስትህ በዝሙት ምክንያት ብትፋቱ እና እንደገና ሌላ ሚስት ለማግባት ብትፈልግ በሦስቱም ዝምድናዎች በኩል የሚስትህ ዘመድ ያልሆነች መሆን አለባት ማለት ነው፤ በንሥሓ አባት አንድ የሆኑ ልጆች ከላይ በጠቀስናቸው ዝምድናዎች ካልተዛመዱ በስተቀር መጋባት ይችላሉ፤ ይህ በሐዲስ ኪዳን በፍትሐ ነገሥት የቀረበው ዝምድና ነው፤ የመንፈሳዊ ዝምድና እስከም የለው ብዙ ነው ካለ በኋላ አንድም እንደሥጋዊው ዝምድና እስከ ሰባት ነው ተብሎ ታትቷል፤ ይህም ቤተክርስቲያን ሰውን ለማዛመድ የሄደችበት ርቀት እጹብ እጹብ ብለን እንድናደንቅ ያደርገናል። ➯ የእንጀራ እናትህን/አባትህን ልጅ ምንም እንኳ በእናትም በአባትም ባትገናኙም ማግባት አትችልም፤ ምክንያቱም የጋብቻ ዝምድና ይፈርሳልና ነው፤ በእጮኝነት ጊዜ ሌላው ትልቁ ጉዳይ የእድሜ ጉዳይ ነው፤ ፍትሐ ነገሥት ሴት 12/15 ዓመት ሳይሞላት ወንድ 18/22 ዓመት ሳይሞላው ማግባት አይገባውም ይላል፤ እጮኛ ልያዝ ቢል እንኳ እድሜው ከዚህ ዓመት በታች ከሆነ በቤተሰቡ ፈቃድ እንጂ እርሱ ራሱ መርጦ ማጨት አይችልም፤ ነገር ግን ይላል ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24 ሴቲቱ በምቾት አድጋ በአካል የጠነከረች ከሆነ ቢያንስ በ12 ዓመቷ ታግባ ይላል።
Показать все...
Показать все...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፱

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Показать все...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፰

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን   ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 ክፍል ሁለት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥         ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ሕይወት         ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  📌 ድንግልናና ቅዱስ ጋብቻ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ 📌 የድንግልና ሕይወት ትርጉምና ዓላማ ❖ ድንግልና ክብረ ሥጋን ፣ ማሕተመ ሥጋንና ማሕተመ ሕሊናን ጠብቆ ከዓለም ርቆ ለመኖር መወሰን ፣ መለየት ፣ መጠበቅ ፣ መጠንቀቅ በሚል ትርጉም ይጠቃለላል፡፡ ❖ የቋንቋው ትርጉም ይህን ይመስላል ሲባልም ፣ ገላጭ ማረጋገጫው ማኅተሙና ምስክሩ የዓላማ ጽናት ነው፡፡ ❖ የድንግልና ሕይወት ትክክለኛ ትርጉም አገኘ የሚባለው ፣ በድንግልና ሕይወት ጸንቶ ለመኖር የወሰነ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ለድንጋሌ ሥጋ መሠረት የሆነውን ድንጋሌ ሕሊናን በጽኑ ዓለት ላይ የመሠረተ መሆኑን እርግጠኛ ሲሆን ነው፡፡ ❖ ድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ሕሊና ልቡና ላይ ከተመሠረተ ፣ ነፋሳት ቢገፉት አይናወፅም ፤ መንገድ ቢረዝምበት ይዘልቃል እንጂ ጉዞው አይሰናከልም፡፡ ❖ የድንጋሌ ሥጋ መሪው ፊት አውራሪው ድንጋሌ ሕሊና ከሆነ ፣ የንጽሐ ሥጋ ልጓሙና ማሕተሙ ንጽሐ ሕሊና ንጽሐ ልቡና መሆኑ ከታወቀ የማሕተመ ሥጋ አዛዡ ናዛዡ ማሕተመ ሕሊና እንደሆነ ከተረጋገጠ የድንግልና ሕይወት ካለምንም ጥርጥር የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ ❖ የድንግልና ሕይወት ዓላማ ለሞት ለኃጢአት ከመገዛት ርቆ ፤ ኅልፈት በማያገኛት ሕይወት አሳርፋ ለማኖር ተዘጋጅታ ያለች የመንግሥተ ሰማይን ርስትን ገንዘብ ለማድረግ ነው፤ መቼም ስለድንግልና ሕይወት ሲነገር የብዙ ደናግላን የቅድስና ሕይወት ማሰብና ማስታወስ ይቻል ይሆናል ፤ ይሁን እንጂ በማንኛውም ክርስቲያን አእምሮ ቀድሞ የሚቀረፀው የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የድንግልና ሕይወት ነው፤ ምክንያቱም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፈጣሪዋን መውለድዋ ፣ ወላዲተ አምላክ ፣ እመ አምላክ ፣ ወላዲተ ቃል ለመባል መብቃትዋ በድንጋሌ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ፣ ድንጋሌ ሥጋን ከድንጋሌ ሕሊና ፤ ንጽሐ ሥጋን ከንጽሐ ልቡና በፍጹምነት አስተባብራ መገኘትዋ ነው፡፡ ❖ ፈጣሪዋን ለድኅነተ ዓለም የወለደች ድንግል ማርያም ቅድመ ወሊድ ድንግል ፤ ጊዜ ወሊድ ድንግል ፤ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናት፤ ድንግል ፍጽምት፥ ድንግል ወእም ያሰኛትም ይኸው ነው፤ ድንግልናዋ ሕፀፅ የሌለበት በመሆኑ ምክሐ ደናግል "የደናግል መመኪያ" ትባላለች፡፡ ❖ ድንግልናዋ ድንጋሌ ሥጋን ከድንጋሌ ሕሊና ያስተባበረ ፍጹም በመሆኑ ድንግል በክልኤ (በ፪ኤ) ትባላለች፡፡ 📖 ኢሳ 7፥24 ፤ 📖 ሉቃ 1፥34-35 📖 ማቴ 1፥18-23 ❖ ድንጋሌ ሕሊናን በፍጹምነት ቢመለከቱት ከባድና ፈታኝ ነው ፤ ሰማያውያን መላእክትን ጭምር የተፈታተነ ሕይወት ነው ፤ ድንጋሌ ሕሊና ዓላማውን ስቶ ፈሩን ለቅቆ ግንቡ ከፈረሰ የድንግልና ሕይወት ከሥር መሠረቱ ይናጋል ፤ መንፈሳዊ ሕይወት ይበላሻል፡፡ ❖ ቅድስና ትርጉም ያጣል ፤ በድንግልና ስም የሚደረገው ጥረት ሁሉ ውጤቱና ትርፉ ከንቱ ልፋት ብቻ ይሆናል፤ አዳምን ከክብሩ ያዋረደ ፤ እግዚአብሔርን ከመሰለ ጌታ ርቆ ገነትን የመሰለች ርስት ተነጥቆ ለግብራተ ዲያብሎስ የዳረገ የድንጋሌ ሕሊና ህፀፅ ነው፡፡ ❖ ቅሩበ እግዚአብሔር ፥ አኃዜ መንጦላዕት ይባል የነበረው ዲያብሎስ ፈጣሪውን ያስካደው፥ ከክብሩ ያዋረደው ፥ ወደ ባሕረ እሳት ያስጣለው "ያስወረወረው" የድንጋሌ ሕሊና ድቀት ነው፡፡ ✍️ "አኅለዮ ለአዳም አምላክና" ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ 📖 3ኛ መቃ 2፥10-17 🔔 ንስሀ ግን የወደቁትን ታነሳለች ቀማኛውን መጽዋች፣ ዘማዊውንም ድንግል ታደርጋለች ይቀጥላል ........ 📌  አዘጋጅ ®  ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ 📌ምነጭ ✍️በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ 📚ሕይወተ ወራዙት ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ   ✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች" 📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                             ይቆየን
Показать все...
Показать все...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፯

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Показать все...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፮

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Показать все...
ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፭

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

Показать все...
ዳግም ትንሣኤ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን ✍️"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል" 📖1ኛ ቆሮ 15÷20 “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) “በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን) “ዐሠሮ ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው) “አግአዞ ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው) “ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ) “እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ) “ኮነ” (ሆነ) “ፍሥሐ ወሰላም” (ደስታ ሰላም) እንኳን ለዳግም ትንሣኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን     ✥•••• ●◉ ✞ ◉●••••✥       ዳግም ትንሣኤ     ✥•••• ●◉ ✞ ◉●••••✥ ቅዳሜን ቤተክርስቲያን "ቅዱሳን አንስት" ብላ እንደምታከብር ትናንት የተመለከትን ሲሆን እሁድን ደግሞ ቤተክርስቲያን…