ALFARUK MULTIMEDIA®
Открыть в Telegram
✨ ቀደምቱ አል-ፋሩቅ ኦዲዮ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን በአዲስ አቀራረብ ተመለሰ! ✨ ጥራት ያላቸውን ፊልሞች፣ ሙሃደራዎችን፣ ነሺዳዎችን እና መንዙማዎችን ይዞላችሁ ቀርቧል። 📌 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 [Join Channel] (https://t.me/ethioalfa) ▶️ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡ 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCDIi
Больше3 897
Подписчики
-324 часа
+447 дней
+19130 дней
Архив постов
3 897
አዲስ እና አስደሳች ዜና ለሲራ እና ታሪክ ወዳጆች!
ከ15 ዓመታት በፊት በአልፋሩቅ ኦዲዮ ቪዥዋል ተዘጋጅቶ በብዙዎቻችን ዘንድ ትልቅ አድናቆትን ያተረፈው ታላቁ የነቢዩ (ሰዐወ) ታሪክ ተከታታይ ፊልም «ቀመሩ በኒ ሀሺም» (Qamru Bani Hashim)
አሁን በከፍተኛ ጥራት (በ4K Digital Quality) ተሻሽሎ በአልፋሩቅ ሱፐር አፕ ሊቀርብላችሁ ዝግጁ ሆኗል! 📱✨
ይህ ድንቅ ፊልም የነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ሙሉ የህይወት ታሪክ (ሲራ) ከስረ መሰረቱ የሚያስጎበኝ ነው፤ ከእሳቸው መወለድ በፊት ከነበሩት ታሪካዊ ክስተቶች (እንደ የዝሆን ዓመት ታሪክ) ጀምሮ፣ የእስልምናን ውብ አጀማመርና መስፋፋት፣ እንዲሁም እሳቸው ካረፉ በኋላ የተከሰቱትን ወሳኝ ሁነቶች በሚማርክ አቀራረብ በጥልቀት ይዳስሳል።
በዚህ ፊልም ውስጥ ምን ያገኛሉ?
°በ4K ጥራት የታደሰና የተሻሻለ የምስልና የድምፅ አቀራረብ
°የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) የተሟላ እና አስተማሪ የህይወት ጉዞ
°ልብ የሚነኩ የመካ እና የመዲና ታሪካዊ ክስተቶች
°ታሪክን በጠራ ምስልና ጥራት ወደ ኋላ ተመልሰው የሚያዩበት፣ እውቀትና መንፈሳዊ መነሳሳትን የሚያገኙበት ልዩ ስራ ነው! እንዳያመልጥዎ!
📲 ይህን እና ሌሎች በርካታ ምርጥ ስራዎችን ለማግኘት አልፋሩቅ ሱፐር አፕን (Al-Faruq Super App) አሁኑኑ ያውርዱ!
👉 [https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alfaruk.app]
#ቀመር_በኒ_ሀሺም #አልፋሩቅ_ሱፐር_አፕ #አልፋሩቅ_ኦዲዮ_ቪዥዋል #AlFaruqSuperApp #4K #IslamicHistory #Seerah
3 897
የበርካታ ተመልካቾችን ቀልብ የሳበው ታሪካዊና አነቃቂው "የአንደሉስ መከፈት" ተከታታይ ፊልም እስከ ክፍል 10 በትርጉም ተዘጋጅቶ ቀርቦላችኋል። አሁኑኑ ገብታችሁ በመመልከት በታሪክ ጉዞው ይደሰቱ! 🔗 [Check out "የአንደሉስ መከፈት" on Al-Faruk! https://alfarukstream.com/content/7e5c1f13-e63b-4585-a57e-fb7055a698ce Download the app to watch now!] #የአንደሉስ_መከፈት #FatihAlAndalus #አዲስ_ፊልም #Cinema
3 897
በ8ኛው ክፍለ ዘመን በታዋቂው የእስልምና ጦር መሪ ጧሪቅ ኢብኑ ዝያድ እና በሙሳ ኢብኑ ኑሰይር መሪነት ወደ አይቤሪያን ባሕረ ገብ መሬት (ስፔን እና ፖርቱጋል) የተደረገውን ታሪካዊ የእስልምና መስፋፋት የሚያሳይ ድቅድቅ ታሪካዊ ድራማ!
የሙስሊም ጦር ያሳየውን ጽናት፣ ከጎቲክ ንጉሥ ሮደሪክ ጋር የተደረጉ ፍልሚያዎችን እና የፖለቲካ ሴራዎችን በጥራት ይመልከቱ።
📲 አሁኑኑ በአልፋሩቅ ሱፐር አፕ ያግኙት!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔗🔗https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alfaruk.app 🔗🔗
3 897
🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉
''ሸውቅ የጥበብ እና የጥናት ማዕከል'' በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ እውቅና አግኝቶ መመዝገቡን በታላቅ ደስታ እናበስራለን!
የማዕከላችን ስያሜ "ሸውቅ" ትርጉምና ዓላማ፡-
ሸውቅ (شوق) ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ "ጽኑ ናፍቆት" ሲሆን፣ በመንፈሳዊ ዕይታ ደግሞ ለአላህ እና ለነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ያለ ጥልቅ ፍቅር እና የመገናኘት ጉጉት ማለት ነው።
በጥበብ ውስጥ ያለው ድርሻ፡- ሸውቅ በኢስላማዊ የጥበብ ሥራዎች (እንደ ነሺዳ እና መንዙማ) የነቢዩን ﷺ ፍቅር በልብ ውስጥ የሚዘራ ማዕበል ነው። እውነተኛ ሸውቅ በስሜት ብቻ ሳይሆን ሱናን በጥብቅ በመከተል፣ ሰለዋት በማብዛትና የሰዎችን ልብ ወደ ኸይር በመሳብ ይገለጻል።
ስለሆነም የ"ሸውቅ የጥበብ የጥናት ማዕከል" ዓላማ በሥራዎቹ ሁሉ የነቢዩን ﷺ ፍቅርና ጽኑ ናፍቆት በጥበብ ሥራዎቹ አማካኝነት ወደ መላው ማኅበረሰብ ማስተላለፍ ነው።
በቅርቡ ይዘናቸው የምንቀርባቸው ዝግጅቶች፦
🔹 ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው የመድረክ ስራዎች
🔹 ትምህርታዊ ስብስቦች
🔹 የጥናት እና ምርምር ስራዎች
🔹 በክልል ከተሞች የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች
አንድነት፣ ጥበብ እና አደብ!
#ሸውቅ_የጥበብ_እና_የጥናት_ማዕከል
✍️AnwarulHadi
3 897
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደራጀ ስቱዲዮችንና በባለሙያዎቻችን አማካኝነት የሚከተሉትን አገልግሎቶች በከፍተኛ ጥራት እናቀርባለን፡
የድምፅ (Audio) አገልግሎቶች
° የነሺዳ እና መንዙማ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ (Menzuma & Neshida Recording, Mixing & Mastering)
° የፊልም ስኮሮችና የጀርባ ሙዚቃ/ድምፅ (Film Scores & Soundtracks)
° የድምፅ ተዋንያንና ትርጉም (Voiceover & Dubbing)
° የኦዲዮ ቡክ ቀረጻ (Audiobook Recording)
የተለያዩ የቲቪ፣ ሬዲዮ እና የሶሻል ሚዲያ ማስታወቂያዎች
📌 ልዩ ቅናሽ: ነሺዳና መንዙማዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራለን!
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን: 0945144444
አልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን (Alfaruk Multimedia Production)
3 897
በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ኘሮዳክሽን የተለቀቀው ይህ አዲስ ነሺዳ የነቢያችን (ﷺ) ውበትና ፍቅር የፈሰሰበት፣ የልብን ስሜት የሚኮረኩር እውነተኛ የመንፈስ ድግስ ነው።
የአለማቱ እዝነት (ﷺ) መወለድ
የነቢያችን (ﷺ) ወደዚች አለም መምጣት የጨለማው ዘመን ማብቂያ፣ የእዝነትና የብርሃን መውጫ ነበረ። ነሺዳው የሳቸውን ታላቅነት፣ ለሰዎች ሁሉ የተላኩት የፍቅርና የሰላም መሪ መሆናቸውን በሚነካ መልኩ በማስታወስ ልባችንን በውዴታና በጉጉት እንዲሞላ ያደርጋል። የሳቸውን መወለድና ታላቅ ባህሪ ሲያወሳ አእምሮን በፍቅር ያንሳፍፋል፤ አይንንም የእንባ ዘንበል ያደርጋል።
የሙአዝ ሀቢቢ የተለየ ስጦታ
የሙአዝ ሀቢቢ ድንቅና ማራኪ ድምፅ ደግሞ ይህንን ታላቅ መልእክት ወደ እያንዳንዱ ልብ በቀጥታ የሚያደርስ ድልድይ ሆኗል። ድምፁ ውስጥ ያለው ጥልቅ ስሜት፣ ቅንነትና መንፈሳዊ ልስላሴ አዳማጩን ከውጫዊው አለም ውካታ አላቆ ወደ ታላቁ ነቢይ (ﷺ) የፍቅር ውቅያኖስ ያጠልቃል።
የኡስታዝ ሰኢድ ድንቅ ስንኞች
የኡስታዝ ሰኢድ ጥልቅና ልብ የሚያቀልጡ ስንኞች ለስራው ልዩ ግርማ ሞገስ ሰጥተውታል። እያንዳንዱ ቃል በጥንቃቄ ተመርጦ፣ በፍቅርና በእውቀት ተጠምቆ የተፃፈ በመሆኑ መንፈስን ያረሰርሳል፤ ነፍስንም በኢማን ብርሃን ያድሳል።
ይህ ስራ የዜማና የቃል ቅንብር ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የነቢያችንን (ﷺ) መንገድ እንድንከተል፣ በሱናቸው እንድንታደስና በፍቅራቸው እንድንመሰጥ የሚያደርግ ጥሪ ነው። በእውነት መንፈስን የሚያረጋጋና ልብን ሙሉ በሙሉ የሚማርክ ድቅስ ስራ ነው።
ተለቋል🔥ተለቋል🔥ተለቋል🔥ተለቋል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
