ጃዚኤል (ማኅሌት)Speech & Language therapy🗣👂🗣
Открыть в Telegram
ጀዚኤል( ማህሌት) ስፒች ቴራፒ የተከፈተው ስለዚህ ህክምና እና በዚህ ህክምና ስለሚሰጡት እክሎች ግንዛቤ ለመፍጠር፣ ህክምና፣ማማከርና ስልጠና ለመስጠት ነው።በዚህ ህክምና የሚሰጡት -ለንግግር እክሎች፣ ለቋንቋ እክሎች፣ ለመዋጥ እክሎች፣ ለድምጽ እክሎች፣ ለመስማት እክሎችና ናቸው።ከእነዚህም ውስጥ ኦቲዝም፣ ስትሮክ፣ መንተባተብ፣ የቋንቋ መዘግየት፣ሲንድሮምስ... @Jazielspeechtherapyclinic1
Больше1 673
Подписчики
-124 часа
-27 дней
+1030 дней
Архив постов
ዲስአርትሪያ (Dysarthria)
👉🏽 ዲስአርትሪያ (Dysarthria) ምንድነው?
☺️ዲስአርትሪያ ማለት ንግግርን ለማውጣት የሚያገለግሉ የጡንቻዎች ድክመት የሚያመጣ የንግግር እክል ሆኖ ንግግርን ግልፅ እንዳይሆን የሚያደርግ ነው።
☺️ይህ እክል የሚፈጠረው ንግግር ለማድረግ የምንጠቀማቸው አካላት (ማለትም ከንፈር፣ ጥርስ፣ የጉሮሮ ጡንቻዎች እና ድምፅ ማውጫ ቱቦዎች) የሚቆጣጠሩት አዕምሮ ወይም ነርቮች ሲጎዱ ነው። በዚህ ጊዜ ጡንቻዎቹ ይዳከማሉ ወይም እርስ በእርሳቸው ተቀናጅተው ለመሥራት ይቸገራሉ።
አፍና አካባቢው ጥንካሬ ምን ይረዳል?
👉🏽ከአፍ፣ ከከንፈር፣ ከጉንጭ እና ከአንደበት አካባቢ የሚደረጉ ልምምዶች እና የጡንቻ ጥንካሬ ለዲስአርትሪያ ተጠቂዎች የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥቅሞች ይሰጣሉ፦
☺️ የንግግር ግልጽነትን ማሻሻል: የአፍ እና የከንፈር ጡንቻዎች ሲጠናከሩ ቃላትን በተለይም ፊደላትን አወጣጥ (ግልጽነት) ከፍ ያደርጋሉ።
☺️ምራቅን መዋጥ እና መመገብን ማገዝ: ለአነጋገር የሚረዱ ጡንቻዎች ለምግብ መዋጥ እና ምራቅን በትክክል ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። ይህም መታፈን ወይም ምራቅን የመውረድ ችግርን ይቀንሳል።
☺️የድምፅ መጠንና ጥንካሬን መገንባት: የደረት፣ የጉሮሮ እና የአፍ ጡንቻዎች መተባበር ድምፅን ከፍ አድርጎ ለመናገር ያስችላል።
☺️በራስ የመተማመን ስሜት መጨመር: ግለሰቡ በግልጽ መናገር ሲጀምር በህብረተሰብ ውስጥ የመግባባት አቅሙ ይጨምራል።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ @ማኅሌት Speech Therapist
+7
የሂሳብ እክል (Dyscalculia) ማለት ምን ማለት ነው?
👉🏽የሂሳብ እክል (Dyscalculia) ማለት አንድ ልጅ ቁጥሮችን ለመረዳት፣ የሂሳብ ስሌቶችን ለመሥራት እና የቁጥር ጽንሰ-ሐሳቦችን ለመረዳት የሚቸገርበት የትምህርት ወይም የእውቀት (Learning/Cognitive) እክል ነው።
👉🏽ይህ እክል የማሰብ ችሎታ (አይኪው) ማነስን አያመለክትም፤
ተማሪዎች በሌሎች የትምህርት አይነቶች ጥሩ ውጤት ቢኖራቸውም በሂሳብ ብቻ ከፍተኛ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ
Repost from ጃዚኤል (ማኅሌት)Speech & Language therapy🗣👂🗣
10 ወላጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ስለ ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚገኙ ልጆች
1. ስፒች ቴራፒ የንግግር ህክምና ማለት መናገር ብቻ አይደለም ማለትም ልጅዎት መናገር ብቻ አይማርም፤ መግባባት፣ እጅ ምልክት (gesture)፣የዓይን መገናኘትና ሌሎችን መረዳት ይማራል።
2. ስፒች ቴራፒ ቀደም ብሎ ከትንሽ ዕድሜ ጀምሮ መጀመር በጣም አስፈላጊ ነው።
3. እያንዳንዱ ልጅ ልዩ ነው
አንዳንድ ልጆች ሊናገሩ ይችላሉ፣ አንዳንዶች ልጆች ቶሎ አይናገሩም። ቴራፒው ሁሉም ለልጆችዎት ተመጣጣኝ ይሆናል።
4. ጨዋታ ዋና መማሪያ መንገድ ነው
ልጆች በመጫወት ይማራሉ፤ ስለዚህ ቴራፒው እንደ ጨዋታ ይመስላል።
5. ወላጆች የቴራፒው ዋና አካል ናቸው።
ወላጆች በቤት ውስጥ እንዴት ልጃቸውን እንደሚረዱ ይማራሉ። ይህ የልጆችን ለውጥና እድገትን ያፋጥናል።
6. መግባባት ከመናገር ብቻ አይመጣም።
ልጅዎት የምልክት ቋንቋ (sign language)፣ ስዕሎች (PECS) እና መሣሪያዎች (AAC) ሊጠቀም ይችላል።
ይህ ንግግርን አያቋርጥም፤ ይበልጥ ይረዳል።
7. ማህበራዊ ተግባቦት በጣም አስፈላጊ ነው።
ልጅዎት ተራ መጠበቅ፣ የዓይን ግንኙነትነኣ ውይይት መጀመር ይማራል።
8.ለውጥ ትንሽ ቢሆንም በጣም ወሳኝና አስፈላጊ ነው።
ለምሳሌ:- የእጅ ምልክት መጠቀም ወይም አንድ ቃል መናገር ትልቅ እርምጃ ነው።
9. ቀጣይነትያለው ቴራፒ አስፈላጊ ነው።
በየቀኑ በቤት ውስጥ መልሶ መስራት እና መደበኛ ቴራፒ በጣም ይረዳል።
10. የቴራፒ ዓላማ እንደየ ልጆቹ ባህርይ፣ ተግባቦት፣ ማህበራዊ ግንኙነት ይለዋዋጣል።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ @ማኅሌት Speech Therapist
10 ወላጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ስለ ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚገኙ ልጆች
ስፒች ቴራፒ የንግግር ህክምና ማለት መናገር ብቻ አይደለም ማለትም ልጅዎት መናገር ብቻ አይማርም፤ መግባባት፣ እጅ ምልክት (gesture)፣የዓይን መገናኘትና ሌሎችን መረዳት ይማራል።
ስፒች ቴራፒ ቀደም ብሎ ከትንሽ ዕድሜ ጀምሮ መጀመር በጣም አስፈላጊ ነው።
እያንዳንዱ ልጅ ልዩ ነው አንዳንድ ልጆች ሊናገሩ ይችላሉ፣ አንዳንዶች ልጆች ቶሎ አይናገሩም። ቴራፒው ሁሉም ለልጆችዎት ተመጣጣኝ ይሆናል።
ጨዋታ ዋና መማሪያ መንገድ ነው ልጆች በመጫወት ይማራሉ፤ ስለዚህ ቴራፒው እንደ ጨዋታ ይመስላል።
ወላጆች የቴራፒው ዋና አካል ናቸው። ወላጆች በቤት ውስጥ እንዴት ልጃቸውን እንደሚረዱ ይማራሉ። ይህ የልጆችን ለውጥና እድገትን ያፋጥናል።
መግባባት ከመናገር ብቻ አይመጣም። ልጅዎት የምልክት ቋንቋ (sign language)፣ ስዕሎች (PECS) እና መሣሪያዎች (AAC) ሊጠቀም ይችላል። ይህ ንግግርን አያቋርጥም፤ ይበልጥ ይረዳል።
ማህበራዊ ተግባቦት በጣም አስፈላጊ ነው። ልጅዎት ተራ መጠበቅ፣ የዓይን ግንኙነትነኣ ውይይት መጀመር ይማራል።
8. ለውጥ ትንሽ ቢሆንም በጣም ወሳኝና አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ:- የእጅ ምልክት መጠቀም ወይም አንድ ቃል መናገር ትልቅ እርምጃ ነው።
9. ቀጣይነትያለው ቴራፒ አስፈላጊ ነው።
በየቀኑ በቤት ውስጥ መልሶ መስራት እና መደበኛ ቴራፒ በጣም ይረዳል።
10. ቴራፒ ዓላማ እንደየ ልጆቹ ባህርይ፣ ተግባቦት፣ ማህበራዊ ግንኙነት ይለዋዋጣል።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ ☎️0954999933 0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ
10 ወላጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ስለ ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚገኙ ልጆች
ስፒች ቴራፒ የንግግር ህክምና ማለት መናገር ብቻ አይደለም ማለትም ልጅዎት መናገር ብቻ አይማርም፤ መግባባት፣ እጅ ምልክት (gesture)፣የዓይን መገናኘትና ሌሎችን መረዳት ይማራል።
ስፒች ቴራፒ ቀደም ብሎ ከትንሽ ዕድሜ ጀምሮ መጀመር በጣም አስፈላጊ ነው።
እያንዳንዱ ልጅ ልዩ ነው አንዳንድ ልጆች ሊናገሩ ይችላሉ፣ አንዳንዶች ልጆች ቶሎ አይናገሩም። ቴራፒው ሁሉም ለልጆችዎት ተመጣጣኝ ይሆናል።
ጨዋታ ዋና መማሪያ መንገድ ነው ልጆች በመጫወት ይማራሉ፤ ስለዚህ ቴራፒው እንደ ጨዋታ ይመስላል።
ወላጆች የቴራፒው ዋና አካል ናቸው። ወላጆች በቤት ውስጥ እንዴት ልጃቸውን እንደሚረዱ ይማራሉ። ይህ የልጆችን ለውጥና እድገትን ያፋጥናል።
መግባባት ከመናገር ብቻ አይመጣም። ልጅዎት የምልክት ቋንቋ (sign language)፣ ስዕሎች (PECS) እና መሣሪያዎች (AAC) ሊጠቀም ይችላል። ይህ ንግግርን አያቋርጥም፤ ይበልጥ ይረዳል።
ማህበራዊ ተግባቦት በጣም አስፈላጊ ነው። ልጅዎት ተራ መጠበቅ፣ የዓይን ግንኙነትነኣ ውይይት መጀመር ይማራል።
8.ለውጥ ትንሽ ቢሆንም በጣም ወሳኝና አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ:- የእጅ ምልክት መጠቀም ወይም አንድ ቃል መናገር ትልቅ እርምጃ ነው።
ቀጣይነትያለው ቴራፒ አስፈላጊ ነው።
በየቀኑ በቤት ውስጥ መልሶ መስራት እና መደበኛ ቴራፒ በጣም ይረዳል።
የቴራፒ ዓላማ እንደየ ልጆቹ ባህርይ፣ ተግባቦት፣ ማህበራዊ ግንኙነት ይለዋዋጣል።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ ☎️0954999933 0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ @Dr.Meskerm Abatkun
የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን (PPSOE) ኢትዮጵያ መስራችና አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ክብራ ከበደ፣ ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን እና እንቅስቃሴ መታወክ ማህበር (International Parkinson and Movement Disorder Society) የ2026 የህዝብ አገልግሎት ሽልማት (Public Service Award) ተሸላሚ ሆነዋል።
ወይዘሮ ክብራ በሀገራችን ብቸኛውን የፓርኪንሰን ህሙማን መርጃ ድርጅት በማቋቋም ላለፉት 15 ዓመታት በርካታ የፓርኪንሰን ህሙማንን ተጠቃሚ ያደረጉ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውነዋል።
በዋናነትም የግንዛቤ ፈጠራ፣ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የድጋፍና እንክብካቤ ሥራዎችን ሲሠሩ ቆይተዋል።
ራሳቸውም የፓርኪንሰን ታማሚ የሆኑት ወይዘሮ ክብራ፣ ላለፉት 26 ዓመታት ከበሽታው ጋር እየኖሩ ይገኛሉ።
በሽታው እንቅስቃሴን የሚያውክ እና ለከፍተኛ የእንቅስቃሴ መታወክ የዳረጋቸው ቢሆንም፣ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እና ለህሙማን የሚደረጉ ድጋፎችን እንዳያደርጉ አላገዳቸውም።
በወይዘሮ ክብራ ጽናትና አመራር የተመሰረተው ድርጅቱ፣ ዛሬ ላይ 1,200 የፓርኪንሰን ህሙማን እና 745 አስታማሚዎችን በአባልነት በመመዝገብ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።
የፓርኪንሰን ህመም 85 በመቶ የሚሆነውን ከ60 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ ቢሆንም፣ ቀሪው 15 በመቶ ከ60 ዓመት በታች ያሉትን ያጠቃል። ወይዘሮ ክብራም ከእነዚህ 15 በመቶ ውስጥ አንዷ ሲሆኑ፣ በ31 ዓመታቸው በበሽታው ተይዘው ከህመሙ ጋር በተያያዘ ተገቢ ህክምና ባለማግኘት እና ከበሽታው ምልክት ጋር ተያይዞ ለከፍተኛ መገለልና ችግር ተጋልጠው ነበር።
መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገው International Parkinson and Movement Disorder Society ከፓርኪንሰን እና ሌሎች ከእንቅስቃሴ መታወክ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ህመሞች ላይ በርካታ ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማከናወን ዋና ትኩረቱ ነው። ማህበሩ የዘንድሮ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በደቡብ ኮሪያ እያካሄደ ይገኛል።
ይህ የተከበረ ዓለም አቀፍ ሽልማት ለወይዘሮ ክብራ ከበደ መሰጠቱ፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፓርኪንሰን ህሙማን የተደረገ ትልቅ እውቅና እና ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡ www.parkinsonethiopia.org
💚ሴረብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy CP)💚
የሴረብራል ፓልሲ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን 💚
💚ሴረብራል ፓልሲ ምንድነው?
ሴረብራል ፓልሲ ገና በልጅነት ጊዜ ውስጥ የሚታይ ያልተለመደ የአንጎል እድገት ወይም በማደግ ላይ ባለው አንጎል ላይ በሚደርስ ጉዳት, የጡንቻ እንቅስቃሴ እና ቅንጅት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የነርቭ እክል ነው።
💚 የሴረብራል ፓልሲ መንስኤዎች
ከወሊድ በፊት
• በእርግዝና ወቅት ኢንፌክሽኖች • ለመርዝ ወይም ለመድሃኒት መጋለጥ • የአንጎል እድገትን የሚጎዳ የዘረመል እክል • ለአንጎል የኦክስጂን እጥረት
2.በወሊድ ጊዜ
• ያለጊዜው መወለድ (ከ37 ሳምንታት በፊት) • ዝቅተኛ የልጅ ክብደት • በወሊድ ወቅት የኦክስጂን እጥረት (perinatal asphyxia) • እንደ የእንግዴ ልጅ መቆረጥ ወይም የእምብርት ገመድ ያሉ ችግሮች
ከወሊድ በኋላ • የአንጎል ኢንፌክሽኖች (ለምሳሌ፡ ማጅራት ገትር፣ ኢንሴፈላይትስ) • የጭንቅላት ጉዳቶች • በአንጎል ውስጥ ስትሮክ ወይም የደም መርጋት
💚 የሴረብራል ፓልሲ ምልክቶች
የሲፒ ምልክቶች እንደ ዓይነት እና ክብደታቸው ይለያያሉ ነገር ግን በተለምዶ የሚከተሉትን ያካትታሉ:
• የመንቀሳቀስ እክሎች • ጥንክር ወይም ግትር ያሉ ጡንቻዎች (ያልተለመደ የጡንቻ እንቅስቃሴ ) • ደካማ ቅንጅት እና ሚዛን • የዘገዩ የእድገት ደረጃዎች (ለምሳሌ፣ መቀመጥ፣ መቆም፣ ማውራት፣ ማኘክ፣ መዋጥና መራመድ ላይ መዘግየት)
💚በእንቅስቃሴ ላይ የተመሰረቱ የ ሲፒ ዓይነቶች
• ስፓስቲክ ሲፒ ፦ በጣም የተለመደ የሲፒ አይነት ሲሆን 70–80% ግትር ያሉ ጡንቻዎች ያሏቸው ሲሆን የእንቅስቃሴ ችግር ያስከትላል። • ዲስካይናቲክ ሲፒ፦ ይህ ደግሞ ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ወይም ያለፈቃድ እንቅስቃሴዎች መኖር ነው። • አታክሲክ ሲፒ፦ ይህ ደካማ ሚዛን እና ቅንጅት እንዲሁም የሚንቀጠቀጡ እንቅስቃሴዎች የሚያሳይ ነው።
📌• የተቀላቀለ ሲፒ፡ ከላይ የተጠቀሱት ዓይነቶች ጥምረት
📌 ተያያዥ ምልክቶች
• የአዕምሮ እድገት ውስንነት • የንግግር እና የቋንቋ እክል • የሚጥል ህመም • የማየት ወይም የመስማት እክል • የመመገብ እና የመዋጥ እክሎች
💚 ሲፒ ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች
• ያለጊዜው መወለድ (በተለይ ከ32 ሳምንታት በፊት)• ዝቅተኛ የልደት ክብደት (<2,500g) • መንትዮች ወይም ከዛ በላይ በአንድ ጊዜ ሲወለድ • የእናቶች ኢንፌክሽን ወይም የጤና ሁኔታ • ወደ ኦክሲጅን እጦት የሚዳርጉ የወሊድ ችግሮች • ከወሊድ በኋላ የአንጎል ጉዳቶች ወይም ኢንፌክሽኖች 💚 ቴራፒዎች ለሲፒ ልጆች •ስፒች ቴራፒ ፡ የንግግር፣ ቋንቋ ፣ የመዋጥ እና የመመገብ ችሎታን ያሻሽላል። • ፊዚዮ ቴራፒ፡ ጡንቻዎችን ያጠናክራል፣ እንቅስቃሴን ያሻሽላል እና የአካል ጉድለቶችን ይከላከላል • የሙያ ቴራፒ፡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን በማላመድ መሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያግዛል። • አጋዥ መሳሪያዎች፡ ብሬስ፣ መራመጃዎች፣ ዊልቸሮችና የመሳሰሉት 💚 ዶክተሮችን፣ ቴራፒስቶችን እና ልዩ አስተማሪዎችን ጨምሮ ሁለገብ እንክብካቤ ለጠቅላላ ክትትል አስፈላጊ ነው። በማሕሌት አዘነ Speech & Language Therapist ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ ☎️ 0940103047 0954999933
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ @ማኅሌት Speech Therapist
🌸በሀገራችን ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው 25 ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒስቶች ብቻ እንዳሉ ያውቃሉ ?
✍በሀገራችን የሚገኙ በስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ በዲግሪ እንዲሁም በማስተርስ ተመርቀው በስራ ላይ የሚገኙ ስፒች እና ላንጉጅ ቴራፒስቶች ስም ዝርዝር ከፎቶ ጋር
1.ማኅሌት አዘነ
2.ልድያ በላይ
3.ብሩክታዊት ማስረሻ
4.ሳራ ተስፋዬ
5.አሚና ኢማሙ
6.ውዳሴ መኮነን
7.ናትናኤል ጌትነት
8.ሳምራዊት በሪሁን
9.ብርሀነ ግደይ
10.ራህማ አረቢ
11.ቢኒያም ገ/አብ
12.ብሩክ ከበደ
13.ራሄል ዮሐንስ
14.ማርቆስ መዝገቡ
15.ብርሀኔ አበራ(ብዙ አመት በዚህ ስራ)
16. አካሉ አሰፋ
17. ልጅአለም መልካሙ
18. ቤተልሄም ፈጠነ
19. ፍቅሩ በዳሳ
20. መሰረት መንግስቴ
21. እየሩሳሌም ተስፋዬ
22. መፅሄት ግርማ
23. ዶ/ር ፅዮን ግርማ
24. ሊድያ ተርዙ
25. ሀናኒያ መልካሙ
26. መልካሙ
27. ቆንጂት
28. እሌኒ
በሀገራችን ስፒች ቴራፒስቶች ያሉባቸው የመንግስት ቦታዎች
🌼የካቲት 12 ሆስፒታል
🌼አለርት ሆስፒታል
🌼 አቤት ሆስፒታል
🌼ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
በሀገራችን ስፒች ቴራፒስቶች ያሉባቸው የግል ውስን ቦታዎች
🌸 ጃዚኤል( ማህሌት) ስፒች ቴራፒ
🌸 ድሮጋ ፊዚዮ ቴራፒ
🌸ኪዩር ሆስፒታል
🌸 ኢስት አፍሪካ ሂሪንግ ኤድ ሴንተር
🌸አሚና ስፒች ቴራፒ
🌸ናቲ ስፒች ቴራፒ
🌸 አኪ ስፒች ቴራፒ
🌸አግዘን ስትሮክ ሴንተር ለአዋቂ
🌸ቤኪ ዴይኬር
🌸አይኪው ዴይኬር
🌸ምግባረ ሰናይ ሆስፒታል
🌸ዋን ፕላኔት ት/ቤት
🌸የኔ ዴይኬር
🌸ብሪቲሽ ፔዲያትሪክ
🌸አጋቶስ ት/ቤት
ናቸው።
📍 ስፒች ቴራፒስት ጋር ሲሄዱ የጤና ቢሮ ብቃት ማረጋገጫ (yellow license) እና ዲግሪውን ወይም ማስተርሱ መጠየቅና ማረጋገጥ አይርሱ!!!
📌 ማሳሰቢያ:- በስልጠና የሚገኝ የስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ ሙያ የለም!!!
📕 በማስተርስ ደረጃ ስለሚሰጥ ለመማር የአዲስ አበባን ዩንቨርስቲ ድረገፅ ይመለከቱ!
ለተጨማሪ ፦
👉 የስፒች እና ላንጉጅ ቴራፒ ለማግኘት
ይደውሉ 👇👇👇
☎️ +251940103047
+251954999933
አድራሻ : መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
ጃዚኤል( ማህሌት) ሰፒች ቴራፒ
በማህሌት አዘነ
ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒስት
Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy
Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic
ፍላሽ ካርዶችን ለማግኘት
https://t.me/JoMaFlashcards

ኮክሌር ኢምፕላንት
ኮክሌር ኢምፕላንት ከተደረገ በኋላ የንግግር ቴራፒስቶች የሚያከናውኗቸው 5 ዋና ዋና ተግባራት፡
1 ድምፅን ማስተዋወቅ: አካባቢያዊ ድምፆችን እንዲሰሙና እንዲለዩ ማሰልጠን።
2 ድምጾችን ማወዳደር: የቃላትን፣ የድምፅ ከፍታ እና ቃና ልዩነቶችን ማጥናት።
3 ቋንቋ ማዳበር: የቃላት ዝርዝርን ማስፋፋት እና አረፍተ ነገር መገንባት።
4 በመስማት ብቻ መነጋገር (AVT): በመስማት ችሎታ ላይ ብቻ ተመስርቶ ንግግርን ማዳበር።
5 የቤተሰብ ስልጠና: ወላጆች በቤት ውስጥ ሊያደርጉዋቸው የሚገቡ የልምምድ እቅዶችን ማዘጋጀት።
ስፒች ቴራፒ ለምትፈልጉ
☎️0954999933
0940103047
📍መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
#ስፒች_ቴራፒ_በኢትዮዽያ #ጃዚኤል_ስፒች_ቴራፒ #speechtherapyinethiopia #speechtherapyinaddisababa #ማሕሌትስፒችቴራፒ @ማኅሌት Speech Therapist
ዳውን ሲንድረም ኖሮባት የመጀመሪያዋ ሕግ ባለሙያ (ጠበቃ) በመሆን የዓለም ታሪክ የሰራችው የ25 አመቷ አና ቪክቶሪያ
አና ቪክቶሪያ የተባለችው የ25 ዓመቷ የዛካቴካስ ሜክሲኮ ተወላጅ ዳውን ሲንድረም (Down syndrome) ኖሮባት የመጀመሪያዋ ሕግ ባለሙያ (ጠበቃ) በመሆን በዓለም ታሪክ ሰርታለች።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት አና ቪክቶሪያ ኤስፒኖ ደ ሳንቲያጎ በዛካቴካስ፣ ሜክሲኮ የሕግ ዲግሪዋን በማጠናቀቅና ተቋማዊ መድልዎዎችን በማለፍ አዲስ የዓለም ታሪክ አስመዝግባለች።
በአፈጣጠር የጤና እክሏ ምክንያት ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ውድቅ ከተደረገች በኋላ፣ በሌላ ተቋም ለአምስት ዓመታት ትምህርቷን ተከታትላ አጠናቅቃለች። አሁን ደግሞ የልዩ ፍላጎት (የአካል ጉዳተኞች) መብቶችን ለመሞገት በስቴቷ ፓርላማ የወንበር እጩ ሆና ለመወዳደር አቅዳለች።
ዳውን ሲንድረም ያለበት ልጅ ቋሚ የህክምና ክትትልና ድጋፍ ከተደረገለት ያሰበውን ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደሚችል ማሳያ መሆኗም ተነግሯል።
DireTube