ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 949 подписчиков, занимая 5 314 место в категории Религия и духовность и 2 236 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 949 подписчиков.

Согласно последним данным от 20 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 404, а за последние 24 часа — 7, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 24.81%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.55% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 957 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 682 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 25.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 21 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 949
Подписчики
+724 часа
+1617 дней
+40430 дней
Архив постов
#ማኅበረ_ዴጎ (ዶጌ) #ማኅበረ_ጻድቃናት)፤ #ጥር_29#ቃል_ኪዳን_የተቀበሉበት፤ #ጥር_30 #ምስዋሮን_በተባለ_ቦታ_የተሰወሩበት_ዕለት_ነው፡፡ ፠ማኅበረ ዴጎ ማለት የደጋጎች ሀገር ማለት ሲሆን የተባለበት ምክንያትም ቅዱሳን ስላሉበት ነው፡፡ በ365 ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ‹‹ ሮምያ›› ከምትባል መንደር የቅዱስ መጽሐፍ ቃል የሆነውን መሠረት አድርገው፤ 1ኛ ‹‹ ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የነርሱ ናትና›› ያለውን 2ኛ ‹‹ አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ብሎ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን አንብበው የዚህን ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው ሃገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ ፠ እነዚህም በአኵሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጢን በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው ለዚሁ ለዚሁማ ከሀገራችን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በጾም በጸሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት ብለው ሱባዔ ገቡ ጾም ያዙ፡፡ ከሱባዔው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልፃ ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው በዚያም በጾምና በጸሎት ፀንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡ ፠ ሦስት ሺህ/3000/ ያህሉ ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሄዱ፡፡ ከነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር፣ ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡ ፠ ተጨማሪ ሦስት ሺ ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋርም ተደመሩ፡፡ ከዚያም የቅዱስ ጳውሎስና የቅዱስ ዮሐንስ መመሪያ ተከትለው ማለት ‹‹ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል›› የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ፀንተው በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማኅበር መጠጣት ጀመሩ፡፡ የማኅበረ ዴጎ ታሪክም ተቀየረ ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ነዳይ ድሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ፡፡ ከእነርሱ ጋርም አንድ ማኅበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃችው፣ እነርሱም ፈቀዱለት እና አንዱ የማኅበሩ አባል ሆነ፤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ፡፡ በዚሁ ጊዜ ‹‹እስቲ ለኔም ተራ ስጡኝ እንደአቅሜ ዝክር ላውጣ፡፡›› አላቸው፡፡ በዚህ ግዜ ግን ድህነቱን አይተው ‹‹አይሆንም አንተ ድሀ ነህ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህና ነው የምትደግሰው ይቅርብህ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹አይሆንም ስጡኝ እንጂ›› አላቸው እነርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡ ፠ ከማኅበርተኞቹ መካከል አሳላፊ ወይም ሙሴ ‹‹ሣይዳ ›› የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው እንግዳና ድሀ ሰው ፈጽሞ አይወድም ነበርና ጌታችንም ከማኅበርተኞቹ መካከል ሲገኝ ደሀ መስሎ ስለነበር በጣም ይጠላው ነበር፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከነርሱ ጋር ሲቀመጥም አንድ ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፡፡ የሆኖ ሆኖ የጌታችን ማኅበር መድረሱ አልቀረም ደረሰ፡፡ እንደማኅበሩ ሥርዐት የወይን ጠጅ የሚጠመቅባቸውን ጋኖች የሚያጥበው ሙሴው /አሳላፊው/ ነው፡፡ ስለሆነም በሥርዐቱ መሠረት ጌታችን ሙሴውን ጠርቶ ጋኖችን እጠብልኝ አለው፡፡ አሳላፊውም በቁጣ ‹‹አንተ ቤትህ የማይታወቅ፤ ከየት አምጥተህ ማኅበር ልታደርግ ነው አንተ ብሎ›› በማለት አናንቆ አልታዘዝህም ብሎ ሄደ፡፡ ይህን የተመለከተው ጌታም አንድ እረኛ ጠርቶ ‹‹አንተ ልጅ ከብቶችህን እኔ እጠብቅልሃለሁና በዚህ ውሀ አምጣልኝ›› አለው፡፡ ትንሹ እረኛ ልጅ ገምቦውን ይዞ ትንሽ ወጣ እንዳለ ጌታ ዘወትር በሚቀመጥበት ድንጋይ ላይ ሆኖ ዘንጉን ወደ ልጁ አቅጣጫ ወረወረው፣ ዘንጉንም ከልጁ ፊት ሂዶ ተተከለ፡፡ ልጁንም ጠርቶ ዘንጉንም እንዲነቅለው አዘዘው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ዘንጉንም ቢነቅለው ውሀ ፈለቀ፡፡ ከርሱ ቀድተህ አምጣልኝ አለው፡፡ ልጁም ከዚህ ውሀ ቀድቶ አመጣለት ጋኖቹን አጠባቸው፡፡ ፠ በበዓሉ ቀን ማህበርተኞቹ ምን ሊያበላን ነው፣ ምን ሊያጠጣን ነው ሳይሉ ኹሉም ተሰበሰቡ፡፡ ጌታችንም በፊታቸው ጋኖቹን ቢባርካቸው የወይን ጠጅ ሞልተው ተገኙ፡፡ ፠ ቀድቶ ቢሰጣቸውና ቢቀምሱትም በጣም ግሩም ጣፋጭ ስለነበር እጅግ አደነቁ፡፡ እነርሱም ጌታን ከጻድቃን አንዱ ስለመሰላቸው ከእግሩ ላይ ወድቀው እስካሁን ድረስ ሳንበድልህ አልቀረንምና ይቅር በለን ብለው ለመኑት፡፡ ተነሱ ብሎ ካስነሳቸው በኋላ እናንተ ምንም አልበደላችሁም የጠየኳችን እድርጋችኋል የበደለኝ ግን አሳላፊው ነው በማለትና አንድም ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ አልሰጠኝምና አፈራርዱኝ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሙሴው/አሳላፊው/ የማያፍር ደፋርና ርጉም ስለነበር ‹‹ይህ ሰው ጌታችን በልቶ አልበላሁም ፣ ጠጥቶ አልጠጣሁም የሚል ስለሆነና ስለማይጠግብ ነው እንጂ እንዲያውም ለናንተ አንድ አንድ ዋንጫ ሲሰጣችሁ ለእርሱ ሁለት ሁለት ነበር የሚሰጠው ብሎ የሐሰት ቃል መለሰ፡፡ ፠ ጌታችንም እንግድያስ እኔ የጠጣሁበት ዋንጫ ትቅረብና ትመስክርብኝ አለው፡፡ በዚሁ ተስማምተው አሳላፊው/ሙሴው/ ሄዶ አንድ ሸራፋ ዋንጫ አምጥቶ በዚህ ነበር የሚሰጠውና የሚጠጣው ብሎ አቀረበ፡፡ ዋንጫዋም ከተቀመጠችበት አንድ ክንድ ከስንዝር ተነስታ ጽዋይቱን ስትመሰክር ‹‹ዓለማትን የፈጠረ አምላክ ምስክሬ ነው እኔ የያዝኩትን የወይን ጠጅ ዕቃ ሙሴም በእጆቹ አልያዝኩትም በከንፈሩ አልነካኝም በሌሎቹ ሰዎች እጅ ግን ተይዤ ያየን ነበር›› አለች ያን ጊዜ እንደ ዳታን እና አቤሮን ምድር ተከፈተችና ሙሴውን ከነልጁ ዋጠቻቸው፡፡ ፠ ማኅበረ ጻድቃንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ተረድተው እንደገና ከእግሩ ወድቀው ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ለመኑት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታ ካደረገላቸው በኋላ ስማችሁ የጠራ በስማችሁ ተዝካር ያወጣ በስማችሁ ድሆችን የረዳ፣ ያለበሰ፣ ያጎረሰ፣ የሰጠ፣ የመጸወተ፣ ቤተ ክርስትያናችሁን የሠራ፥ ያሠራ፣ እሰከ 14 ትውልድ ደረስ ምሬላችኋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይህችን ቦታችሁ መጥቶ የሳመ እየሩሳሌም እንደሳመ አድርጌላችኋሁ አላቸው፡፡ ፠ በኦሪት ሔኖክ፣ ዕዝራ፣ ኤልያስ፤ በሐዲስ ኪዳንም እነ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና በየጊዜውም እንደሚሰወሩ ቅዱሳን እንደዚሁም ጌታችን እነዚህን የማኀበረ ዴጎ ጻድቃንንም ከሞት ተሰወሩ ብሎ በበነጋታው ጥር 30 ቀን ሠውሯቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ይህ ታላቅ በዓል ሆኖ ዛሬም በየዓመቱ ጥር 30 ቀን በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ይኖራል፣ ይከበራልም፡፡ ፠ በገዳመ ዴጎ በዓይን የሚታዩ፥ በእጅ የሚዳሰሱ ተአምራት የታየባቸውና የተደረገባቸው ንዋያት እስካሁንም አሉ፡፡ ወደ አኵሱም ስትሄዱ ታዩት ዘንድ እንጠቁማችሁ፡፡ 1. ጌታችን የተቀመጠበትንና የቆመበትን ድንጋይ ከነምልክቱ 2. ምስዋሮም የሚባል ጻድቃኑ የተሰወሩበትን ስፍራ 3. ከድንጋይ ላይ ሁኖ ወርቅ ዘንግ ወርውሮ ያፈለቀው ማየ ጸሎት ማየ ዮርዳኖስ ብሎ የሰየመው 4. ቁመት ጨምራ ከመሬት ተነስታ እንደ ሰው አፍ አውጥታ የመሰከረችው ዋንጫ 5. ጻድቃኑ ይወቅጡበት የነበረ የድንጋይ ሙቀጫ 6. በማኅበራቸው ጊዜ ሲደግሱባቸው የነበሩ የድንጋይ ገበታዎች 7. ከሀገራቸው ከሮም ያመጡት ባለመስታወት ቋሚ ዕፀ መስቀል፡፡ 8. ርዕሰ ዮሐንስ የሚባል ነገሥታት ከነዘውዳቸው፥ ጳጳሳት ከነአክሊላቸውና ከነመስቀላቸው በዚያን ጊዜ የተሳሉበት ስዕል፡፡

፠#፠ ጻድቁ #አቡነ_ገብረ_ናዝራዊ_ዘደብረ_ኀረይክዋ_ዘጥሙጋ)፤ #ጥር_29_ዕረፍታቸው_ሲሆን፤ የከበረ አጽማቸው በገዳመ ደብረ ኀረይክዋ ከአንድ ቋጥኝ በተጠረበ ሦስት መዓዝን ባለው ድንጋይ ታትሞ ይገኛል፡፡ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ሰሜን ሸዋ ይፋትና ጥሙጋ ደብረ ሲና ተወለዱ፡፡ሥርዐተ ምንኵስናን ደግሞ ከአቡነ ጎርጎሬዎስ (የደብረ ጽጋጋው የታላቁ አኖሬዎስ ልጅ) ከተቀበሉ በኋላ የተወለዱበትን ደብር ሲያገለግሉና በምደረ ሸዋና አካባቢዋ ሲያስተምሩ ቆዩ፤ ንጉሡ ዐምደ ጽዮን የአባታቸውን ሚስት በማግባታቸው ጻድቁ አቡነ ገብረ ናዝራዊ፣ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብና ሌሎች ካህናት ይህንን ተግባር በመቃወማቸው ለጥቂት ሳምንታት በእስር ቤት ቆዩ፤ ጻድቁ ከእስር እንደተፈቱም በላስታ ላሊበላ ለ12 ዓመታት፣ በሐይቅ እስጢፋኖስ ደግሞ ለጥቂት ወራት ሰንብተው፤ ወደ ትግራይ ተጕዘው ከአባ የዕቆብ ዘንድ የመጻሕፍት ትርጓሜን ሲማሩ ቆዩ፤ ዛሬ በስማቸው ወደ ሚጠራው ታላቁ ገዳም እምባ ላህም ደብረ ኀረይክዋ ለምናኔ ከመግባታቸው በፊትም በትግራይ ሃገር እየተዘዋወሩ ሦስት ገዳማትን መሥርተዋል፤ እነርሱም፤ 1ኛ. #አጋዝና_ተራራ /#መበቊል_ቋጥኝ/ (ምዕራብ አዲግራት) 2ኛ. #ከቋጥኝ_ድንጋይ_ፈልፍለው_ያነጿት_ቂዓት_ማርያም፤ /ጻድቁ ለ8ዓመት ቆይተውባታል/ 3ኛ. #ባለ_2ት_ዐምድና_ባለ_1_በር_አድርገው_ያነጹት_ማይ_ኢየሱስ /#ቀበሌ_አዘባ_ቤት_ሓባ_ተራራ/ እነዚህን ገዳማት ከሠሩ በኋላ በዘንዶ እንደ አቡነ አገረጋዊ ወደ ደብረ ኀረይክዋ ተራራ ለምናኔ ወጥተዋል፤ ቦታውን ‹‹ደብረ ኀረይክዋ›› ብለው ራሳቸው ሲሆን የሰየሙት፤ ምክንያቱም ቦታው በተራራማና በተፈጥሮ የተዋበ ቦታ በመሆኑ፤ በተፈጥሮ ቅርጽነቱ ባለ ሦስት ማዕዝን ክብና በገመድ የሚወጣ ገዳም በመሆኑ ሲሆን ደብረ ኀረይክዋ ማለትም የተመረጠ ተራራ (ደብር) ማለት ነው፡ #ላህም_አምባ_ደብረ_ኀረይክዋ #እንደነ #ደብረ_ዳሞ፥ #ደብር_ማርያም #አቤር #አቡነ_ሰላማ ገዳም በገመድ (በመጫኛ) የሚወጣበት ገዳም ነው፤ —— #ጥር_29_ጻድቁና_ሰማዕቱ_አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽና_አቡነ_ማትያስ_በውቢት_ገደል_/ጽላልሽ፥ ከሰም ወንዝ ቆላ ውስጥ የሚገኝ/ #ተወርውረው_ሰማዕትነት_የተቀበሉበት_ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ለብዙ ዓመታት ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2005ዓ.ም. የመቃኞ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶለታል፡፡ ፠ በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው ‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005 ዓ.ም. ጥር 28 ለ29 በዋይዜማ ከገዳመ ማርያም ታቦታቸው ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ምንጭ /ዋልድባ ዋሊ ገጽ/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ #ሰላም_ለዝክረ_ስምከ_ዘይትበደር እምብሩር፤ ወይጥዕም እም ሶከር፡፡ ሰባስትያኖስ ንጹሕ ትሩፈ ምግባር፤ በዝክረ ስምከ ተማኅጸንኩ ኢትኅድገኒ ለገብር፤ አመ ትወፅዕ ነፍስየ እምሥጋ በግብር፡፡ #ሰላም_ዕብል_ለፍጽምከ_መአድም፤ በስመ ሥላሴ ኅቱም፡፡ ሰባስትያኖስ አቡየ ሰላም ሰላም፡፡ በፍጽምከ ተማኅጸንኩ ኢይቅርበኒ ሕማም፤ ማዕተበ ፍጽምከ በፍጽምየ ሢም፡፡ #ሰላም_ለመልክዕከ_ዝብጠታተ ኀጺን ዘተወክፋ፤ ወትዕግስታተ አዝለፋ፡፡ ሰባስትያኖስ ጻማዊ ሱታፌ ሕማሙ ለዘልፋ፤ መልክዐ ገጽከ ኀበ ተጽሕፋ፥ ለመለክዕየ ጸሐፋ፤ ውስተ ምዕራፍከ ረሲ ምዕራፋ፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ #ሰላም_ለዝክረ_ስምከ_ዘይትበደር እምብሩር፤ ወይጥዕም እም ሶከር፡፡ ሰባስትያኖስ ንጹሕ ትሩፈ ምግባር፤ በዝክረ ስምከ ተማኅጸንኩ ኢትኅድገኒ ለገብር፤ አመ ትወፅዕ ነፍስየ እምሥጋ በግብር፡፡ #ሰላም_ዕብል_ለፍጽምከ_መአድም፤ በስመ ሥላሴ ኅቱም፡፡ ሰባስትያኖስ አቡየ ሰላም ሰላም፡፡ በፍጽምከ ተማኅጸንኩ ኢይቅርበኒ ሕማም፤ ማዕተበ ፍጽምከ በፍጽምየ ሢም፡፡ #ሰላም_ለመልክዕከ_ዝብጠታተ ኀጺን ዘተወክፋ፤ ወትዕግስታተ አዝለፋ፡፡ ሰባስትያኖስ ጻማዊ ሱታፌ ሕማሙ ለዘልፋ፤ መልክዐ ገጽከ ኀበ ተጽሕፋ፥ ለመለክዕየ ጸሐፋ፤ ውስተ ምዕራፍከ ረሲ ምዕራፋ፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡

፠ ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡ 1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደር ከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡ 2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡ 3ኛ) መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም፡፡ (አሁን ቅድስት ማርያምበመባል የሚጠራ) እንዲሁም 4ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው ‹‹ኀጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንጽናና ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስብብናል፡፡›› /ቅዱስ እንጦንስ/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑራኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊ
+5
ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑራኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል 2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል 3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/ 4ኛ) አዲስ አበባ አዲስ ሰፈር አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቁ ዮሐንስና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ.ክ. (ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ 5ኛ) ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን) 6ኛ) ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ጥር_22_ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑራኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡
#ጥር_22_ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑራኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡

#ጥር_21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ <<ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡›› ሊቁ ቅዱስ ያሬድ #share ※ዕረፍቷም በደረሰ ጊዜ ጊዜ እመቤታችን በልጅዋ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ መቃብር ላይ ትጸልይ ነበር እንደምታርፍም መንፈስ ቅዱስ ነገራት ከዚህም ቦኃላ ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ እመቤታችንም ጸለየች ልጄ ፈጣሪዩ ሆይ ልመናዬን ተቀብለክ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን አምጣው እንዲሁም ሕያዋን እንደሆኑ ሐዋርያትን ነፍሳቸውንም የለየሀቸውን አምጣቸው አለቸው:: ፠ጸሎትና ምስጋናም አድርጋ ስትጨርስ ሐዋርያት ዕጣን በማጠን የጌታን ስም ጠሩት ከዚያም ጌታ እልፍ አእላፍ ከሚሆኑ መላእክት ጋር ታጅቦ መጣ ፤ያዘጋጀላትንም ነገራት፤ በዙ ተአምራቶችም አመቤታችን ወዳለችበት ስፋራ ለቀረቡ ሁሉ ተደረገ፡፡ ፠#እመቤታችንም የመላእክትን ግርማ እንደምትፈራ ለጌታችን በነገረችው ጊዜ ማንም በእርሷ ላይ ስልጣን እንደሌለው ነገራት:: ፠እመቤታችንም በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ልመናውን #ተቀበለው በመከራ ውስጥም ሆኖ ስሜን ለሚጠራ ከመከራ #አድነው መታሰቢያዬ የሚደረግባትን ቦታ ሁሉ #ባርክ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን መሥዋዕታቸውን #ተቀበል፡፡ ጌታንም #የለመንሺኝንም_ሁሉ_አደርግልሻከሁ_ደስ ይበልሽ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ #ጸጋ_ክብር_ባለመሟልነት ተሰጥቶሻልና #ስምሽን_ተርቶ_የሚለምን_ሁሉ በዚህ ዓለም በሚመጣውም ዓለም አይጠፋም፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀ መዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ … ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ የተጻፈውን ያንብቡ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/ ፠፠፠ ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ ፠፠፠ **#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ #share #share #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት *** (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ ፠ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡ ወረቦቹን ይህን ሊነክ በመጫን ያድምጡ https://t.me/medihanaelem/3679 Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem