ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 16 049 подписчиков, занимая 5 274 место в категории Религия и духовность и 2 238 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 16 049 подписчиков.

Согласно последним данным от 30 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 511, а за последние 24 часа — 3, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 23.32%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.33% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 742 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 658 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 29.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 31 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

16 049
Подписчики
+324 часа
+1077 дней
+51130 дней
Архив постов
#ኒቆዲሞስ፤ #ሰባተኛው_ሳምንት ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፤ በዚህ ሳምንትም ይህ ይታሰብበታል፡፡ ‹‹ኒቆዲሞስ››፤ * አይሁዳዊ ሲሆን ከፈሪሳውያን ወገን የነበረ ነው * በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በዕውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ * ማታ ማታ ጌታችን ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አስቀምጦልናል፦ ፨ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተዓምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ፨ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።›› /ዮሐ. ፫፥ ዘ፩-፲፭/ ለምን በሌሊት ይመጣ ነበር? ⊚ አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን የሆነ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ሀብት ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሥዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ፥ ሀብት ንብረቱን ወዶ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ⊚ በሌላ በኩል ደግሞ የቀን ልብ ባካና ነው፤ ዓይን ብዙ ያያል፥ ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፤ በተጨማሪ ‹‹ሊቅ ነኝ›› እያለ ‹‹እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም›› እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ⊚ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እራሱ እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለዳግም መወለድ /ስለጥምቀት/ በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ስራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡ ⊚ ኒቆዲሞስ በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዐርብ በስቅለቱ ጊዜ፤ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ /ዮሐ. ፲፱፥፴፰/ ከኒቆዲሞስ ሕይወት የምንማረው፡- ፩. ትሕትና፦ ኒቆዲሞስ በትምህርት፣ በሹመት፣ በባለጸግነት የአይሁድ አለቃ ሲሆን አለቅነቱ ግን ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ እርሱ ተገኝቶ ለመማር አልከለከለውም፡፡ /በጽሑፉ መጨረሻ ያለውን ቅኔ ተመልከቱ/ ፪. አለማመካኘት፦ ከመጀመሪያ ሰዎች ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ሰዎች በምክንያተኝነት በአመፅ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ኒቆዲሞስም ወደ ጌታ በመቅረቡ የጸሐፍት ፈሪሳውያን አድማና ግርግር ታላቅ እንቅፋትና ምክንያት መሆን እንደሚችል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት እንደማያዋጣ አውቆ የሚያወጣውን አደረገ፡፡ ፫. ጥበብ፦ በክርስትና ጉዞ ውስጥ ጥበብ የመጀመሪያ ቦታ ትይዛለች፡፡ ኒቆዲሞስም ጕዞውን በጥበብ አደረገ፡፡ በሌሊት ያደረገበት ምክንያት፡- ራሱ መምህር ሆኖ ሌላ ትምህርት አስፈለገው ብለው ሌሎች እንዳይሰናከሉበት፣ የመዓልት ልቦና ስለሚሰበሰብ በቂ ዕውቀት ለማግኘት፣ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት በመዓልትም በሌሊትም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን ለማጠየቅ፣ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲዖል ይገኛሉ ሲል፣ በመዓልትም በሌሊትም ብትፈልጉ ትገኛለች ሲል ነው፡፡ በእውነት ግሩም ጥበብ! ፬. የተነገረውን አምኖ በመቀበሉ፡- ጸሐፍት ፈሪሳውያን ብዙ ምክንያቶች እየደረደሩ የጌታን አምላክነት አምኖ መቀበል ሲያቅታቸው እርሱ ግን ጌትነቱን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ፭. ለእውነት መመስከር፡- እነርሱ ሲክዱ ጌታ ላይም ትርፍ ቃል ሲናገሩ፤ በድፍረት መክሰሳቸውን እየነገራቸው የጌታችን አምላክነቱን በግልጽ ይመሰክር ነበር፡፡ ፮. ጽንዓት፡- ብዙዎች በመከራ ጊዜ ላይለዩት ቃል ቢገቡም መጨረሻ ላይ ያኔ በመከራ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር ሊገኙ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስም በዚች ሰዓት ያንን መከራ ታግሶ በጽነዓት ከዮሴፍ ጋር የጌታን ሥጋ ከመስቀል አውርደው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል፡፡ ምንጭ፤ የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ ፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠ /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

ነገ (ቅዳሜ) ምዝገባው ያልቃል፡፡ እንዳያመለጥዎ!! ከ5 በላይ ጥንታዊ ዋሻ ተቁፋሮ ወደ ተገኘባት፤ በጕዟችን ትምህርትና ምክረ አበው ወደ ሚሰጥባት፤ ወደ ኵሉ ወይን ቅድስት አርሴማ፡፡ 0977 30 17 18

ዛሬና የዛሬ ሳምንት ‹‹ቅዱስ ቊርባን›› በሚል ርዕስ በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ በዐርብ የማታ ጕባኤያችን ላይ ትምህርትና ምክረ አበው አለ፡፡ እንዳያመልጥዎ!

#ክተት_ወደ_ሰሜን_ተራሮች!፤ #ክተት_ወደ_ራስ_ደጀን!፡፡ *የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ወደሆነው፤ *በዓለም ላይ ብርቅዬና ድንቅ የሆኑ እንስሳት (ዋሊያ ጭላቀዳ ዝንጀሮና ቀይ ቀበሮ) የሚገኙበት ወደሆነው! *ብርቅና ድንቅ የሆኑ አዕዋፋት (እነ ላመርጊየር) ማደሪያቸው ወደሆነው፤ *ልዩ ልዩ ዕጽዋት መገኛቸው ወደሆነው፤ *በዓለም ላይ ረጅሙ ፏፏቴ (ጂምባ ፏፏቴ) የሚፈስስበት ወደሆነው፤ *እግሩ ሊማሊሞ አናቱ ራስ ደጀን ወደሆነው፤ *በርካታ ዕንቊ ዕንቊ የሆኑ ገዳማት (ጨነቅ ዋሻ /ቅዱስ ላሊበላ ያነጸው/፤ ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ፤ ሳዶቅ አምባና ሌሎችም ያሉበት ወደ ሆነው፡፡ ….. ……… ወደ ሆነው፡፡ ክተት፥ ክተት ወደ ስሜን!፡፡ በተለይም በቅርብ ርቀት ጎንደርና ትግራይ ያላችሁ፤ በአስቸኳይ ክተቱ፡፡ *ከጎንደር 120 ኪ.ሜ (የ1፡30 መንገድ ጕዞ) *ከሽሬ 100 ኪ.ሜ (የ1 ሰዐት ጕዞ) እንዲሁም ደባርቅ፤ገዲቢዬ፤ ዳባት፤ አምባ ጊዮርጊስ (በጎንደርና ዙሪያዋ፤ በባሕርዳርና ዙሪያዋ ያላችሁ) ባስቸኳይ ክተቱ፤ በአዲዓርቃይ፣ ማይፀብሪ፣ እንዳአባ ጉና፣ አኵሱም፣ አዲግራት (በትግራይና በዙሪያዋ ያላችሁ) ባስቸኳይ ክተቱ፤ #በተለይም ….. የጎንደርና የባሕር ዳር፤ የደብረ ታቦርና የደባርቅ፤ የአኵሱምና የሽሬ፤ የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች … መኪና ከየዩኒቨርሲቲያችሁም ቢሆን ትብብር ጠይቃችሁ ባስቸኳይ ክተቱ፡፡ በአጋጣሚውም የሰሜን ተራሮች እዩ፡፡ #በአካል_መገኘት_ያልቻላችሁ_በጸሎት_አስቡ፡፡ ከአ.አ. ዛሬ ሚያዝያ 4 ያቀኑ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን አሉ፤ ከአ.አ. እስከ ሰሜን ተራሮች ድረስ የምትገኙ በየመንገዱ እንርሱን እየተከታለችሁም ቢሆን ባስቸኳይ ክተቱ፡፡ /ቸር ያሰማን፡፡!!/

#SHAREEEEEEEE_ሼርርርርር_ማድረጋችሁን_እንዳትዘነጉ_!!!!!! መዝሙረ ዳዊት 73፤ ‹‹#መቅደስህንም_በእሳት_አቃጠሉ፤ … #አቤቱ_ተነስ_በቀሌንም_ተበቀል፡፡›› ‹‹በመንጋዎችህ በጎች ላይ መቈጣትን ተቈጣህ፤ መቅደስህንም በእሳት አቃጠሉ፤ አንተ ፀሐይንና ጨረቃን ፈጠርህ፤ ጠላት እግዚአብሔርን ተገዳደረው፤ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣው፤ ዘወትርም የድኾችን ነፍስ አትርሳ፤ አቤቱ ተነስ በቀሌንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜ የተገዳደሩህን አስብ፤ የአገልጋዮችህን ቃል አትርሳ፡፡›› ጽዋው ሞልቶ ተትረፈረፈ፤ 3ት ጊዜ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥሉ፡፡ በጅጅጋ 13 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህናትና ምዕመናን በጭካኔ ተገደሉ ዝም አልን በኤጄሬ 2ት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፣ ካህናት ተደበደቡ ዝም አልን፣ ** ዛሬ ደግሞ በአጣዬ ካራቆሬና ማጀቴ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ፡፤ …….… ከእንግዲህ ወዲያ ግን ዝም አንልም!!!፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ሃይማኖታችንም ሆነ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ዝም አንልም!!!፡፡ #*በአስኬማ ቆብ የተቀዳጃችሁ፤ በፈርጂያ ሰፊ ልብስ የተንቦረቀቃችሁ፤ የመከራ መስቀሉን ምልክት የጨበጣችሁ፤ ….. ለመንግሥትና ለፖለቲካ፤ ለተለያዩ አካላትና ለግለሰቦች ሳይቀር አድር ባይ የሆናችሁ፤ ቤተ ክርስቲያናችንን ያስጎዳችሁ፤ ስትጎዳም እያያችሁ ዝም ያላችሁ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አንስቶ እስከ አናጎንስጢስ መዐርግ ድረስ ያላችሁ፤ *የቤተ ክርስቲያናችንን ከመዐርና ከሱካር የጣፈጠውን፥ ከወተትና ከበረዶ የነጻውን ትምህርቷን ግታችሁ የተማራችሁ ሊቃውንትና መምህራን፤ እናት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሸረበውን ሴራና ደባ፤ የሚደርሰውን ጥፋትና ውድመት እያያችሁና እየሰማችሁ ባልሰማና ባላየ ያለፋችሁ፤ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለመንግሥት አካላትና ለምዕመናን ትክክለኛውንና እውነተኛውን ትምህርት ያላስተማራችሁና ያልገሰጻችሁ፤ *እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስመ ክርስትና ሰጥታ በአገልግሎቷ ተሳታፊ ያደረገቻችሁ ምዕመናን፤ ነገር ግን ጉዳቷን ሰምተን ለሥጋዊ ሕይወታችን ብቻ እየሮጥን ጉዳቷን እንዳልሰማ ዝም ብለን የከረምን፤ *ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ ብላ በሰንበት ትምህርት ቤት ያዋቀረችን ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጉዳት የኛ ጉዳት መሆኑ ሁሉ እስኪዘነጋን ድረስ በአብዛኛው ዘመነኛ ሆነው በመጡ መዝሙር የደነዘዝን፤ የሰ/ት/ቤት ዋና ተልእኮ መዘመር ብቻ የመሰለን፤ ………. ፡፡ *በአንድ ላይ ቢደራጁ ራሳቸው ተጠቅመው ይጠቅሙኛል ብላ ያደራጀችን ማኅበራት፤ የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ከመታደግ ይልቅ በጠበልና ጠዲቅ ብቻ የተወሰንን፤ የቲሸርት ልብስ መልበስን ትልቁ ግልጋሎት ያደረግን …… አብዛኞቻችን ዝም አይነቅዝም ያልነው፤ አምላክ ያያል ይፈርድማልና ይህን አትዘንጉ፤ ታሪክም የዘመኑንና የዕለቱን ታሪክ ይቈጥራልና ይህን አትርሱ፤ ዝምታው ይሰበር፤ ሕግ ከቤተ ክርስቲያን ይወጣልና፤ አጥፊዎችን መንግሥት አልቀጣምና በሕጋችን መሠረት አጥፊዎችን እንገሥጻቸው፥ እንቅጣቸው፡፡ #የመንግሥት አካላትም ሥራችሁ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድማችሁ መጠበቅ፥ መከላከልና መቆጣጠር፤ ችግሮች ሲከሰቱም ባስቸኳይ መፍታት እንጂ፤ …… እንደ ሌላ ሀገር መሪ፤ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ፥ ሰው ከሞተ በኋላ፥ አብያተ ክርስቲያናት ከተቃጠሉ በኋላ፤ ሮጦ ዜናና ዲስኩር መልቀቅ፤ መግለጫ ማውጣት፤ እንዲሁም ለይስሙላ ያህል ድርጊቱን አጥብቀን እናወግዛለን በማለት ምዕምናንንና ሕዝቡን መሸበብና መደለል ሥራችሁ አይደለም፤ ካልቻላችሁ አልችልም ብሎ ቦታውን መልቀቅ አዋቂነት ነው!!፡፡ #የመንግሥት አካላት፤ ከጠቅላይ ሚንስትር እስከ ቀበሌ ሹም፤ ከመከላከያ እስከ ፌደራል፤ ከክልል ልዩ ኀይል እስከ ፖሊስ፤ ከሚሊሻ እስከ አካባቢ ጠባቂ፤ ….. ቤተ ክርስቲያናችን ስትቃጠል ካልደረሰ፤ ሕዝባችን ሲሞት ካልታደገ፤ ችግርን ካልቀረፈ፤ ጉዳትን ካላከመ፤ የራሱን ልብስ ለብሰው አደጋ ጣዮችን ካልገሰጸና ፈልጎ ካልቀጣ፤ ምን ሊሠራ፥ ምንስ ሊያደርግ፥ ስሙስ ለምን መንግሥት ይባላልን!!!!!???? ይግባኝ ለክርስቶስ ፫፡፡ #በጅጅጋ፥ በኤጄሬ፥ በከሚሴና በአጣዬ ያለች ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ባሰብናት፥ ድምጿን በሰማናትና ገጿን ባየናት ጊዜ አለቀስን፤ ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፤ ባላስብሽ አንደበቴ ከጕሮሮዬ ጋር ይጣበቅ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እስከ መሠረቷ ድረስ ፈጽሞ አፍርሱ የሚሉትን ጎስቋሎችን የሚበቀላቸው አምላካችን ብፁዕ ነው፡፡ /መዝ. 136/ #በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ፤ ምንም በመከራ መካከል ብሄድ አንተ ታድነኛለህ፤ በአሕዛብ ቊጣ ላይ እጆቼን ዘረጋህ፤ ቀኝህም አዳነኝ፤ እግዚአብሔር ይበቀልልኛል፤ አቤቱ ይቅርታህ ለዘለዓለም ነው፡፡ /መዝ. 137/ #ኢይትአጸው አናቅጽኪ፤ ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ፥ ሠናይት ሰላማዊት እንተ ናፈቅራ በጽድቅ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፡፡ /ዚቅ ዘሰኔ 21/ (#በተከበሩ_ዕንቊ_የተመሠረትሽ_ቤተ_ክርስቲያን_ሆይ_ደጆችሽ_አይዘጉ፡፡) ##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ፤ አሕዛብ አምላካቸው ማን ነው? ወዴትስ አለ? ቢኖር ኖሮ ለምን ዝም አላቸው? እንዳይሉ ስለ አባቶቻችን ብለህ ተለመንን፤ ኀይልና ብርታቱን፥ ፍቅርና አንድነቱን፥ ጥበብና ማስተዋሉን፥ እውነቱንና ፍርዱን አንተ ስጠን፤ አንተ ተበቀልልን፨ #SHAREEEEEEEE_ሼርርርርር_ማድረጋችሁን_እንዳትዘነጉ_!!!!!!

#ፍኖተ_ሕይወት_/#የሕይወት_ጕዞ/፤ #ሚያዝያ_06/2011ዓ.ም.፡፡ ወደ #ኵሉ_ወይን_ቅድስት_አርሴማ፡፡ **በብዙሃን ዘንድ ዜናው ያልተሰማው፤ 3ት ትላልቅና ሌሎችም ክፍሎች ያሉት፤ ብዙ ንዋያተ ቅድሳት የተገኙበትና በቁፋሮ የተገኘው ጥንታዊ ዋሻ ይጎበኛል፤ **ምክረ አበው በሊቃውንት መምህራን፣ ዝማሬ በዘማርያን ይቀርባል፡፡ **ከሰ/ትቤታችን ምሥረታ ጀምሮ የነበሩና አሁንም ያሉ አባላት በአንድነት የሚሳተፉበት ዐቢይ ጕዞ፡፡ **ለበለጠ መረጃ፤ 0977 30 17 18 (ፎቶው ላይ የምታዩት ተጓዦች፤ ከዚህ በ1990ዎቹ ወደ ደብረ ሊባኖስ የተጓዙ አባላቶቻችን ናቸው፡፡)፡፡

ገብርኄር፤ ስድስተኛው ሳምንት #ገብር ኄር፥ ገብር ምዕመን ፥ ገብር ሀካይ ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ስለ ስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኄር /ስለታማኝ/ አገልጋይ ያስተማረውን ትምህርት ይነገራል ይህንንም የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ይኸውም ማቴ 25፥14-30 ላይ ይገኛል፡፡ (ይህም ክፍል ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል በምሳሌ ካስተማራቸው ትምህርቶች አንዱ ነው)፡፡ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፡ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ፡፡ መክሊት የወርቅ መለኪያ /መስፈሪያ/ ነው፡፡ አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ ፡፡ አንድ ተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቈጣጠራቸው፡፡ *አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክ፤ ‹‹ ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት›› አለ፡፡ ጌታውም፦ ‹‹መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ኄር)፤ በጥቂቱ ታምነሃል በቡዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡፡›› አለው፡፡ *ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፡፡›› አለ፡፡ ጌታውም፡፡ መልካም፡ ‹‹ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ምዕመን) በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ *አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ካልዘራህባት የምታጭድ፥ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ሌቦች እንዳይሠርቁኝ አታላዮች እንዳይቀሙኝ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ መክሊትህ እነሆ›› አለው፡፡ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- ‹‹አንተ ክፋና ሃኬተኛ ባሪያ (ገብር ሀካይ) ካልዘራሁበት እንደማጭድ ፥ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር መክሊትም ላለው ስጡት፤ እሱን ደግሞ ወደ ዘለዓለም ሐዘንና መከራ ወዳለብት ወደ ጨለማው አውጥታችሁ ጣሉት›› አላቸው፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወስድበታል፡፡ አገልጋዮችም ይህንን ክፉ አገልጋይ ወደ ጨለማው አውጥተው ጣሉት፡፡ በዚህ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡ † መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ተሰጥቶናል በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ † በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፤ የሰማነውን ቃለ እግዚአብሔር ለመተግበር እየበረታን ለሌላው ማሰማት ይገባናል፤ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፤ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚያሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ እኛም በሃይማኖት ጠንክረን በምግባር በርትተን ታማኝ ባርያ ልንሆን ይገባል፡፡ ፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠

ማስታወቂያ፤ የጠቅላላ ጕባኤ ጥሪ፤ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የ6 ወር ሪፖርት ቅዳሜ መጋቢት 28 ከቀኑ በ11፡30 ስለሚቀርብ አባላት ሁሉ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ /የቀ.ደ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት/

በቅርበት ላልተገኛችሁ በዓሉን እናስቃኛችሁ፤ ሌሊት ማኅሌቱ በደብሩ ብቻ በሚባሉ የወረብ ቀለማትና በጎንደር የወረብ ቀለማት በድመቅት አደረ፤ (በይበልጥም በመጋቢት መድኀኔ ዓለምና በሐምሌ ገብርኤል ብቻ ተራ በተራ በሚባሉት የዝክረ ስምከ ረግድ ከነቂቃቸው ዕፁብ ነበሩ፡፡/ ሰዐታት ምኑ ይነገራል፤ ጠዋት ኪዳኑን ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ መሩት፤ ረፋድ ላይ ታቦተ ሕጉ ወጣ ብፁዕነታቸውም ካስተማሩት መካከል፤ ‹‹ እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ›› በሚል ርዕስ *መድኀኒትን ለምን ማድረግ አስፈለገው፤ *የማይሞተው ሞተ /ቅዳሴ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፥ ዮሐንስ አፈወርቅ/ *የእኛን ሞት ወስዶ እርሱ ሞተ /ኤፍሬም ሶርያዊ፣ ውዳሴ ማርያም ዘዐርብ/ *የመዳን ቀን ዛሬ ነው፡፡ /ቅዱስ ጳውሎስ/ *በዓሉ ለክርስቲያኖች በንቻ ሳይሆን ለመላው ሕዝበ አዳም ነው፡፡ /እነሆ ለሰው ሁሉ የሚሆን የምሥራች እንግራችኋለሁ፡፡/

#ወጸሐፈ ጲላጦስ መጽሐፈ፤ ወይብል መጽሐፉ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ፡፡ (መስፍኑ ጲላጦስ በመጽሐፉ ‹‹ኢ.ና.ን.አ›› (ኢየሱስ ናእራዊ ንጉሠ አይሁድ ብሎ) ጻፈ፡፡ /ዛሬም በአንገታችን መስቀል ላይ መቀረጽ ያለበት ‹‹ኢ.ና.ን.አ.›› የሚል እንጂ የራሳችንና የሌሎች ስም መሆን የለበትም!!! #አውረድዎ እምዕፅ፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውሰ፡፡ ዘንብን የምትሰጥ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ሆይ ተጠማሁ ባልክ ጊዜ፤ ከርቤና ሐሞት የተቀላቀለበትን አጠጡህ!! ከእንጨት መስቀል ላይ አወረዱህ፤ (ሥዕሉ ከጥንታዊቷ ገዳም ከተድባበ ማርያም ፎቶ የተነሣ ጥኝታዊ ስዕል ነው፡፡)

#ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ምሬሃለሁ ይቅር ብዬሃለሁ በለኝ፤ ከአንተ በቀር ቸር ይቅር ባይ የለምና፡፡ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም፤ እስመ አልቦ ዘእንበሌከ ዘይሜሕር ቃል መድኀኔዓለም፡፡ #በእንተ ማርያም ወላዲትከ፤ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፤ እግዚኦ ኢታስተሃፍረነ በቅድሜከ መድኔዓለም፡፡ (ስለ ወለደችህ እናትህ ማርያም፤ ስለ አጠመቅህ ዮሐንስ ብለህ አቤቱ አምላካችን ሆይ፤ በፊትህ በቆምን ጊዜ እንዳታሳፍረን፡፡