ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 16 047 подписчиков, занимая 5 283 место в категории Религия и духовность и 2 238 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 16 047 подписчиков.

Согласно последним данным от 26 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 518, а за последние 24 часа — 5, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.13%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.43% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 033 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 674 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 29.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 27 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

16 047
Подписчики
+524 часа
+1057 дней
+51830 дней
Архив постов
#ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ #ሰላም_ለዝክረ_ስምከ_ዘይትበደር እምብሩር፤ ወይጥዕም እም ሶከር፡፡ ሰባስትያኖስ ንጹሕ ትሩፈ ምግባር፤ በዝክረ ስምከ ተማኅጸንኩ ኢትኅድገኒ ለገብር፤ አመ ትወፅዕ ነፍስየ እምሥጋ በግብር፡፡ #ሰላም_ዕብል_ለፍጽምከ_መአድም፤ በስመ ሥላሴ ኅቱም፡፡ ሰባስትያኖስ አቡየ ሰላም ሰላም፡፡ በፍጽምከ ተማኅጸንኩ ኢይቅርበኒ ሕማም፤ ማዕተበ ፍጽምከ በፍጽምየ ሢም፡፡ #ሰላም_ለመልክዕከ_ዝብጠታተ ኀጺን ዘተወክፋ፤ ወትዕግስታተ አዝለፋ፡፡ ሰባስትያኖስ ጻማዊ ሱታፌ ሕማሙ ለዘልፋ፤ መልክዐ ገጽከ ኀበ ተጽሕፋ፥ ለመለክዕየ ጸሐፋ፤ ውስተ ምዕራፍከ ረሲ ምዕራፋ፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡ (የስብስትያኖስ ቤተ ክርስቲያን ከአዴት በተጨማሪ ያለበትን ጠቁሙን ቢቻል በፎቶ ጭምር፤ አዴት አካባቢ የምትገኙ የፈትለ ሥላሴን ገዳም ፎቶ ላኩልን) ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

፠ ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡
+5
፠ ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡ 1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደር ከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡ 2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡ 3ኛ) መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም፡፡ (አሁን ቅድስት ማርያምበመባል የሚጠራ) እንዲሁም 4ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው ‹‹ኀጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንጽናና ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስብብናል፡፡›› /ቅዱስ እንጦንስ/ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘው
+5
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል 2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል 3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/ 4ኛ) አዲስ አበባ አዲስ ሰፈር አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቁ ዮሐንስና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ.ክ. (ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ 5ኛ) ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን) 6ኛ) ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን)

#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፯፡፡ #ዐርብ_ጥር_22፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተና
#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፯፡፡ #ዐርብ_ጥር_22፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. ……እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ በብዙ ጕባኤያት ላይ ያልተዳሰሱ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ጕባኤ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ፤ #ደግመን_እንላለን_ይህ_ትምህርት_በፍጹም_እንዳያመልጣችሁ!!!!! ለተከታታይ ሳምንታት፤ ትምህርቱ ተከታታይነት ስላለው መቅረትና ማርፈድ አይመከርም!!፡፡ (፻፶፰ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ) #ዐርብ_ጥር_፳፪፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት አሁንም በድጋሚ እንላለን ለሕይወታችን ወሳኝና በብዙ የትምህርት ጕባኤያት ላይ የማይዳሰሱ ትምህርቶች ስለሆኑ እንዳያመልጣችሁ!!!! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

ለአባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ አስቀድመን መንፈሳዊ ሰላምታችንን በመድኃኔዓለም kርስቶስ ስም እያቀረብን ሰ/ት/ቤታችን ከደብራችን ሙሉ ማኅበረ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር የፊታችን ቅ
ለአባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ አስቀድመን መንፈሳዊ ሰላምታችንን በመድኃኔዓለም kርስቶስ ስም እያቀረብን ሰ/ት/ቤታችን ከደብራችን ሙሉ ማኅበረ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር የፊታችን ቅዳሜ 23/05/2012 ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ በወቅታዊ የሰ/ት/ቤታችን ጉዳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንድናደርግ ቀጠሮ ተይዟል፡፡ ስለሆነም ሁላችሁም የሰ/ት/ቤቱ አባላት ይህንን ጥሪ ቸል ሳትሉ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድንገናኝ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ሰዓት ይከበር!! ላልሰሙ አባላት መልእክቱን እናድርስ!!

#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/ ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ *እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ (የሎዛ ማርያምና የጥር 21 በዓል አከባበሯን ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ፠ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ማኅሌ እነሆ ብለናል፡፡ ፠ ወረቦቹን በድምፅ ከፈለጉ በቴልገራም አድራሻችን ያገኛሉ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ HYPERLINK "https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት- ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤  HYPERLINK "https://t.me/medihanaelem