cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot

Больше
Рекламные посты
9 234
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
+1330 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
#ዕርገት_ክርስቶስ ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ። ~~~ እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ: አምላካችን በመለከት ድምፅ። ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ,,,። መዝ 46(47):5 ጌታችን እንደተነሣ አርብዓ ቀን ሲሆነው ዐረገ። ይህም የአጋጣሚ ሳይሆን በትንቢት የተነገረ ነበር። ሙሴ ዘፍ:3:22 "አዳም መልካሙንና ክፉ እንዲያውቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" እንዳለ። ዳዊትም በመዝ:67(68):18 "ምርኮህን ማርከህ ወደ ሰማይ ዐረግህ።" እንዳለ። ጌታችን ራሱ በዮሐ: 20:17 ለመግደላዊት ማርያምም: "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና: አትንኪኝ።" እንዳላት። ዕርገቱ ቀድሞ የታወቀ ነበር። ጌታችን ለምን ዐረገ? ጌታችን ከሰማያት የወረደው የወደቅነውን ለማንሣት ወደ ክብር ለመመለስ ነውና: ይህንን ፈጽሞ ዐረገ። ለምን? 1: ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ለመላክ። "በዓለሙ ሁሉ እንድታስተምሩ: ኃይሉን ብርታቱን ሙቀቱን መጽናናቱን ጥበብን የሚገልጥላችሁን እልክላችኋለሁ።" እያለ። ዮሐ. 15:26 2: ስፍራን ለማዘጋጀት። ለሐዋርያት ለምእመናን። ራስ ክርስቶስ ካለበት ሕዋስ ምእመናን መገኘት ግድ ነውና። እርሱ ካለበት እኛ እንድንኖር ቦታ ሊያዘጋጅልን ዐረገ። ዮሐ. 14: 2። ይህን መሠረት አድርገን "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር,,," እንላለን። ሀገራችን በሰማይ ከአባታችን ዘንድ ሆነልን። ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ። 3: ክብሩን ገናንነቱን የባሕርይ አምላክነቱን ለመግለጥ ዐረገ። "መላእክትና ሥልጣናት ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።" 1ጴጥ. 3:22። እንዲሁም "በሥጋ የተገለጠ: በመንፈስ የጸደቀ: ለመላእክት የታየ: በአሕዛብ የተሰበከ: በዓለም የታመነ: በክብር ዐረገ። 1ጢሞ. 3:16 "አልቦ ዘዐርገ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ።" ዮሐ3። 4: ዕርገተ ጻድቃንን ለማሳወቅ ዐረገ። "እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው: ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። 1ተሰ. 4:17 ሙሽራዪቱ ከሙሽራው መለየት አትሻምና። "ዐርገ ከመ ያለብወነ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን። የንጹሐን ጻድቃንን ዕርገት ያስረዳን ዘንድ ዐረገ።" እንዲል ስንክሳር። 5: ከድንግል እመቤታችን በተዋሐደ ሥጋ በክብር እንዳረገ: እንዲሁ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኰት እንደሚመጣ ለማስረዳት ዐረገ። ራዕ. 1:7 በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ: "የወጉት ሁሉ ያዩታል።"እንዲል። በመሆኑም እያንዳንዳችን:— 1: ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ። ሁሌ ሳታቋርጡ አመስግኑ: ክብርን ያጎናጸፈን ከክብር ወደ ክብር የመለሰን እርሱ ነውና። "ሀቡ አኬቴተ ለእግዚአብሔር።" እንዲል ዳዊት 2: "እግዚአብሔር ዐረገ" የተባለው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ መሆኑን አውቀን: ሎቱ ስብሐት! "አምላክ አይደለም" የሚሉትን እናስረዳቸው ዘንድ ይገባል። 3: እንዲሁ እያየነው በክብር እንዳረገ ዳግም ይመጣልና: በሃይማኖት ጸንተን በምግባር ቀንተን ልንገኝ ይገባል። 4: በሰማይ መኖሪያ ያለን ሰማያውያን የሰማይ ዘጎች ነንና አምላካችንን ተስፋ እናድርግ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
4459Loading...
02
Media files
3900Loading...
03
Media files
3370Loading...
04
ያረገው ከሰማይ የወረደው ከድንግል ማርያም የተወለደው የፍጥረት አስገኚ የዓለም ሠራኢ መጋቢ እግዚአብሔር ነው ። ༺◉❖═───◉●◉♰♰♰◉●◉────❖◉༻ #በዓለ_ዕርገትን ስናከብር አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በዚህ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ኖሮ ከማኅበረ መላእክት ተለይቶ ይኖር ለነበረ ለአዳም ጽንዐ ነፍስ ልጅነት ስጥቶ ከማኅበረ መላእክት ጋር አንድ አድርጎ ዐረገ ስንል ነው ። ስለዚህ ያረገው #ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ ተብለው ከሚመስገኑ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ መውደቃችንን በግብረ ዲያብሎስ መያዛችንን በእግረ አጋንንት መጠቅጠቃችንን አይቶ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ስለሰው ልጅ ፍቅር ሲል መከራ የተቀበለው በሞቱ ሞታችንን በቁስሉ ቁስላችንን ያደረቀ የሰውን ልጅ ከዲያብሎስ አገዛዝ ያላቀቀ የባርነት መዝገባችንን የፋቀ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። #ነቢዩ_ዳዊት ያረገው የፍጥረታት አስገኚ እግዚአብሔር እንደኾነ ሲዘምር (እግዚአብሔር በዕልልታና በመለኸት ድምፅ ወደ ሰማይ ዐረገ ) ዐረሲል ያረገው ከሰማይ የወረደው ከድንግል ማርያም የተወ ለደው የፍጥረታት አስገኚ የዓለም ሠራኢ መጋቢ እግዚአብሔር እንደኾነ ነግሮናል (መዝ46፥5) ጌታችን ወደ ሰማይ ሲያርግ የነበረውን ድባብ ምን ይመስላል ቢሉ ፦ ቢታንያ ሲደርስ መሄዱን ትቶ ቆመ ደቀ መዛሙርቱም ከበውት ቆሙ ጌታም በፍቅር ዐይን አያቸው እጆቹንም አንሥቶ ሲባርካቸው ከማንኛውም ምድራዊ ስበት በበለጠ ኀይል ከመካከላቸው ተነሥቶ ወደ ሰማይ ዐረገ « ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ዐርጋለሁ » ይህን እየተናገረ ሳለ ደመና ነጠቀው ከዐይኖቻቸውም ሠወረው ። ዳግመኛ መብረቅ የለበሱ ሁለት ሰዎች ታይዋቸው እናንት የገሊላ ሰዎች ቆማችሁ ሰማይ ሰማይን ለምን ትመለከታላችሁ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያርግ እንዳያችሁ ዳግመኛም በክብር ወደ እናንተ ይመጣል ። « ሞቱን እየተናገርን ትንሣኤውንና ወደ ሰማያት ማረጉን አምነን ዳግመኛ በክብር መምጣቱን ተስፋ እናደርጋለን ። » እንዲል ( ድጓ ዘጰራቅለጦስ ) ደቀ መዛሙርቱም ጌታቸውን ከዐይናቸው እስኪሰወርና አይኖቻቸው እስኪፈዙ ድረስ በአድናቆትና በፍቅር ወደ ላይ ተመለከቱ ወዲያውኑ የክብር ደመና ከዐይናቸው ሰወረው ። የጌታ ዕርገት #የርቀት_ያይደለ_የርሕቀት_ነው ይህ ማለት መርቀቅ ሳይሆን መራቅ ነው ለምሳሌ አውሮፕላን ከምድር ሲነሣ ቀስ እያለ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ አካሉ እያነሰ እያነሰ ይሄዳል በመጨረሻም ወፍ እስኪመስለን ድረስ ለዐይናችን ይርቃል አምላካችንም ልክ እንደዚያ የሐዋርያት ዐይን ማየት እስከቻለበት መጠን ድረስ ከፍ ከፍ እያለ ወደ ሰማይ ዐርጓል ። መላእክትም የደመና ሰረገላም መስለው በተቀበሉት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጥዑም የሆነውን የመላእክትን ዝማሬ ሰምተዋል መላእክትም ትኩር ብለው የጌታን ዕርገት ለሚመለከቱ ሐዋርያት « እናንተ የገሊላ ሰዎች ወደ ሰማይ ሲወጣ ያያችሁት ተመልሶ ይመጣል » የሚል ተስፋ አበሠሩአቸው። ደቀ መዛሙርቱም « እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ » ሲል የሰጣቸውን ተስፋ እያስታወሱ ከቢታንያ ተመለሱ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
3773Loading...
05
Media files
4821Loading...
06
የኢትዮጵያን ፡ ህዝብን ፡ አብዝቶ ፡ የሚወደው ፡ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ እንዲህም አላቸው #ወዳጄ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ_ሰላም_ላንተ_ይሁን እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው ። አባታችንም #አቤቱ_ጌታ_ሆይ_የኢትዮጰያን_ህዝብ_ማርልኝ አለው ፤ እነሆ ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው። በግብጽ በርሃ 300 አመት የኖረ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ወጥቶ በዝቋላ ገዳም እህል ሳይበላ ውሃ ሳይጠጣ ልብስ ሳይለብስ 262 አመት የኖረ ኑሮውም እንድ ሰው ያልነበረ በምድር ላይ እንደ መላእክት ሆኖ የኖረ ። የሃይማኖር አርበኛ ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ የበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ የሚወዳት « አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ» ብሎ ፈጣሪውን የለመነ ፤ ምድራዊ ምግብ ያልተመገበ። የእናቱን ጡት እንኳን ያልጠባ፤ ልብስ፤ መጠለያ እንኳን ያልፈለገ ፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ መጋቢት 5 ቀን ሩጫውን ጨረሰ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
5577Loading...
07
የ፳፻፲፮ ዓ.ም ቀሪ ኦርቶዶክሳዊ ዐበይት በዓላት እግዚአብሔር ጠብቆ ያድርሰን።
6094Loading...
08
ነ ባ ቤ ፡ መ ለ ኮ ት ፡ ቅ ዱ ስ ፡ ዮ ሐ ን ስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የኤፌሶን ኮከብ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የወንጌል ሰባኪ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የምድር መልአክ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ምሥጢር ጠባቂ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ እንደ ፀሓይ ብሩህ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ እንደ ጽና ዕጣን ምዑዝ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ በፍጥሞ ያለ የብርሃን ምሰሶ ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ መሐይምናንን የሚጠራ ተናጋሪ መለኸት ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ በቤተ ክርስቲያን የሚሰማ የትንቢት በገና ነው ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የእግዚአብሔር ክብር በአሕዛብ ላይ የገለጠ ነው አነጋገርህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ፤ ለአፌ ከማርና ወተት ይልቅ ጣፈጠኝ የሕግህ ቃል እንደ ማር ወለላ ነው ከብዙ ወርቅና ከብዙ ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል ፣ ስለዚህ ከወርቅና ዕንቍ ይልቅ ትዕዛዝህን ወደድኩ ።
6263Loading...
09
Media files
5400Loading...
10
🌹🌹#ቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መልአክ🌹🌹🌹 "ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ በብርሃን ጽዋ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው" #ሰዳዴ አጋንንት ነው። ሄኖ፡ 10፥8 ድርሳን ዘፋኑኤል #መጋቤ ድንግል ነው፡፡ ተአምረ ማርያም #ማኅሌታዊ ነው። #በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ ሄኖ፡ 20፥39 #ከአራቱ የዓለም ማዕዝናት ሹም አንዱ ነው፡፡ #ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው።መዝ፡33፥7 #ካህነ ንስሐ ነው። ሄኖ፡ 10፥5 #ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ 2ኛ ነገ፡6፥14 #አጭር_ማብራርያ ድርሳነ ፋኑኤል ላይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ሰዳዴ ሰይጣናት ወመድፍነ አጋንንት እያለ ይጠራዋል ይህም ማለት ሰዎችን በልዩ ልዩ በሽታዎች እና እንቅፋቶች ሰዎችን የሚያሰናክሉ አጋንንትን እያሳደደ ወደ ጥልቁ የሚከታቸው መልአክ ነው ሲል ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል በ2ኛነገ፡ 6፥14 ላይ የሶሪያ ንጉሥ ወልደ አዴር እሥራኤልን በቁጥጥር ሥር ባደረገ ጊዜ ኤልሳዕንም ሆነ የእሥራኤልን ልጆች ለማዳን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ሰራዊቱን አስከትሎ በከተማዋ ሠፈረ ከዛም የጠላትን ሰራዊት ዐይን አጠፋ ለኤልሳዕም ሆነ እሥራኤል ልጆች የድል ካባ በአንድ ምሽት አለበሳቸው ከዐይናቸውም ተሰወረ ይህ ታላቅ መልአክ በ1ኛነገ፡ 19፥5-18 በምናገኘው ታሪክ ላይ ነቢዩ ኤልያስን ከተኛበት እየቀሰቀሰ እንጎቻን ብላ ሲለው የነበረው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ነው፡፡ ሌላው የአዳም 7ኛ ትውልድ የሆነው ሞትን ሳያይ የተሰወረው ሄኖክ እንዲህ ሲል ጠቅሶታል ‹‹አራተኛውም የዘለዓለም ሕይወትን የሚወርሱ ሰዎች ተስፋ ሊሆን ንሥሓ በሚገቡ ሰዎች ላይ የተሾመው ፋኑኤል ነው›› ሄኖ፡ 10፥15 #ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና_ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና #ጠብቆቱ_ያግዘን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
6833Loading...
11
#በዓታ_ለማርያም እንኳን እናታችን እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት የመታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ ከትናንት ወዲያ ኦ ማርያም መንክር ልደትኪ ወዕጹብ ግብርኪ እያልን በታላቅ ደስታ አክበረናል በሶስተኛው ቀን ደግሞ እናታችን እመቤታችን ወደቤተመቅደስ የገባችበትን የመታሰቢያ ቀን ካህናት በቤተመቅደስ ኦ ማርያም በመኑ ወበአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ እያሉ ሊቃውንቱ በማህሌት በቅኔ በዜማ ያከብራሉ የኃዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦዕኪ እንዘ ትጠብዊ ኃሊበ ሀና፤ ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤ ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና፤ ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና። ማርያም ሆይ የእናትሽን የቅድስት ሐናን ጡት እየጠባሽ ከእናትሽ ተለይተሽ ወደ ቤተመቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽን ሳስብ ያሳዝነኛል በደመና የሚረማመድ የእሳት አበባ ቅዱስ ፋኑኤል ከጓደኞቹ እሳታውያን መላእክት ጋር ሰማያዊ መና እየመገበሽ በቅድስና ማደግሽንም ሳስብ እጅግ ደስ ይለኛል ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና፤ ከመ ታቦተ ዶር ዘሲና፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በቅድስና፤ ሲሳያ ህብስተ መና፤ ወስቴሃኒ ስቴ ጽሙና። ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የሆነች ድንግል ማርያም እንደ ቃል ኪዳኑ ታቦት በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖረች ምግቡዋም ሰማያዊ መና ነበር መጠጥዋም ሰማያዊ መጠጥ ነበር ጽርሕ ንጽሕት ማርያም፤ ተፈሥሒ ሀገረ እግዚአብሔር፤ ቃል ቅዱስ ይወጽእ እምኔኪ፤ አእላፍ መላእክት ይትለአኩ የእግዚአብሔር ሀገሩ የምትሆኝ ንጽህት አደራሽ እመቤታችን ሆይ ደስ ይበልሽ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከአንቺ ሰው ይሆናል እልፍ መላእክትም ያገለግሉሻል ይላኩሻል እያሉ ሙሉ ሌሊት ያመሰግኗታል በረከትዋ ይደርብን የእግዚአብሔር ሀገር የቅዱሳን ከተማ የምዕመናን መጽናኛ ድንግል ማርያም በጎ በጎውን ታሰማን ክፉውን ታርቅልን አማላጅነትዋ ቃልኪዳንዋ አይለየን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
6182Loading...
12
Media files
5300Loading...
13
༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻ #ሊቁ_ማሕሌታይ_ቅዱስ_ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ስለ እመቤታችን እንዲህ እያለ ይመሰክርላታል ❝ በመላእክት ትመሰገናለች ደም ግባቷ ያማረ ነው ቃሏ እንደ ማር የጣፈጠ ነገሯ ኹሉ በሰላም የተመላ ነው ....ውበቷ ደም ግባቷ ከጨረቃና ከፀሓይ ይልቅ ያምራል ከንፈሮቿ ፍሕሶ እንደሚባል አበባ ቀይ ናቸው የጒንጯ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው ። ❞ እያለ ይመሰክርላታል #አይ_መታደል_አይ_መባረክ . #የአምላክ_እናት_ሆይ_ዛሬም_ለእኛም_በእጅጉ_ለምንወድሽ . #ለልጆችሽ_በአማላጅነትሽ_በረድኤትሽ_ነይልን ፡፡
8202Loading...
14
ጸ ጋ ን ፡ የ ተ መ ላ ሽ ፡ ሆ ይ ፡ በ ም ን ፡ ስ ም ፡ እ ን ጥ ራ ሽ ? መርከብ እንበልሽ ይሆን ? ቀዛፊው ልጅሽ ነው ጽዋ እንበልሽ ይሆን ? ልጅሽ የመለኮት ወይን ነው የግንብ ቤት እንበልሽ ይሆን ? ገንቢው ልጅሽ ነው ሰማይ እንበልሽ ይሆን ? ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው የአትክልት ቦታ እንበልሽ ይሆን ? ልጅሽ የወይን ተክል ነው መሶበ ወርቅ እንበልሽ ይሆን ? ልጅሽ የሕይወት እንጀራ ነው መሠዊያ ( መንበር ) እንበልሽ ይሆን ? ልጅሽ ሊቀ ካህናት ነው የብርሃን ደጃፍ የእውነተኛ ፀሐይም መውጫ የገነት መክፈቻ በጎ ነገርንና ቅድስናን የተመላሽ እመቤታችን ማርያምሆይ ምስጋና ልመና ላንቺ ይድረስ!
7275Loading...
15
#የመጥምቀ_መለኮት_የቅዱስ_ዮሐንስ ራስ የገዳዮቹን ኃጢአት አጉልቶ የሚያጋልጥ መብራት ነበር #መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ በቃሉ ከተናገረው በላይ በሞቱ የሔሮድስን ኃጢያትን ከፍ አድርጎ አሳይቷል ። አሁንም ክፋታቸውን ለመደበቅ እንደ ሔሮድስ ንጹሐንን የሚያስሩ የልባቸውን ሠርተው በግድያው ላይ አሲረውና ተስማምተው መግደል የፈለጉትን ሰው በሞተላቸው ጊዜ የውሸት የኀዘን መግለጫ የሚሠጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንደ ሔሮድስ ዕብደት ነው ገድሎ መገላገል አይቻልምና ። ከማንም በላይ የሟች ደም የሚጮኸው በገዳይ ሕሊና ውስጥ ነው ሔሮድስ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስን ገድሎ ተረበሸ ። መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስን በሰይፍ መቅላትና ስብከቱን ዝም ማስባል የሚቻል መስሎት ነበር ነገር ግን መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ ሰማዕት ሲሆን በገዳዩ ሔሮድስ ልብ ውስጥ ስብከት ጀመረ መስታወቱን በመስበር የፊት ላይ ጉድፍን መደበቅ እንደማይቻል ሁሉ ንጹሐንን መግደል በሞታቸው መሳቅ ይቻል ይሆናል ። የደማቸው ድምፅ ግን ከራስ ከሕሊና ማጥፋት አይቻልም ። . #አሁንም_እንላለን_ከሟች_በላይ_ገዳይ_ያሳዝናል
8603Loading...
16
Media files
7000Loading...
17
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤ 3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤ 6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
9480Loading...
18
#በየወሩ_28_በመጣ_ቁጥር_የመላእክት_እና_የሰው_ልጅ_የአንድነት_ምስጋና_ይታሰባል የሰው ልጅ ጥንቱንም ለምስጋና እንደተፈጠረ የሚያሳየው በቤተልሔም ለምስጋና ከመላእክት ጋር መሰለፉ ነው እንደ መላእክት እያመሰገነ ምስጋናው እረፍቱ ምስጋው ስራው ሁኖ ይኖር ነበር እንዳለመታደል ሁኖ የጠላት ምክር ሰምቶ ከመላእክት ማህበር ተለይቶ ስርቆት ተሠማራ የሚወዱት የሚያከብሩት ቅዱሳን መላእክት ፊት ነሱት ከጠላት ጋር እየመከርክ በጌታህ ላይ እያመጽክ በዚህ አትኖርም ውጣ አሉት ፍጥረት አመጸበት የሰው ልጅ ከትናንቱ ስህተት መማር አቅቶት ዛሬም በስህተት ላይ ስህተት እየሰራ ተፈጥሮን እየተቃወመ በእግዚአብሔር ላይ ዳግም እያመጸ ለስደት ይዳረጋል ዓለምን ምስቅልቅል ያደረጋት የዓመጻ ውጤት ክፋት ነው ዛሬ በሰው ልጅ ላይ ያላመጸ የለም ምድር አምጻለች ወንዞች አምጸዋል አዝርዕት አትክልት እፀዋት አምጸዋል አየሩ አምጾዋል ነፋሱ በሽታ ሁኗል እኛ እስካልተመለሰን ድረስ አመጻው ይቀጥላል እኛም የዓመጻ ፍሬያችንን እየበላን እንቀጥላለን የአማኑኤል መገለጥ አማኑኤል በቤተልሔም ሰው ሁኖ ተገለጠ እንስሳት ሳይቀር አምሓ እጅ መንሻ አቀረቡለት ፍጥረት ሁሉ በየችሎታው እጅ መንሻ አቀረበ ዕፀዋት ያለጊዜያቸው በፍሬ አሸበረቁ ወንዞች ማር ወተት ዘይት ወይን ሆኑ መላእክት በተለየ ምስጋና አመሰገኑት ከዚያ በፊት አመስግነውት በማያውቁት ምስጋና አመሰገኑት ምክንያቱም እግዚአብሔርን በድምጽ እንጂ በመልክ አያውቁትም ነበርና በድምጽ የሚያውቁትን በአካል አይተውት ደስ ብሏቸዋልና በአዲስ ምስጋና አመሰገኑት ይላል ከመላእክት ጋር በአንድነት እንድናመሰግነው የፈቀደልን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን!
8797Loading...
19
#እባክዎን_ከእሳቱ_ላይ_አይውረዱ አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። አገልጋይም (መነኩሴም) ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወትዎ ቀዝቅዛብዎታለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደው በርደዋልን? የሕያውነትዎ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን ? ድስት የተባለ ሰውነትዎ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን ? ዙሪያ ገባዎ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነቶ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ አጋንንት ተወሮ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ይውጡ፡፡ #ወዳጄ_ሆይ! ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፡49) ላይ ተቀምጠው የድስትነትዎን ሙቀት ይመልሱ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፡13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደው የሕይወትዎን የኃጢአት ብርድ ያስወግዱ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትዎን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ይንሱ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትዎን በከዊነ እሳትነት ይቀድሱ፡፡ እባክዎን በቶሎ ወደ እሳቱ ይውጡ፡፡ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካሉ ድረስ እርሶ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት የራቁ ኖት፡፡ ወዳጄ እባክዎን ከእሳቱ ላይ አይውረዱ፡፡ #ወዳጄ_ሆይ! እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርዎን እንዳይዘነጉ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነትዎ ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ይድናሉ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክዎን ከእሳቱ ላይ አይውረዱ፡፡ በኃጢአት እጅ እጅ ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን! #በኅሊና_በለጠ #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
8305Loading...
20
#ቅዱስ_አማኑኤል ‹‹እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› ኢሳ 7፤14 በማለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ መልአኩ እንዲህ ሲል አበሠራት፤ ‹‹እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይለዋለች፤ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።›› ማቴ.፩፥፳፫ አማኑኤል ‹አማነ› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፤ ትርጓሜውም የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ የተዋሐደ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደኛ የሆነ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ እንዳስቀመጠው "...እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?..." ሮሜ. 8፥31 አምላካችን ሀገራችንን ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን። ቸርነቱ አይለየን!
7785Loading...
21
#መድኃኔ_ዓለም " ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ክርስቶስ ሆይ ቤተ ክርስቲያንህ ትሰግድልሃለች፣ ሙሽራህም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፣ በልዑላን ጥቅም፣ በሱራፌል ቅዳሴና በኪሩቤል ውዳሴ በመላእክትም ምስጋና፣ በትጉሃን ልመና ፣ በቅዱሳንም ፍጹምነት፣ በአዳም ንጽሕና በኖኅም መሥዋዕት በአብርሃም እንግዳ ተቀባይነት፣ በይስሐቅ ቸርነት፣ በያዕቆብ መገለፅ። በዮሴፍ እሥራት ፣ በኢዮብ ትዕግሥት በሙሴም የዋህነት በኤልያስም ምስጋና። በሐዋርያትም ማፍቀር፣ በቅዱሳንም ልመና፣ በተሰደዱ ሰዎች ድካም፣ ባልበደሉ ሰዎች ጽድቅ ንጽሕናን ባገኙ ሰዎች ትሕትና፣ በንጹሐን ገድል፣ ከምግብ በተለዩ ሰዎች ትምህርት፣ ፍጹማን ስለሆኑ ቅዱሳን ጽድቅ ፣ በምድር ዳርቻ ርቀት፣ በባሕር አዝዋሪም ጥልቅነት፣ በመባርቅት፣ ብልጭታ፣ በደመናትም መውጣት፣ በመላእክት ምስጋና፣በቅዱሳንም ምስጋና፣ በትጉሃን ንጽሕና፣ በልዑላንም መስማማት ፣ በመንፈሳውያን ብርሃን፣ በካህናት ቀኝ ፣ በሰማዕታት መሞት ፣ በምዕመናንም ደም፣ በብርሃናውያን መላእክትም ገናንነት። በልጅህ መመታት በአንድ ልጅህ ሕማማት ሁሉን በያዘ ሥልጣንህም፣ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አባት በምታርግ ጸሎት። " ቅዳሴ ቄርሎስ
9077Loading...
22
#የንጉሥ_ግብዣ_አለ_ተጠርተሃል_እንዳትቀር ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡ ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርዬት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰) ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሀዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም! ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡ የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል? የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::" ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሱ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡ ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡ ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡ (#የነፍስ_ምግብ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው - ገጽ 105-107) #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
8914Loading...
23
Media files
6920Loading...
24
...« ቅድስት ዮስቴና ሆይ ከሕጋዊ ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ፣ ሰው ሁሉ የሚማፀነው ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም የሚነገርለት ፣ በነፍስም በሥጋም የሚያማልድ ፣ እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ የሚሰጠው በምድር ሆኖ መንበረ ጸባኦትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ » ተብሎ ትንቢት የተነገረላቸው የአባታችን የጻድቁ #የአቡነ_ሀብተ_ማርያም ልደት ግንቦት 26 ቀን በታላቅ ድምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች ። « በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ ስምህን የጠራውን ዝክርህን የዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ ። » ብሎ ቃልኪዳን የተገባልህ እኛን ደካማ ልጆችህን በምልጃህ በቃል ኪዳንህ አስበን!!
1 0199Loading...
25
....ከዓመታት በፊት በታኅሣሥ ሃያ አራት የጻድቁ አባታችንን በዓል ለማክበር በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ቁስቋም ወዳለው የጻድቁ ቤተ መቅደስ በሌሊት ይደርሳሉ ። በስፍራው እንደደረሱም ከበሮ ይዘው #የኤቲሳ_አንበሳ_ተክልዬ_ተነሣ እያሉ እየዘመሩ በዛፎች እስከተከበበው እጅግ ሰፊው የገዳሙ ግቢ የውስጠኛ ክፍል ድረስ የጻድቁ አባታቸውን ስም እየጠሩ ገሠገሡ ። ይህንን የተመለከቱ የገዳሙ አባቶች በደስታ ተውጠው ሲመለከቱ አንድ አባት ግን እየተንሰቀሰቁ ያለቅሱ ጀመር ። እኚህ አባት የተክለ ሃይማኖት መቅደስ ያለበትን ቤተ ክርስቲያን ቁልፍ የሚይዙ መነኩሴ ናቸው ። የሚዘምሩትን ወጣቶች እያዩ በመደሰት ፈንታ ዕንባቸውን ለመግታት አልቻሉም ። ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ኢትዮጵያውያኑ ወጣቶች ዝማሬአቸውን ገታ አድርገው እኚህን አባት ቀርበው የለቅሶአቸውን ምክንያት ለመጠየቅ ተገደዱ ። መነኩሴውም እንዲህ ሲሉ ከዕንባ ጋር ነገሩአቸው ። ትናንት ማታ ከሰርክ ጸሎት በኋላ እንደተለመደው ቤተ ክርስቲያኑን ልቆልፍ ስል ከተክለ ሃይማኖት መቅደስ ውስጥ ጢስ ሲወጣ ተመለከትሁ ። ምናልባት የሚነድ ነገር ይኖር ይሆናል ብዬ ወደ ውስጥ ስገባ መቅደሱ በዕጣን ጢስ ተሞልቷል ። ምንም የሚነድ ነገር ግን የለም ። በነገሩ ተገርሜ ቤተ ክርስቲያኑን ቆልፌ ሔድኩ ። ለካስ አባታችሁ እናንተ ዛሬ እንደምትመጡ አውቀው መቅደሱን አጥነው እየጠበቁአችሁ ነበር !! አሏቸው ። #የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ከመላእክት_ጋር_የዘመረ_ቅዱስ_ያሬድን #ከካህናተ_ሰማይ_ጋር_ያጠነ_ተክለ_ሃይማኖትን_ያፈራች_ቤተ_ክርስቲያን #ናት ። #ከግዮን_ወንዝ_መጽሐፍ_የተወሰደ
9668Loading...
26
በ ዓ ተ ፡ ግ ብ ጽ #ግንቦት_24 ቀን እመቤታችን ከተወዳጅ ልጅዋ ጋር በስደት ግብጽ የገባችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው አበው የአበባን በዓል በአበባ ዘመን ብለው ማኅሌቱንም በዓሉን በወርኃ ጽጌ በጥቅምት ቢወስዱትም ጥንተ መሠረቱ ግንቦት 24 ቀን ነው ። እመቤታችን ቀጥኖ ከሚያመነምን ክፉ ዘመን ትሰውረን እፎይ ከምንልበት ዘመን በምልጃዋ ታድርሰን!!
8302Loading...
27
https://t.me/mekanehyawan2016
1 0350Loading...
28
Media files
1 0601Loading...
29
Media files
1 2751Loading...
30
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው። 1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ 2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ 3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ 7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ምንጭ ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት
1 2002Loading...
31
Media files
6320Loading...
32
#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤ ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
7150Loading...
33
በመጨረሻም ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
7970Loading...
#ዕርገት_ክርስቶስ ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ። ~~~ እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ: አምላካችን በመለከት ድምፅ። ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ,,,። መዝ 46(47):5 ጌታችን እንደተነሣ አርብዓ ቀን ሲሆነው ዐረገ። ይህም የአጋጣሚ ሳይሆን በትንቢት የተነገረ ነበር። ሙሴ ዘፍ:3:22 "አዳም መልካሙንና ክፉ እንዲያውቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" እንዳለ። ዳዊትም በመዝ:67(68):18 "ምርኮህን ማርከህ ወደ ሰማይ ዐረግህ።" እንዳለ። ጌታችን ራሱ በዮሐ: 20:17 ለመግደላዊት ማርያምም: "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና: አትንኪኝ።" እንዳላት። ዕርገቱ ቀድሞ የታወቀ ነበር። ጌታችን ለምን ዐረገ? ጌታችን ከሰማያት የወረደው የወደቅነውን ለማንሣት ወደ ክብር ለመመለስ ነውና: ይህንን ፈጽሞ ዐረገ። ለምን? 1: ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ለመላክ። "በዓለሙ ሁሉ እንድታስተምሩ: ኃይሉን ብርታቱን ሙቀቱን መጽናናቱን ጥበብን የሚገልጥላችሁን እልክላችኋለሁ።" እያለ። ዮሐ. 15:26 2: ስፍራን ለማዘጋጀት። ለሐዋርያት ለምእመናን። ራስ ክርስቶስ ካለበት ሕዋስ ምእመናን መገኘት ግድ ነውና። እርሱ ካለበት እኛ እንድንኖር ቦታ ሊያዘጋጅልን ዐረገ። ዮሐ. 14: 2። ይህን መሠረት አድርገን "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር,,," እንላለን። ሀገራችን በሰማይ ከአባታችን ዘንድ ሆነልን። ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ። 3: ክብሩን ገናንነቱን የባሕርይ አምላክነቱን ለመግለጥ ዐረገ። "መላእክትና ሥልጣናት ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።" 1ጴጥ. 3:22። እንዲሁም "በሥጋ የተገለጠ: በመንፈስ የጸደቀ: ለመላእክት የታየ: በአሕዛብ የተሰበከ: በዓለም የታመነ: በክብር ዐረገ። 1ጢሞ. 3:16 "አልቦ ዘዐርገ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ።" ዮሐ3። 4: ዕርገተ ጻድቃንን ለማሳወቅ ዐረገ። "እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው: ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። 1ተሰ. 4:17 ሙሽራዪቱ ከሙሽራው መለየት አትሻምና። "ዐርገ ከመ ያለብወነ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን። የንጹሐን ጻድቃንን ዕርገት ያስረዳን ዘንድ ዐረገ።" እንዲል ስንክሳር። 5: ከድንግል እመቤታችን በተዋሐደ ሥጋ በክብር እንዳረገ: እንዲሁ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኰት እንደሚመጣ ለማስረዳት ዐረገ። ራዕ. 1:7 በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ: "የወጉት ሁሉ ያዩታል።"እንዲል። በመሆኑም እያንዳንዳችን:— 1: ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ። ሁሌ ሳታቋርጡ አመስግኑ: ክብርን ያጎናጸፈን ከክብር ወደ ክብር የመለሰን እርሱ ነውና። "ሀቡ አኬቴተ ለእግዚአብሔር።" እንዲል ዳዊት 2: "እግዚአብሔር ዐረገ" የተባለው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ መሆኑን አውቀን: ሎቱ ስብሐት! "አምላክ አይደለም" የሚሉትን እናስረዳቸው ዘንድ ይገባል። 3: እንዲሁ እያየነው በክብር እንዳረገ ዳግም ይመጣልና: በሃይማኖት ጸንተን በምግባር ቀንተን ልንገኝ ይገባል። 4: በሰማይ መኖሪያ ያለን ሰማያውያን የሰማይ ዘጎች ነንና አምላካችንን ተስፋ እናድርግ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Показать все...
አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

🔔🔔🔔 አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ🔔🔔🔔 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች ፣ወቅታዊ መረጃ፣ሥርዓተ ማኅሌት ፣ዝማሬ፣የቅዱሳንን ታሪክ የምታገኙበት ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት @SDS12317212729 @Dn_amu_ki_17

Фото недоступноПоказать в Telegram