cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot

Больше
Рекламные посты
9 218
Подписчики
-424 часа
-47 дней
+4130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#አነ #ውእቱ #ሩፋኤል #አሐዱ #እምሰብዓቱ #ሊቃነ_መላእክት ከሰባቱ የመላእክት አለቆች አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ ( መጽ ቀሌምንጦስ) ጌታ በደብረዘይት ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ጉባኤ ዘርግቶ እያሰተማረ ባለበት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መጣ ጌታም ስምህን ለደቀመዛሙርቴ ንገራቸው አለው የመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጸሐፊ ያንጊዜ ነው ስሙን እስከትርጓሜው የነገራቸው ይላል በረከቱ ይደርብን የቁስጥንጥንያው ሊቀጳጳስ ካሳነጻቸው ሰባት አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ነው ቤተክርስቲያኑ የታነጸው ደሴት በሚመስለው በአሳ አንበሪው ጀርባ ላይ ስለነበር በቅዱሱ አባት አባ ቴዎፍሎስ ተባርኮ አገልግሎት ሲጀመር አጋጣሚው ተጠቅሞ አሳ አንበሪውን ሰይጣን እንዲናወጥ በማድረግ ሊያጠፋቸው ሲል ያዳናቸው መልአኩ እንደሆነ ድርሳኑ ይናገራል ቤተክርስቲያንዋን እና በውስጥዋ የነበሩትን አገልጋዮች ምዕመናን ከመሰጠም ታድጓቸዋል ዛሬም በውስጥም በውጭም ሁነው እንደ አሳ አንበሪው ቤተክርስቲያንን ከሚያናውጧት አገልጋይ ከሚመስሉ ቁማርተኞች አጋንንት ቤተክርስቲያንን ይታደግልን ቅዱስ ሩፋኤል ሰባት ዓመት ሙሉ እንደተራ ሰው ያገለገለው ከዓይነ ስውርነት የፈወሰው የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ጦቢያ ስለቅዱስ ሩፋኤል ምልጃና ተራዳኢነት በሰፊው ጽፏል ጦቢያን የፈወሰ የቅዱሳን ባለሟል ቅዱስ ሩፋኤል ሁላችንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ከሚያናውጠን ከእርስ በእርስ የጦርነት ማዕበል ይታደገን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Показать все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Фото недоступноПоказать в Telegram
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ሲናገር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Показать все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Фото недоступноПоказать в Telegram
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። ምልጃውና የከበረች ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን!
Показать все...
#ቅዱስ_ሚካኤል #እስራኤል_ዘሥጋን • የመራቸውና የጠበቃቸው • ባህር የከፈለላቸው • ጠላት ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያጠፋላቸው • በአምላኩ ፈቃድ መና ከሰማይ ያወረደላቸው • በለዓም እንዳይረግማቸው ሰይፉን መዞ መርገማቸውን የመለሰላቸው • ለመራገም የሄደው እንዲመርቃቸው ያደረገው ....በዚህም መጋቤ ብሉይ ተብሎ የተጠራው • የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረው • የቅድስት አፎምያን ፈታኝ በሥልጣን የረገጠው ... መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!!! ቅዱስ ያሬድ "አስተምሕር ለነ ሰአልናከ በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ " ብሎ እንደለመነው.... እኛም እስራኤል ዘነፍስ በቅዱስ ያሬድ ቃል ♥ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ!♥ ተማጽነንሃል! በአሥራ አራቱ ምልጃዎችህ ማልድልን" እንደ አምላክህ በሆነው ርኅሩህነትህ ከፈጣሪያችን ጋር አስታርቀን ክፉዎን ሁሉ በምልጃህ ተቋቋምልን በጠላቶቻችን የተጻፈብንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይርልን በልዩ ልዩ ፈተና የሚፈትኑንን አጋንንትን ከአምላክህ በተሰጠህ ሥልጣን እርገጥልን .. እያልን እንለምነዋለን! የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Показать все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Фото недоступноПоказать в Telegram
. #ተክለ_ሃይማኖት . #የሃይማኖት_ተክል_ተክለ_አብ_ተክለ_ወልድ_ተክለ_መንፈስ_ቅዱስ ༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻ #ሐዲስ_ሐዋርያ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ዘደብረ_ሊባኖስ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ተወለዱ ። ጸድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ❝ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ❞ ማለትም ❝ አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው ❞ በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል ። #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ 15 እና በ 22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ ( ጌርሎስ ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤ.ክ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቃል ። ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ምድር በኖሩባት 99 ዓመት ውስጥ ለአገልግሎት የሚያበቃ ሃይማኖታዊ ትምህርታቸውን ከቀሰሙ በኋላ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመዘዋወር ዕውቀታቸውን ያሰፉበትንና ለሐወርያዊ ተልዕኮዎች የተሰማሩባቸውን ጊዜያትና ቦታዎች እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስም የፈጸሙትን ተጋድሎ በአጭሩ የሚከተለውን ይመስላል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1219-1222 ዓ.ም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ወንጌልን አስተማሩ ቀጥለውም ዘጠኝ ወር በዊፋት አገልግሎታቸውን ፈጸሙ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ12 23-12 34 ዓ.ም ዳሞት በተባለው ስፍራ ወይም በወላይታ ሀገር ለ12 ዓመታት ሕዝቡን በማስተማር ከአምልኮተ ጣዖት ወደአምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል ። ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል። በዚም ሀገር ዲያብሎስ በዛፍ ላይ አድሮ አምላክ ነኝ እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሳት የሚጠቀምበትን ዛፍ በተአምራት ከሥሩ ነቅለው አፍልሰውታል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1234-1244 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ወደ አማራ ሳይንት ወሎ በመሄድ ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኲስናን እየተማሩ ለ 10 ዓመታት የተለያዩ ገቢረ ታምራትን በማድረግ በጉልበት ሥራም ሲያገለግሉኖሩ #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1244-1254 ዓ.ም አባ ኢየሱስ ሞዐ ወደሚገኙበት ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ሐይቁን በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት በመርገጥ ወደ ደሴቱ በመግባት የአገልግሎትና የትሩፋት ሥራን በማብዛት የምንኲስናን ተግባራቸውን በመቀጠል ከፍጻሜ አድርሰዋል በአባ ኢየሱስ ሞዓ እጅም የንጽሕና ምልክት የሆነውን የምንኲስናን ቀሚስ ተቀብለዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1254-1266 ዓ.ም ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ12 ዓመታት በገዳሙ በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1266-1267 ዓ.ም ለአንድ ዓመት ያህል የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ጎብኝተው መጥተዋል ። ከዚህ በኋላ ዳዳ በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን 75 ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበውበት በተአምራት ገድለውታል ። በቦታው ላይ በአርባዕቱ እንስሳ ስም ቤተ ክርስቲያን አንጸው ታቦተ ሕግ አስገብተውላቸዋል ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው መልሰው አጥምቀው አቍርበዋቸዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን ሁለቱን በፊት ፣ ሁለቱን በኋላ ፣ ሁለቱን በቀኝ ሁለቱን ደግሞ በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት ፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትናቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1289-1296 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኀነትን ሲለምኑ ኖረዋል ። ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል ። #ይኸውም ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ ። ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ ። ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ ። በሰባት ዓመታት ቍመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ። ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና ። በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ። ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ ሲነግራቸው ❝ እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል ከ 57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ ❞ አላቸው ። በመጨረሻም አባታችን ለ10 ቀናት ያህል በተስቦ ሕመም ቆይተው ፈጣሪያቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመነኰሳት መንፈሳውያን ልጆቻቸው ከነገሯቸው በኋላ ( ነሐሴ 24 )ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል ። #የቅዱስ_አባታችን_በዓላት_እነዚህ_ናቸው ✟ ኅዳር 24 ቀን ከ 24 ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ። ✟ ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ልደታቸው ። ✟ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ቀን ነው ( ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ 24 ይከበራ ) ✟ መጋቢት 24 ቀን 11 96 ዓ.ም ፅንሰታቸው ። ✟ በግንቦት 12 ቀን 13 53 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው ✟ ነሐሴ 24 ቀን 12 96 ዓ.ም ዕረፍታቸው ። . #ጸሎታቸው_በረከታቸው_ረድኤታቸው_ምልጃቸው_በመላው_ሕዝበ_ክርስቲያን_አድሮ_ይኑር_ለዘለዓለም።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
02:46
Видео недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram