cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

አቡቀለምሲስ ማለት ረአየ ኅቡኣት አበ ራዕይ አበ ትንቢት ማለት ሲሆን የተሰወረውን የተደበቀውን የተከደነውን የሚገልጥ ማለት ነው። መሠራታዊ ዓለማው በሀገረ ስብከታችን ብሎም በመላ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰወሩ ገዳማትን የተደበቁ ሊቃውንትን የተከደኑ ታሪኮችን የተሸሸጉ ቅርሶችን ማውጣት እና የተንሸዋረረ ታሪክ ማስተካከልና የጎበጠውን አዲሱን ትውልድ ማነጽ ነው

Больше
Рекламные посты
2 176
Подписчики
-224 часа
+47 дней
+2730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት ተከበረ። ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን) ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ ++++ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተከበሯል። በበዓሉ ላይ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ሓላፊዎች ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት ነው የተከበረው። ክቡር ሥራ አስኪያጁ በዓሉን በማስመልከት "በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን" በሚል ኃይለ ቃል ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን በእኛ ላይ ይድርስ የነበረውን ግርፋት ያስወግድልን ዘንድ 6 ሺህ 6 መቶ 66 ጊዜ በጅራፍ መገረፉን አስተምረዋል። ክርስቶስ በመስቀል ሳለ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል እና 13ቱን ሕማማተ መስቀል በመፈጸም አስተምሮናል ክርስቶስን በቀራንዮ ያየንበትና ያገኘንበት የድኅነት ቀን ነው ብለዋል። አቡቀለምሲስ ተዘዋውሮ በጎበኛቸው በደብረ ገነት ቅዱስ ዑራኤል እና በጠባሴ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናትም የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በዓሉ የተመለከተ ግብረ ሕማማት ልዩ ልዩ ጸዋትወ ዜማ ከሰኞ ሌሊት 11 ሰዓት ጀምሮ የየእለቱ ንባብ እና ዜማ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ ሲደርስ ሰንብቷል። በዛሬው እለትም የስቅለት በዓል የተመለከተ ንባብ እና ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደርስ ውሏል። ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ባስተላለፉት ቃለ በረከት ምስጉን የሆነው አምላካችን እኛን ለማዳን መከራን ተቀብሏል የሰው ልጅ ለማዳን ከሰው አዕምሮ በላይ የሆነ ዋጋ ከፍሎልናል ብለዋል። እስራኤልን ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ዛሬም ከእኛ ጋር በመሆኑ እነሆ ወደ ቀደመ ክብራችን መልሶናል ክርስቶስ በፍቅር የከፈለልልን ዋጋ በእጅጉ ከባድ ነው እኛም ይህንን የክርስቶስን ፍቅር እያሰብን በፍቅር ልንኖር ይገባል ብለዋል። ብፁዕነታቸው በዓሉን ስናከብር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት ፣ አረጋዊያንን እና ሕጻናትን ፣ የተቸገሩ ወገኖቻችንን መርዳትና ማገዝ አለብን በማለት መልእክት አስተላልፈው በብፁዕነታቸው ጸሎት የበዓሉን ፍጻሜ ሆኗል።
Показать все...
ልዩ የትንሣኤ በዓል ዝግጅት ቅዳሜ በEOTC TV ይጠብቁን
Показать все...
Перейти в архив постов