EECSF
Открыть в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Больше508
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
508
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድርገን የምንተናነጽባቸውን ፍሬ ነገሮች እንከፋፈላለን፤ አብራችሁን ቆዩ።
508
✝ ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።
¹¹ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
¹² መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
¹³ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።
¹⁴-¹⁵ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
¹⁸ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤
508
ሀሳቦቻችን ምንጫቸው ከየት ነው?
ሁልጊዜ ወደ ጌታ መቅረብ ይሁንልን ሀሳቦቻችንንም ፣ ድርጊቶቻችንንም ሊቀይስልን ወደ መልካሙ ሊመራን የሚችል እርሱ ብቻ ነው።
የዛሬው ኘሮግራማችን በዚህ አልቋል
አግዚያብሄር ይባርካችሁ
508
የህይወት መውጫ
ሰላም ለሁላችን ይሁን ወዳጆቼ የዛሬውን መልዕክት እግዚአብሔር በልባችን ያኑርልን እንዲሁም ስለ ብዙ ምህረቱ እና ፀጋው አምላኬን አመሰግናለሁ::
በቅርቡ በካናዳ የሚገኘው Queen's University ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ ሰው በአማካይ በቀን ከ 6,000 ሀሳብ በላይ እንደሚያስብ አመላክቷል:: ይህን መረጃ በግርድፉ እንኳ ብንቀበለው የሰው ልጅ ምን ያህል ሀሳባዊ ፍጥረት መሆኑን እንረዳለን::
ሀሳብ በአእምሮ ተፀንሶ በውሳኔ ዳብሮ ድርጊት ይሆናል::የእነዚህ ድግግሞሽ ደግሞ ልማድ አልፎም የሰው ባህሪ እስከመሆን ይደርሳል::
አንዳንዱን "ይህ ባህሪዬ ነው::ምንም ማድረግ አልችልም " የምንላቸው ስር የሰደዱ ባህርይ/ልምምዶችም አሉ::
አንዳንዱን ደግሞ " ለዚህ ባህርይ/ድርጊት እገሌ ነው ተጠያቂ" በማለት ጣታችንን እንቀስራለን:: ምናልባትም እግዚአብሔርን ወይም ሰይጣንን አሊያም ሰዎችን ጠቅሰን ድርሻቸውን እናከፍፍላለን::
ሌሎቹን ደግሞ " ይሄ እኮ ምንም ማለት አይደለም" ብለን ለከሳሽ አእምሮ ማስታገሻ መርፌ እንወጋለን::
አንዳንድ የህይወት ሙግቶች በአንድ ጀንበር ይረታሉ:: ሌሎች ደግሞ ዕለት ተዕለት መጋደልን የሚፈልጉ ናቸው::
ይህን እንደመንደርደሪያ አነሳሁት እንጂ ሁላችንም የምንጋደለው እና የሚያታግለን የህይወት ፈተና ልዮ ልዮ ነው::
የትኛውም ፈተና ግን ሀሳባችንን ሳይነካ አያልፍም:: ሁሉም አእምሮን ዘልቀው በሚሰጡ ምላሾች ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: ይህም ባየነው: በሰማነው: ባሸተትነው: በዳሰስነው ነገር ወደ ልባችን ዘልቆ በእሽታ ድርጊት ይሆናል አሊያም በእንቢታ ይከስማል::
መልካም ሀሳብ ምንጭ አለው::
ክፍም ሀሳብ ምንጭ አለው::
ከእነዚህ ምንጮች የሚቀዱ ቃላት ምክሮች ብቻ አይደሉም ሀይልም ጭምር ናቸው:: ወይ ብርሀን አሊያም ጨለማ::
የተጨነቅንባቸው እና ግራ የተጋባንባቸው ባህሪዎች/ድርጊቶች ሁሉ ምንጭ አላቸው:: ጠራርገው የሚወስዱን ወንዞችም በውሀ ጠብታ የሞሉ ናቸው:: ከጨለማ እየቀዳን ብርሀንን ልንመለከት አንችልም::
ብርሀን ብቻ ነው ጨለማን የሚያበራው:: የዲያብሎስን ሀሳብ በሚያነቃቁ ቃላት ማሸነፍ አንችልም:: የሚሸነፍት በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው::
“ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው” (መዝ 119፡ 105)
“የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል” (መዝ 119፡ 130)
የአብርሀም ፈተና ከያዕቆብ ይለያል
የዮሴፍ ፈተና ከዳንኤል ይለያል
የጳውሎስ ፈተና ከዩሐንስ ይለያል::
የሁሉም ፈተና ግን ለሰው ከሚሆነው በላይ አልነበረም::
1ኛ ቆሮንቶስ 10:13
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል
"ትላንት የያዘው ዛሬ ለነገ አይሆንም"
ልባችን በላይ ያለውን እንዲያስብ
እግዚአብሔር ይርዳን!!!
508
አሜን
አሁን ደግሞ አብረን እግዚያብሄርን እናመልካለን
እግዚያብሔር ትልቅ መሆኑን አያሰብን
በሁኔታ እና በእኛ እውቀት የሚገመት እንዳልሆነ እያመንን
እግዚያብሔርን እናመልካለንኔ
508
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድርገን የምንተናነጽባቸውን ፍሬ ነገሮች እንከፋፈላለን፤ አብራችሁን ቆዩ።
508
That your faith should not stand in the wisdom of men, but in the power of God.
1 Corinthians 2: 5
508
" እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።"
(ወደ ዕብራውያን 11: 1)
"ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።"
(ወደ ዕብራውያን 11: 6)
Don't be moved by what you hear, see and by what majority believes
Have faith
508
👉 "በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እርሱን ያወቅንበት ልክ ነው ፤ የበለጠ ባወቅነው ቁጥር መታመናችን ይጨምራል"
📌 ሩጫችን ፣ ናፍቆታችን ፣ ጥረታችን ፣ አላማችን እግዚአብሔርን ማስደሰት ከሆነ እርሱ ከሁሉ በላይ ከኛ የሚፈልገው እንድናምነው ነው!
✝ ❝ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።❞
—ዕብራውያን 11: 6
508
2ኛቆሮንቶስ ምዕ. 5
6-7፤ እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥
8፤ ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።
508
ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል።
ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት።
ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።
ምሳሌ 4:20-23
508
(ወደ ሮሜ ሰዎች 12 )
------------
1 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
