EECSF
Открыть в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Больше508
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
📌 2ኛ ሳምንት
ርዕስ - መልካሙን ህይወት መኖር
ቀን 3፦ 1ኛ ጴጥሮስ 2:13- 25
📌 አምላካችን እግዚአብሔር ዛሬም ከሁሉ በላይ ስለሆነ ፤ የሁሉ ተቆጣጣሪ ስለሆነ
እያመሰገንን እንፀልይ
📌 ሰዎችን የሚወድ፤ የሚያከብር
ስለሰዎች የሚያስብ
ልብ እንዲሰጠን እግዘብሔርን እጠይቅ
ሰዎች ክፍ ነገር አድርገውብን እንኳን ፤ እኛ በመልካም መመለስ እንድንችል እግዚአብሔር እንዲረዳን እንፀልይ
📖 በቃል የሚጠና ጥቅስ፦
❝ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2: 15) ።❞
**
የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት
2012 ዓ. ም.
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
📌 2ኛ ሳምንት
ርዕስ - መልካሙን ህይወት መኖር
ቀን 2፦ 1ኛ ጴጥሮስ 2:11- 12
📌 እንግዶች እንደመሆናችን መጠን ፤ እግዚአብሔር ለኛ ሌላ የተሻለ ነገር ስላዘጋጀልን
አሁን በዚህ አለም ስንመላለስ
ሀጢአትን ተፀይፈን፣ ሸሽተን፤ ከዚህ አለም መጥፎ ተግባር ተለይተን ለጠራን ጌታ መኖር እንድንችል እግዚአብሔር እንዲረዳን እንፀልይ
📌 ሰዎች ቢበድሉንም አሁንም እየወደድናቸው
መልካም እያደረግን
ሩጫችንን በትእግስት እንድንሮጥ
እግዚአብሔር እንዲረዳን
እንፀልይ
📖 በቃል የሚጠና ጥቅስ፦
❝" " ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2: 11)።❞
**
የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት
2012 ዓ. ም.
508
እሺ....ጌታ ይመስገን!!
ዛሬ ቀለል ያሉ የ 100 MB ሽልማት የሚያስገኙ ጥያቄዎች አሉ። ቀድሞ ለመለሰ ብቻ😊!!!
እንሂድ...................😊
508
ስለ ቃሉ ጊዜ ጌታችን የተመሰገነ ይሁን!!
በሕያው ቃሉ መሰረት የምንኖር እና የምናድግ እንድንሆን ጌታ ይርዳን፤ አሜን። መልዕክቱን ያካፈለችንን እህት ቦንቱ እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!
508
🗒 በእግዚአብሔር በፍፁም ልብ መታመን🙏
(እህት ቦንቱ ታሪኩ)
ሰላም👋እንዴት ናችሁ?
በያለንበት የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛልን🙌
➕ስለረዳን፣ ስላሻገረን፣ ጥበቃዉ ስለበዛልን እግዚአብሔር ይመሥገን
📌ዛሬ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ እወዳለው
(ትንቢተ ኢሳይያስ 26 )
------------
3 በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
4 ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
📌እግዚአብሔርን ምን ያህል እናምነዎለን? የምንተኛበት አልጋ እንደሚሸከመን 💯% እንደምናምነው ወይም ሀኪም የሚያዝልንን መድሀኒት💊 እንደሚያሽለን የምናምነውን ያክል እናምነው ይሆን? ወይስ ከዛ በላይ ወይስ ደግሞ ከዛ በታች?🤔🤔
📌በህይወታችን ለሚያጋጥሙን አጋጣሚዎችስ በእግዚአብሔር ለመደገፍ( ለማመን) ያስቀመጥነው limit ይኖረን ይሆን??🤔
➤Why do we need to trust in God?
✅በምድር ላይ የምንታመንባቸው ነገሮች:-
►ቤተሰብ 👨👩👧👦፣
►ሀብት💰💵 ፣
►ጓደኛ🙎🙎♂፣
►ስልጣን......
👆➥ዘላቂነት የለውም(ጊዜያዊ ነው)⏱
👆➥ እነዚህ ነገሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ለመደገፍ ወይም ደግሞ ለማመን ምንም ዋስትና የለንም
👆➥ተሸክመውን የት ድረስ እንደሚያደርሱን ማወቅ ከባድ ነው
✨ነገር ግን እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነው("... everlasting strength:"
(Isaiah 26: 4)
✨እግዚያብሔር ታማኝ አምላክ ነው
✅እግዚአብሔርን ማመናችን ደግሞ የሰላማችን ምንጭም ነው👇
(" በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 26: 3)
📌እግዚአብሔርን በመታመናችን የምናገኘዉ ሰላም፦
✔️ ፍፁም ሰላም ነው( inner peace beyond any situations)
✔️አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ነዉ
✔️ልብንና ሀሳብን በክርስቶስ ኢየሱስ የሚጠብቅ ሰላም ነዉ
👇👇
" አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4: 7)
▪️በምድር ላይ ስንኖር ብዙ
👉ተስፋ የሚያስቆርጡ ፣
👉 ልብን የሚሰብሩ ፣
👉ሀሳባችንን የሚሰርቁ ሁኔታዎች ሊከሰቱብን ይችላሉ 🙁😫😰🤦♀
🔸🔸ነገር ግን በነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ውስጥ ልባችንን እና ሀሳባችንን የሚጠብቅ ከአእምሮ የሚያልፈው 💥▻የእግዚአብሔር ሰላም🦚🦚◅💥ብቻ ነው‼️
🔷🔷So Guys what ever is the situation we are in, lets just trust in God since he is in control❕❗️
እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልን🙏
ተባረኩ🙏
