1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
4 ኪሎ ፕላዛ፣ 4 ኪሎ የገበያ ማዕከል እና መኪና ማቆሚያ የድል ሃውልታችንን ከበው ትላንታችንን ከዛሬ እና ከነገአችን ጋር አገናኝተው ደምቀው አድምቀውናል…
See more
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት መርቀው አገልግሎት ያስጀመሯቸው በአራት ኪሎ ፕላዛዎች :4ኪሎ የገበያ ማእከል እና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክቶች- በምስል
አዲስ አበባን ከቀድሞ ታሪኮቿ ጋር እያጣጣምን ዘመናዊ ከተማ እያደረግናት እንገኛለን።
ዛሬ 4 ኪሎ ፕላዛን፣ 4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን እና መኪና ማቆሚያን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
የአገራችን ብሎም የከተማችን አበይት ታሪካዊ ስፍራ እና የድል ሀውልታችን መገኛ የሆነውን ፣ የተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶችን ያነበብንበትን፣ እውቀት የቀሰምንበትን፣ ስራ ፍለጋ ማስታወቂያ ለማንበብ የተመላለስንበትን የ4 ኪሎ አደባባይ አካባቢን መልሰን ገንብተን የያዘውን ግዙፍ ታሪክ የሚመጥን፣ ትላንታችንን ከዛሬ እና ከነገአችን ጋር የሚያገናኝ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ዘመናዊ የከተማ ዲዛይን እና እሴት ያለው ውብ የ4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን፣ መኪና ማቆሚያን እና 4 ኪሎ ፕላዛን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
ፕሮጀክቱ ከመሬት በታች የተገነቡ እጅግ ዘመናዊ 102 የስጦታ እና የአልባሳት መደብሮች፣ ካፌዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች ፣ ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ እና በአንድ ጊዜ እስከ 5 ሺህ ሰዎችን መሰብሰብ የሚያስችል የፕላዛ፣ የአንፊ ቴአትርና የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ማቅረቢያ ስፍራዎችን የያዘ፤ የሲቪል ተሳትፎን፣ የባህል ዕድገትን፣ የእግር ጉዞን የሚያበረታታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው።
ፕሮጀክቱ ከወዲሁ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ የቱሪዝም ፍሰቱን በመጨመር ለዘርፉ ዕድገት የራሱ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይሆናል ።
ይህ ፕሮጀክት በታለመለት ልክ እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል ስታደርጉ የነበራችሁ ባለ ድርሻ አካላት፣ አመራሮች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአንድ ጀንበር 714.7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ከዕቅድ በላይ መሳካቱን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ ።
በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 714.7 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል ፡፡
አጠቃላይ 29.7 ሚሊዮን ሕዝብ እንደተሳተፈ የተናገሩት ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ፤ የዛሬው ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕብረት ታሪክ የሠራበት ዕለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መርሐ ግብሩ እንዲሳካ በማስተባበር እና በመሳተፍ ታሪክ የሰሩ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስሬ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካባ መብራሐቱ በአንድ…
See more
በነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት የተካሄደው የአንድ ጀምበር የቾግኝ ተከላ መርሐግብር በምስል:-
አሳክተነዋል፤ እናመሰግናለን!
በዘንድሮው የ7ኛ አመት አረንጓዴ አሻራን የማፅናት ተግባርም በመላው አዲስ አበባ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አገር በቀል፣ ለምግብነትና ለከተማ ውበት የሚሆኑ ችግኞች ተተክለዋል።
ከማለዳው አንስቶ ሁሉም የከተማችን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደወትሮዉ ሌላ ደማቅ አረንጓዴ ገድል አሳክተዋል። ለዚህም ምስጋናዬ የላቀ ነው። በመትክል ያሳካነውን ድል በመንከባከብም እንድንደግመው አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
See less
ይህ ኢትዮጵያ ትልልቅ ነገር አስባ፥ ትልልቅ ነገር ተልማ ህዝቦቿን አስተባብራ ማሳካት እንደምትችል ለእኛም ለሌሎችም ማሳያ ነው።
ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተአምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም ታይቷል።
"በመትከል ማንሠራራት" በሚል መሪ ቃል ፣ በአንድ ቀን 700 ሚልዮን ዛፎችን ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷል።
አመራሮችና ሠራተኞች፣ የግልና የመንግሥት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አረጋውያን፣ ወንዶችና ሴቶች ለአረንጓዴ ዐሻራ፣ ዛሬ በማለዳ፣ ከወፎች ቀድመው ወጥተዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያውያን ባህል እየሆነ ነው። የኢትዮጵያን መልክም እየቀየረ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክም እየቀየረ ነው። የዓለምንም መልክ እየቀየረ ነው።
ይሄንን ተልዕኮ የሚያስተባብሩትን፣ ጥሪያችንን ሰምተው ወጥተው የተከሉትን ሁሉ እናመሰግናለን። ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች በብዛት እና በምልዐት ስላደረጉት ተሳትፎ በኢትዮጵያ ስም እናመሰግናለን።
መትከል ለልጆቻችን ጥላ መዘርጋት ነው!
Itoophiyaanonni yoo walta'an ajaa'iba hojjechuu akka danda'an har'as irra deebiidhaan mul'ateera.
Yaada ijoo "Dhaabuudhaan Bayyanachuu" jedhuun karoorri guyyaa tokkotti biqiltuuwwan miliyoona 700 daabuuf karoorfanne isa yaadamee ol milkaa'eera.
Hooggantoonnifi hojjettoonni, dhaabbileen dhuunfaafi mootummaa, embaasiiwwaniifi dhaabbileen idil-addunyaa, daa'imman, dargaggoonni, gaheessonni, maannguddoonni, dhiironniifi dubartoonni har'a barii Ashaaraa Magariisaaf simbirroowwan dursanii bahaniiru.
Ashaaraan Magariisaa aadaa Itoophiyaanotaa ta'aa jira. Bifa Itoophiyaas jijjiiraa jira. Seenaa Itoophiyaas jijjiiraa jira. Bifa addunyaas jijjiiraa jira.
Warra ergama kana qindeessan, kanneen waamicha keenya dhagahanii bahanii dhaaban hunda ni galateeffanna. Itoophiyaanonni, dhalooteen Itoophiyaafi lammiileen biyya alaa hirmaannaa baay'inaafi guutummaatti taasisaniif maqaa Itoophiyaatiin ni galateeffanna.
Dhaabuun ilmaan keenyaaf dibaabee diriirsuudha!
በምክትል ከንቲባ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስሬ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካባ መብራሐቱ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐግብር ላያ ያስተላለፉት መልእክት:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
