1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎችና በተለያዩ ቦታዎች ላይ በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊየን አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዋሬ አካባቢ ግንፍሌ ወንዝ ዳርቻ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አካሂደዋል።
በመርሀግብሩ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዛሬ በመላው ሀገሪቱ 700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሀግብር እየተከናወነ ይገኛል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የዘንድሮውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በታላቅ ድምቀት በይፋ አስጀምረናል ።
ከሀይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ከተለያዩ የሙያ ማህበረሰቦች ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ጠረኗ እና መልኳ ተቀይሮ ባማረችውና ውበት በተጎናጸፈችው አዲስ አበባ በግንፍሌ ወንዝ ዳርቻ ችግኝ ጀምረናል።
በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች በተዘጋጁ 271 ቦታዎች መላው የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት በነቂስ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ማለዳ ላይ በጀመርነው መንፈስ ቀጥለን በእቅድ ከያዝነዉ ግብ እንደምናሳካ እርግጠኛ ነኝ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
"ዛሬ ማለዳ የዘንድሮውን የ #አረንጓዴዐሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስጀምረናል። ለሰባተኛው አመት ግባችን:-ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኞች ነው። በጋራ እናሳካው"!!!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከንቲባ አዳነች አቤቤ "በመትከል ማንሰራራት" በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ከሚሽኑ የአቅመ ደካሞችን የቤት ዕድሳትና ግንባታ መርሀግብርን አስጀመረ ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ90 ቀናት ዕቅዱ አካል የሆነው የቤት ዕድሳትና ግንባታ መርሀግብርን ዛሬ ሀምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 አስጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሸነር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ የሚሰ ጠው ሰብአዊ አገልግሎት እንደመሆኑ በዛሬው ዕለት የተጀመረው የአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳትና ግንባታ ስራም ከኮሚሽኑ ተልዕኮ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ነው ብለዋል ።
ኮሚሽኑ በ90 ቀናቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በሆኑት የደም ልገሳ ፣ የችግኝ ተከላና የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብርን አዘጋጅቶ ሁሉም አመራርና ሠራተኞች መሳተፋቸውን ኮሚሸነር አህመድ መሀመድ አስታውቀዋል ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው እንደተገሩት በዛሬው ዕለት የተጀመረውን የአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳትና ግንባታ የሚያስጠይቀውን ወጪ ኮሚሽኑ ሀብት የማሰባሰቡን ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ቤቱ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል::
በዛሬው ዕለት የተጀመረው የቤት ዕሳ ትና ግንባታ በነሀሴ አጋማሽ ተጠናቅቆ ከ ነዋሪዎቹ ጋር ርክክብ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
አዲስ አበባ ዝግጁ!
ያለፉት 6 አመታት ገድል በነገዉ እለትም ይደገማል! መላው የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ ዕድሜ ፣ ብሔር፣ ኃይማኖት፣ የኑሮ ደረጃ ሳይለያቸው ነገ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ ኢትዮዽያ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የያዘችዉን እቅድ ለማሳካት፣ በአራቱም አቅጣጫ ድርሻችን በነቂስ እንነሳለን።
አዲስ አበባ በዕለቱ ዳግም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አንድነታችንን ፣ ቁርጠኝነታችንን እና ፅናታችንን የምናሳይበት እለት ይሆናል ።
ዉብ፣ አረንጓዴ፣ ጤናማ መዲና እንፈጥራለን !
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1 ቀን ቀረው!
ሐምሌ 24 ፣2017 በ7ኛው ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር እንተክላለን። እኛ ተዘጋጅተናል! እርሶስ?
1 day remaining!
July 31, 2025 on the 7th year #Ethiopia will attempt planting 700 million seedlings in one day.
We are ready? And you?
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia
የአገልግሎት ወረፋን በገንዘብ ሲሸጡ የነበሩ የወረዳ ባለሙያዎች ቁጥጥር ስር ዋሉ
በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የነዋሪዎች አገልግሎት እና የማህደር ክፍል ባለሙያዎች የሆኑ ከህብረተሰቡ በመጣዉ ጥቆማ መሰረት "ወረፋ ብዙ ነዉ" በማለት ገንዘብ ተቀብሎ አገልግሎት ሲሰጡ ተይዘዉ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ኤጀንሲዉ ገልጿል።
ህብረተሰቡ ከተቋሙ የሚያገኘዉ አገልግሎት ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ተቋማዊ ሪፎርም እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ ፡፡
ለዚህም ተቋማዊ ሪፎርም ተገልጋይ ህብረተሰብ የጎላ ሚና ያለዉ ሲሆን አሁንም ለተቋሙ ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብራችሁን እየጠየቅን አገልግሎታችንን ከሌብነት የጸዳ እና የተቀላጠፈ እንዲሆን እየሰራን ስለሆነ በተቋሙ ነፃ የስልክ መስመር 7533 በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡን ኤጀንሲዉ ይጠይቃል፡፡
ለበለጠ መረጃ ወይም ጥቆማ 7533 ይደውሉ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ!
በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ አረንጓዴ እና ለፈተና የማይበገር ነገዋን ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት እንደገና ትነሳለች። ነገ ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን አካል የሆነውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አላማን ለማሳካት እንነሳለን። ከፍ ያለ ግብ ነው። ግን ጥንካሬያችንን፣ አንድነታችንን እና ለሕዝባችን ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይኽ ችግኝ ከመትከል በላይ ነው። ትንሽ ትልቅ፣ የከተማ የገጠር ሳንል ዜጎች ሁሉ አካባቢያችን እንዲያገግም፣ የውሃ ምንጮቻችን እንዲጠበቁ፣ የኑሮ ሁኔታችን እንዲሻሻል እንዲሁም ለመጪው ትውልዶች ዘላቂነት ያለው ነገን ለማረጋገጥ የምንሳተፍበት ተግባር ነው።
ሁላችሁም በዚህ ታላቅ ሥራ እንድትሳተፉ እና እንድታስተባብሩ አሳስባለሁ። በጋራ ጠንካራ ዛፎችን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና የበለጠ አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን እናሳድጋለን።
