ru
Feedback
ETHIO CIVIL ENGINEER

ETHIO CIVIL ENGINEER

Открыть в Telegram

For all CENG & others, we will help you on:- =)Scholarship infos =)Tutor for Exit Exams. =)Integrated civil Engineering Design. =)B.Sc. Thesis =)#YouTube ቻናላችንን subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ https://www.youtube.com/channel/UC8h1sfALxrsNbYbXNPuChvw/

Больше
3 217
Подписчики
+224 часа
+147 дней
+2830 день
Архив постов
+4
exit civil engineering .pdf4.87 KB

photo content

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል #Ethiopia | የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል። የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡- - Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc) - Nuclear Physics and Technology (BSc) - Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc) - Heat Power Engineering (BSc) - Management in Technological Systems (MA) የመወዳደሪያ መስፈርቶች ? • ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ። • ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ። ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

#Update የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡ በ
+2
#Update የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡ በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity

Repost from Tikvah-University
#Update የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡ በ
+2
#Update የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡ በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity

N. Claims and Disputes (ጥያቄዎች እና ክርክሮች) ይህ ክፍል፦ • Claim Procedures • Notice Periods • Arbitration • Adjudication • Court Jurisdiction ያካትታል። 2. PCC (Particular Conditions of Contract) PCC ማለት ለተወሰነ ፕሮጀክት ብቻ የሚተገበሩ ልዩ የኮንትራት ሁኔታዎች ማለት ነው። PCC የሚያደርገው፦ • GCCን ማሻሻል • ተጨማሪ መመሪያ መስጠት • ለፕሮጀክቱ የሚስማሙ ልዩ ሁኔታዎች መጨመር ነው። PCC ዋና ዓላማ ምክንያቱም ሁሉም ፕሮጀክቶች አንድ አይደሉም። ልዩነቶች፦ • የአካባቢ ሁኔታ • የቴክኒክ ውስብስብነት • የአደጋ ደረጃ • የፋይናንስ ሁኔታ ስለዚህ PCC እያንዳንዱን ፕሮጀክት በተለየ ሁኔታ ያስተካክላል። PCC ከGCC ጋር ያለው ግንኙነት አስፈላጊ መርህ፦ PCC ከGCC ጋር ቢጋጭ PCC ይቀድማል። ምሳሌ፦ GCC: Retention = 10% PCC: Retention = 5% ተግባራዊ የሚሆነው 5% ነው። PCC የሚያካትታቸው ዋና ነጥቦች A. Contract Data (የኮንትራት መረጃ) • የፕሮጀክት ስም • የEmployer ስም • የሥራ ቦታ • የኮንትራት ዋጋ • የሥራ ጊዜ • የEngineer ስም B. Time Requirements (የጊዜ መስፈርቶች) • Completion Period • Milestones • Sectional Completion • Rainy Season Restrictions C. Payment Details (የክፍያ ዝርዝሮች) • Advance Payment % • Retention % • Currency • Minimum IPC Amount D. Liquidated Damages (የመዘግየት ቅጣት) ምሳሌ፦ • 0.1% በቀን • ከፍተኛ 10% እስከሚደርስ E. Defect Liability Period ምሳሌ፦ • 365 ቀን • 730 ቀን F. Performance Security (የአፈጻጸም ዋስትና) ይወስናል፦ • የዋስትና መጠን • የዋስትና አይነት • የሚቆይበት ጊዜ G. Insurance Limits (የኢንሹራንስ ገደቦች) ለምሳሌ፦ • የThird Party Liability ዝቅተኛ ሽፋን H. Site Specific Conditions (የቦታ ልዩ ሁኔታዎች) • የደህንነት ችግሮች • መዳረሻ ገደቦች • የአካባቢ ጥበቃ • የትራፊክ ቁጥጥር I. Taxation and Duties (ግብርና ቀረጥ) • VAT • Withholding Tax • Customs Exemption J. Special Technical Requirements (ልዩ የቴክኒክ መስፈርቶች) • የቁሳቁስ መስፈርቶች • ልዩ የሙከራ መስፈርቶች • የጥራት ደረጃዎች K. Funding Agency Requirements (የፋይናንስ ተቋማት መስፈርቶች) እንደ፦ • World Bank • African Development Bank ያሉ ተቋማት ልዩ የግዥ መመሪያዎችን ሊጨምሩ ይችላሉ። GCC እና PCC በቀላሉ GCC “በሁሉም ኮንትራቶች ላይ የሚተገበሩ አጠቃላይ ሕጎች” PCC “ለዚህ ተወሰነ ፕሮጀክት ብቻ የተዘጋጁ ልዩ መመሪያዎች” በኢትዮጵያ የግንባታ ሥራ ተግባር GCC እና PCC በስፋት የሚጠቀሙባቸው፦ • የመንግስት መንገድ ፕሮጀክቶች • የህንጻ ግንባታ • የውሃ ፕሮጀክቶች • የከተማ ልማት ሥራዎች • በውጭ ድጋፍ የሚፈጸሙ ፕሮጀክቶች ላይ ነው። አስፈላጊ ሙያዊ ግንዛቤ ብዙ ጀማሪ መሐንዲሶች ትኩረታቸውን በ፦ • Drawings • BOQ • Specifications ላይ ብቻ ያደርጋሉ። ነገር ግን በእውነተኛ ፕሮጀክቶች GCC እና PCC የሚወስኑት፦ • ማን ክፍያ እንደሚያገኝ • ማን አደጋ እንደሚሸከም • ማን ለመዘግየት ኃላፊ እንደሚሆን • Claim ይፈቀድ ወይስ አይፈቀድ • EOT ይሰጥ ወይስ አይሰጥ Mekamu Mohamed

📶 በኢትዮጵያ የመደበኛ የጨረታ ሰነድ (Standard Bidding Document – SBD) ውስጥ የኮንትራት ሁኔታዎች በአብዛኛው በሁለት ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ:- 1. GCC (General Conditions of Contract) — አጠቃላይ የኮንትራት ሁኔታዎች 2. PCC (Particular Conditions of Contract) — ልዩ የኮንትራት ሁኔታዎች እነዚህ ሁለት ሰነዶች በአንድነት ይሰራሉ። GCC አጠቃላይ የሕግና የአስተዳደር መሠረት ሲያቀርብ፣ PCC ደግሞ ለተወሰነ ፕሮጀክት የተለዩ ማሻሻያዎችንና ተጨማሪ መመሪያዎችን ያካትታል። 1. GCC (General Conditions of Contract) GCC ማለት በሁሉም የግንባታ ኮንትራቶች ላይ በአጠቃላይ የሚተገበሩ መደበኛ የኮንትራት ውሎች (standard contractual clauses) ማለት ነው። ይህ ሰነድ፦ • የሕግ ግዴታዎችን (legal obligations) • የአስተዳደር ሂደቶችን (administrative procedures) • የአደጋ ኃላፊነት ክፍፍልን (risk allocation) • የክፍያ ሥርዓቶችን (payment procedures) • የክርክር መፍቻ ሥርዓቶችን (dispute resolution mechanisms) • የሥራ አፈጻጸም መመሪያዎችን ይወስናል። GCC ብዙ ጊዜ ከ፦ • FIDIC የኮንትራት መርሆች • የኢትዮጵያ የመንግስት ግዥ ህጎች • ዓለም አቀፍ የግንባታ ውል መርሆች ተነስቶ ይዘጋጃል። GCC ዋና ዓላማ GCC የሚያደርገው፦ • የኮንትራቱን የሕግ መሠረት መፍጠር • የተዋዋይ ወገኖችን መብትና ግዴታ መግለጽ • የአሠሪውን (Employer) እና የተቋራጩን (Contractor) ጥቅም መጠበቅ • የሕግ እና የቴክኒክ ግልጽነት መፍጠር • በሁሉም ፕሮጀክቶች ተመሳሳይ የውል ሥርዓት መፍጠር ነው። GCC የሚያካትታቸው ዋና ዋና ክፍሎች A. Definitions and Interpretation (ትርጓሜዎች እና የቃላት ትርጓሜ) ይህ ክፍል በኮንትራቱ ውስጥ የሚጠቀሙ ቃላትን ይገልጻል። ምሳሌዎች፦ • Employer — አሠሪ • Contractor — ተቋራጭ • Engineer — መሐንዲስ • Contract Price — የኮንትራት ዋጋ • Site — የሥራ ቦታ • Variation — የሥራ ለውጥ • Defect Liability Period — የጉድለት ኃላፊነት ጊዜ • Interim Payment Certificate (IPC) — የጊዜያዊ ክፍያ ማረጋገጫ ይህ ክፍል በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ የኮንትራት ክርክሮች የሚመጡት ከቃላት የተሳሳተ ትርጓሜ ነው። B. Priority of Contract Documents (የኮንትራት ሰነዶች ቅድሚያ) ይህ ክፍል ሁለት ሰነዶች ቢጋጩ የትኛው እንደሚቀድም ይወስናል። ብዙ ጊዜ ቅደም ተከተሉ፦ 1. Contract Agreement 2. Letter of Acceptance 3. PCC 4. GCC 5. Specifications 6. Drawings 7. BOQ 8. Contractor’s Bid አስፈላጊ ነጥብ፦ PCC ከGCC ጋር ቢጋጭ PCC ይቀድማል። C. Scope of Works (የሥራው ወሰን) ይህ ክፍል፦ • ተቋራጩ ምን እንደሚገነባ • የሚከተለው የጥራት ደረጃ • የሚተገበሩ መመሪያዎች • የቴክኒክ መስፈርቶች ይገልጻል። D. Responsibilities of Parties (የተዋዋይ ወገኖች ኃላፊነቶች) 1. Employer Responsibilities (የአሠሪው ኃላፊነቶች) • የሥራ ቦታ ማስረከብ • ክፍያ መፈጸም • ዲዛይን ማጽደቅ • Engineer መመደብ • መዳረሻ መስጠት 2. Contractor Responsibilities (የተቋራጩ ኃላፊነቶች) • ሥራውን ማከናወን • ቁሳቁስና ማሽን ማቅረብ • የጥራት ቁጥጥር • የደህንነት ጥበቃ • የአካባቢ ጥበቃ • ሕጎችን መከተል E. Time Control and Completion (የጊዜ ቁጥጥር እና ማጠናቀቅ) ይህ ክፍል፦ • Commencement Date (የሥራ መጀመሪያ ቀን) • Completion Period (የማጠናቀቂያ ጊዜ) • Extension of Time – EOT (የጊዜ ማራዘሚያ) • Delay (መዘግየት) • Suspension (ሥራ ማቆም) ይቆጣጠራል። F. Payment Provisions (የክፍያ ድንጋጌዎች) በጣም አስፈላጊ ክፍል ነው። ይዟል፦ • Contract Price • Interim Payment • Advance Payment • Retention Money • Final Payment Interim Payment በሥራ ሂደት ውስጥ የሚፈጸም ጊዜያዊ ክፍያ። Retention ጉድለት እንዲስተካከል በጊዜያዊነት የሚያዝ የገንዘብ መጠን። Advance Payment ሥራ ከመጀመሩ በፊት ለሞቢላይዜሽን (mobilization) የሚሰጥ ቅድመ ክፍያ። G. Variations and Change Orders (የሥራ ለውጦች) በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለውጦች መኖራቸው የተለመደ ነው። ይህ ክፍል፦ • ለውጥ እንዴት እንደሚታዘዝ • የዋጋ ግምገማ • የጊዜ ተፅእኖ • የማጽደቅ ሂደት ይገልጻል። Variation ሊሆን የሚችለው፦ • የብዛት መጨመር • የብዛት መቀነስ • ተጨማሪ ሥራ • የዲዛይን ለውጥ H. Quality Control and Testing (የጥራት ቁጥጥር እና ሙከራ) ይህ ክፍል፦ • Inspection (ምርመራ) • Laboratory Testing (የላብራቶሪ ሙከራ) • Defective Work Rejection (ጉድለት ያለበት ሥራ መከልከል) ይዟል። Engineer የሚኖረው ሥልጣን፦ • ሥራ መመርመር • ደረጃ ያልጠበቀ ሥራ ማስወገድ • ድጋሚ ሙከራ ማድረግ I. Defects Liability (የጉድለት ኃላፊነት) ይህ ክፍል፦ • Defect Liability Period • የጥገና ግዴታ • ጉድለት ሪፖርት ሂደት ይገልጻል። በአብዛኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚገኙ ጉድለቶች በተቋራጩ ወጪ ይስተካከላሉ። J. Insurance and Risks (ኢንሹራንስ እና አደጋ ኃላፊነት) የሚፈለጉ ኢንሹራንሶች፦ • Works Insurance • Workers Insurance • Third Party Liability Insurance • Equipment Insurance እንዲሁም አደጋዎች በማን እንደሚሸፈኑ ይወስናል። K. Health, Safety and Environment (HSE) ይህ ክፍል፦ • የሰራተኛ ደህንነት • የትራፊክ ቁጥጥር • የአካባቢ ጥበቃ • የአደጋ ሪፖርት ያካትታል። L. Force Majeure / Exceptional Events (ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ክስተቶች) ምሳሌዎች፦ • ጦርነት • ጎርፍ • መሬት መንቀጥቀጥ • ወረርሽኝ ይህ ክፍል፦ • ኃላፊነት እፎይታ • EOT • ሥራ ማቆም • ኮንትራት ማቋረጥ ይወስናል። M. Termination (የኮንትራት ማቋረጥ) በEmployer • ሥራ መተው • ኪሳራ (bankruptcy) • ደካማ አፈጻጸም • ከፍተኛ መዘግየት በContractor • ክፍያ አለመፈጸም • ረጅም የሥራ ማቆም • ከባድ የEmployer ጥፋት

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቶቹን የም
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች በ https://vacancy.eep.com.et/VacancyList በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የምዝገባ ጊዜ፡ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡ ዝርዝሩን በተያያዘው ምስል ይመልከቱ! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

+7
RC I Questions for Tutoarial.pdf1.32 MB

AASTU MOCK-2 [2025] EXIT EXAM MODEL

foundation engineering objective questions.pdf0.72 KB

+1
Road & Transport Engineering Module.pdf2.77 MB

Answer.pdf4.24 KB

Exit 2030,.pdf3.45 MB

Civil Engineering Model Exit Exam_2016 2nd roundpdf

Civil Engineering 2nd round model exam pdf

+3
Department of Civil engineering

AASTU MOCK-2 [2025]

AASTU MOCK-2 [2024]

AASTU MOCK-2 [2023]