ru
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Открыть в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 19 949 подписчиков, занимая 1 157 место в категории Медицина и 1 681 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 19 949 подписчиков.

Согласно последним данным от 27 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -557, а за последние 24 часа — -23, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 26.07%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 6.79% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 5 203 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 354 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 10.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 28 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Медицина.

19 949
Подписчики
-2324 часа
-1257 дней
-55730 день
Архив постов
የኩላሊት ጠጠር እንዳለብዎት የሚያሳብቁ ምክያቶች 1. ኃይለኛና የማያቋርጥ ህመም በብሽሽቶ እና በጀርባዎ የታችኛው ክፍል ላይ መሰማት 2. በሽንቶ ውስጥ ደም መኖር 3. ደስ የማይል እና እንግዳ ያለው ሽታ በሽንቶ ላይ መታየት 4. ትውኪያና ማቅለሽለሽ 5. ነጭ የደም ህዋሰ ወይም መግል በሽንትዎ ላይ መታየት 6. ሽንቶ አንዳንዴ ድፍርስ ውሃ መምሰል 7. የሚሸኑት ሽንት መቀነስ 8. በሚሸኑ ጊዜ የማቃጠል ስሜት መኖር 9. ሽንቶ ቶሎ ቶሎ መጣው ማለት 10. በጠጠሩ ምክንያት ኢንፌክሽን ከተፈጠረ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ሊያጋጥሞ ይችላል፡፡ የኩላሊት ጠጠር እንዴት ይከሰታል 1. ለኩላሊት ጠጠር ዋነኛ መከሰት መንስሔ ተደርጎ የሚወሰደው በቂ ውሃ በየዕለቱ ያለመጠጣት ነው ፡፡ በዚህም የተነሳ ዩሪክ አሲድ የተሰኘው የሽንታችን አካል ታጥቦ ወደ ውጭ ስለማይወጣ ወደ ኃይለኛ አሲድነት ይቀየራል፡፡ በዚህ የተነሳ አሲዱ በቀጥታ ወደ ጠጠርነት ራሱን በሂደት ይለውጣል፡፡ 2. ጨው የበዛባቸው ምግቦች መመገብ፡- ይሄ ደግሞ ድርቀትን በመፍጠር በሽንት አማካኝነት ታጥበው የሚወጡ ነገሮች በጊዜ ሂደት ወደ ጠጠርነት እንዲቀየሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ 3. በፕሮቲን የበለጸጉና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የኩላሊት ጠጠር እንዴት እንከላከል 1. በቂ ውሃ በየቀኑ ይጠጡ ቢያንስ ከ6 እስከ 8 ብርጨቆ 2. የአልኮል አወሳሰድ መጠን ይቀንሱ 3. ጨው የሚበዛባቸው ምግቦችን ይቀንሱ፡- የድንች ጥብስ፣ የስጋ ቋንጣ፣ የታሸጉ ምግቦች፣ ኑድሎችን ከመግብ ገበታዎ ያስወግዱ 4. ስኳር፣ካፊን እና ካርቦኔት ያለባቸውን መጠጦች አይውሰዱ 5. ካልሲየም እና ሲትሪክ አሲድ በከፍተኛ ሁኔታ የያዙ ምግቦችን እንደ ሎሜ፣ ብርቱካንና ማንጎ ጭማቂዎችን ያዘውትሩ 6. በቂ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ፡፡ ክብደቶን ያስተካክሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

️እርግዝና እና ወሲብ አንዳንድ ጥንዶች የሴቷ ማርገዝ በወሲብ ህይወታቸው ላይ ምንም አይነት ለውጥ ባይፈጥርባቸውም በአብዛኛው እርግዝና የወንዱንም ሆነ የሴቷን የወሲብ ፍላጎት ይቀይረዋል። የተወሰኑ ጥንዶች እርግዝና የተሻለ የወሲብ ህይወት እንደሰጣቸው ሲመሰክሩ ሌሎች ከባድ ጊዜ ሊያሳልፉ ይችላሉ። ሆኖም በተለይ ከወሊድ በኋላ ብዙዎች ረዘም ያለ እረፍት ይወስዳሉ። pregnancy-sexበዚህ ወቅት በፊት የነበራችሁ ጥሩ የወሲብ ህይወት በጣም እንዳይቀየር ዋናው መፍትሄ ስለምትፈልጉት እና ስለሚሰማችሁ ነገር በግልፅ መወያየት ነው። ሁለታችሁንም የሚያረካ መፍትሄ ፈልጉ። ከዚህ በታች ብዙ ጥንዶች ስለ ወሲብ የሚያሳስቧቸው ነገሮች ተዘርዝረዋል። በሃገራችን ባህል ስለነዚህ ጉዳዮች በግልጽ ማውራት ሊከብድ ይችላል። ይህ ከሆነ ከባለቤትሽ/ባለቤትህ ጋር በመሆን ይህንን ፅሁፍ ማንበብ ነገሮችን ሊያቀል ይችላል። የግብረ ሥጋ ግንኙነት በእርግዝና ወቅት በእናቲቱ ወይም በልጁ ላይ ችግር ይፈጥር ይሆን? ይህ ጥያቄ ብዙዎችን የሚያሳስብ ነው። በአጠቃላይ መልሱም በፍፁም ነው። ሴቷ በወሲብ ወቅት በምትረካበት ጊዜ በማህፀን ላይ የመኮማተር (የመጫን) ስሜት ሊፈጥር ይችላል። የማህጸን ግርግዳ ስለሚሳሳ በግንኙነት ወቅት በትንሹ ሊደማ ይችላል። እኚህ ሁኔታዎች ባይመቹም በብዛት አደጋ የላቸውም። ለመጀመሪያ ጊዜ የደማሽ እንደሆነ ወይም አደማምሽ ካሳሰበሽ ሃኪምሽን አማክሪ። የደማሽው መጠኑ ብዙ ከሆነ ግን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ሂጂ። በባለቤትሽ ብልትና በልጅሽ መካከል ብዙ ርቀት ስላለ በተጨማሪም ልጅሽ በማህፀን ግርግዳ፣ እንዲሁም የማህፀን በሩን ዘግቶ ባክቴሪያና የውንዱ የዘር ህዋስ እንዳይገባ በያዘው ዝልግልግ መድፈኛ ከዚያም አልፎ በክርታሱና ውስጡ ባለው የሽርት ውኃ ተከልሎ ስለሚገኝ ወሲብ ልጅሽ ላይ የሚፈጥርበት ችግር አይኖርም። ጥሩ ግንኙነት ስለመፈፀም ብዙ እናቶች በእርግዝና ምክንያት በሰውናታቸው ውስጥ ባሉ ሆርሞኖች አማካኝነት እና የብልት ግርግዳዎች ስለሚለሰልሱ በወሲብ ወቅት በቀላሉ ለመራስ ይችላሉ። ስለዚህም በዚህ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይመቻቸዋል። በጣም ጥሩው ጊዜ በተለይ የመጀመሪያው ሶስት ወር (ብዙ ማቅለሽለሽ የሚሰማበት) ካለፈ በኋላ ፅንሱ ትልቅ ሆኖ ሆድ በጣም እስከሚገፋ በመኃል ያለው ነው። ሆድሽ ወደፊት ሲገፋስ? ሆድሽ በሚገፋበት ጊዜ ለወሲብ የሚመች አኳኋን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ዋናው ነገር የሚመቻችሁን አይነት መንገድ እስክታገኙ መሞከር ነው። ሴቷ በጎኗ ብትተኛ ወይም በጉልበቷ ብትንበረከክ የበለጠ ሊመቻችሁ ይችላል። ወደ እርግዝና መጨረሻ በዚህ ጊዜ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል። ጉልብት የበዛው ግንኙነት ማድረግ አይመከርም። ቢሆንም አንደኛው ወገን ወሲብ ማድረግ ፈልጎ ሊላኛው ወገን ባይፈልግ ሌሎች ፍቅርን ለመግለፅ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮች አሉና መረሳት የለባቸውም። ከወሊድ በኋላ ወሊድ በእያንዳንዷ እናት ላይ የሚፈጥረው ስሜት ይለያያል። ቀላል ወሊድ ከነበረ በቶሎ ወደነበረው ሁኔታ ለመመለስ ይቀላታል። ከባድ ወሊድ ያሳለፈች እናት ደግም አእሮዋም ሆነ ሰውነቷ ዝግጁ እስኪሆን ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባት ይችላል። በወሊድ ወቅት የማህፀን መውጫ እና አካባቢው ሊቆስልና ህመም ሊሰማ ይችላል። ሆኖም ይሄ የሚድን ሁኔታ ነውና ሊያሳስብሽ አይገባም። በሰውነትሽ ውስጥ ያለው የኤስትሮጅን መጠንም ይቀንሳል። በዚህ ምክንያትም እንደበፊቱ እርጥበት ላይሰማሽ ይችላል፤ ነገር ግን ይሄ የተለመደ ነው። ሊረዳሽ የሚችል ቅባት በፋርማሲዎች ስለሚገኝ ሐኪምሽን ማማከር ትችያለሽ። ከወሊድ በኋላ ግንኙነት ማድረግ የሚቻለው መቼ ነው? ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች በፊት እንደነበሩት ለመመለስ ቢችሉም ብዙ ጥንዶች የበለጠ ጊዜ ይወስድባቸዋል።፡አዲስ ወላጆች እንደመሆናቸው በቤታቸው ለመጣው እንግዳ ህይወት ብዙ ትኩረት ስለሚሰጡ ላያስባቸውም ይችላል። አብሮ በመተኛት እና በመጨዋወት ቀስ በቀስ ድሮ ወደነበረው ፍቅራቸው በሂደት መመለስ ይችላሉ። ይህ እንደገና ለመላመድ እድል ይሰጣቸዋል። ስለስሜታቸው በግልፅ መወያየት በጣም ጥሩ ነው። በተጨማሪ ስለዚህ ጉዳይ ሐኪምን ማማከር ይቻላል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias @DrSofonias ❤️❤️

የጫት ሱስ የጫት ተክል ቀይ ባህር ዳርቻና ምስራቃዊው የአፍሪካ ክፍል አካባቢዎች ላይ በሰፊው የሚበቅል የእጽ አይነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ሶማሊያ፣ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ማዳጋስካርና የመን በብዛት ከሚበቅልባቸው ሀገራት መሀል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ረጅም ለሚባል ጊዜ ይህንን ተክል እየተጠቀሙ እንዳሉ ይነገራል፡፡ የጫት ተክል እንደሚበቅልበት አካባቢ የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት ይገኛል፡፡ ቃት፣ቃድ፣ሚራ፣ማይሩግጊ፣ካት እና ካታ የጫት ተክል የሚጠራባቸው ስሞች ናቸው፡፡ የጫት ተክል ሌሎች የተክል አይነቶች ሊበቅሉ በማይችሉባቸውና በረሀማ ቦታዎች እንደዚሁም ከፍተኛ ስፍራዎች ላይ አመቱን ሙሉ ሊበቅል ይችላል፡፡የጫት ተክል በውስጡ ከ40 ያላነሱ ንጥረ ቅመሞችን በውስጡ ይዟል፡፡ ከነዚህ ንጥረ ነገሮች መሀልም የማይጠቅሙ የፕሮቲን የመጨረሻ ውጤቶች እንደዚሁም ከእጽዋት የሚገኙና ናይትሮጅንን በብት የያዙ ንጥረ ቅመሞች (አልካሎይድስ) በዚህ ተክል ውስጥ በብዛት የሚገኙት ናቸው፡፡ ጫትን ጥቅም ላይ የሚያውሉ ሰዎች ውጤቱን የሚያዩት ‹ካቲንና ካቲኖን› በሚባሉ ሁለት ንጥረ ቅመሞች ምክኒያት ነው፡፡ ጫት የደስታ ስሜትን መስጠት የሚጀምረው ገና ማኘክ ሲጀመር ነው፡፡ በጫት ውስጥ ያለውና ካቲኖን የሚባለው ንጥረ ነገር ውጤት የሚታየው ታዲያ ከአምስት አስከ አስር ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ንጥረ ነገር አንዴ ሰውነት ውስጥ ከገባ በሗላ ጥቅም ላይ የመዋል ፍጥነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ሂደቱ የሚጀምረው በመጀመሪያ በጉበት ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ነው፡፡ በጣም ትንሽ መጠን ያለው (ሁለት በመቶ ያህሉ) ሽንት ላይ ይታያል፡፡ ‹ካቲን› የሚባለው ንጥረ ቅመም በአንጻሩ ዘግየት ያለ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ በ24 ሰአታት ጊዜ ውስጥ ምንም ለውጥ ሳያደርግ ከሰውነት ይወገዳል፡፡ ጫት ለረጅም ጊዜያት የሚቅሙ ሰዎች የሚገጥሟቸው የጤና እንከኖች፡ 1. የጥርስ መበስበስ 2. የምግብ ፍላጎት መቀነስ 3. የስሜት መረበሽ 4. ከፍተኛ የድካም ስሜት 5. ስንፈተ ወሲብ 6. የአእምሮ ህመሞች 7. የሆድ ድርቀት የጫት ሱሰኝነትን ለማቆም መደረግ ያለባቸው ነገሮች -በተቻለ መጠን ተመሳሳይ የሱስ ችግር ካለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መራቅ - ጫት የሚያዘወትሩበትን ጊዜዎች ለይቶ ማወቅና በነዚህ ወቅቶች ሊያስረሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን መፍጠር -የጓደኛ ግፊትን ለመከላከል መሞከር -የህክምናና የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ምክር መሻት እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias @DrSofonias

የወተት ነገር ወተት ቀልድ እንዳይመስልህ የወተት ጥቅሞች በርካታ ናቸው ለአብነት የወተት 9 ጥቅሞች እንመልከት 1. ለጉንፋን እና ሳል ህክምና። 2. ለሰውነታችን መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ያመክናል፡፡
የወተት ነገር ወተት ቀልድ እንዳይመስልህ የወተት ጥቅሞች በርካታ ናቸው ለአብነት የወተት 9 ጥቅሞች እንመልከት 1. ለጉንፋን እና ሳል ህክምና። 2. ለሰውነታችን መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ያመክናል፡፡ 3. የአርትራይተስ እና መገጣጠሚያ ህመሞችን ያስታግሳል፡፡ 4. የራስ ህመምን ያስታግሳል፡፡ 5. በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል የተለያዩ በሽታዎችን ይከላከላል፡፡ 6. ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ ይረዳናል፡፡ 7. በወር አበባ ጊዜ የሚከሰትን የሆድ ቁርጠት ይቀንሳል፡፡ 8. የሚያምር የሰውነት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 9. የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትን ያፋጥናል፡፡ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ይህን ያውቁ ኖሯል???? ስለ ሰውነታችን አስገራሚ እውነታዎች ክፍል 1 👉 ሰው የውጪ ቆዳውን አራግፎ እንደገና በአዲስ የሚተካው በየሀያ ሰባት ቀን ልዩነት ነው!!! 👉 የአፍንጫችን ሁለቱ ቀዳዳዎች
ይህን ያውቁ ኖሯል???? ስለ ሰውነታችን አስገራሚ እውነታዎች ክፍል 1 👉 ሰው የውጪ ቆዳውን አራግፎ እንደገና በአዲስ የሚተካው በየሀያ ሰባት ቀን ልዩነት ነው!!! 👉 የአፍንጫችን ሁለቱ ቀዳዳዎች ኖስትራልስ ይባላሉ!!! 👉 ልክ እንደ እጃችን አሻራ የምላሳችን አሻራም ይለያያል!!! 👉በአለም ላይ በብዙ ሰዎች የሚገኘው የደም አይነት o የደም አይነት ነው!!! 👉የሰው ከንፈር ቀይ የሚሆነው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቀጫጭን የደም ሥሮች ከከንፈራችን ቆዳ ሥር ስለሚገኙ ነው። የደም ማነስ ወይም በእንግሊዘኛው (አኒሚያ) ሲያጋጥመን ከንፈራችን ይገረጣል ወይም አመዳም ይሆናል!!! 👉የተኛንበት ክፍል በጣም ቀዝቃዛ ከሆነ አስፈሪ ህልም የማየት እድላችን ሰፊ ነው!!! 👉 እንባና ለሀጭ ባክቴሪያን መሰባበር የሚችል "ላይሶዞም" የተሰኘ ኢንዛይም አላቸው። ለዚህም ነው በአፍንጫ፣ በጉሮሮና አይናችን ውስጥ ባክቴሪያዎች እንዳይገብ ጠንካራ መከላከል የሚሰሩት!!! 👉ሰውነታችን በ30ደቂቃ ውስጥ የሚያመነጨው 98.6ዲግሪሴንቲግሬድ ሙቀት ፖስታ የማብሰል አቅም አለው!!! 👉ስንፈራ ጆሯችን ብዙ የጆሮ ኩክ ያመነጫል!!! 👉ሰው ራሱን በራሱ ኮርኩሮ ማሳቅ አይችልም። ምክንያቱም ኩርኮራው ከየት እንደመጣ አዕምሯችን ቀድሞ ስለሚገነዘብ!!! 👉ሁለቱን እጆቻችንን ወደ ጎን ስንዘረጋቸው የሚኖረው ርዝመት ከሙሉ የሰውነታችን ቁመት ጋር እኩል ነው!!! 👉ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ስብ የሚያቀልጡት በዝግታ ነው!!! እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

የልብ ህመም ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች • ድካም • የሁለቱም እግር እብጠት • ለመተንፈስ መቸገር • ከሌላው የተለየ ጠቆር ያለና የሚተጣጠፍ ቆዳ አንገት ፣ ብብትና ሌሎች መገጣጠሚያ አካባቢ
የልብ ህመም ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች • ድካም • የሁለቱም እግር እብጠት • ለመተንፈስ መቸገር • ከሌላው የተለየ ጠቆር ያለና የሚተጣጠፍ ቆዳ አንገት ፣ ብብትና ሌሎች መገጣጠሚያ አካባቢዎች ካለ • የድድ መድማት • ሰማያዊ እና ግራጫ የእጅና የእግር ጣቶች • ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች • እራስ የማዞር እና ብዥ የማለት ችግር • ከጥፍር ስር ጥቁር ነጠብጣብ ካለ • ነገሮችን በእጅ አጥብቆ ለመያዝ መቸገር • በሚተኙበት ጊዜ የትንፋሽ መቆራረጥ (መተንፈስ ማቆም ካለ)የልብ ህመም ሊኖር እንደማይችል ይጠቁማል ። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

እርጎ በመጠጣት የምናገኛቸው የጤና ጥቅሞች 1. እርጎ በጠቃሚ ንጥረ ነገር የበለፀገ ነው፡- በካልስየም የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችን ከሚያስፈልገው የእለታዊ ካልስየም ፍላጎት(Need) ውስጥ 49 በመቶ የሚሆነውን ካልስየም ከአንድ ኩባያ እርጎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህም የጥርሳችንንና የአጥንታችንን ጥንካሬ አስተማማኝ በማደረግ ጤንነታቸውን ይጠብቃል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ቫይታሚን ቢ፣ፎስፈረስ፣ማግኒዜየም እና ቫይታሚን ዲ አለው፡፡ በዚህም የልብ በሽታን፣የደም ግፊትንና ድባቴን የመሳሰሉ የጤና ችግሮችን ይከላከላል፡፡ 2. ከፍተኛ የፕሮቲን ንጥረ ነገር ስለያዘ ለሰውነት ግንባታና ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ በተጨማሪም የምግብ ፍላጎትን (Appetite) በመቀነስ የሰውነት ክብደታችንን ለመቆጣጠር ይረዳናል፡፡ 3. የሆድ መንፋት፣ የአይነምድር ድርቀትና ተቅማጥን በማስወገድ ጤናማ የሆነ የምግብ ሥርዓተ ልመት (Boost digestive health) እንዲኖር ያደርጋል፡፡ 4. የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጠናክራል፡፡ በተለይ በየዕለቱ እርጎ የሚጠቀሙ ሰዎች በበሽታ የመጠቃት እድላቸው ከማይጠቀሙት ጋር ሲነፃፅር በእጅጉ የቀነሰ ነው፡፡ 5. እረጎ የአጥምት መሳሳትን ይካላከላል፡፡እርጎ በቫይታሚንና በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ ለአጥንት ጤና ወሳኝ ነው፡፡ በየእለቱ ከተመገቡ ደግሞ ከዕድሜ መግፋት ጋር የሚከሰተውን የአጥምት መሳሳት ይከላከላሉ፡፡ 6. የደም ቅባትና የደም ግፊትን በመቀነስ አርጎ ለልብ ጤና ተስማሚ መሆኑን ይነገርለታል፡፡ 7. የአለርጂ (ያለመስማማት) ምልክቶችን ይቀንሳል፡፡ ከውጭ አካባቢ ከወቅት ጋር ተያይዞ በሰውነታችን ላይ የሚያጋጥሙ የአለርጂ( የአለመስማማት) ምልክቶችን አንድ ኩባያ እርጎ በየዕለቱ በመጠጣት መቀነስ ይቻላል፡፡ አለርጂው የቆዳ፣የአፍንጫ፣ የጀሮ ወይም ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሊሆን ይችላል፡፡ 8. እርጎ በጉንፋንና በኢንፍሎይንዛ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል፡፡ እርጎ በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማችንን በማሳደግ በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ቲ-ሴልስ (ቲ- ሕዋሳት) ኢንፌክሽኖችን እንዲዋጉ ያጠነክራቸዋል፡፡ 9. የእርሾ ኢንፌክሽንን (yeast infection) ለመከላከል ይረዳል፡- ፀረ-ተዋህሲያን (antibiotic) መድኃኒት በተደጋጋሚ ጊዜ መወሰድ ለእርሾ ኢንፌክሽን ያጋልጣል፡፡ ስለዚህም በእርጎ ውስጥ ያለው ባክቴሪያ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የፒኤች ደረጃ ሚዛናዊ በማድረግ በእርሾ ምክንያት የሚመጣውን የኢንፌክሽን ሕመምና ምቾት ማጣት ይከላከላል፡፡ 10. ከፍተኛ የደም ግፊት ይቀንሳል፡- በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ጥናቶች እርጎ በየዕለቱ መጠጣት ከፍተኛ የደም ግፊትን በጥሩ ሁኔታ መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ራሰ በራነት ወይም የፀጉር መመለጥ ምንድን ነው? መነሻው እና ህክምናው ምንድን ነው? ፀጉር ኬራቲን(keratin) ከሚባለው ፕሮቲን በዉጨኛው የቆዳ ክፍል የፀጉር ፎሊክል ዉስጥ ይሰራል፡፡ ፎሊክላችን አዲስ የፀጉር ሴል ሲሰራ/ሲያመርት አሮጌ ሴሎቻችን በአመት 6 ኢንች ወደ ዉጪ ቆዳችን ተገፍተው ይወጣሉ የምናየው ፀጉር የሞተ ክር መሳይ ኬራቲን ሴል ነው፡፡ በአማካይ የአንድ አዋቂ ሰው ጭንቅላት ከ 100,000-150,000 የሚደርስ ፀጉር ሲይዝ በቀን 100 ፍሬ ፀጉር በራሳቸው ጊዜ ይነቀላሉ በማበጠሪያች ውስጥ ትንሽ የተነቀሉ ፀጉር ማግኝት የተለመደ እና ሊያስደነግጠን የማይገባ ጤናማ ሁኔታ ነው፡፡ የወንዶች እና የሴቶች ራስ በራን ከአፍላ የጉርምስና ዕድሜ አንስቶ ሊጀምር ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው በ30ዎቹ ዓመት መገባደጃና በ40ዎቹ ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው የፀጉር መርገፍ በብዙ ወንዶች ላይ የሚደርስ ቢሆንም መጠኑ ከዘር ወደ ዘርና ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ይለያል፡፡ ያም ሆነ ይህ ለዚህ ችግር የተረጋገጠ መድሃኒት ማግኘት አልተቻለም፡፡ አንዳንዶች በራቸውን ለመሸፈን ሰው ሰራሽ ፀጉር ለማድረግ ወይም በቀዶ ህክምና ፀጉር ለማስተካከል ይመርጡ ይሆናል፡፡ ለተቀረው ፀጉር ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ፀጉር እንዳይረግፍ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ የፀጉር መሳሳት መንስኤዎች የተለያዩ ብዙ ምክንያቶች ፀጉራችን እንዲረግፍ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ከነዚህም መካከል ሆርሞን የተዛባ የአንድሮጂን ሆርሞን መጠን (የወንድ ሆርሞን ሲሆን በወንድና ሴቶች ይመረታል) ጂን(ዘረ መል) ከሁለቱም ወንድ እና ሴት ወላጆች ለወንድ ወይም ሴት ልጅ መመለጥ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ጭንቀት፣ ህመም እና ወሊድ ጊዜያዊ የሆነ የፀጉር መርገፍ ያስከትላል፡፡ የሆድ ትላትሎችና የፈንገስ ኢንፊክሽን ተጠቃሽ ናቸው መድሃኒቶች ለካንሰር ህክምና የሚዉለው ኬሞቴራፒ፣ የደም መቅጠን፣ ለደም ግፊት የሚዉሉ መድሃኒቶች፣ አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች ጊዜያዊ የሆነ የፀጉር መርገፍ ሊዳርጉን ያችላሉ፡፡ ቃጠሎ፣ አደጋና ራጅ ጠባሳ እስካልተከሰተ ድረስ አደጋው በሚድንበት ጊዜ መደበኛ ፀጉራችን መብቀል ይጀምራል፡፡ የኮስሞቲክስ ውጤቶች በብዛት ሻምፖ፣ ፐርም እና የተለያዩ ንጽህና መጠበቂያዎች ፀጉር በቀላሉ እንዲሰበር በማድረግ ለፀጉር መሳሳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ለራሰ በራነት ላይዳርጉን ይችላሉ፡፡ የጤና ችግሮች የታይሮይድ በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ የብረት እጥረት፣ የአመጋገብ ችግርና የደም ማነስ የፀጉር መመለጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ ምግብ የፕሮቲን መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦችና የካሎሪ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦች የፀጉር መመለጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡ የፀጉር መሳሳት ወይም የራስ በራነት መፍትሔ የልት ቅጠል እና ሥር (የማርያም አንባሻ) malva parviflora ይህ ከስር የምትመለከቱት ዕፅ በብዛት ልት በመባል የሚጠራ አረም መሳይ ዕፅ ሲሆን በብዛት ወይና ደጋ እና ደጋ አከባቢ የሚገኝ ዕፅ ሲሆን! ልት ዕንጨቱ ጥንካሬ የሌለው የደረቀ ቍስል የሚያለሰልስ ማላጋ ቅጠል የታወቀ ዕውቅ ፤ እንደ ጐመን እየቀቀሉ ሲበሉት ለሆድ መድኅኒት የሚሆን ዕጽ ነው። ከመርዛማነት ውጭ የሆነ ዕጽም ነው። የፀጉር መነቃቀል መፍትሔ አጠቃቀም የልት ቅጠል እና ሥር በእርጥቡ በንጽህና በመጨቅጨቅ! ሁለት የሾርባ ማንኪያ የተጨቀጨቀው ዕፅ ከንፁህ የፀጉር ቅቤ ጋር በማቀላቀል ሙሉ ፀጉሮትን መቀባት ለ ስድስት ሰዓታት ያክል አቆይቶ በደንብ ሳያሹ ቀስ አድርጎ በሻምፖ መታጠብ ። ከ ታጠቡ በኃላ በልት ቅጠል ብቻ ቀስ አድርገው በድጋሚ መታጠብ። ይህ ድርጊት በሳምንት ሶስት ጊዜ ደጋግመው ለ አንድ ወር ያክል ይጠቀሙ። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

Hypospadia
Hypospadia

Undescended testis
Undescended testis

በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማምለጥ vimax አወሳሰድ/አጠቃቀም እንዷ ብልቃጥ 60capsule/60እንክብል ነው ምቲዘው ባለ 30capsule የምቲዝም አለች ግን እኔ የማወራው ስለ original ነው አወሳሰዱ በቀን አንድ አንድ ቢሆን ይመከራል በቀን ሁለት ሁለትም መውስድ ይቻላል። Side Effect/የጎንዮሽ ጉዳት እነሱ እንደሚሉት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ይበሉ እንጅ እኔ ከማቃቸው ተጠቃሚዎች እንደተረዳሁት የጨጓራ በሽታ ያለባቸው ላይ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ነግር ግን ጎን ለጎን የጨጓራ መዳኒት እየወሰዱ የሚጨርሱም አሉ ከዚ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት ጎዳት የለዉም አንድ አንዶች ላይ አላርጂክ ከሞሆን በስተቀር። የሚከለክላቸው ነገሮች መዳኒቱን መጠቀም ከጀመራቹ መዉሰድ/መጠቀም የሌለባቹህ ነገሮች .አልኮል/አረቄ ነገሮች ናቸው። መዳኒቶቹን መግዛት የምትፈልጉ እኔ ትክክለኛው Original Vimax አስመጪዎችን ስልካቸውን ልሰጣቹህ እችላለው መዳኒቱ ሀገር ዉስጥ እንዲሸጥ ገና ፍቃድ ስላላገኘ በዚም ምክንያት ዋጋው በጣም የተጋነነ ነው በዛ ላይ አስመጪዎቹ እየሸጡ ከተያዙ ወይም እጃቸው ላይ ከተገኘ የሚቀጡ ነው የሚሆኑት እናም ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚሸጡት ነገር ግን እኔ በትክክል ስለማዉቃቸው ችግር አይኖርም መዳኒቱም ፍቃድ ሊያገኝ በሂደት ላይም ስለሆን ብዙም አያሳስብም። በተጨማሪም የኔ ምክር ነው ጫት እየቃማቹ መዳኒቱን ባትወስዱ/ባትጠቀሙ ጥሩ ነው ቢያንስ መዳኒቱን እስክጨርሱ ጫቱን ብተዉት እላለው ስለ ጫት የጎንዮሽ ጉዳቶች በቅርቡ ፅፍላቹኃለው የአስመጪዎችን ስልክ እና አድራሻ በብዛት inbox ላይ ስትጠይቁኝ የነበራቹ ስልካቸው 0992484672 በ inbox ለማግኘት https://t.me/Sellerman12 አመሰግናለው እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias