cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

@Tewahdo27 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮች 🌠በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇 ✅መዝሙሮች✅ የንስሐ መዝሙሮች✅ ያሬዳዊ ዜማ✅ የማርያም ውዳሴዎች✅ መፅሐፍ ሀይማኖት........ ወ.ዘ.ተ 🔵 YouTube 🔴ለሃሳብ እና አስታያየት @Tewahdo27

Больше
Рекламные посты
3 796
Подписчики
+324 часа
+627 дней
+22330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ቸሩ መድኃኔዓለም እንኳን ለወርሃዊው የመድኃኔዓለም የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!! " የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው..." ሉቃ. ፲፱፥፲ /19፥10/ ❤ የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ህይወቱን ለዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠው በዚህ ቀን ነው ❤ ይህ ቀን ስለ ክርስቶስ ሕማም፣ ስለ መከራ መስቀሉና ስለሞቱ የተነገሩ ትንቢቶችና ምሳሌዎች ሁሉ የተፈጸሙበት ነው ❤ ሰማያዊው አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ምትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት ነው ❤ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርን ገለ፣ መስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለሙን ነጻ አወጣ ❤ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ፍቃዱ ለየ ❤ የሥቅለቱና የሞቱ መታሰቢያም በዚህ ቀን ነው በምህረትና ቸርነቱ ይጠብቀን #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #አንዲት_ጥምቀት #ተዋህዶ #orthodoxchurch #ኢትዮጵያ @ortodox_27
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
✝️ እኔን የሚጠብቀኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ እናንተም ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ። ሠናይ ዕለተ ሰንበት 🌹

Показать все...
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሰን !!! ✝️ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፦ ➻ በትንሿ ምስራቃዊ እስያ በጥር ፪ ፪፻፸፯ ዓ.ም ቀጰዶቅያ በምትባል አከባቢ ተወለደ፣ ➻ በክርስትና የጸና የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ሳይክድ ሰማዕት የሆነ ቅዱስ ነው፣ ➻ ሚያዚያ ፳፫ ቀን ፫፻፫ /303/ ዓ.ም በልዳ ሰማዕትነትን ተቀበለ፣ የላቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ምልጃና ልመና አይለየን። በጸሎት ያስበን። #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #ተዋህዶ @ortodox_27
Показать все...
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡ ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 🔸 @ortodox_27 🔸🔹🔸 @ortodox_27 🔸 @ortodox_27 ✍️Comment
Показать все...
የመንፈሳዊ ጥያቄ ተሳትፎ ጥያቄ ቁጥር 104 💌💌💌💌💌💌💌💌 🌹🌹 ሰኔ [22}  ቀን 🌹🌹 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ❖ እንኳን አደረሳችሁ  ❖ ✞    እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †††  ✝ ✝ 💌----💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌 የኦርቶዶክሳዊ_ጥያቄ_ቁጥር_103_መልስ   "መ"  ''ሁሉም መልስ ነው  " ያላችሁ በትክክል   መልሳችኋል። ለተሳትፏችሁ  እግዚአብሔር አምላክ ቃለ ህይወትን ያሠማልን ማስተዋልና ጥበቡን ያድለን። ማብራሪያ መልሱ መ ሁሉም ነው። ቤተክርስቲያን የሚባለው ፨ የክርስቲያን ቤት የክርስቲያን መሰብሰቢያ የክርስቲያን መገኛ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ክርስቲያኖች የሚጸልዩበት ሥጋ እና ደሙን የሚቀበሉበት የሚሰግዱበት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት የጸሎት ቤት ማለት ነው( ሉቃ. 19፡46 ) ፨ እያንዳንዱ ሰው/ግለሰብ ይህም ቤት ማለት ወገንን የሚመለክት በሚሆንበት ጊዜ ነው ቤተ ያዕቆብ፣ ቤተ ሌዊ፣ ቤተ እስራኤል እንደሚባሉ ሁሉ የክርስቶስ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ። ፨ የክርስቲያኖች ሕብረት/አንድነት ቤተ ክርስቲያን ዘግብጽ፣ ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ የሚል ንባብ ቢገኝ በግብጽ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ማኅበር፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ማኅበር ማለት ነው ይኸውም በቅዱስ ጴጥሮስ አነጋገር ይታወቃል፡፡ 1ኛ ጴጥ 5፣13  ይመልከቱ 💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌💌 አሁን ወደ ዛሬው ጥያቄ እንመለስ ዝግጁ ናችሁ?  ዩቱዩብ ቻናሉን  ላይክ ሼር ሰብስክራይብ ማድረጋችሁን አትርሱ https://youtube.com/@meklit-the-tewahido?si=0unswl3PIwBaXtho ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 💌💌💌💌💌💌💌💌💌 ኦርቶዶክሳዊ_ጥያቄ_ቁጥር_104 የመጀመሪያዋ ቤተክርስትያን በየት ተሰራች ? ሀ//      በፊልጵስዩስ ለ//      በቆሮንቶስ ሐ//      በተሰሎንቄ መ//     ኤፌሶን ይህ ዩቱዩብ ቻናል ስለ ቅዱሳን ክብር ተዓምር ገድል ይናገራል::መክሊት ዘተዋሕዶ  ዩቱዩብ ቻናል  ትምህርተ ወንጌልን፣ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን፣ የቅዱሳንን ተጋድሎ፣ መንፈሳዊ ድራማዎችን፣ መንፈሳዊ ጥያቄዎች እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎች   የሚተላልፍበት  መንፈሳዊ ሚዲያ ነው፡፡ልብዎን ይክፈቱና ቃለ እግዚአብሔርን ያድምጡ። ሰብስክራይብ ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን https://youtube.com/@meklit-the-tewahido?si=0unswl3PIwBaXtho ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 💌💌💌💌💌💌💌💌💌 ዩቱዩብ ቻናሉን #Share በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ! #Like በማድረግም ድጋፋችንን እናሳይ!  🙏🙏🙏
Показать все...
መክሊት ዘተዋሕዶ Meklit the Tewahido

Welcome to " Meklit the Tewahido Youtube channel " On this sprtiual channel ,you will find ancient Ethiopian church history, preachings ,songs of praise , sprtiual films,history of saints and other videos. Open your heart and enjoy God's miracles. GOD BLESS YOU እንኳን ወደ "መክሊት ዘተዋሕዶ ዩቲዩብ ቻናል " በደሕና መጡ። ይህ ዩቱዩብ ቻናል ስለ ቅዱሳን ክብር ተዓምር ገድል ይናገራል:: መክሊት ዘተዋሕዶ  ዩቱዩብ ቻናል  ትምህርተ ወንጌልን፣ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን፣ የቅዱሳንን ተጋድሎ፣ መንፈሳዊ ድራማዎችን፣ እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎች   የሚተላልፍበት  መንፈሳዊ ሚዲያ ነው፡፡ልብዎን ይክፈቱና ቃለ እግዚአብሔርን ያድምጡ። ሰብስክራይብ ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን

Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰኔ 22 ቅዱስ አባ ጳዉሊ የዋህ እዚህ ይጫኑ https://youtu.be/b3O6zMw9aCk?si=ou5J6J_RMritN_lZ ☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 💌💌💌💌💌💌💌💌 እንኳን #ለቅዱሱ #አባታችን #የዋህ #ጳውሊ ፣ ለቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስ ና ድምያኖስ (ሰማዕታት)፣ለ ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት (እናታቸው) እንዲሁ ም ለአንቲቆስ ፣ዮንዲኖ ስና አብራንዮስ (ሰማዕታት) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣አደረሰን። ††† 💌💌💌💌💌💌💌💌💌 💌 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† 💌💌💌💌 💌ቅዱስ ጳውሎስ የዋህ 💌 💌በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ጳውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ጳውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ የላይኛውን ሊንክ ሲጫኑ ታሪኩን ያገኙታል በረከቱ ይደርብን 💌💌💌💌💌💌💌💌💌 ይህ ዩቱዩብ ቻናል ስለ ቅዱሳን ክብር ተዓምር ገድል ይናገራል::መክሊት ዘተዋሕዶ  ዩቱዩብ ቻናል  ትምህርተ ወንጌልን፣ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን፣ የቅዱሳንን ተጋድሎ፣ መንፈሳዊ ድራማዎችን፣ መንፈሳዊ ጥያቄዎች እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎች   የሚተላልፍበት  መንፈሳዊ ሚዲያ ነው፡፡ልብዎን ይክፈቱና ቃለ እግዚአብሔርን ያድምጡ። ሰብስክራይብ ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን https://youtube.com/@meklit-the-tewahido?si=0unswl3PIwBaXtho ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 💌💌💌💌💌💌💌💌💌 ዩቱዩብ ቻናሉን #Share በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ! #Like በማድረግም ድጋፋችንን እናሳይ!  🙏🙏🙏
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰኔ 22 መልክአ ዑራኤልን ያድምጡ እዚህ ይጫኑ https://youtu.be/U5sH2IbcdFY?si=mJp6pqUR9Yvp5sh- ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 💌💌💌💌💌💌💌 ወር በገባ በ22 የቅዱስ ዑራኤል መታሰቢያው ነው ለዕዝራ ሱቱኤል፤ ለቅዱስ ያሬድ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስ ጫ እና ለሌሎችም ቅዱሳን ጽዋ ልቦና አጠጥቷቸዋል፡፡ 👉 ወደ ሔኖክም እየመጣ የተሰወሩት ን ምስጢር እና ያያቸውን ራእዮች ይተረ ጉምለት ነበር። 💌💌💌💌💌💌💌💌 ☞ በድርሳኑ እንደ ተገለጸው በረዳትነቱ በአማላጅነቱ ብዙ ደጋጎችን ረድቷል። 💌💌💌💌💌💌💌 ☞የክርስቶስንም ደም በብርሃን ጽዋዕ ተቀብሎ የኢትያጵያን ምድር የረጨ ሲኾን ሥላሴን በቅዳሴ በውዳሴ ከሚያመሰግኑና ለሰው ልጆች ለምሕረት ለብሥራት ከሚላኩ መላእክት አንዱ ነው፡፡ ሊንኩን ተጭነው መልክአ ዑራኤልን ያድምጡ 💌💌💌💌💌💌💌💌 መ ክ ሊ ት ዘ ተ ዋ ሕ ዶ 💌💌💌💌💌💌💌💌 ዩቱዩብ ቻናሉን #subscribe#like#_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም በየዕለቱ የቅዱሳንን ታሪክ ያድምጡ 💌💌💌💌💌💌💌
Показать все...
እናት አባቴ ባያስታውሱኝ ይህቺ አለም ንቅ ገፍታ ብተወኝ አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ አውሎ ንፋሱን ባህሩን አልፋለሁ ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም አላቋርጥም የአንቺን ምስጋና ውለታሽ ድንግል አለብኝና ስምሽን ጠርቼ መቼ እወድቃለሁ ማርያም ብዬ መቼ አፍራለሁ ❤️‍🩹 #Share 💚 @ortodox_27💚 💛 @ortodox_27💛 ❤️ @ortodox_27❤️
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ድንግልን ጠይቄ መድኃኔዓለም ከልክሎኝ አያውቅም ❤️‍🩹 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏🏼 #Share 💚 @ortodox_27💚 💛 @ortodox_27💛 ❤️ @ortodox_27❤️
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.