cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

قَنَاةُ أَبِــي عَبْــدِ الَّله جَــمَالِ بْــنِ حُــسَيْنْ

Рекламные посты
444
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-1230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
አል ኢማም አህመድ አል ነጅሚ رحمه الله እንዲ ይላሉ «ወንድ ልጅ ሁኔታው አይሰተካከልለትም እንዲሁም ህይወት መልካም አትሆንለትም በመልካም ሚስት ቢሆን እንጂ... 👑ሴትም አትረጋጋም እንዲሁም ህይወት መልካም አትሆንላትም መልካም ባልን በማግኘት ቢሆን እንጂ» منقول تأسيس الأحكام بشرح عمدة الأحكم  ١٢ https://t.me/Abulabashsen https://t.me/Abulabashsen
Показать все...
👉•ኢብኑ አልቀይም እንድህ ይላሉ አሏህ ይዘንላቸው قال الإمام ‎ابن القيم رحمه الله : " قِيامُ اللَّيْلِ مِنْ أنْفَعِ أسْباب حِفظِ الصِّحة، و مِن أمْنَعِ الأمور لكثيرٍ مِن الأمراض المُزْمِنة، و مِن أنْشط شيْءٍ لِلْبَدَنِ و الرُّوحِ و القلْب ". زاد المعاد ( ٢٢٧/٤ የለይል ሶላት ጤንነትን ከሚጠብቁ ዋነኛ ሰበብ ነው። ለረጅም ግዜ ከሚዳርጉ በሽታዎች ከሚከላከሉ ዋነኛ ነገር ነው። ለቀልባችን፣ለሩሀችን፣ ለአካላችን፣ ዋነኛ አነቃቂ ነው ። ምንጭ ዛዱል መአድ ✍አቡል አባስ https://t.me/Abulabashsen https://t.me/Abulabashsen
Показать все...
ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት ~ ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን። * ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል። * የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው። * የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም። * ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦ { وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ } "አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10] የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
እምነታዊ ጥንካሬህን ለመገንባት ምናልባትም አመታት ያስፈልጋል ... በረጅም ግዜ ልፋት የተነገባው ተቅዋና ጥንካሬ ግን በደቂቃዎች ዓመፅ ይናዳል ... በአንዲት የሐራም እይታ ይሸረሽራል .. እናማ ... አይኖችህን ፣ ምላስህንና እጆችህን በመሰብሰብ እምነትህን በስስት ጠብቅ ! የትም ብትሆን አላህን ፍራ ! መጨረሻችንን አላህ ያሳምረው! https://t.me/Muhammedsirage
Показать все...
ልቦችን በማሸፈት የመጀመርያውን ሚና የሚወስዱት ስልኮች ናቸው ስለ ስልኮቻችን አጠቃቀም የተሰጡ ምክሮች ስብስብ በሙሐመድ ሲራጅ
Показать все...
ስልክ እና ልብ
የልብ ድርቀት
ልብን የተመለከተ
ኢንተርኔት
የወንጀል ሂደቶች
ወጣቶች ሆይ....
እጆቻችን ባስቀደሙት ነው
ወንጀሎችን ማጣጣም
በራስ መተማመን
አኺራን ማስታወስ
ዋና አላማችን
የጥመት መንስኤ
ቀልብን ማከም
ታጥቦ ጭቃ
እቺ ዱንያ
የባህሪ ለውጥ ምክንያቶች ~ አንዳንዴ ለዘመናት በመልካምነት የምናውቃቸው ሰዎች የማናውቃቸው እስከሚመስለን ድረስ ባህሪያቸው ተቀይሮ ለመሸከም የሚከብዱ ይሆናሉ። ምክንያቱ ምን ይሆን? የችግሮቹን መንስኤዎች ማወቅ ለማስታመም፣ ለማለፍ፣ ለመረዳት፣ ... ያግዘናል። የሰዎችን ባህሪ ከሚቀይሩ ነገሮች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። 1- ስልጣን፦ ስልጣንና ኃላፊነት ሲያገኙ የሚቀየሩ ብዙ ሰዎች አሉ። የሚያውቁትን እንደማያውቁት ይሆናሉ። ንቀትን ንቃት ያደርጋሉ። ውለታ ይረሳሉ። 2- ስልጣን ማጣት፦ ከስልጣንና ኃላፊነት ሲነሱ በብስጭት፣ በቁጭት እየተብከነከኑ ለሩቁ ቀርቶ ለቅርብ ሰዋቸው ጭምር ባህሪያቸው የሚፈትኑ ይኖራሉ። 3- ሃብት፦ ትሁትና ደግ የነበሩ ሰዎች ሃብት ካገኙ በኋላ ትእቢት፣ ንቀትና ኩራት የሚባሉ ነውሮችን ጌጥ የሚያደረጉ የዋሆች አሉ። 4- ድህነት፦ አግኝቶ ማጣት ትልቅ ህመም አለው። ድህነት ሲዳብሳቸው መልካም ባህሪያቸው ከገንዘባቸው ጋር ጥሏቸው የሚጠፋ ሰዎች አሉ። መቼም አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው። 5- ሱስ፦ በሱስ በመጎዳታቸው የተነሳ ከጊዜ ጊዜ ትእግስት እንደ ቁምጣ እያጠራቸው የሚሄድ፣ ይሉኝታ የማያውቁ፣ "ሰው ምን ይለኛል?" የማይገዳቸው ሰዎች ቁጥራቸው ከብዙም የበዛ ነው። 6- ሃሳብ፦ የሰው ልጅ በህይወቱ ለተለያዩ ሃሳቦች መጋለጡ የሚጠበቅ ነው። የሃሳብ መደራረብ፣ የአእምሮ መወጠር ደግሞ የሰው ባህሪ ላይ ግልፅ ተፅእኖ ያሳድርበታል። 7- ህመም፦ ህመም ባህሪን ይቀይራል። ያነጫንጫል። ከሰው ቀርቶ ከእንስሳ፣ ከግድግዳ ጋር ሁሉ ያጋጫል። 8- እርጅና፦ እርጅና እንደ ልጅ ያደርጋል። እንዲያውም ሊብስ ይችላል። ልጅን ተቆጥተህ ታስደነግጠዋለህ። ከእርጅና ጋር የሚመጣ ክፉ ባህሪ ግን ለገላጋይ አይመችም። እርጅና ላይ ሌሎች ገፊ ችግሮች ሲደረቡበት ደግሞ በቡሃ ላይ ቆረቆር ይሆናል። ምንጭ፦ አብዛኛው ሃሳብ ከሸይኽ ዐብደላህ አልፈውዛን (ሚንሐቱል ዐላም፡ 10/295 - 296) የተወሰደ ነው። Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ወንድሜ & እህቴ ጓደኛችሁ ምን አይነት ሰው ነው? ለዛሬ በትንሹም ቢሆን ላካፍላችሁ ያሰብኩት #ስለ…ምንቀርበው ሰው እና ጓደኛ አድረገን ስለምንዘው ሰው ነው ። አንድን ሰው ለጓደኝነት ከመምረጣችን በፊት ኡሱ ማነው የሚለውን ማጤት ትልቅ ብልጠት ነው። ብዙ ሰወች ከተለያዩ ሰወች ጋር ጓደኝነት መስረተው እናያለን ነገር ግን የት ይደርሳሉ ስንል በአጭር ግዜ ውስጥ ሁሉም ከንቱ ሆኖ እናያለን እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ቢኖር ① እራሳችንን ለጓደኝነት ማብቃት ነው፣ ይህ ማለት እኔ ለአንድ ሰው ጓደኛ ስሆን ምን ይጠበቅብኛል የሚለው ማጤን ነው ② ጓደኛ አድርገን የምንዘው ሰው በቻልነው አቅም የስነ ምግባል ባለቤት መሆኑን ማወቅ መቻል አለብን ③ ጓደኛ አድርገን ልንይዘው የሚገባ ሰው አስተዋይ ቁም ነገረኛ ለሰው ተጨናቂ በሆን አለበት ④ኛው እና ዋነኛ ለጌታው ታማኝ የሆነ ሰው አንተን ወዴ አላህ ሊያቃርብህ የሚችል መሆን አለበት እነዚህ ነገሮች ከለሉ ግን የውሻውሸት ወይንም ግዛዊይ ጓደኝነት ሆኖ ይቀራል። ሰው ነንና በጓደኝነት መካከል የሆነ ችግር ቢፈጠር ይቅር ባይነት እና ነገሮችን ችሎ ማለፍ ይልመድብን በ لاإله الا الله የማይበጠስ ገመድ ያስተሳሰረ ወንድማማቾች መሆን አለብን ለጓደኛህ ታማኝ ቀልበ ንፁህ ሁነህ ተገኝ ✍ወንድማችሁ አቡል አባስ https://t.me/Abulabashsen https://t.me/Abulabashsen
Показать все...
ራስህን አትርሳ ~ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦ "ትኩረትህ ሁሉ የራስህ ጉዳይ ላይ፣ ሃሳብህ ሁሉ የራስህ ሃሳብ ላይ ይሁን። ወደሚጠቅህ ነገር ተመልከትና ፈፅመው፡፡ የማይጠቅምህን ተወው። የማይመለከቱህን ነገሮች ማሰስ ከኢስላምህ ውበት ውስጥ አይደለም።" [ሸርሑ ሪያዲ ሷሊሒን፡ 1/511] Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
📍ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ። «እውቀት ከበላጭ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ነው። በጣም የላቀና ከጥቅም በኩል እጅግ ተገዘፈ ኢባዳ ነው። ለዚህም ነው ሸይጧን ሰዎችን ከእውቀት በማገድ ላይ እጅግ ብርቱ የሆነው።» 📚فتاوى نور على الدرب / ج2 / ص12. 📍ኢብኑል ጀውዝይ "አላህ ይዘንለት" እንዲህ ብሏል። «እወቅ! ኢብሊስ በሰዎች ላይ ከሚያለባብሳቸው ማለባበሶች ውስጥ አንዱና ዋናው፦ ሰዎችን ከእውቀት መንገድ መዝጋት ነው። ምክንያቱም እውቀት ብርሀን ነው። ይህንን የእውቀት ብርሀናቸው ካጠፋባቸው በኋላ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደፈለገ "በቀላሉ" ይጥላቸዋል።» 📚تلبيس إبليس (1/289) http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.