ru
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Канал የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 14 319 подписчиков, занимая 6 154 место в категории Религия и духовность и 2 360 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 14 319 подписчиков.

Согласно последним данным от 22 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 507, а за последние 24 часа — 11, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 49.23%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 13.09% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 0 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 875 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 0.

📝 Описание и контентная политика

Описание канала не предоставлено.

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 23 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

14 319
Подписчики
+1124 часа
+1077 дней
+50730 день
Архив постов
"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" ዮሐ 4፡42 እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገ
"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" ዮሐ 4፡42 እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፥12 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! ሰናይ ሌሊት! (የሰንበት
"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፥12 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! ሰናይ ሌሊት! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

ማኅሌተ ጽጌ አምስተኛ ሰንበት ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube �
ማኅሌተ ጽጌ አምስተኛ ሰንበት ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃ ለድሬደዋ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድሬደዋ ሀገረ ስብከት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ለአንድነቱ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ። በዕለቱም የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ እማምሰው ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ሐላፊዎች ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መርሐ ግብሩ የተከናወነ ሲሆን በመርሐ ግብሩም በአንድነቱ ቀጣይ አገልግሎት ዙሪያ ታዳሚዎችን ያሳተፈ ምክክር ከተደረገ በኋላ የተገዛውን ንብረት ለአንድነቱ ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ሀብታሙ ሽፈራው ክቡር መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ ያስረከቡ አስረክክበዋል። በማስከተልም የወጪ ዝርዝር ሪፖርት ለእንግዶች በማሰማት ይህን ስራ ሲያስተባብሩ ለነበሩ የኮሚቴ አባላት እና ለደብራት አለቆች ዕውቅና ተሰጥቷል። በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ተስፋዬ ይህን ስራ ከመነሻው እስከ መድረሻው በቅርብ በመከታተል አባታዊም አስተዳደራዊም መመሪያ በመስጠት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሀገረ ስብከቱን ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስን ያመሰገኑ ሲሆን በተመሳሳይ ለአጥቢያ አለቆች እና ለአንድነቱ አባላትም በሙሉ በዚህ ስራ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና በማቅረብ መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል። መረጃው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ነው። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

"ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውኃ ምንጭ ናት። የማሕጸንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድኗልና።" ውዳሴ ማርያም ዘዓርብ ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰ
"ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውኃ ምንጭ ናት። የማሕጸንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድኗልና።" ውዳሴ ማርያም ዘዓርብ ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆኑ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን፤ ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት 21ቀን 2017ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

“ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።” መኃ 4፡7 ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉
“ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።” መኃ 4፡7 ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘን
"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡” ማኅሌተ ጽጌ ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

ማኅሌተ ጽጌ አራተኛ ሰንበት ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉
ማኅሌተ ጽጌ አራተኛ ሰንበት ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok

"ድንግል ሆይ ፤ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ከአገር ወደ አገር ስትሽሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ፤ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስ
"ድንግል ሆይ ፤ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ከአገር ወደ አገር ስትሽሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ፤ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤" ቅዳሴ ማርያም ሰናይ ሌሊት! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok