ru
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

Открыть в Telegram

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

Канал ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 11 983 подписчиков, занимая 17 269 место в категории Образование и 2 838 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 11 983 подписчиков.

Согласно последним данным от 04 марта, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -107, а за последние 24 часа — 0, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 0%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает N/A% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 0 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 0 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 0.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 05 марта, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Образование.

11 983
Подписчики
Нет данных24 часа
-337 дней
-10730 день
Архив постов
👉 ስልክን የፈጠረው ሳይንቲስት "አሌክሳንደር ግራምሀም ቤል" ሲሆን ሚስቱና ወላጅ እናቱ ጆሮአቸው በፍፁም አይሰማም ነበር በመሆኑም እነዚህ መስማት የተሳናቸው የቅርብ ቅርብ ቤተሰቦቹ የእርሱን ድንቅ የፈጠራ ውጤት ተጠቃሚ ለመሆን አልቻሉም። © smile wonder facts ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

👉 ስልክን የፈጠረው ሳይንቲስት "አሌክሳንደር ግራምሀም ቤል" ሲሆን ሚስቱና ወላጅ እናቱ ጆሮአቸው በፍፁም አይሰማም ነበር በመሆኑም እነዚህ መስማት የተሳናቸው የቅርብ ቅርብ ቤተሰቦቹ የእርሱን ድንቅ የፈጠራ ውጤት ተጠቃሚ ለመሆን አልቻሉም ©smile wonder facts @techhabesha

ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ ለዊንዶውስ 7 የሚሰጠውን ድጋፍ ሊያቋርጥ ነው Thu, Jan 02, 2020 ዋልታሳይንስና ቴክኖሎጂ ኩባንያው ዊንዶውስ 7 አገልግሎት ላይ ከዋለበት ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.
ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ ለዊንዶውስ 7 የሚሰጠውን ድጋፍ ሊያቋርጥ ነው Thu, Jan 02, 2020 ዋልታሳይንስና ቴክኖሎጂ   ኩባንያው ዊንዶውስ 7 አገልግሎት ላይ ከዋለበት ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አሥር ዓመታት ቴክኒካዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ነው የገለጸው። የአሥር ዓመት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎም ለዊንዶውስ 7 የሚደረገውን ድጋፍ በማቋረጥ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና ሌሎች ልምዶች ላይ ያተኮረ ኢንቨስትመንት ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አድርጓል። ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ ለዊንዶውስ 7 የሚሰጠውን ድጋፍ ከጥር 05 ቀን 2012 ጀምሮ የሚቋረጥ መሆኑንም ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ ቀናት በኋላ ለዊንዶውስ 7 የሚደረገው ቴክኒካዊ ድጋፍ ብሎም ሶፍትዌሩን የማደስ ተግባራት ስለሚቆሙ፣ ይህንን ዊንዶውስ የሚጠቀሙ አካላት ይደረግላቸው የነበረው የጥቃት ጥበቃ እንደሚቋረጥ አመልክቷል። በመሆኑም ኩባንያው ተጠቃሚዎቹ ጊዜው ከመጠናቀቁ እስቀድሞ ችግር እንዳይገጥማቸው ለመከላከል አገልግሎታቸውን ወደ ዊንዶውስ 10 እንዲያዞሩ መክሯል። (ምንጭ:- Walta) ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

sticker.webp0.50 KB

በመገባደድ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2019 የተከሰቱ ዋና ዋና የሳይበር ጥቃቶች ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ የፈረንጆቹ 2019 እንዳለፉት ዓመታት የመረጃ በርባሪዎች ህገ-ወጥ ተግባራቸው ላይ ተጠምደው ነው የከረሙት፡፡ በ2019 የመረጃ በርባሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋና ዋና ከተሞችን፣ መንግስታትን፣ ግዙፍ የገንዘብ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች እና የትምህርት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶችን ሰንዝረዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ የተፈጸመው የሳይበር ጥቃት የቅርብ ጊዜ መረጃ ሲሆን ጥቃቱን ተከትሎ 30ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲከፍሉ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው እንደነበር መግለጻቸው ይታወቃል፡፡ በመጋቢት ወር 2019 ግዙፉ የአምልሙኒየም ምርት አቅራቢ ተቋም ላይ ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ አዲስ በሆነው የአጥፊ ሶፍትዌር ሎከርጎጋ/LockerGoga/ ኖርስክ ሃይድሮ /Norsk Hydro/ ኩባንያ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ የኩባንያው ስርዓተ ኮምፒውተሮች ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ኮምፒውተሮች ለመግዛት ተገዷል፡፡ በሚያዚያ ወር ኖርስክሃይድሮ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በተፈጸመው የሳይበር ጥቃት ለደረሱ ጉዳቶች 52 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉን ገልጿል፡፡ በግንቦት ወር 2019 በባልቲሞር ከተማ የተከሰተው የሳይበር ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ኮምፒውተሮች አገልግሎታቸው ተቋርጧል፡፡ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃትም ከተማው 18 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራዎችን ማስተናገዱን ገልጿል፡፡ በባልቲሞር በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ወሳኝ የኮምፒውተር ስርዓቶችን ጨምሮ የሰራተኞችን የኢ-ሜይል አገልግሎት ማቋረጥ ፣ የውሃ ሂሳብ ክፍያን ማስቆም እና የሪል እስቴት ግብይቶችን እስከማገድ ደርሷል፡፡ የአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛትም በ2019 የሳይበር ጥቃት ካስተናገዱ መካከል አንዷ ሆናለች፡፡ በተፈጸመው የራንሰምዌር ጥቃትም 23 የሚሆኑ የግዛቲቱ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰለባ ሆነዋል፡፡ ግዛቷ በተፈጸመባት የሳይበር ጥቃት እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል፡፡ እነዚህ እና መሰል የሳይበር ጥቃቶች በአለም አቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ 2019 ተከስተዋል፡፡ ምንጭ፡ globalsign.com ©INSA ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

sticker.webp0.07 KB

መደመር ሙሉ መፅሃፍ.pdf17.04 MB

📚 የጠቅላይ ሚኒስተራችንን "መደመር" የተሰኘው መፅሀፍ በ PDF. 📌 Size 17 MB ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

⚠️በመጀመሪያ አንድ ስልክ ኔትወርኩ ሲጠፋ የ Sim Card ችግር ወይም የ ኔትወርክ ችግር መሆኑን መለየት ያስፈልጋል ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ❇️እንድ ስልክ የኔትወርክ ችግር ነው ማለት የምንችለው ከታች ያሉትን ምልክት ሲያመጣ ነው 👇👇 👉No Service 👉Emergency Call 👉Regisretion Failed 👉Invalid Sim ... እነዚ በ 3 አይነት ችግር ሊበላሹ ይችላሉ 👉በ IMEI NO ችግር 👉Antrna (Hardware Problem) 👉Network IC ችግር (Hardware Problem) አብዛኛውን ጊዜ ግን 90% የ IMEI NO ችግር ሰለሆነ IMEI NO መቀየር ነው። IMEI NO በተን ስልክ ላይ እና ተች ስልክ ላይ አቀያየሩ ስለሚለያይ ዛሬ #እንዴት_በተን_ስልክ_ላይ_እንደምንቀይር_እናያለን በተን ስልኮች ላይ ምንቀይረው በ Code ነው በተን ስልኮች ላይ IMEI NO. መቀየሪያ ኮዶች👇 *#0160# ብዛት Techno ስልኮች ላይ እንቀይርበታለን *#0161# *#0162# *#0066# ብዛት Isim ስልክ ላይ እንቀይርበታለን *#0011# ብዛት Smadel ስልክ ላይ እንቀይርበታለን *#346# *#020*# *#0120# *#1120# *#*#601*#*# *#8378#1# ሁሉም በተን ስልክ ላይ ይሰራል መጀመሪያ የስልካቹን IMEI NO. ለማየት *#06# ስትነኩት 15 ዲጂት ያለው ቁጥር ያመጣላችዋል ልክ እንዲ👇👇 354688225789335 ካመጣላቹ በዋላ እሱን አጥፍታቹ አዲስ IMEI NO. ታስገቡበታላቹ ካዛ ስልኩን አጥፍታቹ ታበሩታላቹ ካዛ Networku ይመለሳል። ❇️ Sim Card Hardware Problem 👉Insert Sim Card #sim_card_እያለው 👉No Sim Card Present #sim_card_እያለው 👉No Sim Card Interted #sim_card_እያለው 👉Sim Card Regitortion Faild #sim_card_እያለው 👆👆እነዚ ችገሮች የ Sim Card ማስገቢያው መደብ ችግር ስለሆኑ ወደ ሞባይል ጥገና ቤት ይዞ ሄዶ ማሰራት ነው። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

sticker.webp0.07 KB

📚 የጠቅላይ ሚኒስተራችንን "መደመር" የተሰኘው መፅሀፍ በ PDF. 📌 Size 3.8 MB ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

‍ 📚 የጠቅላይ ሚኒስተራችንን "መደመር" የተሰኘው መፅሀፍ በ PDF. 📌 Size 3.8 MB ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃ 1. #የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ #ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች #(ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው። እነዚህ #ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ #ማስወገድ ተገቢ ነው። 2. #ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ #ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ #የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት #እርምጃ ይውሰዱ አልያም #ባለሙያ ያማክሩ። 3. #የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ #ስልክዎ ከፍተኛ #ሙቀት አለው ማለት ደግሞ #የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው። #ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና #ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል #ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ #ይህ ካልሆነ ስልክዎ #ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ። 4. #ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ #ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው #መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ #መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ #የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል። ወደ እርስዎ የሚላኩ #መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ #ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል። 5. #ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን #(ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት #ወደ ሌላ ድረ-ገጽ #የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ #የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል። #መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ #ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ። 6. #አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች አንዳንድ ጊዜ እርስዎ #ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ #ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም #የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ #ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ። የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ #ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ። #ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና #የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም #በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። 7. #ያልተለመዱ ድምጾች #የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች #የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ #የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ #እየተቀዱም ሊሆን ይችላል። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ 🏷 #መፍትሄዎች ━━━━━━ ▫️የስልክ #ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት ▫️እርስዎ #የማያውቋቸውን #መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት ▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው #ነጻ የኢንተርኔት #አገልግሎቶችን አለመጠቀም ▫️ስልክዎን #በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል #የይለፍ ቃል መዝጋት ▫️ከማይታወቁ #ምንጮች #መተግበሪያዎችን አለመጫን ▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ #መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ #ማሳደስ (update) ▫️#የስልክ ክፍያዎንና #የዳታ አጠቃቀምዎን #ይቆጣጠሩ #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

sticker.webp0.24 KB

ታኅሣሥ 16 በ2012 ዓ.ም ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ❡▅▅▅▅▅▅▅▅▅▅▅▅▅▅❡ ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ከጠዋቱ 12:37 ጀምሮ 1:26 ላይ የሚጠናቀቅ በአጠቃላይ 49 ደቂቃዎች የሚፈጅ ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ በዐዲስ አበባ ይከሰታል። በዚ ሰዓት ፀሐይን መመልከት ዐይን ሊያጠፋ ስለሚችል ግርዶሹን ለመመልከት eclipse glasses ወይም sun filter ብቸኛ አማራጭ ነውና ቤታችሁ eclipse glasses ያላችሁ ክስተቱን ያለ ስጋት ማየት ትችላላችሁ። ⚠️⚠️ በፀሐይ ግርዶሽ ወቅት ከእነዚህ ውጪ በተራ መነጽር፣ በከለር ፊልም፣ በራጅ፣ በተቃጠለ ፊልም፣ በፍሎፒ ዲስክ መመልከት በጣም የተሳሳተና የፀሐይ UV ጨረር ሬቲና የተባለውን የዐይን ክፍላችንን ሊያጠፋው፤ ዕውር ሊያደርገን ይችላልና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።❗️❗️ ❖ እንደ ሳይንሱ ምልከታ የፀሐይ ግርዶሽ ጨረቃ በፀሐይና በመሬት መሓከል ገብታ ፀሐይን የምትጋርድበት ክስተት መሆኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው ጠፍ ጨረቃ (new moon) በምትሆንበት የለውጥ ሂደት ወቅት ነው፡፡ ❖ ይህ ወቅት ጨረቃ መሓከል ላይ ስላለችና ለፀሐይም የምትቀርብበት ወቅት ስለሆነ ፀሐይን የመጋረድ አጋጣሚው ይፈጠራል፡፡ በዓመት ውስጥ የፀሐይ ግርዶሽ ቢያንስ ሁለት ጊዜ የሚታይ ሲሆን በዓመት ውስጥ የሚታየው ከዐምስት እንደማይበልጥ ግን ሳይንሱ አረጋግጧል፡፡ በ1935 ዓ.ም. ዐምስት የፀሐይ ግርዶሽ በዓመቱ ውስጥ የታየበት ዓመት ነበር፡፡ ❖ የፀሐይ ግርዶሽ ሦስት ዓይነት ሲኾን፤ እነዚህም “ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ” (total solar eclipse)፤ “ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ” (partial solar eclipse) እና “ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ” (annular solar eclipse) የሚባሉት ናቸው። ❖ እንደ ሳይንሱ ጥናት ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ የሚታየው ጨረቃ ሙሉ ለሙሉ ፀሐይን እንዳናይ ስትጋርደንና ሙሉ ጥቁር በሆነው ጸሊም ጥላ (umbra) ውስጥ ስንሆን ነው፡፡ ❖ ጨረቃ ከፊሉን የፀሐይ ክፍል ብቻ የምትጋርድብን ከሆነ ደግሞ “ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ” (partial solar eclipse) ይባላል፡፡ ❖ ጨረቃ ፀሐይን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ሳትችል ስትቀር በጨረቃ ጠርዝ ዙሪያ ቀለበት ሠርታ ፀሐይ የምትታየን ከሆነ “ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ” (annular solar eclipse) ይባላል፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ጨረቃ ከመሬት እርቃ ባለችበትና “አፖጊ” (apogee) ተብሎ በሚጠራው ርቀት ላይ ስትሆን ነው፡፡ በዚህ ወቅት የጨረቃ ጥቁሩ ጥላ (ጸሊም ጽላሎት) መሬት ላይ ላያርፍ ይችላል፡፡ ❖ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጁን 21/2020 (በእኛ በኢትዮጵያ አቈጣጠር ሰኔ 14/2012 ዓ.ም.) ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡ ክስተቱም ወለጋ አካባቢ ጀምሮ፣ ከፊል ጎጃምን፣ ከፊል ጎንደርን ዐልፎ ወደ ወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ድረስ ስለሚታይና ቀኑ የሚጨልምበት ስለሚሆን በሕይወት ዘመናችን ልናየው የምንችለው አስደማሚ የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡ ❖ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ አንባቢዎች ወቅቱን ጠብቀው እንዲመለከቱ በአንድሮሜዳ መጽሐፍ ላይ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና ዶክተር ጌትነት ፈለቀ የወደፊቱን የ10 ዓመታት የግርዶሽ ቀናት ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ ስለነበሩ ግርዶሾችና ቀደምት ኢትዮጵያን በግርዶሽ ላይ የነበራቸው ዕሳቤ ስለጻፉት አንድሮሜዳ መጽሐፍ ላይ ያንብቡ። ©[ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ 🌀 share በማድረግ የበለጠ እንድንሰራ moral ሁኑን! እውቀትንም ለ ወዳጆቻቹ ያካፍሉ! ቻናሉን በማስተዋወቅ ያግዙን!

የከፊል የጸሃይ ግርዶሽ በመላው ኢትዮጵያ ———————————— ሃሙስ ታህሳስ 16 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12:37 እስከ 1:26 ****** ⚠️ማስጠንቀቂያ ወደ 🔆ጸሃይ ያለ መከላከያ ፊልተር እንዳይመ
የከፊል የጸሃይ ግርዶሽ በመላው ኢትዮጵያ ———————————— ሃሙስ ታህሳስ 16 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12:37 እስከ 1:26 ****** ⚠️ማስጠንቀቂያ ወደ 🔆ጸሃይ ያለ መከላከያ ፊልተር እንዳይመለከቱ ‼️ via:-Ethiopia Space Science Society 🇪🇹 #ኢትዮጵያዊነት_መልካምነት ነው። #እባኮትን #ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @Computer_Android_tricks        ━ ••• ━ ••• ━━•••━━━

AnimatedSticker.tgs0.02 KB

🔒ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን መክፈቻ ዘዴ ================== ✏️የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ። ✅የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro" ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ የምታገኙት ስለሆነ እኛ የገዛንውን ለውድ የቻናላችን ተከታታዮች sofrwarun ከላይ ለቀንላችኋል። 🔒በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:- 🔘ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡ 🔸Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን 🔸Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡ 🔸Step3: ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡ 🔸Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡ 🔸Step5: ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡ 🔸Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡ 🔸Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡ 🔸Step8: “Please select the target widows” ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/ 10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡ 🔸Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡ 🔸Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል። 🔒በ "iSee password windows password recovery Pro" ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ ሶፍትዌሩን ቻናላችን ላይ ለቀንዋል Registered የሆነውን የሚከተለውን step ይከተሉ። 1⃣ ሶፍትዌሩን Download ያድርጉ ። 2⃣ ሌላ Computer ላይ install ያደርጉት 3⃣ ሶፍትዌሩን ስከፍቱት ከላይ በምስል እንደምታዩት ያመጣላችኋል። 4⃣ ባዶ Flash or CD ትከቱና 🔘ፍላሽ ከሆነ የከተታችሁት Create password Reset Usb Flash drive ከሚለው ስር የፍላሹን ስም መርጣችሁ "Burn Usb" የሚለውን ስነኩት Burn አድጎ ሲጨርስ flashun ትነቅላላችሁ። 5⃣ከዛ በፓስዎርድ የተዘጋብንን ኮምፒዩትራችንን Turn OFF ማድረግ 6⃣ፍላሹን/ሲዲውን/ ከኮምፒዩተራችን ጋር አገናኝተን Turn On ማድረግ ከዛም (F12 ለቶሽባ/ዴል) F9 ለHp Computer (Boot key) መንካት 7⃣ " Boot sequence" የሚል ሲመጣልን " USB" የሚለውን መርጠን "Enter"ን በመንካት ትዕዛዙን መከተል። 8⃣ ኮምፒዩተራችን ከተከፈተ ብኋላ "isee password Windows recover pro" ይከፍትልናል ከአፕልኬሽኑ ላይ ካሉት አማራጭች(Option) ውስጥ "Admin Password Resetter" የሚለውን መንካት ከዛም "yes" የሚለውን እንጫናለን። 9⃣ ትንሽ ከቆየ ብኋላ(max. 2mint) "password is reset Successfully" የሚል መልዕክት ያሳየናል። 🔟 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot) 👽ፓስዎርዳችሁ ምንም አይነት file/data ሳይጠፋ ተከፈተ ማለት ነው አሁን የሚፈልጉትን password ማድረግ ትችላላችሁ። ✅ Proof 100% ይሰራል። 🇪🇹 #ኢትዮጵያዊነት_መልካምነት ነው። #እባኮትን #ለ10 ጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @Computer_Android_tricks        ━ ••• ━ ••• ━━•••━━━

🔑 iSee Password Windows Password Recovery Pro v2.6 Key included. Safe and Easy to Reset Administrator and User Passwords on Any Windows without Reformatting/Reinstalling System. 💵 Paid Software