ru
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Открыть в Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Больше
1 679
Подписчики
+224 часа
-47 дней
-1730 дней
Архив постов
photo content

Nu Chika Enabuka Art Center will host a toy and children's books donation day on Saturday 12 June 2021. The event will have c
Nu Chika Enabuka Art Center will host a toy and children's books donation day on Saturday 12 June 2021. The event will have children send toys, books and letters to children in different parts of the country. Children will also have a storytelling time with popular guests along with other activities. The entrance to the event is a toy with a children's book. Doors will open at 9:00am. @linkupaddis

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 A night out with a twist on an already unique frequency - angelic musical performances, sweet poetry, and a fascinating live painter. A night like none other full of soulful/expressive/underground vibes. We can’t wait to see you at FreeSoul ✨ When Saturday, June 12 @ 7pm Where Olympia Heights (unfinished bldg) Across from Dembel, beside the Deluxe furniture & Awash bank @Betty_bae

#የሞት ጥቁር ወተት የግጥም መድበል 📚📗📒📕📚 የመጽሐፍ ምርቃት ኑ አብረን እንመርቅ . . . 🗓 ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ኀሙስ በ11:30 ሰዓት 📍 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት 🎙 #የ
#የሞት ጥቁር ወተት የግጥም መድበል 📚📗📒📕📚 የመጽሐፍ ምርቃት ኑ አብረን እንመርቅ . . . 🗓 ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ኀሙስ በ11:30 ሰዓት 📍 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት 🎙 #የዝግጅት አቅራቢዎች ገጣሚ ነቢይ መኮንን ገጣሚ ፍሬዘር አድማሱ ደራሲ አዜብ ወርቁ ተዋናይ መስከረም አበራ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ ድምፃዊ ካሥማሰ 🎤 #ግጥም በውዝዋዜ ገጣሚ ተስፋኹን ከበደ ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን #መድረክ መሪ ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ 🎼 #ሙዚቃ በኢትዮ ጣዕም የሙዚቃ ባንድ #አጋዥ_አካላት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አ.ማ ጦቢያ ግጥምን በጃዝ አርትስ ቴሌቭዥን ጃጃው አታሚዎች ኃ.የተ.የግ.ድርጅት ማፊታ ዲዛይንና ዲኮር ጃሎ ፒክቸርስ

ዓለም 'የለም!' ብትለኝም እንደው ርዕስ ሆኜ 'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ የት አገኘሽው በሉልኝ የታል ዱካ ፈለጉ ምናልባት ስፋቷ ነቅቶ ምናልባት ንቃቷ ሰፍቶ አሻራዬ (ash-አርዓያዬ) ተገኝቶ መንበሬን ያመነች እንደሁ እንደኖረ መንበር አጥቶ 'አለም የለም ለማለት ማን ነበርሽ አንቺ!' በሉልኝ በዓለም ላለም በሙሉ የሄድኩበት ላይ አብሩልኝ እንደው እን'ዳጋጣሚ እግሬ ያረፈበት ላይ ይረግጥ እንደሆን ገጣሚ እንደው እንደ ዕድል ሆኖ (ክፉ ዕድል) 'መምህር' ይደግመው እንደሁ የለፈፍኩትን ቃል ዘግኖ እንዲገለጥለት በፈለገው መጠን ለስንቱ ተገልጧል እስኪገነጣጠል ብላችሁ ንገሯት ለዝ'ች ሟርተኛ ዓለም መኖር ለምትሰፍር ስፍር ለምታኖር በዘርና ቀለም! የለም!!! የለም!!! እንደውም ምንም አትበሏት ብጨልምም ብበራባት አልነበር 'አለው' ለማለት እንድትነቃ እንጂ ወደ 'ውነት እንድትቀና እንጂ ከጥመት የላ የላ ዝም በሏት እኔው ላውራት ዓለምዬ ዓለም ብርቁ የቱ ነው የግብርሽ ጥድቁ እንዳንቺስ ሆኖ ሳይነቁ መኖር ምንድነው ስንቁ? ጽልመትሽ ብራ'ን የጠላ ብርሃንሽ ጽልመት የከላ 'አለ'ምሽ መኖር የፈራ 'የለም'ሽ ተኑሮ ያልጠራ 'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ ከየት ተገኘ ዓለሜ ያለመኖሬስ ፈለጉ [የዓለም መኖሬስ ፈለጉ ያለ መኖሬስ ፈለጉ ያ ለመኖሬስ ፈለጉ ያ ዓለም መኖሬስ ፈለጉ ያለም መኖሬስ ፈለጉ ያለመ ኖሬስ ፈለጉ. . . ] . . . ዱካዬን ብት'ደብቂም ባለሽበት ሁሉ አለሁ መንበሬም ካነበረሽ ነው! የሚያኖርሽ እንደኖረው አለም - አለሁ! ዓለም አለሁ! አለማለሁ! ©️ሰይፈ ተማም

Busara Championship is starting on 19 June 2021 at Goethe Institut. The event will mainly feature three games in one srage br
Busara Championship is starting on 19 June 2021 at Goethe Institut. The event will mainly feature three games in one srage bringing young and talented players together on one court. The games that will be featured at the event will be Joteni (Foosball), Gebeta and Busara. Training will be provided for those who do not know how to play the games. For more info about the events, go to: https://bit.ly/3v1b5Dv. Download and enjoy the June 2021 edition of LinkUp Addis: https://bit.ly/34zMpY5. @linkupaddis

#አንተ_ማነህ ? ከመፍራት የሚሻል መፍትሄ ከመትረፍ የሚዘል ህላዊ ከመትረፍ የሚገዝፍ ፍፃሜ ከመንገድ የማይጠም መንገድ ከሰው መስማሚያ መውደድ ከአገር የሚገዝፍ ጥበብ ታስሳለህ ? አንተ ማነህ ? _ ፈጥሮ ጨርሶኻል ወይስ ራስህን ትፈጥራለህ ? አንተ ማነህ? ልብህ ምን ይልሃል ሰው ሰበረህ ? አሻገረህ ? አፈዘዘ አደመቀ ? በሰው ተሰራህ ወይስ ፈረስክ ? በረርኩ ስትል አነስክ አንተ ማነህ ? ምንድነህ ? ወዴት ነው የምትሄድ ? _ አንተ ማነህ ተደሰተ ሲሉህ ምትነደው ፈፀመ ሲሉህ ምጀምረው አፈረሰ ሲሉ ምትገነባ ፈገገ ሲሉህ ምትባባ አንተ ማነህ ? _ ንጉስ ነኝ ባልክ ማግስት በጥበቃ ከበር ሚመልሱህ ዙፋንህን ወንበር የሚሉት አንተ ማነህ ? ደምና ላብህን እንዲያልፍልህ ብት. ገብር ዜና የምትሆነው ስት ሰበር አንተ ማነህ ? መደዴ እየጠሉ ከመደዴው አንሶ መኖር ብዙ ዘርቶ እፍኝ መልቀም በክብ ጥያቄ መታነቅ እፍኙንም ማስነጠቅ የምር ማነህ ? _ ብትኖር ትጠቅማለህ ? ብትሞት ታጎላለህ ? እህል ከመጨረስ አልጋ ከመከስከስ ፍራሽ ከማድቀቅ ድንጋይ ከማሞቅ ራስ ከመውቀስ ትዘላለህ ? አንተ ማነህ ? ምንድነህ ? _ _ ያስፈራሃል ይህ ሁሉ ጥያቄ ያነድሃል____ ይህ ዕድሜ እደርሳለሁ ያልከው እንኳ ልትደርስ መታጠፊያው ራሱ የጠፋህ አንተ ማ ነ ህ ? _ _ ግንድ ነኝ ብለህ ስትወጣ ____ሲቲክኒ አከልክ ? የሰፈር ምላስ መሞረጃ ጥርስ መጎርጎሪያ ሆንክ ? ማነው የፈጠረህ ለምን ነው የገጠመ ታውቀዋለህ ? ምን ያነድሃል ? ምን ያፈዝሃል ምን ያቀዝሃል ምን ያስሮጥሃል . _ _ ህልም ምንድነው ? ልብ እያፈሰሰ ሰላም ምንድነው ? ሩቅ ካላስኬደ ደም ካፋሰሰ ' ጠላት ' ካስለቀሰ መንገድ ምንድነው ? ወረት ። ተጓዥ እያዩ መቅረት ከራስ መራቅ ከሰው ለመድረስ "የሆነ ሰው ለመሆን ' ያልሆነውን ማሰስ ? አ ን ተ ማነህ ? __ በቸከ ቀን በቸከ ህይወት ወረቀት የሚያሰኝህ መፅሐፍ የሚያስገልጥህ ውስኪ እንደመቅመስ ሴት ከንፈር እንደመንከስ ወገብ እንደመጨረስ በቸከ ህመም በቸከ ወረቀት የሚያስቸከችክህ አንተ ማነህ ? _ የእሳት ግለት የበረዶ ብርደት የፍጥረታት መሞት መራባት መባላት የእግዜር ዝም ማለት የሚያስጨንቅህ ? አንተ ማነህ ምንድነህ ወዴት ነው የምትሄደው ? #1ዱ ©️አንዱ ጌታቸው

Our dreams are wet contrary to our realities. To a habit i couldn't left completely Like talking in darkness Like Crawling back to a lullaby Like running to the water Because sometimes that's how i remember to feel. And to the things i 'almost' have Like the chatter of a wind The enchant of a river The laughter of a child I wanted to tell them no, I'm not nostalgic, I don't have anything to shed for a different time continuum, yet everything for a different space continuum.

#የመጽሐፍ_ምርቃት 🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊 #የሞት_ጥቁር_ወተት የግጥም መድበል በተስፋኹን ከበደ 🎉 ኑ አብረን እንመርቅ 📍 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት 🗓 ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ኀሙስ በ11
#የመጽሐፍ_ምርቃት 🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊 #የሞት_ጥቁር_ወተት የግጥም መድበል በተስፋኹን ከበደ 🎉 ኑ አብረን እንመርቅ 📍 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት 🗓 ሰኔ 03/2013 ዓ.ም ኀሙስ በ11:30

Shifta presents Gitem Sitem an open mic circle of fun and poetry. on every first Wednesday of the month with your hosts Heran
Shifta presents Gitem Sitem an open mic circle of fun and poetry. on every first Wednesday of the month with your hosts Heran and Seife. We have very simple rules: 1. Sign up online https://forms.gle/oEbMTixhnKu4HKox7 or by the gate prior to the event 2. 5 minute per performer 3. Be respectful to the performers and all beings around you 4. Be you 5. Make sure you follow all the precaution measures for Covid 19 https://www.facebook.com/gitemsitem ሽፍታ የግጥም ሲጥምን የክፍት መድረክ ክበብ አቀረበላችሁ! ረቡዕ, ግንቦት 25 ከ 1 ሰዓት ጀመሮ በሽፍታ ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ መጻሕፍት፣ የቁም ኩምክና፣ ስዕል እና ሌሎችም አዝናኝ የጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ። ስራችሁን ለማቅረብ ማስፈንጠሪያውን ተጠቅማችሁ በምታገኙት ቅጽ ተመዝገቡ! https://forms.gle/WveKjAsZ5PBx9MVr9 https://t.me/GitemSitem

Pain augments the depth within my poems Peace of mind lets my words breathe I want to keep writing I must Somedays I will tell you about my bruises, the tears I can’t cry away, the grief pressing on my chest, and the breaths I hold to punish myself Other days I will tell you how life is so good with a cup of tea in your hands, love in your heart, yellow before your eyes, sun kisses on your skin, and music in your head And dear reader, I don’t mean to betray you by the latter I will always remain a poet In peace or in pain. ©️Kalkidan Getnet Everted https://www.facebook.com/Everted https://t.me/Everted

የቃል ስፍር ንፋስ ከብርሃን ይረቃል ያ'ንተም ቃል! ከነፍሴ ማሳ ይፀድቃል የንፋስ መንገድ የብርሃን ሞገድ ቃል ተመስሎ ውበት ተኹሎ ሲገለጥ በተስፋ አምሳል ካንተ እኩል ይተካከላል እምነት ባንተ ይበረታል ኹሉ በቃልህ ይረታል እኔም! ©️መንበረማርያም ኅይሉ መንቢ የሎዛ

photo content

Grand Eliana Hotel will host an exhibition and cartoon book launch titled Funteziya on Friday 04 May 2021. The event will sho
Grand Eliana Hotel will host an exhibition and cartoon book launch titled Funteziya on Friday 04 May 2021. The event will showcase the launch of a cartoon book titled Funteziya by Alex Terefe. Doors will be open the whole day until 7:00pm. @GitemSitem

We need you And by we, me and you We need you Not for me not for you But for us by the bayou Lost in life lost in the woods C
We need you And by we, me and you We need you Not for me not for you But for us by the bayou Lost in life lost in the woods Craving signs hope in words Hooked up in lust longing for a fix Crumbling, Crawling, souls entangled Not up front or behind Side by side We need you Me and you To stand still against the wind roaring towards us Or we can kiss And forget you and I, if that’s what you please That is what I please Us ©️YeGetanehLij

Victim #297 I looked at her, I see your reflection in her eyes, I told myself you found another victim The flicker of trust that you offer The promises that you made, cuffed her The hope that runs through her vain I felt it, Your momentarily satisfaction Your endless need of validation Your being prisoned her in terms of your condition She feels obligated to satisfy your vanity Sadly, the notion about one day you will be hers made her heart aches Yet she killed parts of her to keep you smiling Then I saw you, In your eyes there is only illusions of her,You never sure Even when she's standing wearing red dress, bleeding love in drizzling night She fall to be enough in your eyes, @freetalkk 🦋🦋🦋

ምን አገራረፈን? ዘመን ፈልፍሎብህ፥ ጅራፍ የጨበጠ፥ ክፉ ተጣማሪ በተቀኘኸው ልክ፥ ገዳይና ማሪ መቀበል ያስጠቃል፥ አቀብል አዝማሪ። ..........አቀብል...እንካማ... .....||ዐይን ሰርግ ሊሄድ፡ ሲኳኳል ቆቡ ስር .....ማን ይየው የታቹን? .....ደምቶ ማለቁ ነው፡ አፍንጫ በነስር።|| የሚያዘንቡብህን፥ ስንኞች ወጥረህ፥ በማሲንቆህ ቆዳ የሚቀዱብህን ፥ አዙረህ ብትቀዳ ጥያቄ እንደፈራ፥ ሰነፍ አስተማሪ ምላሹ ጅራፍ ነው፥ አትቀበል ተወው፥ አቀብል አዝማሪ። ............አቀብል... እንካማ .....||እንደአረፋ ሙክት፡ ልክ እንደዒድ በሬ .....ሰርክ የሚያሳርደኝ፡ አለመሶበሬ|| የመንደሩ ወግ ነው ፥ ግንድ እየደበቁ፥ ንፋስ መማገሩ አቀባይ እጅ እንጂ፥ ተሸካሚ ጀርባ፥ የለውም ሀገሩ ብልጥ...ሁን ... እባክህ ገንዘብ እንደሌለው አራዳ ቆማሪ ሳትሰጥ ሳትቀበል፥ አየር ባየር ብላ፥ አቀብል አዝማሪ ............አቀብል... እንካማ ....« በሳቅ መፍረስ የሚል ፡ ፈሊጥስ ነበረን ..... ፈርሶ መሳቅ ደሞ፡ ማነው ያስተማረን? ©ረድኤት አሰፋ

የሐውልት ላይ ጽሑፍ • • • • • ፨••••••••••• "ጸሐፊው በምን አረፈ?'' ተብላችሁ ብትጠየቁ ኑሮውን ስትዘክሩ፣ እንዲህ ብላችሁ መስክሩ… ጸሐፊው ነቢይ ነበረ፣ ብዕሩ ቀለም ተሞልቶ ልቦናው በሀሳብ ታጭቆ፣ እንዲጽፍ የተፈጠረ። አንጋሹ ቀቢው በርክቶ፣ ከፍ ከፍ አድራጊው በዝቶ፣ በእብሪት እንደተበተ፣ ጥቂት መስመር እንደጫረ፣ በሆነ መድረክ ግረጌ፣ ጭብጨባ ጨፍልቆት ሞተ። ••••••••• ••••••••••••• ቴዎድሮስ ጸጋዬ "ነፍሰጡር ስነንኞች" የግጥም መድብል