ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
Открыть в Telegram
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Больше1 720
Подписчики
-124 часа
-47 дней
-1430 день
Архив постов
እዬዬ አልባ ሞቴ
ለራሴ አዝኜ ሳልጨርስ
ባዘንኩብሽ ቀን ሳልተክዝ
በሬን ሳልዘጋ ለእዬዬ
ሳልደበር ተበድዬ
አዬ. . .
በብርዳም ኮተታም ዓለም
ቁር ከውስጥሽ ሲፋለም
ጨለማ ጮሆ ሲንጫረር
ዝምታሽ ታሞ ሲጫፈር
ክፍተትሽ ከፍቶ ሲዛባ
ዛቢያሽ ከራሱ ሲቃባ
ማን ነበረ ያለበሰሽ - ያንን ጸዓዳ ጋቢ
እርምሽንም ባታወጪ - ከድንኳኑ እንድታድሪ
ብርዱን ችለሽ እንድትበሪ
ለቅሶኛውን እንድትመስዪ
አዪ. . .
የኔም ተራ ደረሰና
ስወድቅልሽ ከወና
ስንከባለል ዝምታ ጋር
እነጋንጩርን ሳናግር
እነጽልመትን ስጋግር
ከነ ጋኔንም ስበደር
ማን ነበረ ያሰከረኝ - በዚህ የሃቅ አረቄ
በወጉ እንኳ ሳላዝን - ከለቅሶ ቀድሞ ሳቄ
ድሮስ መቼ ለ'ኔ አውቄ
ብርቄ. . .
ለራሴ አዝኜ ሳልጨርስ
ባዘንኩብሽ ቀን ሳልተክዝ
በሬን ሳልዘጋ ለእዬዬ
ሳልደበር ተበድዬ
አዬ አዬ . . .
ይኸው ክፉ ቀን መጥቶ
ደጄም አደረ ተዘግቶ
ሞት ቢሞላው መንገዱን
እኔስ ሞትኩኝ የምለው
አንቺ ውስጥ ሞቼ እንደሆን
ድብን. . .
#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ @poeticsaturdays @artsmailinglist
Hello Tibeb community,
Due to the current situation of the Corona virus, the application deadline for Tibeb Be Adebabay has been postponed for two weeks!
Which means you will have more #time ⏰⏳to work on your applications!
📝 Work on your ideas and apply before April 2, 2020!
Find out more: http://bit.ly/2Id4yQk
Apply: https://bit.ly/2SMzU6o
Call us on +251 98 332 031
#tibebbeadebabay #TBA2020 #Tibeb #AddisAbaba #ArtinAddis
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስን በማስመልከት በተቻለ መጠን ሰዎች በአንድ ቦታ መሰባሰብን መቀነስ እንዳለብን አሳስቧል። በዚህም መሠረት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን የብሔራዊ የሥነ-ግጥም ግጥሚያ(ውድድር) ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ተገደናል።
ከሚመለከተው መንግሥታዊ አካል "ሕዝባዊ መሰባሰቦችን" ማድረግ እንደሚቻል ሲነገር ውድድሩን የምናደርግ መሆኑን እያሳወቅን ሁላችንም የግጥማዊ ቅዳሜ ቤተሰቦች በያለንበት ደኅና እንድንሆን ልባዊ ምኞታችንን እንገልፃለን።
Relying on recommendations from the Ethiopian government due to the spread of COVID-19 in Ethiopia, we have decided to postpone the 1st Annual Ethiopia National Poetry slam until a later time in which it is safer to have large, public gatherings. We will rely on guidance from public health officials about when we may reschedule so that everyone in our Poetic Saturdays family can remain as safe as possible. We look forward to rescheduling our very first National Poetry Slam so that a National Champion may be crowned! Stay safe out there, you beautiful people!
Follow me on Instagram! Username: gitem_sitem
https://www.instagram.com/gitem_sitem?r=nametag
Morning Tibeb community, the second week to submit your applications since it's opened! 🤩🤩 We are excited to receive them! 🗃
So here is the link to the application form https://bit.ly/2SMzU6o for those who apply online.
We will send tips and suggestions through the week!
Good luck!
ላንቺ
#ሰይፈተማም #poeticsaturdays #ግጥምሲጥም
ከሰውነትሽ በላይ - ሰው ለመሆንሽ ክብር
ዘንባባ እንኳን ባልዘነጥፍ - ቄጤማ ፊትሽ ባልከምር
ከመንገድሽ ጋሬጣውን ባልመነጥር
እንቅፋት አልሆንብሽም - እንደው ሌላው ሌላው ቢቀር
ላንቺ
የሚገባሽ እንዲገባሽ - መስመሮቼን አነጻለሁ
በለከፈሽ እንዳይከፋሽ - መልካም አፎች እጣራለሁ
ባንቀመጥ በእኩል ሚዛን - የሰው ነገር ቢሆን ግራ
እስከማይሽ እተጋለሁ - ውጅንብሩ እንዲጠራ
ላንቺ
መሞቱን እየረሳ ሰው - ቀኑ ላይ ቀመር ሲያበዛ
የህይወት መስመር ተስታ- በጾታ ዳስ ስንገዛ
ዓለምሽ ተንቃ ሳይ - መከበርሽ ተወዛውዛ
ሳንካ አልባ ምድር ስዬ - ብራ ቀንሽን ላወዛ
ቀስቃሽ አለሁሽ ለፋፊ - እንዳትታዪ በዋዛ
ላንቺ
አቅሜን የማልለካብሽ - እንደሰው ላይሽ ሰው ሆኜ
እራሴን የማነጻልሽ - ከመንገድ ሳይሽ ሰክኜ
ለራሴ ስል የማግዝሽ - ከወንድ ጉራ መንኜ
የምነቃ በጥበብሽ - የነቁ ቃላት ሰንኜ
ላንቺ
እንደ ራስሽ ስትኖሪ - የምትችይውን ይውቁ
በሴትነት ምሽግ ከትተው - አቅምሽን እንዳይንቁ
ብርሃን ይሁን መንገድሽ
የሚመራሽም ልብሽ
የምትመሪውም እራስሽ
የልብሽ ብርሃን ፈክቶ - ድቅድቃችን ላይ ያብራ
ቀስቃሽ ነኝ ያለው ሁላ - ተቀስቅሶ ይጠራ
ተቀስቅሶ ይጣራ
ተቀስቅሶ እንዲበራ
የተፈጥሮ አካል ሆነሽ - እሱም ተፈጥሮን ይኑራ
ነጻ አውጥተሽው ደሞ - ነጻ ይሁን ከአጥሩ
ነጻ አውጥተሽው ደሞ- ባንቺው ይኩራ እንዳገሩ
ላንቺ እምር እንዳሉ - ላንቺ ይሁኑ ቀናት ሁሉ
ሰይፈ ተማም 2012
.........ለጀግኒት...........
አንቺ ጀግኒት
የጀግና ሰው ዘውድ
አንቺ ውድ ሰው
የውድ ሰው ልጅት
አንቺ የእንቁ ፍልቃቂ
የወርቅ ሰው ውበት
የተኖረልሽ የሚኖርልሽ
የተኮራብሽ የሚኮራብሽ
አንቺ የአንቺ የእሷ የእሱ የእኔ መከታ እመቤቲቱ
ስለ ነፃነትሽ አባትሽ በእናትሽ እዝጎይታ ክንዱ የጠነከረው እንደልብሽ ውለሽ በሀገርሽ ቋንቋ ደስታሽን ከሀዘንሽ እንድተርኪበት ሸማሽ ጃኖ እንዲሆን እንድትቆነጂበት
ሲያሻሽ ጥጡን ፈትለሽ
ሲልሽ ጠጅ ጥለሽ
ጎጆ ታሞቂበት ሞቶልሻል፡፡
ግን ደግሞ ብትልፈሰፈሺ ብትፈሪና ትቢትሽ ቢበዛ የሞተልሽ ጀግና ይፋረድሻል፡፡
ስንፍናሽ ከላቀ ተራራው ያኮርፍሻል
ወንዙ ያለቅስብሻል፡፡
ተነሺ
ካባ ልበሺ
ታሪክ ታጠቂ
ጉራን አውልቂ
ስንፍናን ናቂ
ታሪክ አቅልሚ
ክብር ጠምጥሚ
ሀገርን አልሚ
ልህቀት ቅሰሚ
ኑሪ ክበሪ
ጠ
ን
ክ
ሪ፡፡
ውድ ኢትዮጲያዊቷ
ኑሪ
ክበሪ
እንኳን አደረሰሽ፡፡
👑👑👑👑👑
መልካም አድዋ
ተፃፈ:- በርብቃ ሲሳይ
2010
@getem
@getem
@getem
ስንል ጥቅም ጥቅም
ፍቅርን ጥርቅምቅም
ስንል ፍቅር ፍቅር
ጥቅማችን ላይ ቅርቅር
አቤቱ አድለነ
ጥቅማጥቅም ያለው
ፍቅር አዘግነነ
#ጥቅር #ሰይፈተማም
ተዘዋውሯል!
በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት የሀገራዊ የግጥም ውድድራችንን ወደ መጋቢት 11 አዘዋውረነዋል።
ያኔ እንገናኝ!
POSTPONED! Due to scheduling concerns, we have decided to postpone the National Poetry Slam to March 20th! See you there!
ማን ያውቃል?🙇♂️
በ ቶማስ አድማሱ @Mmiinnuu
. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
ከደስታና ከሐዘን የቱ ይሰነብታል
ለአ'ንዲት ቅጽፈት ሳቅ ዓይን እንባ ያግታል?
ለመውለድ ያቀደ ገና ከመውደዱ የምሩን ይሞታል?
ማን ያውቃል?
ባይኔ መኃሉ ላይ ካይኔ ጥቁሩ ላይ
ብሌኔን ታቅፈሽ በዓለም ሌላ ላላይ
ላንቺ እየዘመርኩ ሆንኩኝ ማኅሌታይ።
....
እተረከዝሽ ስር ላንቺ ስል ወረድሁ/ኝ
ትተሺኝ ብትበርሪ መልአክ ነች አልሁ/ኝ
ማን ያውቃል እውነትን ፤ እውነትም ማን ያውቃል?
ማን ነው የሚጸና ከሃቅ እና ከቃል??
ማን ያውቃል?
እጄን ይዘሽ ከእጅሽ ሆኜ በመሃሉ
ከብደሽ ላይኔ ሌላው አንሶ ቀልሎ ሁሉ
በሳቀብን ስናሽካካ የረታንን ስንጥለው
ባረፍድ እንኳ እንዳይስቁ አጣት ብለው
ታቅፈኝ ይሆን ፤አውቃት ይሆን፤ አያት ይሆን?
ቀን መቃዠት አንቺን ማለም ሌሊት ሲሆን
ማን ያውቃል ?
መገጣጠም እንጂ አሁን አለ "እውነት"?
የቱ ነው ሃቅ ሚሆን ከህልም እና ቅዠት?
የቱ ነው የሚያም
ከእውነት ማጣት እና የውሸት ከማግኘት?
ከደስታና ከሐዘን የቱ ይሰነብታል
ለአ'ንዲት ቅጽፈት ሳቅ ዓይን እንባ ያግታል?
ማን ያውቃል?
በከፍታ መብረር ከመሬት ያርቃል ብለው የመከሩ ፡ ሠጎን እና ዶሮ ተመሬት አደሩ ። ሁለቱም ልክ ነው ያለችው ሦረኔ ትንሹን ተራምዳ፡ ትንሹን በራ ነው ፡ ሠማይ እን ምድርን የምታሥታርቀው ፡ በሠማዩ ነጥታ በምድሩ ጠቆረች ፡ ባለ ሁለት መልኳ
በመዘነቋ ነው ጅግራ የተባለች ። የጅግራም ትርጉሙ ፡ ከጃችን ሥያሜ "ጅ" እየጎተተ ከታች ካለው እግር ... ግንን እየሣበ ...
ትሑት ምህላ
=========
አቤቱ ጌታ ሆይ ፣
የኢትዮጵያውያንን እምነት
የግሪክን ጥበብ መሻት
የአይሁድን ምልክት ጥማት
የፈሪሳውያንን የአመክንዮ ሙግት-
ልክፍት
የሱፊን ተደሞ
የዜንን አርምሞ
የተመሥጦ መገለጥን ምትሐት ፣
......አጣምረህ ለነብሴ ሥጣት!
በዚህ፣ኃይሏ ግርማ
እንደ ጨለማ ፣ ቀለም ድንበርን ታሥማማ.....።
አሜን።
ዲበኩሉ ጌታ
ሰኔ ፳ ፳፻፰ ዓ.ም
-----------//----------
የምድር ዘላለም ድንቅ መፅሀፍ ነው በተገኘበት ይነበብ!! ያነበበ ብዙ ያተርፋል
#
@sufafel
@sufafel
@sufafel
Abstract
Utter silence
I listen
Whooshing sound of
cars
Some how it makes me calm
The moon lighting the darkness
Some how it heals
Some how the beauty
Puts me in trance
Some how it is easier
To bare my soul
To people I barely know
It is okay to be bare
And sometimes
it is okay
To wallow in pain
I want to live here
Here is just me
Here is just me alone
Here is my home
Do we have a meaning?
Do you have a meaning?
Do I?
We work, sleep and eat
Wake up to do it all again
What if this is hell?
What if hell is just like a broken
Record
Repitition of the same thing over and over
Suddenly you wouldn't know when it will be over
I say all this while I am sober
When you pause
Only eyes can see
Ears can hear
Fears dissapear
life reappear
And you exist
I crave this pause
The one that closed the door
Is my shadow
who likes to to oppose
He is in control
I suppose
Somehow they misunderstood
It is he who is talking
Not me
It is he who you seeing
Not me
"Me" is a misconstruction
Made by the perception of what I think is others perception of me
I really don't know what "Me" is
I don't know "I"
As soon as the word "I" exist
We perish
This abstract mind
Science couldn't decode
History couldn't record
This isn't my mind speaking
This isn't my body your witnessing
Just the formation of DNA
Manifestation of information
That lived for decade
-Anima
#Existence
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
