እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
Открыть в Telegram
215
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
ቃላት ቅመም
ሚደብቅ የነፍስ ህመም
ጣፋጭ ዜማ ለህሊና
......ለእስትንፋስ.......
እውነት ሚያጭቅ።
፧
ግጥም አለም፦
ዝለት ጉድለት የህሊና እምባ
ለጨለማው መሸሸጊያ
ከብርሀን በዝምታ መታረቂያ
...................ብቸኛ አምባ።
፧
ለስላሳ እውነት
ህመም መንፈስ የሚቃኘው
ክህደት ሀጥያት መከራ የደረሰው።
፧
ግጥም እናት፦
ፍቅር ሲወርድ ከጥልቁ
ዳፍንትና ፅልመት ከብርሀን ሲርቁ
እንዲ ደረመስ የጥርጣሬው ድንበር
መንገድ መሪ ድኅነት ምስጢር
ለፍርስራሽ ቀልቤ ነፃነት
ቃላት ፊደል ንፁህ እምነት።
፧
ግጥም አባት፦
ጠንከር ያለ ሆሄ የሚዳኘው
ለስለስ ያለ ሀቅ የከበበው
በጠለቀ ህሊና የሚተከል
ምርጥ ዜማ ቆንጆ ቅኔ
እንደዚህ ነሽ አንቺ ለእኔ።
©ezra kassahun
6/2/19
@melos3
የቡናው ፡ ጠይም ፡ መልክ
የሽታው ፡ መዓዛ፥
ሙዚቃና ፡ ዜማው
መፅሃፍ ፡ ከብእር ጋ'፤
ስጡኝ ፥ ነፍሴ ትረፍ
ልቤ ፡ ከአለም ፡ ብዙም ፡ አትሻ'።
አቅርቡ ፡ ቡና ቁርስ
ፈንድሻውም ፡ ይፍካ
ሉባንጃውም ፡ ይጢስ
አቦል ፡ ከበረካው በቶና ፡ ይተካ።
፧
ለእኔ ፡ በቂዬ ነው
በእፍኝ ፡ ከሰል ፡ ሙቀት፤
የብርድ ፡ ዝምታ
የሸክላው ፡ እሳት ፡ ሐሩር፤
የቡናው ፡ ከበጃ'
በማሰብ ፡ ነፃነት፤
ሰው ፡ የመሆን ፡ እርካታ።
ስጡኝ..........፦
የጢስ ፡ ዳንኪራውን፥
የዜማ ፡ አድባሩን
ያለ እርሱ ፡ እኔስ ፤
መክረሜንስ ፡ እንጃ።
አምጡ ፡ ክራር ፡ ልምታ
ድምፁ ፡ ያቃስር
አእምሮ ፡ ይሰርስር
ይዳብስ ፤ ያስስ
የልብን ፡ ማህደር።
ቡና ፡ ፉት ፡ ልበል
ከዛሬ ፡ ልነጠል
በሀሳብ ፡ ሽቅብ ፡ ልጓዝ፤
........ ልሻገር .........
ከምናቤ ፡ ድንበር።
ልናፍቃ ፡ ልተክዝ
ነፍሴ ፡ እንድትቦርቅ
ካለፈው ፡ ትዝታ ፤
ከምርጡ ፡ ልታረቅ።
እኔ ፡ ከእራሴ ፡ ጋር
በልክ ፡ እንዳወጋ፤
ዝምታን ፡ እንዲያከብር
የነገር ፡ አለንጋ
ሌላ ፡ አልፈልግም፤
፧
ስጡኝ፥
ቡና ፣ መፅሀፍ ፣ ብእርና' ሙዚቃ።
5/2/19
©ezra kassahun
@melos3
ስፈራ በተስፋ
እስትንፋሴን እምቅ
አየር ምን አባቱ...፤
፧
ዘመን ከተዋጀ
ሳዝን አጨብጭቤ
የዘራሁት ደርሶ
ያጨድኩትም ጎድሎ'
አየሁ ተደብቄ።
፧
አየሁኝ.............
አግኝቼ አጥቼ
በኩርማን እንጀራ
ቀኔን አንጣጥቼ
ሕመሞች ማያልፉኝ
ቆየው...........፥
ደስታዬም ነጥፎብኝ።
፧
አለው
አንድ እኔ የሰው ልጅ
የተውኩት ችላ ያልኩት ቀንቶ
ውሃ ያላጠጣሁት አብቦና ፈክቶ
በመፈለግ ትክት ልቤ ግራ ገብቶት።
፧
በነተበች ነፍስ ውስጥ
በዚህ የጊዜ ንፋስ
በዚህ የሕይወት ቅዠት
እንኳን ለመቆም አይደለም
ለማረፍ እኔ የለኝም እረፍት።
፧
ደሞ ለዳተኛ
መቆም አይቻልም
ወደፊት ከመዳህ
መንገድ ከመከተል
ሌላ አማራጭ የለም።
፧
እናም መጨረሻው
ጥላዬ ሳይጠፋ
በብዕሬ ላስቀምጠው
የነበርኩበትን የዳናዬን መስር
የተሰበረውን የከረመውን ሀቅ
እሾሁ አቁስሎ ፍሬው የፈካበት
..................የጊዜን እጥፋት።
©ezra kassahun
27/1/19
@melos3
እናቴ አደራ አስብላኝ
አላፊ ጠልፎ እንዳይረሳኝ
ለሚቀር......................
ቃል ስቼ እንዳልቀር፥
ለሚሞት.....................
ነፍሴን ሰጥቼ እንዳልከስር፤
ፀጥ!
ለአላፊው አፌን ሳልከፍተው
ዝግ' ዝም ብዬ እንድተው።
፧
እናቴ አደራ ብላኝ
ተባይ' ቃል እሳት የሚጭር
ትንፋሽ ሚያሳጥር....፥
ነዳፊ ጩኸታም ቢያዝብኝ
ከንፈሬ ደርቆ ምላሴ ታስሮ
ስንቱን ዝም አልኩት
አይቼ አለፍኩት
ታዝቤ ተውኩት
.................መኣት እሮሮ።
፧
ዘመኑ የበቀል ወፍጮ
ዙሪያዬ የነገር እቁብ
ሀሳቤን ላይቀበሉት
ከቁብ ላይቆጥሩት ፥
ጣል ቢሉኝ ቃል ከኣንደበቴ
አደራ ይዞኝ የእናቴ፤
አቋምና አቅሜን ደብቄ
ስንቱን አሳለፍኩት ታምቄ፣
የዋህ..............
ራሴን አለማወቄ!
፧
የሚያልፈው ካፊያ ሳይመታኝ
ለማለፍ ዙሪያዬን ስቃኝ
በአየሁት ቃሌ እየቃጣ
ስውጠው ፈርቼ ጣጣ፤
ሳምቀው ኖሬ ሳፍነው.
ምስኪን!
ይሁሉ ድካም እኔው ለማልፈው!
©ezra kassahun
22/1/19
@melos3
ቀዥቃዣ ልቧ ከእኔ ረጋ ያለ ግራ መጋባት ጋር ስትገናኝ፤ ማንም የማይረዳውን ድንበር አልባ መኖሬን ታገኘዋለች። መውደዷ የማይከብድ ጉልበት አለው።
፧
ለዛም' ይመስኛል ዓለም ሥርዓትና አጥር ስትፈልግ፥ እኛ የሌሊቱን ንፋስ በቅዱስ ወሲብ የምንባርከው። መሸሸጊያችንም አልጋችን ግን ስሜት ብቻ አይደለም። ከንጋትም ጋር የምንወዳጀው በራሳችን ህግ ነበር።
፧
ተፈጥሮ ጠዋት ነው ብላ ቁጥርና ስም ልትሰጠን ከምስራቅ ብቅ ስትል እኛ ገና ትንፋሽ ከመዋዋስ አንወጣም ነበር። የነጋው ከቅዱሱ ተግባር ላልሆኑት ነው፤ ለእኛ የሌሊቱ ድፍረታችን ይቀጥላል።
፧
ፍሬው ከገለባ በንፋስ እንደሚለይ ፥ ያልተጨከነበት ፍቅር፤ ያልተረጋጋች ነፍስ ፥ የነበረበትን አጥር ሁሉ አፍርሶ ሜዳ ላይ የሚያስቀር ውብ ድፍረት አለው።
፤
ትዝታ በነበር ብቻ መወሰኑ ያናድዳል!
፧
@melos3
©ezra kassahun
21/1/19
የጥል መጋረጃ የብርሃኑን በር ጋርዶ
ሰው በራሱ ምስጢርና እውነት ተናዶ
በእሳትና ውኃ መካከል ሲጋደል
በእምነት ጭልፋ ከሐሰት ድስት ይቀዳል
እያወቀም ይሁን ወይም በቸልታ
የራሱን ምስጢር ከራሱ ይጥላል።
ይሄ መቅበዝበዙ
የነፍሱን እንቆቅልሽ ሊፈታው ሲቃረብ
ወዴት ይሄዳል ሲጣደፍ መነሻው ተረስቶት
ማን ማንንስ ፍለጋ ይከንፋል ተራርቦት?
ሰው በብርሃንና በጥላ መካከል የሚወዛወዝ፣ የራሱን ምስጢር ለመፍታት ሲታገል የራሱ እንቆቅልሽ የሚሆን ጥልቅ ፍጡር ነው። በእሳቱ የሚቃጠለውንና የሚያቃጥለውን ያህል በውኃው የሚበርድ፣ በሐሳብ ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የexistenceን ትርጉም ይፈልጋል።
የነፍሱን ጥያቄዎች ለመመለስ በራሱ የልብ ምት ውስጥ ይጓዛል። ነገር ግን የመልሱን በር ለመክፈት ሲቃረብ የራሱን ጥላ ፈርቶ ወደ ኋላ ይመለሳል። በመንፈሱ ውስጥ የሚነደውን እሳት በቃል አልባ ሕመም እያዳፈነ፤ ከምድር አፈርና ከሰማይ መንፈስ የተሰራውን እውነተኛ ማንነቱን ፍለጋ ይደክማል፥ ይኳትናል። በመጨረሻም ፈጣሪን ወይም ሰውን ለማወቅ ሲሻ፥ በመስታወቱ ውስጥ የተደቀነውን የራሱን ምስጢራዊ ገጽታ እያየ በተመስጦ ይቆማል።
©ezra kassahun
20/1/19
@melos3
አንድ-አንዴ እወድሻለሁ....‼️
፧፧፧፧፧
ከውቂያኖሱ ዳር ከማዕበሉ ጠርዝ መጨረሻ
ከነጣው አሸዋ ባልኖር ከአጠገብሽ
በቃላት ፍተጋ በሆሄሃት ዳዴ አሁን የምነግርሽ
አንድ-አንዴ ስወድሻ'ለሁ።
፧፧፧
በእርግጥ ፤ አንዴ ነሽ እኔም አንድሽ
በመፍጠር እውነት በቀናት ጉም ዝግነት
ለነፍሴ ውሃ ልክ በልኬ የተሰራሽ።
፧፧፧
አንቺ ንፅህና ፥ የቀናነት ሙዳይ
የክብር ዙፋኑ ከውሸት ተገንጣይ
የአንዴ ውበት ፥ የአንድ ጊዜ ስጦታ
የትህትና እናት የመኖር ከፍታ።
፧፧፧
ጥዑም ለሚሰማሽ ማትሰለች ዜማ
ልብን ምትዳብሽ............፤
እንደ ታቦት ሸኚ ዝማሬና እልልታ።
የደስታ እርካቡ ለሀሴት እርጋታ
ለህይወት ጋጋታ ምትታመኝ አለኝታ።
፧፧፧
አንድ በሆነው ልቤ፣ በበራው ስንቅሽ
ባለፈው ትዝታ በዛሬው እውነትሽ፤
እወድሻለሁኝ በአንዴም በአንድሽ።
፧፧፧
አንድ በአሃዝ ቁጥር፣ አንዴ በጊዜ ስፍር፣
ቀመር የማይተካው፣ የነፍሴ መዘውር፤
ጊዜውን የቀደምሽ ችሎም' ማይመልስሽ፣
የፅናት ጉልላት ፤ ትውስታሽ የቅጽበታት ክምር።
፧፧፧
አንድ ነሽ በአካል፣ የለሽም አምሳያ፣
አንዴ ነሽ በምድር፣ የኑሮዬ መንታ
የተስፋ መስታውት፥ የህይወት መታያ።
፧፧፧
ስለዚህ እወድሻለሁ...
ከመኖር ሚተርፈው ትዝታ ቢሆንም
ዘመን በማይደግመው፣ በአንዱ ማንነትሽ፣
አንዴ በተሰጠኝ፣ በዚያ በአንድ ፍቅርሽ።
©ezra kassahun
24/9/18
@melos3
@melos3
ፀሀይ ለሁሉም ቀን አዲስ ቀን ይዛ አትመጣም። አንዳንዱ ቀን ራሱን ይደግማል ።ደግሞ አንዳንዱ ዕለት የምስራች ይዞ ሲመጣ ፣ ሌላው ቀን መርዶ ሊተረክክ ወጋገን ይሰዳል።
በሌላኛው ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ የቤታችን ቆርቆሮ ክዳን በላይችን ላይ አልነበረም። ዓይኖቼ ያረፉት ወደ ሰማያዊ ሰማይ ነበር።በደመ ነፍስ እየተጣዳፍኩ ከወደቅኩበት ተነሰቼ ወደ አባ አመራሁ።ልባቸው እንደ ከበሮ መደለቅ ጀምራ ቁና ቁና እየተነፈሱ ሲያጣጥሩ ከአልጋቸው አጠገብ ደረስኩ። ቤታችን ቅሪት እንኳ አልነበረውም። አውላላ ሜዳ ላይ ነበርን።
ጦርነቱ በህልውናዬ ላይ የፈጠረው ኪሳራ ነበር። ሕይወቴንና ማንነቴን በአንድ አፍታ ቀይሮታል። የማንነቴ ካስማ የተጣለበት ስፍራ እንዳልነበር ኾኗል። በዙሪያዬ ነፍሴን የማስጠልልበት ዓለም አልነበረኝም።
ደካሞች እግዚአብሔርን ምርኩዛቸው ሲያደርጉ ኃያላን ግን በሥልጣናቸው ይመካሉ። ታሪክ የሚያስረዳው ፈጣሪ ይህችን ምድር ይፍጠራት እንጂ በአዛዥ ናዛዥነት የሚያስተዳድሯት ሊቀ መናብርት ሰዎች ናቸው። በየዕለቱ ንጹሓን በግፍ ይገደላሉ። በጨለማ የማሰቃያ ማጎሪያዎች የምስኪኖች ቅስም እንደ አጥንት ሲከተከት እግዚአብሔር የፍጥረታቱን የማያልቅ ሰቆቃቸው እየታዘበ ስለምን ዝም አለ?
ስንት ሰው ሲሞት ነው የእግዚአብሔር ኃይል የሚገለጠው? በመንግሥተ ሰማያት መካሻ ስላዘጋጀ በሰው ልጆች ምድራዊ ሕይወት ጣልቃ አይገባም? ወይስ እንደ ቅጠል የሚረግፉትን ንጹሐን ይታደጋቸው ዘንድ በእርሱ ላይ ያላቸው እምነት ጎዶሎ ነው? ፈጣሪን ልክ ለማድረግ በሚኬድ ርቀት እግዚአብሔር እንዲታደጋቸው ያስጥላቸው ዘንድ ቢማጸኑትም እጁን ከአርያም ሳይሰድላቸው ቀርቶ መከራ ሞትን የተቀበሉ ሰዎች የሰማዕትነት ማዕረግ አልተሰጣቸውምን? ይህስ የሕይወት ወለፈንዲዊነት አይደለምን?
ይህ መከራና ሰቆቃ ዕውቅና የለሽ ነው። እንደ አደባባይ ምሥጢር በግልጽ የሚያወራው የለም። መሃል ከተማ ጥሩ ቀን እያለፈ ይመስላል። የዳር ሀገር ጩኸት የመሀሉ ሀገር ግድ አይሰጠውም እዚ የተለኮሰው እሳት እዛ አይደርስ ይመስል!!
መሽቶ ሲነጋ ከፀሓይ መውጣት ጋር ለኑሯቸው የሚዳክሩ ሰዎች ማልደው ከእንቅልፋቸው ይነቃሉ። በዚህች ቀን ማን መንቃትን በብርቱ እየተመኘ እስከ መጨረሻው አሸልቦ ይኾን? ማንስ በጥልቅ ከዚህች መከረኛ ሕይወት መገላገል እንደ ፈለገ ሳይሳካለት ቀረ ይኾን?
ይብቃ‼️‼️‼️
@melos3
©zephilosophy
«My crime was feeling everything too deeply _»
Fyodor Dostoevsky
፧
Depth is not a gift.
It is a liability in a shallow world. To feel deeply is to refuse numbness. To see meaning where others see routine. To carry weight others are too distracted to notice. That is the crime.
The Real Punishment
« my punishment was surviving it.»
Not death. Not collapse. But continuation. Because surviving means remembering. It means carrying every disappointment, every truth, every realization without escape. Most people are protected by ignorance.
We are not.
The Hidden Cost of Awareness
Depth isolates. We start to see through people their words, their masks, their inconsistencies. Conversations become predictable. Connections become rare. And slowly, the world feels smaller not because it is, but because we outgrow it.
The Critical Truth
Feeling deeply is not the problem.
Staying there is. If depth does not transform into: Clarity, Control & Creation
Then it becomes self-destruction.
©ezra kassahun
@melos3
መውለድ ሞራላዊ ነውን?አንድ ሰው ወደዚህ ዓለም ከመጣ ቢያንስ ጥቂት ስቃዮችን መቅመሱ የማይቀር ሀቅ ነው ይህ ደግሞ የህይወት ጨለማው ገጽታ ነው። ከአደጋ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አደጋን አስቀድሞ ማስቀረት የተሻለና አስተዋይነት የተሞላበት የሞራል ምርጫ ነው። ስለዚህ አዲስ ህይወትን አለመፍጠር ማለት ሊመጣ የሚችለውን እርግጠኛ ስቃይና መከራ አስቀድሞ መግታት ማለት ነው።
ተፈጥሮ የሰጠችን ጉቦ እና አንቲናታሊዝምአንቲናታሊዝም አንድን ሰው ወደዚህ ዓለም አለማምጣት የተሻለ የሞራል ምርጫ ነው ይላል። ታዲያ የሰው ልጅ ይህንን አመክንዮ ስቶ ለምን መውለዱን ቀጠለ? ለዚህ ጥያቄ ጓደኛዬ አንድ የሚገርም ምልከታ ሰጥቶኛል፦ ወሲብ እንደ መጨባበጥ ያለ ምንም እርካታ የሌለው ተራ ድርጊት ቢሆን ኖሮ ስንት ሰው ይወለድ ነበር?" ተፈጥሮ የሰው ልጅ መወለድ ያለውን ስቃይ እና ሃላፊነት አስቦ እንዳይተወው ወሲብን በከፍተኛ ደስታ ሸፍናዋለች። ተፈጥሮ የራሷን ዓላማ (ዝርያን ማስቀጠል) ለመፈጸም እኛን በደስታ ስሜት ታታልለናለች። እኛ ለራሳችን ደስታ የምናደርገው ይመስለናል ግን እያገለገልን ያለነው የእኛን ደስታ ግድ የማይላትን ተፈጥሮን ነው። ሰው የሚወለደው በወላጆቹ ደቂቃዊ እርካታ ምክንያት ነው። ነገር ግን ለዚያች ደቂቃዊ እርካታ ሲባል የሚፈጠረው አዲስ ሰው የህይወትን ሙሉ ስቃይ ይጋፈጣል። ሀይማኖይቶች ልክ ሚሆኑበት እድል ካለ የገሃነም ስጋት እና ለዘላለም አደጋ ይጋለጣል። ይሄ ሁሉ የሚሆነው ግን እሱ ሳይስማማ ነው። በሌላ አነጋገር የወላጆች ደስታ የልጁ እጣ ፈንታ ላይ ቁማር ይጫወታል ወሲብ እንደ መጨባበጥ ተራ ቢሆን ኖሮ የሰው ልጅ በምክንያታዊነት ያስብ ነበር።ይህ ልጅ ሲወለድ የሚደርስበት ስቃይ ዋጋ አለው? ብሎ ይጠይቅ ነበር። ተፈጥሮ ግን ይህ ጥያቄ እንዳይነሳ አእምሯችንን በወሲብ ደስታ በሆርሞን ትጋርደዋለች። አንቲናታሊዝም ግን ይህንን የሆርሞን ግርዶሽ ገልጠን በምክንያት እንድንወስን ይጋብዘናል የሰው ልጅ መብዛት የጥበቡ ውጤት ሳይሆን የተፈጥሮ የወሲብ ደስታ ጉቦ ውጤት ነው። ያ ጉቦ ባይኖር ኖሮ ማንም ሰው በራሱ ፈቃድ ወደዚህ አስቸጋሪ ዓለም ሌላ ሰው አይጋብዝም ነበር። እናንተስ ምን ታስባላችሁ? መውለድ የነጻ ምርጫ ውጤት ነው ወይስ የተፈጥሮ ወጥመድ? @melos3 @melos3 #life true meaning
Fasika is not just a celebration it’s a reflection. ✨
Coz ፆም፣ ጸሎት እና ሥርዓትን ብቻ አይደለም የሚያሳየን it’s how we treat others that defines us. 🤝
«መንፈሳዊነት genuinely በምናደርገው ነው የሚለካው ፥ እንጂ በምንናገረውና በሥርዓታችን ብቻ አይደለም።»
ፆም እና ጸሎት ከፍ ያሉ መንፈሳዊ ልምዶች ቢሆኑም፣ እውነተኛው ፍሬያቸው ለሰዎች የምናሳየው ምሕረት፣ ክብር እና ፍቅር ነው። ❤️
ይህ ተግባር ደሞ ከሰው ጋር የምንኖርበትን የነፍሳችን ጥራት የሚታይበት የህሊና መስታወት ነው ብዬ አምናለሁ።
ፋሲካ ደሞ የመከራ መጨረሻ እና የእድሳት መጀመሪያ ነው። 🌅 ይህም ከውጭ ልማዶች ወደ ውስጣዊ ለውጥ መሻገር ነው።
የክርስቶስ መነሳት መታሰብ መልዕክቱም ይህ ነው፦
፧
ይቅር ማለት ከክብር ጋር 🤍
ሰውን ከፍ ማድረግ ከትህትና ጋር 🙏
በፍቅር እና በ'ርካታ መኖር ከእርጋታ ጋር 🌿
ምክንያቱም true resurrection is not just spiritual it is behavioral.
That is why our actions toward people are the true mirror of our soul. 🪞
በዚህ ፋሲካ፣ let’s go beyond tradition - kindness, respect, and forgiveness should be our real practice. 🌍
እንግዲህ ይህ ፋሲካ ፆምና ጸሎት እንዲሁም የምግብ እልህ መወጫ አይሁን፤ በህይወታችን ለመንፈሳዊ እይታችን መንቃት ይሁን።
Happy Fasika 🍾 let our life reflect our faith. ✨
#Easter #Reflection #FaithInAction #SpiritualGrowth #Leadership #Values #Kindness #Respect #Forgiveness
Manipulation
ብዙ ጊዜ በፍልስፍና እና የስነልቦና ውይይቶች ውስጥ በተለይም በሃይማኖት እና ፖለቲካ ርዕሶች ላይ Manipulation የሚል ቃል እንጠቀማለን። ይህ ግን ቃል ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ሃሳብም ጭምር ነው።
Manipulation ምንድን ነው? ማኒፒዩሌሽን የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ማታለል ወይም ማጭበርበር ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን ሃሳቡም:
የሰዎች ሃሳብ፣ ስሜት ወይም ድርጊት ላይ ከዕውቅናቸው ውጪ ወይም ሳያስተውሉት ተጽዕኖ ማድረስ ወይም መቆጣጠር የሚል ነው።
Manipulation ግልጽ የሆነ ስለት ያለው ዓይነት ብቻ ሳይሆን ፈገግታ የሚለብሰም ነው። ፍቅርን፣ ፍርሀትን እና ቋንቋን እንደ መሳሪያ የሚጠቀም አይነት ነው።
Manipulation ስለ ጥንካሬ አይደለም። ትክክለኛውን ስሜታዊ ጊዜ የመጠበቅ ችሎታ ነው። ስትደክሙ፣ አብሮነትን ስትራቡ ወይም ትርጉም ስፈልጉ ያውቃል። በሩን አይንኳኳም—በወረስናቸው ታሪኮች እና እኛ ለመፈተሽ በጣም በምንፈራቸው እምነቶች ውስጥ ይንሸራተታል።
ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በመተማመን ነው። አንድ ሰው የእናንተን እሴቶች ያንጸባርቃል፣ ቋንቋችሁን ይናገራል፣ ፍርሃታችሁን “ቅዱስ”፣ ህመማችሁን “የእቅዱ አካል” ብሎ ይጠራቸዋል። ድንገት ስትነቁ እሱን እየተከተላችሁ አይደለም—እሱ እንድትሆኑ የገነባላችሁን የእራሳችሁን ስሪት እየተከተላችሁ ነው።
Manipulation በሃይማኖታዊ አመራር ውስጥ እንደ መለኮታዊ ማስፈራሪያ ሆኖ ይመጣል።
“ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ አትጠይቁ” ተብላችኋል።
ግን የእግዚአብሔር ድምፅ ጭምብል ለብሶ ወግ ቢሆንስ የሚያስተጋባው?
የገሃነም ፍርሃት፣ የመዳን ተስፋ—እነዚህ ሁልጊዜ መንፈሳዊ እውነቶች አይደሉም። ስሜታዊ መልህቆች ናቸው። እምነትን እየመረጣችሁ አይደለም። ከእሳት እየሸሻችሁ ነው።
በፖለቲካውም ውስጥ ተመሳሳይ ቲያትር ነው።
መሪዎች “እኛ የህዝብ ነን እነሱ ጠላት ናቸው” ይላሉ።
እና ልክ እንደዚህ ውስብስብነት አፈር ይበላዋል።
Manipulation ሐሰተኛ ግልጽነትን ይፈጥራል። እንድታስቡ አይፈልጉም—ቶሎ ምላሽ እንድትሰጡ ይፈልጋሉ፣ እንድታስተጋቡ።
ቁጣ ምንዛሬ ይሆናል። ታዛዥነት መልካም ባህርይ ይሆናል። ጥርጣሬ ክህደት ይሆናል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ እውነተኛ ችግሮች— ድህነት፣ ኢፍትሃዊነት፣ ድንቁርና—ዝምታን ለብሰው ባሉበት ነው።
አንዳንዶች "ሁሉም Manipulation ክፉ አይደለም
አንዳንድ ጊዜ እናት ለልጇ ስለ ከባድ እውነት ለስላሳ ታሪክ ትናገራለች።
አንዳንድ ጊዜ አስተማሪ የተኛ አእምሮን ለመቀስቀስ ምቾት መንሳት ያመጣል።
ያ ጭካኔ አይደለም—ስልታዊ እንክብካቤ ነው።" ሲሉ ይሞግታሉ።
ስለዚህ ጥያቄው የሚሆነው: የማንቂያ Manipulation ስህተት ነው?
ወይስ አሳሪ ሰንሰለት ሲሆን ብቻ ነው ስህተት የሚሆነው?
እና ከዚያ Self-manipulation አለ—በጣም ቅርብ የሆነ አይነት—ራስን ማጭበርበር።
መታዘዝ ጥበብ እንደሆነ እራሳችንን እናሳምነዋለን።
የተወረሱ እሴቶችን እንደ ግላዊ እውነቶች እንቆጥራለን።
ጥርጣሬን ባላየ ፈገግ እንላለን።
ሥነ ምግባር ብለን እንጠራዋለን፤ ግን ምናልባት የተለባበሰ ፍርሃት ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ Manipulationን እንዴት እንዋጋለን?
በንዴት አይደለም። በኩራት አይደለም። በግልጽነት ብቻ።
እንጠይቃለን፡ ይህ እምነት ከየት ነው የመጣው?
የማንን ድምጽ ነው የምታዘዘው?
እያሰብኩ ነው—ወይስ ሀሳብን እየተወንኩ?
ማጭበርበር አንዴ ከተሰየመ ኃይሉን ያጣል።
እና ፍርሃት አንዴ ከተጠየቀ፣ መንገዳችንን ሊመራ አይችልም።
ቀዳማዊ ፍልስፍና
(ዮናታን በጋሻው)
@melos3
@melos3
«እውነት ከሰው ልጅ ፍላጎት ውጭ ነው በስምምነት አይፈጠርም፡፡ እውነት ከሰው ልጅ ፖለቲካዊ ስልጣንና ሀይል ጋርም ግንኙነት የለውም፤ የኃይል ብዛት እውነትን ማጥፋትም ሆነ መፍጠር አይችልም፡፡
፧
በርግጥ እውነትን የኃይለኞች ፍላጎት አድርገው የሚተረጉሙ አሉ፡ የራሳቸውን ፍላጎት ህዝቡ ሁሉ የሚገዛበት እውነት አድርገው ለማቅረብ ቄሱ መፅሐፍ ቅዱስን፣ ሼሁ ቁርዓንን፣ ሀብታም ገንዘቡን፣ ባለስልጣን ደግሞ ህግንና ሚዲያን ይጠቀማሉ፡፡
፧
በዚህም የተነሳ ሀይማኖት፣ ገንዘብ፣ ስልጣንና ሚዲያ እውነትን የመፈብረኪያ ማሽኖች እየሆኑ በዘመናት ሁሉ ታይተዋል፡፡»
ኢትዮጵያዊው ዘርዓያዕቆብ
@melos3
@melos3
«አንድ ክርስቲያን ነበር፤ እሱም በመስቀል ላይ ሞቷል»
ፍሬደሪክ ኒቼ
«በዚህ በማይታወቀው ድብቅና ውስብስብ አለም ውስጥ የምንኖር ነጻ ነፍሶች፣ በሴራው፣ በተንኮሉ፣ በሰላ ብልጠቱ አዝዞ አናዝዞ በሚገዛው ስርአት ውስጥ የምንኖር እምቢ ባዮች፤ አንዳንዴ ስርአቱን ለመውደድ አንዳንዴም ለመፍራት እንገደዳለን፡፡ ይህን ከእይታ ውጪ የሆነ ስልና ውስብስብ ስርአት አሻፈረኝ የማለት አቅም እንኳ እንዳይኖረን የፊጥኝ ታስረናል፡፡ ሁላችን ከተጣለብን ሀላፊነትና ግዴታ እንዳናፈገፍግ ተደርገን ተጠፍረናል፡፡ በርግጥ አንዳንዴ እጅና እግራችንን የጠፈረንን ካቴና፣ የአንገታችንን ካራ ተሸክመን ብንቦርቅም ብዙውን ጊዜ በዚህ የእጣ-ፈንታችን አምባገነን ስርአት ላይ ጥርሳችንን እንነክሳለን፣ ግንባራችንን እንቋጥራለን፡፡ እናም ያሻንን አድርገን ያሻንን እንሆናለን፡፡ ተርታውም ተመልካች ሀላፊነት ከማይሰማቸው ስርአት አልበኞት ይመድበናል፡፡ በርግጥ ሁሌም ቢሆን የተቺዎች ውግዘት ድርሻችን ነው፡፡
«እናንተ ነጻ ነፍሶች ምናልባት ለስርአቱ ያለን ታማኝነት፣ የከንቱነታችን ስር እንዳይሆን?! ምናልባት ስርአቱ የጣለብን የስነ ምግባር ቀምበር የደካማ ጎናችን፣ የድድብናችን ምንጭ እንዳይሆን?! ምናልባት ለስርአቱ ባለን ታማኝነት ለዛ ቢስ፣ ደባሪ ፍጡራን እየሆንን እንዳይሆን - በዚህች አጭር ህይወት፣ እፍኝ ለማትሞላ እድሜ ደባሪ ሆኖ መገኘት አያሳስብምን?»
እ.ኤ.አ ከ844 - 1900ዓ.ም የኖረው አወዛጋቢው ፈላስፋ ፍሬደሪክ ኒቼ የዘመኑ የግብረ ገብ አስተምህሮ ከእውነተኛው ግብረ ገብነት ፍጹም ተቃራኒ እንደሆነ ይገልጻል፡፡
ምክንያቱም ማንኛውም አይነት የስነ ምግባር አስተምህሮ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር የሚጣጣም እንጂ በፍጹም የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡ ኒቼ የሰው ልጅ ተፈጥሮውን፣ ደመ ነፍሱንና ውስጣዊ ፍላጎቱን መሰረት እድርጎ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚዋትት ፍጡር ነው በሚለው የአርተር ሾፐንሀወር አስተሳሰብ ይስማማል፡፡ ይሁን እንጂ ከሾፐንሀወር የጸለምተኝነት ፍልስፍና በተቃራኒ ኒቼ ውስጣዊ ፍላጎታችንን ከማጥፋት ወይም አንዳንድ የዘመኑ አስተምህሮቶች እንደሚሰብኩት ከማፈን ይልቅ ሙሉ በሙሉ በማሟላት ስኬትና እርካታ መጎናጸፍ ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡
የኒቼ ልእለ ሰብ (Super human) የአስተሳሰብ ምጥቀትን ከአካላዊ ልእልና ጋር አቀናጅቶ የተላበሰ ሰው ነው፡፡ እስካሁን ከዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው ባይኖርም ኒቼ ከመጪው ትውልድ ይከሰታል ብሎ ያምናል፡፡ እስካሁን በእጅጉ ሀያል የሆኑ ታላላቅ ሰዎች ቢከሰቱም ልእለ ሰብ ከመባል የሚያጎሏቸው ባህሪያት ነበሩ፡፡ የኒቼ የልእለ ስብ እሳቤ የቄሳርን ታላቅነትና ግርማዊነት ከእየሱስ የሞራል ምጥቀት ጋር አቀናጅቶ መላበስ ነው፡፡
ሰው ከዝንጀሮዎች ሁሉ የላቀ እንደመሆኑ የኒቼ ልእለ ሰብም ከሰዎች ሁሉ በደረጃ የላቀ ልዩ ፍጡር ነው፡፡ በአስተሳሰብ ከሁሉ የላቀ በመሆኑ ይቅርታና ምህረት አይፈልግም፤ ማንኛውንም ስህተት መተውና መርሳት ይችላል፡፡ በመንፈስ እንደ እየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ለጠላቶቹ ምህረት እየጠየቀ ነው፡፡
ፍሬደሪክ ኒቼ እየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የሆነ የክርስትና ተምሳሌት እንደነበር አበክሮ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ክርስቲያኖች ይህን ፍጹም ተምሳሌት መከተል ተስኗቸዋል፡፡ በመሆኑም በኒቼ አባባል «አንድ ክርስቲያን ነበር፤ እሱም በመስቀል ላይ ሞቷል» ይላል።
ኒቼ በአምላክ መኖር ባያምንም በአምላክ እናምናለን እያሉ በሀጢያት በሚጎድፉት ላይ የሚያወርደው ትችት በእጅጉ ስልና ገደበ ሰፊ ነበር፡፡
@melos3
@melos3
ፈገግታ ይሸውደኛል። ሳቅ ድብን አድ'ርጎ ነው የሚያታልለኝ። ጎበዝ ሌባ ተኮሳትሮ አይሰርቀኝም፤ ስቆ ግን ከኪሴ ፍራንክ ወስዶ ሰርቀኸኝ ነው ብሎ ያሳምነኛል። እስከዛሬ ድረስ መንገዴ ላይ ያስከፋኝ ሁሉ ፈገግታውን ጋሻ አድርጎ ነው የወረደብኝ። የጎዳኝ ሁሉ ከጀርባዬ በጸጥታ ሰንዝሮ ነው የተመለሰብኝ።
፧
ፈገግታ ስስ ጎኔ ነው!
፧
ቤተሰቦቼ ቀጥተኛና ግልፅ ነበሩ ፥ አጥፍቼ የሚፈግግልኝ አልነበረም። ወድቄ ፈገግ ብሎ ያባበለኝን፣ ጦስህን ይውሰድ ያለኝን አላውቅም። እኛ ቤት ስሜት ፊት ለፊት ነው ፥ እውነት በlogic ይፈተናል። ስሜት በስሌት ነው value የሚሰጠው። ቅሬታ ፊት ለፊት ነው የሚነበበው ፥ ፍቅርም ሆነ ቁጣ ከልብ እስከ አፍ በጉዞው መንገድ አይቀይርም።
፧
እናቴና አባቴ ተደባብረው ህመማቸውን በፈገግታ ሲሸፍኑ አላየሁም ፤ ወንድሞቼ ቃልን በፈገግታ ጠቅልለው መቀበል ካለብኝ እውነት አላሳቱኝም። እኛ ቤት ላይ ሰው የሚታገል ከሆነ ከፊታችን ይቆማል ፥ ከሚሰማው ስሜት ርቆ አይሄድም ከሄደም አይመለስም። ስለዚህ ፈገግ እያለ የሚታገል ሰው ይጥለኛል። ፈገግታ ካየሁ ትግል የምር አይመስለኝም።
፧
አቅፎ ሰላም የሚለኝ ከልቡ የሚወደኝ ይመስለኛል፤ በልቦናው መጥፎ የሚያስብልኝ ሰው ጥርሱን አሳይቶ አጥብቆ የሚያቅፈኝ መሆኑ አይገባኝም ነበር።
፧
አይወደኝም ያልኩት ሰው ቀርቦ በልስላሴ ካወራኝ ጦርና ጋሻዬን እጥላለሁ። የዋህ ሆኜ ይሆን እንጃ ስልት ያለው ጥላቻ አይገባኝም።
አባቴ አጥፍቼ እንዳይመታኝ ተማፅኜው ይቅር ብሎኝ አረሳስቶ መቶኝ አያውቅም። ለዛም ነው መሰለኝ የተጣላሁት ሰው ፈገግ ብሎ ካወራኝ ይቅር ብሎኛል ብዬ የማስበው።
፧
ነገር ግን ፈገግ እያሉ ክፋት የሚጎነጎኑ ሰዎች ሳይጥሉኝ ቀርተው አያውቁም። እኔ የፊት ሰው ነኝ፤ እነሱ ደሞ ከፈገግታ ጀርባ የሚኖሩ ናቸው። በርግጥ የሰው ልጅ መሸነፊያ ስፍራ አያጣም ፤ አንዳንዶቻችን ግን ያ ስፍራ ፈገግታ መሆኑን ዘግይተን እንማራለን።
©ezra kassahun
22/06/18
@melos3
@melos3
❝ሀብታምን ለማስከፋት ውሸት ንገረው፤ ደሀን ለማስከፋት ደሞ እውነት ንገረው❞ ይል ነበር አባቴ ከመሞቱ በፊት። በሰዓቱ ለምን እንደዛ እንዳለ ባላውቅም ይህ ሀሳብ ግን ሰውን በንብረቱ ሳይሆን በውስጣዊ መመኪያው የሚመዘን ጥልቅ ፍልስፍና ይመስለኛል።
ምክንያቱም ሀብታም በያዘው ላይ የተመሠረተ እርግጠኝነት ይኖረዋል፤ ውሸት ግን ያን እርግጠኝነት በዝምታ ያናውጠዋል(ተደጋግሞ የተነገረ ውሸት በዝምታ ሲዋብ ለሀቅ የቀረበ እውነት ይሆናል)። ይህ ምን ማለት ነው፥ ሀብት እንደ ሀብት ለመቆየት በእውነታ አይመራም። እውነትንም አይፈጥርም፤ ለእውነት መከላከያ ብቻ ነው።
፧
ደሀ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ተስፋው የህይወቱ መርፌ ነው። እውነት ሲመጣ ያ መርፌ ይወጋል፥ መዛከርን ቀጥታ ይቆርጣል። እንደ መስታወት ይሰበራል። ሎጂኩ ግልፅ ነው፤ ሰውን የሚያስከፋው ነገር የሚሰማው ቃል አይደለም፣ የሚመታው የልቡን መሠረት፤ የመሻቱን ውጤት ነው። የህይወት ዋናው ነጥብ እርሱ ይመስለኛል! የሆነው ሆኖ መከፋት overrated ነው🙁and የልብ መሠረት ከቃል ይበልጣል‼️
፧
«ሰው ሁሉ የሚያምነው ነገር በተነካ ጊዜ ነው በእውነት የሚቆጣው።»
©ezra kassahun
13/6/18
@melos3
@melos3
