cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቅድሚያ ለተውሒድ/ተከታታይ ደርሶች /

ተከታታይ ደርሶች በሰለፊይ ኡስታዞች የሚለቀቅበት ቻናል ===========♣♣♣♣♣♣============

Больше
Рекламные посты
257
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ይህ Hafu graphics design ቻናል ነው ። ያጀማዐ ለግሩፕ ወይም ደግሞ ለቻናልዎ እንደዚህ አይነት ያማሩ ፕሮፋይሎችን ማሰራት ይፈልጋሉ ? መልሱ አዎ ከሆነ በ @Abu_teymiyah ያናግሩኝ በፈለጉት መልኩ ባማረ ሁኔታ እንሰራለን። من أخيكم عبدالحفيظ - t.me/hafugraphics - t.me/hafugraphics
Показать все...
ወቅታዊ ማስታወሻ ~ በሰሞንኛው የነሳራዎች ጉዳይ አንዳንድ ሙስሊሞች ብሄራቸውንና የፖለቲካ አሰላለፋቸውን ተከትለው ገብተው እያቦኩ ነው። ወንድሜ ይሄ ጉዳይ አ ደ ገ ኛ ነው። እምነትን ሊነካ ስለሚችል ጥንቃቄ እናድርግ። እንዴት ነው አንድ ሙስሊም "#ቅድስት ቤ/ክ" እያለ የሚፅፈው? እንዴት ነው" ብፁእ አባታችን አቡነ ..." የሚለው? ማነው ብፁኡ አባትህ? በተረፈ "ለነባሩ" ሲኖዶስ ድጋፍ የሚሰጡ አንዳንድ ሙስሊሞችን ምክንያት በማድረግ "የሰሜን ሙስሊሞች" እያሉ በጅምላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን የሚያ ጠ ለሹ ፀሐፊዎችን እያየሁ ነው። ይሄ የለየለት ብ* ል * ግና ነው። ከአማራ ጋር ባላቸው እልህ "ለአዲሱ ሲኖዶስ" ድጋፍ እየሰጡ ያሉት ደቡባውያን ሙስሊሞች'ኮ ቁጥራቸው ከሰሜናውያኑ የሚያንስ አይደለም። እነዚህን መነሻ በማድረግ ድፍን የደቡብ ኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ብንወነጅል ልክ ይሆናል? ችግር እንኳ ቢኖር መማማር እንጂ ብሄርና አቅጣጫን ተከትሎ መፈራረጅ ማንንም አይጠቅምም። ፖለቲከኞች አበጀን ብለው ስንጥቃት እንዳይፈጥሩ እድል አንስጣቸው። በየትም ቦታ ያለው ሙስሊም አንዱ ለሌላው ጋሻውና ጌጡ እንጂ ጠ ላ ቱ አይደለም። ደግሞም ለብዙ ክ/ዘመናት የወረደበትን መአት ተቋቁሞ ዛሬ ላይ የደረሰን የሰሜን ሙስሊም የእውነት ችግር ቢኖር እንኳ (ያውም የተለየ ችግር ከኖረ) ከጎኑ መቆም እንጂ ማ ጠ ል ሸት አይገባም። እውነቱን እናውራ ከተባለ የሰሜኑ ሙስሊም ዛሬም ድረስ ከሰሜኑ ጭ ቆ ናና ጥ ቃ ት አልወጣም። በተሰደደበት አንዳንድ የደቡብ አካባቢ ደግሞ እጅግ ዘ ግ ናኝ የሆነ ጭ * ፍ * ጨ * ፋና መፈናቀል እያስተናገደ ነው። በዚህ መከራው ላይ ብሄርና ፖለቲካ ሳይለይ ከጎኑ የሚቆሙት ግን ከጥቂትም ያነሱ ናቸው። ስለዚህ ከጅምላ ፍረጃ ይልቅ በመከራው መተባበር ነው የሚሻለው። ወንድሜ ሰሜን ደቡብ ሳይል ሁላችንም ታመናል። አንዳችን ከሌላው የምንሻልበት የተሻለ ቁመና ላይ አይደለንም። ችግራችን የራሳችንን በሽታ እንዳናይ፣ ሌሎችን ደግሞ በቀላል እንድንፈርጅ የሚያደርግ የዘረ ኝነት በሽታ ተጠናውቶናል። መሆን ያለበት ጥንቃቄ እንድናደርግ መመካከር ብቻ ነው። የሚመለከተንን ነገር እንለይ። በሆነ መነሻ ይመለከተኛል የሚል ካለም የራሱን የሸሪዐ ግንዛቤ መጠን፣ በግራም በቀኝም ያለዉን የፖለቲካ ትኩሳትና መዘዙን በሚገባ ሳያጤን ምንም ሊናገር አይገባውም። አቅም አለኝ የሚል ካለም የቃላት አጠቃቀሙንም ሊያስተውል ይገባል። ከዚህ ይልቅ እኛን የሚመለከተን * በዚህ ጊዜ እንኳ ኢስላምንና ሙስሊሞችን ከመንካት ላልታቀቡት እንደ ዲያቆን ዘመድኩን እና ምህረታብ ላሉ ነውረ - ኖች ምላሽ መስጠት ነው። ከእምነታችን እንከላከል። ብዙ ሚሊዮኖች ናቸው የነሱን ፀያፍ ስራ የሚከታተሉት። * ሰሞኑን ወለጋ አኖ ላይ ብዙ ሙስሊሞች ተጨፍጭፈዋል። አጀንዳ ያደረጋቸው ግን የለም። በወሎ ኦሮሚያ ብሄረሰብ ዞንም ከባድ ጥቃት ሙስሊሞች ላይ ደርሷል። ብንችል ለነሱ ድምፅ እንሁን። ከወለጋ ተፈናቅለው ሰሜን ሸዋና ወሎ መጠለያ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ብዙ ናቸው። "ምን አደረግንላቸው?" እንበል። በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ላይ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውም የሚታወቅ ነው። በዚህ ላይ እንስራ። * በመጅሊሱ ጉዳይ ያኮረፉ አሕባሾች ሰሞንኛውን ክስተት ሊጠቀሙበት እየሞከሩ እንደሆነ እናስተውል። ከፊሎቹ ለሲኖዶሱ ድጋፍ እየሰጡ ያሉት በዚህ ስሌት ነው። * በተረፈ በራሳችን ጉዳይ እንጠመድ። የራሳችንን ጉዳይ ጨርሰን ነው በዚህ መጠን ሚዲያው ሁሉ ስለዚህ የሚያወራው? አልፈን እኛም የምንጠመደው? እግር ከወርች ተብትቦ የያዘ ብዙ ችግር አለብን። በሱ ላይ እንስራ። እንማማር። እናስተምር። እናሰራጭ። እንተጋገዝ። እናስተባብር። የሚመለከተን ይሄ ነው። = ኢብኑ ሙነወር የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ሊንካችንን ሸር በማድረግ ቻናላችንን ስላስተዋወቁ እናመሰግናለን። እባክዎ የህክምናና ህክምና ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ብቻ ይጠይቁን! ላገልግሎታችን ማስከፈል ስላልጀመርን የነፃ ማማከር እገልግሎት መጠቀም ይችላሉ። https://t.me/Abufewzanconsultancy
Показать все...
ዶ/ር አቡ ፈውዛን ሁሉም አይነት ህክምና ማማከር አገልግሎት

ማንኛውንም አይነት የህክምና ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን፤ ለማንኛውም የህክምና ችግር ምክር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ፃፉ (DM)። @DrAbufewzan

የነብዩላህ ዩሱፍ ወንድሞች ታሪክ 〰〰〰〰〰♦️♦️〰〰〰〰〰 ነብዩላህ ዩሱፍ ከሌሎች ወንድሞቹ ይልቅ ነብዩላህ ያእቁብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነበር። ይህንን ሁኔታ እንቅልፍ የነሳቸው ወንድሞቹ በቅናት መንፈስ ተነሳስተው ዩሱፍን ለመግደል አሰቡ። ነገር ግን መገደሉ አላህ አልፈቀደውምና በጉድጓድ ሊጥሉት ወሰኑ። ዩሱፍን ከአባቱ ያእቁብ ለመነጠል ብዙ አሴሩ። በመጨረሻም እናጫውተው እናዝናናው ብለው ከአባቱ ነጥለው የጥፋት መረባቸው ውስጥ አስገቡት። እንዲህም አሉ፦ «ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ - 12)» በዚያ በጨቅላ እድሜው መሸከም ከሚችለው በላይ በደል አሸከሙት። ያደረጉትን ካደረጉ በኋላ አባታቸው ያእቆብን ለማሳመን የውሸት መላ ዘየዱ። ያሳምንልናል ብለው ያሰቡትን ሁሉ አደረጉ። «አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ - 16)» ይህንን የውሸት ለቅሶ እውነት ለማስመሰል ሌላ ውሸት መፈብረክ ቀጠሉ። «አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡ ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡ አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም አሉ፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ - 17)» አባታችን ሆይ እውነተኞች ነን እመነን ብለው ድርቅ አሉ። ይህም አልበቃ ብሏቸው ሌላ የውሸት ጥግ ሄዱ። «በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ - 18)»። ይህ ሁሉ ለቅሶ፣ ይህ ሁሉ ውሸት፣ ይህ ሁሉ ስም ማጥፋት ውስጥ የገቡት የፈፀሙትን በደልና ያሉበትን ውሸት እውነት ለማስመሰል ነው። ነገር ግን ውሸት የፈለገ ቢገን፣ ብዙዎችን ቢያሳስትም፣ ለጊዜው እውነት መስሎ ቢታይም መወገዱ አይቀርም። እውነት መቸም ቢሆን ተዳፍኖ አይቀርም አንድ ቀን ፈንቅሎ መውጣቱ አይቀርም። በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡ (ሱረቱ አል-ኢስራእ - 81)» በዘመናችንም ይህንን የዩሱፍ ወንድሞች ታሪክ የሚያስታውሱ ነገራቶች በብዛት ይከሰታሉ። ተበዳይ እያለ በዳይ የሚጮህበትና በውሸት እምቦ የሰዎችን ልብ ለመስረቅ የሚደረጉ ጥረቶች እጅግ ብዙ ናቸው። የውሸቱን እምባ እውነት ለማስመሰል የሚቀጠፋ ቅጥፈቶችም ይሰማሉ። እውነቱና ውሸቱ እስኪለይ ጊዜ ቢፈጅም አንድ ቀን መታወቁ ግን አይቀርም። ካልሆነም አላህ ሁሉን ያያል። ሁሉንም ይሰማል። የፍርዱ ቀን እያንዳንዱ የእጁን ያገኛል። http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Показать все...
በስሞቻችሁ እንደዚህ የሚያምሩ ምስሎችን ማሰራት ከፈለጉ በ @Abu_teymiyah ያናግሩኝ ተጨማሪ ለፕሮፋይል የሚሆኑ ምስሎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ T.me/hafugraphics T.me/hafugraphics T.me/hafugraphics this is our lovely channel
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሸሪዓ ትምህርት እድል ለህፃን መስዑድ ወድ እና የተከበራቹህ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች መስዑድ የተባለን ታዳጊ ህፃን  መርከዝ አቡ ሙሳ የቁርአን ሂፍዝ የሸሪዓ እውቀቶች ማእከል ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ቁርአን ለማስሀፈዝ እና መሰረታዊ የሸረዓ እውቀቶችን ለማስተማር ስለሚፈልግ የልጁን ቤተሰቦች በማናገርም ሆነ ከኛ ጋር በማገናኘት የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታበረከት በአላህ ስም እንጠይቃለን ። የተቋሙ አድራሻ 0913939993 or 0930547776 የማእከሉ የቴሌግራም አድራሻ https://t.me/Kurantejwid
Показать все...
ተይሚያህ የቁርአን መማሪያ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ ጀምረናል =====================   መርከዝ ተይሚያህ ለመጀመሪያ ዙር በኦንላይን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን የጨረሰ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች መማር የምትፈልጉ ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑንን በደስታ እንገልፃለን። በተጨማሪም ========== መመዝገብ ለምትፈልጉ ወንድም እና እህቶች በአጠቃላይ ከታች በተቀመጠው ሊንክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። የሚሰጡ ትምህርቶች =============== ✔ቃዒደቱኑራኒያ ለጀማሪዎች ✔ቁርኣን ነዘር ✔ ቁርአን ሂፍዝ ✔ የተጅዊድ ትምህርት ✔ ሙኽተሶር ኪታቦች ለመመዝገብ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን 👇👇 ◎ t.me/abu_reeemt.me/abu_teymiyah በኢሞ ለማናገር - https://call.imo.im/abu_rumeysa ትምህርቱ የሚሰጠው  ◍ በቴሌግራም live ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁ. ✔️ 0983840108 የምንቀበለው ተማሪ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይወዝገቡ የቴሌግራም ግሩፕ👇👇👇 https://t.me/umul_kitab https://t.me/umul_kitab https://t.me/umul_kitab https://t.me/umul_kitab
Показать все...
أبو ريم

الم تعلم أن السيف ينقص قدره إذا قيل أن السيف أمضى من العصى

ሳዑዲና ሃሎዊን ~ ሰሞኑን በሳዑዲ ሪያድ ውስጥ ሃሎዊን የሚያከብሩ ሰዎች መታየታቸውን ተከትሎ ጫጫታ እያየን ነው። የሳዑዲ መንግስት ላይ፣ ከዚያም በሱ በኩል አቆራርጦ ዑለማዎቹ ላይ፣ አሁን ካሉትም አልፎ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ላይ የሚዘምቱ ሰዎችን በተደጋጋሚ አይቻለሁ። የሆነ ነገር በለጠፍኩ ቁጥር ደጋግመው እየመጡ 'ኮሜንት' ላይ ብዙ ነገር የሚለቀልቁም ገጥመውኛል። "ስለዚህ ግን ትንፍሽ አትሉም" ይላሉ። ብዙዎቹ ከሁኔታቸው መውሊድን በማውገዛችን ቂም ያረገዙ እንደሆኑ ያስታውቃሉ። ሃሎዊን ምንድነው? - የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ስመለከት ያገኘሁት እንዲህ የሚል ነው፦ Halloween "የሁሉም ቅዱሳን ቀን" ማለት ሲሆን በአብዛኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ ሃገራት የሚከበር በዓል ነው፡፡ የሚከበረውም በፈረንጆች October 31 ነው። ህፃናት የተለዩ አስፈሪ ልብሶችን በመልበስ በየቤቱ እየዞሩ ከረሜላና መሰል ነገሮችን ይጠይቃሉ። ምንጭ፦ http://en.wiktionary.org/wiki/Halloween መነሻው ኬልቲክ አካባቢ ቢሆንም አሜሪካ ከገባ በኋላ ወደሌሎች ሃገራት ተሰራጭቷል። ከህፃናት አልሮ በ "አዋቂዎችም" ይከበራል። የሰይጣን አምልኮ ነው እያሉ የፃፉ አይቻለሁ። ሊሆን ይችላል። እኔ ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም። በዓሉ መነሻው የጣዖታውያን ልማድ እንደሆነ፣ ከዚያም ከፊል ክርስቲያኖችና የሁዶች እንደሚያከብሩት ከክርስቲያኖችና የሁዶች ውስጥ እራሱ አጥብቀው የሚያወግዙት እንዳሉ አንብቤያለሁ። ሃሎዊን በኢስላም ~ በኢስላም የትኛውንም የጃሂሊያ (ኢስላማዊ ያልሆነ) ስርአት በአል ማክበር አይፈቀድም። ነብያችን ﷺ የመዲና ሰዎች ሲያከብሯቸው የነበሩ የፋርስ ዞራስቲያኒዝም ሃይማኖት በዓላትን መከልከላቸው የሚታወቅ ነው። በተጨማሪም "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው" ብለዋል። [አቡ ዳውድ፡ 4031] ይሄ እጅግ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው። ሃሎዊን በሳዑዲ ~ ሳዑዲ ውስጥ እስከ ቅርብ አመታት ድረስ የሃሎዊን በዓል አልነበረም። የሚፈልግ ስለሌለ ሳይሆን በመንግስት ስለተከለከለ ነበር። የክልከላውን መላላት ወይም መነሳትን ተከትሎ ግን - በአንድ ዌብሳይት ላይ እንዳየሁት - ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየተከበረ ነው። ይሄ በጣም ዘግናኝ ጥፋት ነው። ጥፋቱ በሳዑዲ ስለተፈፀመ የሚቀየር ብይን የለም። ማንም ለዚህ ወግኖ የሚከራከርም የለም። ከኖረም ባይፈፅመው እንኳ የጥፋቱ አካል ነው። ለኢኽዋኖ - አሕባሽ መንጋዎች! ~ ለብዙኛ ጊዜ ደጋግሜ የምናገረው ነገር ቢኖር ሳዑዲ ውስጥ ከዚህም ውጭ ብዙ ጥፋቶች እንዳሉ እናውቃለን። አንዳንድ ቂላቂሎች እንደሚያስቡት ሳዑዲን ፍፁም አድርገን የምንስል አይደለንም። ግን እናንተ የመጮሁንም የማስጨሁንም ሞራል ከየት አገኛችሁት? ምዬ እናገራለሁ ከአብዛኛቻችሁ ጩኸት ጀርባ ያለው ለኢስላም መቆርቆር አይደለም። የጩኸታችሁ ቀዳሚ መንስኤ ቡድናዊ ልዩነት ነው። ይሄ በዓል እኮ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎ ጀምሮ ቱርክ ውስጥ ይከበራል? በዚህ መልኩ አስጩሃችሁት ታውቃላችሁ? ለምን? አንዱ ሳዑዲን በዚህ ሰበብ እያብጠለጠለ በለቀለቀበት ፅሑፍ ላይ ኳታርን ሲያወድስ አይቻለሁ። እስኪ Halloween in Qatar ብለህ ጉግል ላይ ፈልግ። የእውነት ለዲን መቆርቆር ከሆነ ምክንያታችሁ ምነው ስለ ኳታር እስከዛሬ አልጮሃችሁም?! እነዚህ አካላት በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ፊት የሚያሳዩ፣ በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ስፍር የሚሰፍሩ፣ ሃይማኖትን ለፖለቲካዊ ንግድ የሚጠቀሙ ቆሻ - ሻ ፍጥረቶች ናቸው። ሲጀመር የኢኽዋን አንጃ በምን መለኪያ ነው ከሳዑዲ መንግስት የሚሻለው? የቡድኑ መሪ ዑመር ቲልሚሳኒይ ገንዘብ እየከፈልኩ የፈረንጅ ዳንስ ተምሬያለሁ፣ ሲኒማ ለማየት ብዬ ሁለት ሶላቶችን በአንድ ላይ ጀምዕ እያደረግኩ እሰግድ ነበር አላለም? ቀርዷዊ ነፃነትን መተግበር ከሸሪዐ ይቀድማል አላለም? የቡድኑ መስራች ሐሰነል በናና ዩሱፍ አልቀረዳዊ በተጨባጭ ሐዲሥ የተረጋገጠውን የመህዲን መምጣት አላስተባበሉም? መውዱዲ የደጃልን መምጣት አላስተባበለም? ቱራቢ በርካታ መረጃዎችን ረግጦ የቀብር ቅጣት የሚባል የለም፣ ነኪርና ሙንከር የሚባል የለም አላለም? ነብያት መዕሱም አይደሉም አላለም? የዒሳን ዳግም መምጣት አላስተባበለም? ቀረዳዊና ሙርሲ የክህደት ቁንጮ ለሆኑ ጳጳሶች አላህ እንዲምራቸው ዱዓ አላደረጉም? ሰይድ ቁጥብ ከሶሐቦች አልፎ ነቢያትን አልጎነተለም? ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከኢስላም እያስወጣ አልፃፈም? ሰዕድ አልከታቲኒ በግብፅ ምርጫ ብናሸንፍ አስካሪ መጠጥ አንከለክልም፣ የብልግና ድረ ገፆችን አንዘጋም አላለም? እስኪ ምናችሁ ተሽሎ ነው ምላሳችሁን የምታሾሉት? የእውነት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ተቆርቁራችሁ ከሆነ ይሄንን እያንሸዋረረ የሚያሳያችሁን ቡድናዊ መነፅር አሸቀንጥራችሁ ጣሉና በስርአት አስተምሩ። ኢስላም በሚያስተምረው መልኩ ከሃሎዊንም፣ ከቫሌንታይኑም፣ ብብሄራዊ በአላትም፣ ከኢሬቻም፣ ከገናም፣ ከመስቀልም ፣ ከመውሊድም፣ ወዘተ አስጠንቅቁ። ከፊሎቻችሁኮ ለመስቀል ስታፀዱ እናውቃችኋለን! ከፊሎቻችሁኮ ኢሬቻን ለማውገዝ የምትሽኮረመሙ ናችሁ። የምን ማስመሰል ነው? እምቢ ብላችሁ ስለ ሳዑዲ ብቻ ከሆነ ማውራት የምትፈልጉት ቢያንስ በሌላ ሃገር የሌለ ጥፋት እየጠበቃችሁ ብትጮሁ ይሻላችኋል! ያለበለዚያ ግን ጧት ማታ ሙገሳ በምትሰፈሩላቸው ሃገራት ውስጥ ያለው ሲወጣ አስመሳይነታችሁ ይጋለጣል። በርግጥ ለኛም ቢሆን የሳዑዲ ይለያል! ምክንያታችን ግን እንደናንተ የገነፈለ ጥላቻ አይደለም። አዎ ከሌሎቹ በበለጠ ሳዑዲ ላይ ይሄ መሆኑ ያመናል። ተሽለው መገኘት እንዳለባቸው ስለምናምን። ለሃገሪቱ ካለን መቆርቆር። የኢስላምና የሙስሊሞች ምልክት (symbol) በመሆኗ። የአሕባሸና የኢኽዋን ጩኸት ግን "ከፍየሏ በላይ ነው።" የተጠራቀመ ቂም ስላላቸው አጋጣሚ እየጠበቁ ከሳዑዲ መንግስት አልፈው ዑለማዎች ላይ ዘመቻ ለመክፈት ነው አድብተው የሚጠብቁት። የሙዚቃ ኮንሰርት ሲካሄድ ልክ ዑለማዎቹ የፈቀዱ ይመስል እነሱም ላይ ጭምር ይዘምታሉ። ልክ በግልፅ ሙዚቃ የሚፈቅደውን ቀረዷዊን እንደማይንቆለጳጵሱ። ልክ ቱርክና ኳታር የሙዚቃ ድግስ እንደሌለ። ይሄው በቅርቡ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የሙዚቃ ድግስ እየተዘጋጀ እንደሆነ አልጀዚራ እየዘገበ ነው። ሪያድ ሲሆን እንደምታወግዙት ታወግዙታላችሁ? አታደርጉትም። ምክንያቱም መስፈሪያችሁ የሚታወቅ ነው። حصانة إخوانية . ሁኔታችሁን እያየሁ ልመለስ እችላለሁ፣ ኢን ሻአ'ላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

እናቴ...! ↪️ አዲስ ሙሓደራ 🎙በ አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን 🕌በኢማሙ ማሊክ መስጂድ አሶሳ t.me/abu_fewzan_abdu_shikur t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
Показать все...
እናቴ...!.mp32.63 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
‹‹ልጆቻችንን በማለዳ ማን እንደወሰደብን አናውቅም፡፡ እባካችሁ ልጆቻችንን አፋልጉን፡፡›› ወላጆች (Please SHARE! Spread it.) ********** በፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ሁለት ሕጻናት አስማ ናስር እና ሐሰን ናስር ይባላሉ፡፡ ወንድምና እህት ናቸው፡፡ አስማ ዕድሜዋ 13 ሲኾን፣ ሐሰን የ10 ዓመት ሕጻን ነው፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የተወለዱት እነዚህ ሕጻናት፣ ከወላጆቻቸው ጋር በቅርቡ ነው ወደ ኢትዮጵያ ተባረው የመጡት፡፡ በደንብ መናገር የሚችሉት ቋንቋም አረብኛ ነው፡፡ ትናንት ሐሙስ ማለዳ 11፡00 ገደማ አሸዋ ሜዳ፣ አብድ ኖኖ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ጀርባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ወላጅ አባታቸው አቶ ናስር ለሱብሒ ሶላት ወደ መስጊድ ሲወጣ በመኝታ ክፍላቸው ነበሩ፡፡ ነገር ግን አቶ ናስር ከሶላት ሲመለስ ሁለቱን ሕጻናት ልጆቹን ና ለጊዜው ፎቶዋ ያልተገኘ አብራቸው የምታድግ ፈትሂያ ኑራ የተባለች የ11 ዓመት ሕጻን በቤቱ ውስጥ አጥቷቸዋል፡፡ እናታቸው ተኝታ ስለነበር፣ ልጆቹ ወዴት እንደሄዱ፣ ምን እንዳገኛቸው፣ ማን እንደወሰዳቸው ያወቀችው ነገር የለም፡፡ እናም፣ "እባካችሁ ወገኖቻችን፣ ልጆቻችንን አፋልጉን" ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል፡፡ የአባታቸው ስልክ ቁጥር 0960-04 37 67 ነው። *** እባካችሁ ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ ሦስቱ ሕጻናት እንዲገኙ እንተባበር፡፡
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.