cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ትንሳኤ ዘኢትኤል መማሪያ

የአባቶቻችን እና የሀገራችን ታሪክና ጥበብ ግዕዝን, ስለጥንት ነገስታት ታሪክ፣ ስለዕፆች፣ መድሀኒቶች፣ መሰውሮች፣ የደመና ጥበብ ፣ቅርሶች፣ጥንታዊ የብራና መፅሐፍት፣ስነ ፈለክ ፣አክሲማሮስ፣ራዕየ ሳቤላ፣መፅሐፈ ጅማትርያ ፣መፅሐፈ ፓዝዮን፣መፅሐፈ ፀሐይ፣መፅሐፈ ልሳን፣መፅሐፈ ጥበብ፣የመላእክት ቋንቋ ወዘተ ... ለጓደኛ ያስተላልፉ ኢትኤልን ስለመረጣቹ አመሰግናለሁ ይቆየን.. 👳‍♂

Больше
Рекламные посты
6 700
Подписчики
-324 часа
-197 дней
-8130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሰላም ለሁላችሁም ይሁን ውድ የትንሳኤ ዘኢትኤል መማማሪያ ተከታታዮች ወዳጆቼ የማከብራችሁ እንደምን አላችሁ ብርሀነ ልደቱን በሰላም አሳልፈን ፆሙን በበረከት በረድኤት ጎብኝቶን ለብርሀነ ትንሳኤው ደግሞ እንደቸርነቱ አድርሶናልና የአምላካችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን በእውነት እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በአሉ የሰላም የጤና የመደጋገፍ የመረዳዳት ይሁንላችሁ ።በፆሙም ከፆሙም ውጪ ቅር የተሰኛችሁብኝ ያስቀየምኋችሁ ሁሉ ይቅር እንድትሉኝ እናንተም ያስቀየማችሁትን ይቅር በሉ ያጠፋውትን ክሳለሁ በፀሎት አስቡኝ እግዚአብሔር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
Показать все...
ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ። “ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)
Показать все...
ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ  የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ /2/  የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል  የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/ አዝ ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለእኛ  መሰቀል አሸክመው አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ/2/  አዝ እጅና እግርህን በብረት ተመታ የዓለም ጌታ  የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/ አዝ ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው  ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/ አዝ  በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል  ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/ አዝ ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ  አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/  💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показать все...
ለሁሉም ሼር ያድርጉ 🔺
ንሴብሖ ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር /2/  ስቡሐ ዘተሰብሐ /4  እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን /2/  ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/  ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር ጉልበታችን ቢዝል መከራም ቢበዛ ሃይላችን ጌታ ነው የዓለም ቤዛ ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆ እንደጠጣነው ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግነው ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ ሃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показать все...
ለሁሉም ሼር ያድርጉ 🔺
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ #አዝ ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ ማርና ወተትን ለሚመግበው ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው #አዝ አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም #አዝ እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ ሊቀ-መዘምራን ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показать все...
​​​​👉 ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30) 👉 ሰባቱ ተዐምራት ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት 1. ፀሐይ ጨልሟል 2. ጨረቃ ደም ሆነ 3. ከዋክብት ረገፉ 4. ዐለቶች ተሠነጠቁ 5. መቃብራት ተከፈቱ 6. ሙታን ተነሡ 7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ 👉 አምስቱ ችንካሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች 1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት 4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት 5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показать все...