የጥበብ እመቤት 📜
Открыть в Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
271
Подписчики
-124 часа
+77 дней
+15230 день
Архив постов
272
“Courage is rightly esteemed the first of human qualities, because, as has been said, 'it is the quality which guarantees all others.'”
— Winston Churchill
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አንዳንዴ ስማችንን ብቻ ማወቅ ያለባቸው ሰዎች ሚስጥራችንን ያውቃሉ። ይህንን ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በህይወታችን ውስጥ ማን ምን ያህል እንዲያውቅ መፍቀድ እንዳለብን ድንበር ማበጀት ትልቅ ብልሃት ነው። ሁሉንም ነገር በጊዜው እና በሂደት ማወቁ መልካም ቢሆንም፣ አንዳንድ ነገሮችን ካለጊዜው ቀድሞ ማወቅ ግን የራሱ የሆነ አደጋ አለው።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
𝚗𝚎𝚟𝚎𝚛 𝚐𝚒𝚟𝚎 𝚞𝚙
ህይወት ሁልጊዜ የምንፋልገዉን አትሰጠንምም ነገር ግን የምያስፋልገንን ትምህርት ትሰጠናለች ዛሬ የምታላቅሱባት ምክንያት ነጌ የምትጣናካሩባት ታሪክ ሊሆን ይቺላል ስለዚህ ታገስ ታስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ቆንጆ ቀናት ገና ከፊት አሉ ❤️
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
በዱንያ ላይ ሁለት አይነት ህመም ታስተናግጃለሽ።
አንዱ ይጎዳሻል ሌላኛው ደግሞ ሰባብሮ አፈር ደቼ አስበልቶሽ ያስተምርሻል ያጠነክርሻል
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አይዞህ! በርታ! በህይወት ጉዞ ውስጥ ፈተናዎች ሲገጥሙን ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በጽናት መቆም እና ወደፊት መገስገስ ትልቅ ድል ነው።
ጉልበት እንዲሞላህ እና አዲስ መንፈስ እንዲፈጥሩ የሚያግዙህን አንዳንድ አጫጭር ሀሳቦች እነሆ፦
እረፍት ውሰድ፡ ለአእምሮህ እና ለአካልህ ትንሽ እረፍት ስጠው። ይህ ማለት ግን ተሸነፍክ ማለት አይደለም።
ግብህን አስታውስ፡ ለምን እንደጀመርክ እና ያሳካኸውን ድል አስብ።
አቅጣጫህን ቀይር፡ የምታደርገው ነገር ካልተሳካ፣ ሌላ የተሻለ አማራጭ መፈለግ ትችላለህ።
እገዛ ጠይቅ፡ ከቤተሰብህ ወይም ከጓደኞችህ ጋር መነጋገር አዲስ እይታ ይሰጥሃል።
መንፈስህን የሚያድስልህ የተለየ አነቃቂ ሀሳብ፣ ጥበብ የተሞላበት አባባል ወይም የመፍትሄ ሃሳብ እንድፈልግልህ ትፈልጋለህ?
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
---- አዳሜ -----
ጠበቅኩህ እኔማ-እዚያው ሥፍራ ቆሜ
በአክሱም ቁመና- በላሊበላ ዕድሜ
እግሮቼን ተክዬ-ቀኔን አስረዝሜ
በሄድክበት መንገድ- ልቤ እንደነጎደ
ስንት ነገር መጣ-ስንት ነገር ሄደ
ስንት ጊዜስ ነጋ- ስንቴ ጎህ ቀደደ
ስንቴ ዝናብ ጣለ-ስንት ጊዜ አባራ
ትመጣለህብዬ -በቆምኩበት ሥፍራ
ስንቴ አድማሱን ማተርኩ-ስንትና ስንት ዓመት
አንገቴን አስግጌ-በራስ ዳሽን ቁመት
በአክሱም ቁመና- በላሊበላ ዕድሜ
በቀጠርከኝ ሥፍራ-ስጠብቅህ ቆሜ
ስንት ሳቅ አለፈ-ስንትና ስንት ዕንባ
ስንቴስ ክረምት ሆነ-ስንቴ ፀደይ ጠባ
ስንቱ ተገናኘ-ስንቱ ሰው ተጋባ
ሽል ስንቴ ልጅ ሆነ-ስንትስ ጊዜ አረጀ
ስንት ኮት ጨረሰ- ስንት እንጀራ ፈጀ
ስንት ዓይነት ሞት አየሁ- ስንት ዓይነት ፍፃሜ
በአክሱም ቁመና-በላሊበላ ዕድሜ
በቆምኩበት ሥፍራ-ስጠብቅህ ቆሜ?
ስንት ውበት አለፈ-ስንት ውበት ነጎደ
ስንት ትውልድ መጣ -ስንት ትውልድ ሄደ
ስንት ዕውነት ከፍ አለ-ስንት ዕውነት ወረደ
ስንት ዓለም ተሻረ- ስንት ዓለም ነገሠ
ስንት ሀገር ተሰራ-ስንት አገር ፈረሠ
ስንት ሺህ ዓመት ሸኘሁ-ስንት ሺህ ተቀበልኩ
እዚያች ሥፍራ ቆሜ-አንተን እየጠበቅኩ
እግሬን አስረዝሜ-ቆየሁ ቆየሁና
በላሊበላ ዕድሜ- በአክሱም ቁመና
ሳትመጣ ወደኔ-ሳላገኝህ ገና
ብዙ ነገር መጥቶ -ብዙ ነገር ያልፋል
የራስ ዳሽን ራስ-አንገቱን ይደፋል
አክሱምም ተንዶ- እንደጨው ይረግፋል
ላሊበላም ወርዶ-ቁልቁል ይነጠፋል
ሰማይና ምድርም ያልፋሉ ትላለህ
እኔ ግን እዛው ነኝ እስክትመለስ ልጠብቅህ…
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
በመሆኑም ደስታ መልካም ነው አልኩ ምክንያቱም ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ከመደሰት የተሻለ ነገር የለም ከፀሐይ በታች እውነተኛው አምላክ በሚሰጠው የሕይወት ዘመን በትጋት ሲሠራ ይህ ደስታ ሊርቀው አይገባም።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ በሆነበት ወቅት ሕይወት አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ሕይወት ከባድ እንዲሆንብህ የሚያደርጉ አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህስ?
ለምሳሌ ያህል፣ በከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት አብዛኛውን ንብረቷን ያጣች በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ሳሊ የተባለች ሴት እንዲህ ብላለች፦ “የሚሰማኝ ጭንቀት ልሸከመው ከምችለው በላይ እንደሆነ ተሰምቶኝ ነበር። ‘አሁንስ በቅቶኛል’ ያልኩባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ።”
በሕይወታችን ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችለው ሌላው ተፈታታኝ ሁኔታ ደግሞ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ነው። በአውስትራሊያ የምትኖረው ጃኒስ እንዲህ ብላለች፦ “ሁለቱንም ወንዶች ልጆቼን ሞት ሲነጥቀኝ ሁሉ ነገር ጨለመብኝ፤ ወደ ቀድሞ ሕይወቴ ለመመለስ ብዙ ጥረት ጠይቆብኛል። ‘ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም! እባክህ ሞቼ ልገላገል። ዳግመኛ መንቃት አልፈልግም’ በማለት አምላክን ተማጽኜው ነበር።”
በሌላ በኩል ደግሞ ዳንኤል፣ ባለቤቱ በትዳራቸው ላይ ክህደት እንደፈጸመች ሲያውቅ ስሜቱ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ባለቤቴ ምንዝር እንደፈጸመች ስትነግረኝ ልቤ ላይ ጩቤ የተሰካብኝ ያህል ሕመም ተሰምቶኝ ነበር። ይህ አካላዊ ሕመም በተደጋጋሚ እየመጣ ለብዙ ወራት አሠቃይቶኛል።”
ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በሚከተሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሥር እንኳ፣ ‘በሕይወት መኖር ዋጋ አለው’ የምንልበትን ምክንያት ያብራራል፦
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ማይበገር ከፍተኛ የራስ ምታት
ምልክቶች
〰️〰️〰️〰️〰️
ከባድ ራስ ምታትሊያስከትል የሚችለው የነርቨ ችግር ነው ።አብዛኛው ጊዜ የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ እንዲሁም የብርሀንና የድምፅ አለመፈለግ ስሜት ይኖረዋል።
ታድያ በቤት ውስጥ እንዴት እንድን እንችላለን
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
⓵ ዘንጀብል፦ የዘንጅበል ሻይ በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ መጠጣት ።ወይም ጥሬ ዘንጅብል መኘክ።
⓶ 🧊 በረዶ ፦ በአንገት ጀርባ ላይ ማድረግ
⓷ አንድ የሻይ ማንኪያ አፕል ከ አንድየሻይ ማንኪያ ማር ጋ በወሀ ቀላለቅሎ መጠጣት።
⓸ ሮዝመሪ ፦ የሮዝመሬ ዘይት ጭንቅላት እና ግንባር ቀብቶ ማሳጅ አድርጎ ለጥቂት ደቂቃ መቀመጥ።
⓹ በቂ ወሀ መጠጣት
⓺ ቡና መጠጣት
⓻ማሳጅ
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ዝም ብላ የቆመች ይመስላል። የምንጠብቃቸው ነገሮች ይዘገያሉ፣ የምንፈልገው
ለውጥ አይታይም፣ ጥረታችንም ፍሬ እንዳላፈራ ይሰማናል። ግን እውነቱ ይህ አይደለም። ዛፍ ከመሬት በላይ ከመታየቱ በፊት ሥሩን በጥልቅ ያሰፋል፤ እንዲሁም በሕይወትህ ውስጥ የማታየው ብዙ መልካም ነገር እየተዘጋጀ ሊሆን ይችላል።
ዛሬ ላይ የቆምክበት ቦታ የመጨረሻ መድረሻህ አይደለም። የዛሬ እንባ የነገ ፈገግታ ሊሆን ይችላል፤ የዛሬ ድካምም የነገ ስኬት መሠረት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እምነትህን ጠብቅ፣ ተስፋህን አትልቀቅ፣ የምትችለውን ሁሉ አድርግ።
ዛሬ ለራስህ አንድ ነገር ንገር፦ "ምንም ቢከብድ አልቆምም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፣ የተሻለ ቀንም በፊቴ አለ።"
ሰላም፣ ብርታት እና በረከት ይሙላልን ❣️
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ጥበብ ማስተዋል በታከለበትና አሳማኝ በሆነ መንገድ መናገር እንድንችል ይረዳናል። ለምን? ምክንያቱም ልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ “መልካም ነገርን” ለማግኘት የሚሞክር ከመሆኑም በላይ ‘በይሖዋ ይታመናል።’ የሌሎችን መልካም ጎን ለማየት ጥረት ስናደርግ ስለ እነሱ የምንናገረው ነገር ይበልጥ አዎንታዊ እየሆነ ይሄዳል። ቃላቶቻችን ደግነት የጎደላቸውና ቁጣ የሚንጸባረቅባቸው ከመሆን ይልቅ ጣፋጭና አሳማኝ ይሆናሉ። ሌሎች ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ጠለቅ ብለን ማስተዋላችን፣ እየደረሰባቸው ያለውን ችግርና ይህንንም እንዴት እየተቋቋሙት እንዳሉ እንድንገነዘብ ይረዳናል።
ጥበብ
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አንድ አሳማ ጭቃ ውስጥ ሲንከባለል ቆይቶ ወጣ። መንገድ ላይ ሲጓዝም በአጋጣሚ ከአንድ ግዙፍ ዝሆን ጋር ተገናኙ። ዝሆኑም አሳማውን ሲያየው ወዲያው መንገድ ለቆለት አለፈ።
...
አሳማው በነገሩ ተደስቶ "ጉድ እዩ! ያ ግዙፍ ዝሆን ሳይቀር የሚፈራኝ እኔ ምንኛ ጀግና ነኝ!" እያለ በትዕቢት ይፎክር ጀመር።
...
ይህን የታዘቡ ሌሎች እንስሳት ዝሆኑን ጠጋ ብለው ጠየቁት። "ለመሆኑ አንተን የሚያህል ግዙፍ የተከበረ ፍጡር አሳማ መሰል አነስተኛ እንስሳ መንገድ እንዴት መንገድ ለቀቀለት?"
..
ዝሆኑም "እኔ እኮ አሳማውን ፈርቼው አይደለም፤ ቆሻሻው እንዳይነካኝ ብዬ ነው!" አላቸው።
..
ሰዎች ርቀው የሚሄዱት ስለፈሩ ሳይሆን 'ቆሻሻ' አስተሳሰብና ንግግር እንዳይበክላቸው ብለው ነው።
...
ዝምታንና መራቅን ሁልጊዜም ፍርሃት አድርገህ አትተርጉመው፤ ብልህነት ነው!
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
“...
.
.
. 🌺💫የሰው ልጅ አላማውን ለማሳካት ሲነሳ አልጋ ባልጋ የሆነ ጉዞ መጠበቅ የለበትም፤ምክንያቱም አልጋ ባልጋ የሆነ የህይወት መንገድ ሁሉም ሰው ስለሚጓዝበት ተራ መንገድ ነው፤ ውጤቱም ተራ ነው፡ ትልቅ ነገር ለማግኘት ትልቅ ጥረት ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡🥰
መልካም ቅዳሜ ☕️🫖🥀
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
"እራስን መሆን"
ፈራጅ በበዛበት በዚህ ምድር ላይ፤
እራስን መሆን ነው ከምንም በላይ።
የሰውን ወሬማ ንፋሱ ይውሰደው፤
የራስን ማንነት ጠብቀን እናኑረው።
የራሱን ጥላሸት ለሰው የሚቀባ፤
ሲያገኘን ሊያጠፋን የሚጥር በደባ።
ታግለን ባናሸንፈው በተንኮል በውሸት፤
ትልቅ ምላሻችን መሆን ታማኝነት።
እኛ ባልኖርንበት ቢወራ በሰዎች አፍ፤
ታሪክን ቢፅፉ የሀሜት መፅሀፍ፤
ነገር ግን እንወቀው የሰው ፍርድና ስም፤
ለእኛ የተሰጠን ክብር አይቀንስም።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
🏃♀️ 🏃♂️ የራስን ሩጫ መሮጥ
በሌሎች ሰዎች ስኬት በጭራሽ አትረበሽ
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታያቸው ሰዎች ስኬት ፣ የነሱ የሩጫ መንገድ እንጂ ያንተ የሩጫ መንገድ አይደለም። የራስህን ሩጫ ለምን ትተዋለህ?
ሁሉም ሰው የራሱ ሰዓት አለው። አንድ ሰው በ20 አመቱ የደረሰበትን ደረጃ አንተ በ30 ወይም በ40 ልትደርስበት ትችላለህ። ያ መዘግየት ሳይሆን፣ የራስህ ታሪክ ነው። የሰዎችን ስኬት እንደ መነሳሻ እንጂ እንደ ፉክክር አትመልከተው።
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
Having a Best Friend
A story tells that two friends were walking through the desert. During some point of the journey they had an argument, and one friend slapped the other one in the face.
The one who got slapped was hurt, but without saying anything, wrote in the sand “Today my best friend slapped me in the face”.
They kept on walking until they found an oasis, where they decided to take a bath. The one who had been slapped got stuck in the mire and started drowning, but the friend saved him. After he recovered from the near drowning, he wrote on a stone “Today my best friend saved my life”.
The friend who had slapped and saved his best friend asked him, “After I hurt you, you wrote in the sand and now, you write on a stone, why?” The other friend replied “When someone hurts us we should write it down in sand where winds of forgiveness can erase it away. But, when someone does something good for us, we must engrave it in stone where no wind can ever erase it.”
Moral: Do not value the things you have in your life. But value who you have in your life.
በጣም አስተማሪ ታሪክ ነው ይነበብ
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አለማችን በሁሉም ነገር ላይ እንድንቸኩልና እንድንጣደፍ ትገፋፋናለች።
የቸኮለ ውሳኔ፣ የቸኮለ ውይይት፣ የቸኮለ ግንኙነት (Relationship)፣
እና የተጣደፈ የህይወት ጉዞ...
ይህንን የተጣደፈ አዝማሚያ (Trend) አለመቀበል ውስጥ ግን እጅግ ታላቅ የሆነ ኃይል አለ።
እስቲ ረጋ በሉ! በግልፅና በጥራት ለማሰብ ለራሳችሁ በቂ ጊዜና ቦታ ስጡ።
#ህይወት #መረጋጋት #ትዕግስት #የህይወት #እርጋታ
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
"አንዳንዴ ራስን ማግለል ሰላምን ፍለጋ ነው። አለም በጫጫታ በሞላችበት በዚህ ዘመን፣ በገዛ ብቸኝነትህ ውስጥ የምታገኘው ጸጥታ ትልቅ መታደል ነው። ራስህን የምታደምጥበት፣ የምታክምበትና የምታድስበት እረፍት!"
"ብቸኝነትን እንደ ብቸኝነት ሳይሆን፣ እንደ ነፃነት ስታየው ሰላሙ ወደር የለውም። ከማንም ምንም ሳትጠብቅ፣ በራስህ አለም ውስጥ የምትገነባው ሰላም ማንም ሊቀማህ የማይችለው ሀብትህ ነው። ☕📖"
https://t.me/mekuytrrwxnc
