ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
907
Подписчики
-224 часа
-127 дней
+4630 дней
Архив постов
ሰይድ ቁጥብ ማለት ይሄ ነው ?? 👉 ከ 10 አመት በፊት የተደረገ 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed/10695

2⃣ ወደ ተውሒድ ጥሪ ለማድረግ ከሽርክ ለማስጠንቀቅ ከኛ ምን ይጠበቅብናል ፦ በመካከላችን ውደታ እንዲመጣ ምን ማድረግ አለብን በሚል ርዕስ የተደረገ ሙሐደራ ፡፡ በኡስታዝ አቡ ረያን (ሰዕድ ጀላሉ) (በቱሉ አውሊያ ጊንባ ከተማ)

የርቀት ትምርት ይመስል የርቀት ጋብቻ አስፈላጊ አይደለም። የኋላ ኋላ ብዙ ነገር ይጠፋል። = [ሸርሑ ሱ፞ና ሊል በርበሃሪ (31፣ 65')፣ ኢብኑ ሙነወር]

ማውጫ የዳእዋ ብቻ الدعوة فقط 📢📢መሳጭ ዳእዋወችን በተለያዩ ርዕሶች በተለያዩ ኡስታዞች የተደረጉ ሙሓደራወች ስብሰብ ለማገኘት ከታች ርዕሱን በመንካት ማዳመጥ ይቻላል ከርዕሱ ፊት የዳእዋ ብዛቱ ተቀምጧል ። ➊ ስለ አህባሽ =31 ➋ ስለ መውሊድ =48 ❸ ስለ ኢኽዋን ሙፍሲድን =42 ➍ ስለ ሐጃዊራ ሀዳድያ ተክፊሩ ሙስጠፋ አብደላ ❹➋ ➎ ስለ አድስ አመት ፥ ቋግሜ ፤እንቁጣጣሽ ፣ዘመን መለወጫ ፣ቅድስ ዩሀኒስ ➊➎ ❻ ስለ ሲህር (ድግምት ) መተት ➋➋ ሸር በማድረግ እናዳርሰው ✅ኢንሻአላህ ይቀጥላል

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته، والحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله ➡️ውድ እና የተከበራችሁ የሸይኻችንን ደርሶች በመከታተል ላይ የነበራችሁና ስላሉበት ወቅታዊ ሁኔታ አሳስቧችሁ በየጊዜው በመጠየቅ ላይ ለነበራችሁ እህትና ወንድሞች! አልሃምዱሊላህ እንኳን ደስ አለን ሸይኻችን አፍያቸው በጣም ጥሩ ወደ ሆነ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን ልናበስራችሁ ወደድን!!! ስለሆነም ከዚህ በፊት በሸይኻችን የተጀመሩ የኪታብ ቂርዓቶች  ኢንሻአላህ ከሰኞ መስከረም 04/2019 ጀምሮ ቀስበቀስ ለመጀመር ታስቧል። በዚህም መሰረት ለጊዜው ዘወትር ከሰኞ - ሐሙስ ከሱብሂ ሰላት በሗላ ሲሰጥ የነበረውን የሪያድ አስ‘ ሷሊሂን ኪታብ ደርስ ከሰኞ 04/01/2019 ጀምሮ ከሰኞ– እሮብ ከመግሪብ – ኢሻ የሚሰጥ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። إن شاء الله አጠቃላይ ደርሶች የሸይኽ የጤና ሁኔታ ሲስተካከል ወደነበሩበት እንደሚመለሱ ለማሳወቅ እንወዳለን። ሁላችንም በያለንበት ለሸይኻችን አላህ ረጅም እድሜን ከሙሉ ዓፊያና መልካም ስራ ጋር እንዲለግሳቸው በዱዓ አትርሷቸው። 📢ማሳሰቢያ:  የቂርዓት ቦታ ከዚህ በፊት በነበረበት አቡበክር መስጂድ( ፉሪ ከኳስ ሜዳው ፊትለፊት) የሚቀጥል ይሆናል። والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ሸይኽ ሱለይማን ኢብኑ ሰሊሙላህ አር-ሩሀይሊይ እንድህ ይላሉ፦ 👉የየመን ጀግኖች፣ የጥበብ፣ የልበ ሙሉነት፣ የኩራትና የጠንካራ ቁርጠኝነት ባለቤቶች ሆይ! በአላህ ገመድ ላይ በፅናት ተጣበቁ፤ አንድነታችሁንም አጥብቃችሁ ያዙ። የመን ወደ ቀድሞ ደስታዋ እንድትመለስ በአንድ ልብ በአንድ እጅ ምቱ። ተስፋ ለሚያስቆርጡ አዳካሚዎች እንዲሁም ከሰውም ሆነ ከጂን ለሆኑ የሰይጣን ጉትጎታዎች ጆሮ አትስጡ። እናንተ ምስጋና በሚገባው ትግል ጂሃድ ውስጥ ናችሁና፤ በአላህ ፈቃድ በቅርቡ ለሚያምረው መጨረሻችሁ ምስጋና ታቀርባላችሁ። ነገ አላህ ፊት ለምንጠየቅበት ምስክርነት እውነተኛ ምስክርነታችንን እንሰጣለን፦ ወንድሞቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ የሆኑት ሳዑዲዎች ለእናንተ መልካምን፣ ለሀገራችሁም ክብርን ይመኛሉ። ህጋዊ በሆነው አመራራችሁ ጥያቄና ቅንጅት መሰረት ሀገራችሁን ከሁቲዎች ጥፋት ለማጽዳት በሚደረገው ትግል አብረዋችሁ ይሳተፋሉ። በዚህም ምክንያት የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ፈተና አንዳች ውለታ እንደዋሉላችሁ ሳይቆጥሩና ሳይመፃደቁ ይታገሳሉ። ስለዚህ ከእነሱ ጋር ተባበሩ፤ ከእነሱ ጋር መተባበር ግዴታ ነውና። ከዚህ ውጭ ወዳለ መንገድ የሚጠራችሁ አካል ከትክክለኛው መንገድ ያፈነገጠና ሌሎች ድብቅ ዓላማዎች ያሉት መሆኑን እወቁ፤ ስለዚህም ከዘንጊዎች አትሁኑ።

يارجال اليمن ، يا أهل الحكمة والشهامة والأنفة والعزايم القوية ، الاعتصام الاعتصام بحبل الله ، والجماعة الجماعة ، والضرب بيد و
يارجال اليمن ، يا أهل الحكمة والشهامة والأنفة والعزايم القوية ، الاعتصام الاعتصام بحبل الله ، والجماعة الجماعة ، والضرب بيد واحدة لتعود يمنكم سعيدة ، ولاتلتفتوا للمخذلين ولا لوساوس شياطين الإنس والجن فأنتم في جهاد تحمدون عليه وبإذن الله عما قريب تحمدون العاقبة. ونشهد شهادة نُسأل عنها أن إخوانكم وجيرانكم السعوديين يريدون لكم الخير ولبلادكم العزة ويشاركونكم عملكم لتطهير بلادكم من عبث الحوثة بطلب من قيادتكم الشرعية وتنسيق معهم ، ويتحملون مايتحملون بسبب ذلك من غير منة عليكم ،فتعاونوا معهم فالتعاون معهم فرض ، واعلموا أن من يدعوكم إلى خلاف ذلك منحرف عن جادة الصواب وله مآرب أخرى فلاتكونوا من الغافلين. https://t.me/mousua/854032

Be serious about your boundaries. ድንበራችሁ እንዲጣስ የፈቀዳችሁ እለት ውደቀታችሁ ውርዳታችሁ ይቀርባል። ይህንን ለማወቅ እስኪደርስባችሁ አትጠብቁ። ይህንን ለመረዳት እስክትወድቁ አትጠብቁ። ይህንን ለመገንዘብ እስክትዋረዱ አትጠብቁ። ሁለት ጊዜ መማር ቁስለትን ያወርሳልና። የተወሰደ

👉 ማንም ሰው ጠላት ሆኖ ሊያጠቃኝ አልሞከረም፤ አላህ ተንኮሉን በራሱ ላይ የመለሰበት ቢሆን እንጂ። ማንም ሰው ከጀርባዬ (በድብቅ) አልወጋኝም፤ አላህ እውነተኛ ማንነቱን ያጋለጠው ቢሆን እንጂ። ማንም ሰው በግብዝነት (አስመስሎ) አልቀረበኝም፤ አላህ መጥፎ ሀሳቡን ግልጽ አድርጎ ያሳየኝ ቢሆን እንጂ። በየትኛውም ጊዜ ከአላህ እዝነት ስር ነበርኩ፤ አላህም ከተሳሳተ ጥርጣሬ ጠብቆኝ እውነታዎችን ልክ እንዳሉ አሳየኝ። የልቦናዬን እይታ (ማስተዋሌን) አብርቶልኝ እና ከመከዳት የመጣውን ድንጋጤዬንም ወደ ንቃት (ትምህርት) ቀይሮልኝ እንጂ፣ በማንም ሰው ተታልዬ እንድቆይ አላደረገኝም። አላህ በውስጣቸው ባለው መጥፎ ነገር ልክ ይመነዳቸዋል። አንተንም በኒያህ ንፅህና ልክ ይጠብቅሃል።

لم يُحاربني أحد الا ورد الله كيده في نحره ولم يطعنني أحد في ظهري الا وكشف الله حقيقته ولم يُنافقني أحد الا وأراني الله سوء نيته كنت تحت رحمة اللٰه في كل الوقت وحماني الله من الظنون وأراني الحقائق كما هي ،ولم يجعلني يوماً مغشوشاً بأحد الا وأنار بصيرتي وجعل من صدمتي يقظة. سيجزيهم اللّٰه بسوء ما عندهم ويحميك بطهر نيتك 🤍

ጀግናዬ! 👉የደስታችን ምንጭ ለማድረግ አስበናቸው የሀዘናችን ውቅያኖስ የሆኑ ሰወች አሉ።ግን #ክፉ አንመኝላቸውም። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

ጊዜህን ተቆጣጠር፣ ሕይወትህን ቀይር፡ ምርታማነትን የምታሳድግባቸው ወርቃማ መርሆዎች ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ ከምንም በላይ ውድ እና ሊመነዘር የማይችል ሀብት ነው። አንዴ ካለፈ በኋላ ተመልሶ የማይመጣ ሲሆን፣ እንዴት እንደምንጠቀመው ደግሞ የኑሮአችንን ጥራት፣ ስኬታችንን እና የእርካታ ደረጃችንን ይወስናል። ብዙዎቻችን ግን ጊዜያችንን በአግባቡ ባለመጠቀም፣ በቀን ተቀን እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሰጥመን፣ ዋና ዋና ግቦቻችንን ለማሳካት እንቸገራለን። ታዲያ ይህን ውድ ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ምርታማ፣ ተረጋግቶና ትርጉም ባለው ሕይወት ለመኖር የሚያስችሉ ወርቃማ መርሆዎች እነሆ፦ *   የጊዜ አጠቃቀምህን ተረዳ (Track Your Time):     ምንም ነገር ከማስተካከልህ በፊት አሁን ያለውን ሁኔታ መረዳት ወሳኝ ነው። ለተወሰነ ጊዜ (ለምሳሌ ለአንድ ሳምንት) የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችህን በዝርዝር አስፍር። የትኞቹ ተግባራት ምን ያህል ጊዜ እንደወሰዱ፣ ጊዜህን የት እንዳጠፋህ በትክክል ስታውቅ፣ ለአባካኝ ተግባራት የሚውለውን ጊዜ ቀንሰህ ለአስፈላጊ ነገሮች ማዋል ትችላለህ። *   ግልጽ እና ሊለኩ የሚችሉ ግቦችን አውጣ (Set Clear & Measurable Goals):     ጊዜህን ለምን ዓላማ እንደምትጠቀም ማወቅ ግልጽ መንገድ ያበጅልሃል። ግቦችህ SMART (Specific-ግልጽ፣ Measurable-ሊለካ የሚችል፣ Achievable-ሊደረስበት የሚችል፣ Relevant-አግባብነት ያለው፣ Time-bound-የጊዜ ገደብ ያለው) መሆን አለባቸው። ትናንሽ ግቦችን በማስቀመጥ እና እነሱን በማሳካት ለትላልቅ ስኬቶች መዘጋጀት ትችላለህ። *   ተግባራትን ቅድሚያ ስጥ (Prioritize Your Tasks):     ሁሉም ተግባራት እኩል አስፈላጊ አይደሉም። አስቸኳይ እና አስፈላጊ የሆኑትን (ለምሳሌ የጊዜ ገደብ ያላቸው ፕሮጀክቶች)፣ አስፈላጊ ግን አስቸኳይ ያልሆኑትን (ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ ስኬት የሚረዱ ዕቅዶች)፣ አስቸኳይ ግን አስፈላጊ ያልሆኑትን (ለምሳሌ የተወሰኑ ኢሜይሎች) እና አስቸኳይም አስፈላጊም ያልሆኑትን (ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም) በመለየት ሥራህን አደራጅ። የአይዘንሃወር ማትሪክስ (Eisenhower Matrix) ይህንን ለመለየት ይረዳል። *   ከአባካኝ ነገሮች ራቅ (Avoid Distractions):     ስልኮች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማሳወቂያዎች፣ ኢሜይሎች እና አላስፈላጊ ንግግሮች የጊዜ ሌቦች ናቸው። ለአንድ ተግባር ስታተኩር እነዚህን ከጎን አስወግድ። ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በአንድ ነገር ላይ በማተኮር (ለምሳሌ የፖሞዶሮ ቴክኒክ) ምርታማነትህን ማሳደግ ትችላለህ። የስራ ቦታህ ንጹህ እና የተደራጀ መሆኑም ትኩረት እንዳይሰረቅ ይረዳል። *   የጊዜ አጠቃቀም መሳሪያዎችን ተጠቀም (Utilize Time Management Tools):     የቀን መቁጠሪያዎች (ዲጂታልም ሆኑ በእጅ የሚያዙ)፣ የዕቅድ ደብተሮች (planners)፣ የሞባይል አፕሊኬሽኖች (to-do list apps, reminder apps) እና ሌሎች መሳሪያዎች ተግባራትህን እንድትከታተል፣ ቀጠሮዎችህን እንዳትረሳ እና ጊዜህን በአግባቡ እንድታስተዳድር ያግዙሃል። የሚስማማህን መሳሪያ መርጠህ በቋሚነት ተጠቀምበት። *   ውክልና መስጠትን ተለማመድ (Practice Delegation):     ሁሉንም ነገር ራስህ ማድረግ አይጠበቅብህም። ሌሎች ሰዎች ሊያከናውኗቸው የሚችሉ ተግባራት ካሉ፣ በብቃት እና በሙሉ እምነት ውክልና መስጠትን ተማር። ይህ የእራስህን ጊዜ ለበለጠ አስፈላጊ እና ውስብስብ ተግባራት እንድታውል ይረዳሃል። *   እረፍት መውሰድ እና ራስን መንከባከብን አትርሳ (Don't Forget Breaks & Self-Care):     ያለ እረፍት በከፍተኛ ፍጥነት መስራት፣ በመጨረሻ ምርታማነትን ከመቀነስም በላይ ቃጠሎ (burnout) ያስከትላል። አጭር እረፍቶች መውሰድ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ከጓደኞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ የአእምሮ እና የአካል ጤናህን ይጠብቃል፤ ይህም ለተሻለ ምርታማነት መሠረት ነው። *   በየጊዜው ገምግም እና አስተካክል (Review & Adjust Regularly):     የጊዜ አጠቃቀምህ ፍጹም ላይሆን ይችላል። በየሳምንቱ ወይም በየወሩ የጊዜ አጠቃቀምህን እና ግቦችህን ገምግም። የትኞቹ ስልቶች እንደሰሩልህ፣ የትኞቹ እንዳልሰሩ እና ምን ማሻሻል እንዳለብህ ለይተህ እቅድህን አስተካክል። መማር እና ማደግ ቀጣይ ሂደት ነው። ጊዜን በአግባቡ ማስተዳደር ማለት ሁሉንም ደቂቃ በሥራ መሙላት ማለት አይደለም። ይልቁንም፣ ለእራስህ፣ ለቤተሰብህ፣ ለስራህ እና ለግል እድገትህ ትርጉም ባለው መንገድ ጊዜ መመደብ ማለት ነው። ጊዜህን በስትራቴጂያዊ መንገድ ስትቆጣጠር፣ ውጥረትን በመቀነስ፣ ግቦችህን በማሳካት እና እርካታ የተሞላበት ሕይወት በመኖር የሕይወትህን መሪ ትሆናለህ። ዛሬውኑ እነዚህን መርሆዎች በመተግበር፣ ወደምትመኘው ምርታማ እና ሚዛናዊ ሕይወት ጉዞህን ጀምር! https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf

የሱና ሰዎች ለሌሎች መመራት ይጨነቃሉ እንጂ  በሌሎች መሳሳት አይደሰቱም!! ሀቅን የያዝከው በአሏህ ፍቃድ እንጂ በራስህ ብልህነት, እውቀት, ጉልበት… አይደለም: ስለሆነም በያዝከው ሀቅ ቀጥ ትል ዘንድ ጠዋት ማታ አሏህን መለመን ግድ ነው! እንዲሁም በሌሎች መመፃደቅ, መሳለቅና በእነሱ ላይ ፈፅሞ ዱኣ ማድረግ የለብህም በል የነሱ መንገድ መሳት  ሊያሳዝንህ ሊያስከፋህ እና ብሎም ዱኣ ልታደርግላቸው ነው ሚገባው  ቀደምት ሰለፎች ይታወቁ የነበረው በእዝነት በትህትና በመምከርና ለሌሎች ዱኣ በማድረግ ነበር! ዛሬ የኛን ሁኔታ ግን  ከሰለፎች አንፃር ማገናዘቡ ያባት ይሁንና… እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ አስመልክቶ  ሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ: ​"የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች በዓርሽ  ጉዳይ፣ ቁርኣን የአሏህ ቃል በመሆኑ እና በአሏህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ መውረድ(ኑዙል) ጉዳይ ምክንያት በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱት በደል በበረታ ጊዜ፤ ወንድማቸው ሸይኽ ሸረፉዲን ተማጽኖ በማቅረብ በእነርሱ ላይ ዱዓ ማድረግ (እንዲጠፉ) ጀመረ።" ​"ሸይኽ አል-ኢስላም ግን ከለከሉትና እንዲህ አሉት፦ 'በል እንዲህ በል፦ አላህ ሆይ! ወደ እውነት የሚመሩበትን ብርሃን ስጣቸው።'" ​ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ይህን ንግግር አስመልክተው እንዲህ ይላሉ: ​"ለአላህ ምስጋና ይሁንና! ይህ ምንኛ ታላቅ ስነ-ምግባር ነው! ምንኛ የላቀ ባህሪ፣ የነፍስ ዝቅታ (ትህትና) እና እውነትን መፈለግ ነው! በአላህ ይሁንብኝ! ይህች (ትምህርት) ብቻዋን ረጅም ጉዞ ሊደረግላት የሚገባት ፋይዳ ናት።" ​"እኛ ካለንበት ሁኔታ ጋር ይህ ምንኛ ይራራቃል! ከእኛ መካከል አንዱ በትንሹ እንኳን ሲበደል ወዲያው ቁጣና ጥላቻ ይወርረዋል፤ በጠላቱ ላይም የዱዓ አይነቶችን ሁሉ ያዘንባል። አላህ ሆይ! ለእኛም ሆነ ስለ አንተ ብሎ ለበደለን ሰው ወደ እውነት የምንመራበትን ብርሃን ስጠን።" አቡ ፈውዛን

ደግ አንደበተ ርቱዑ ሼይኽ አዚዝ ቢን ፈርሃን አል-ዐነዚ አላህ ይጠብቃቸውና «ቢዩቱን ሙጥመኢንናህ» (የተረጋጉ ቤቶች) በተሰኘው ማራኪ ፕሮግራማቸው አማካኝነት የልባችንን እይታ የኑሯችንን ሁኔታ በጣፋ
ደግ አንደበተ ርቱዑ ሼይኽ አዚዝ ቢን ፈርሃን አል-ዐነዚ  አላህ ይጠብቃቸውና «ቢዩቱን ሙጥመኢንናህ» (የተረጋጉ ቤቶች) በተሰኘው ማራኪ ፕሮግራማቸው አማካኝነት የልባችንን እይታ የኑሯችንን ሁኔታ  በጣፋጭ አንደበት በጥልቅ አይታ መቃኘታቸውን ቀጥለዋል። «እረፍትን (ስኪናን) አታዘግዩ» በሚል ርዕስ ባቀረቡት ሦስተኛው ትምህርታቸው ውስጥ ከተናገሩት ምክር መካከል ይህ ላካፍላችሁ «ልጄ እህቴ ሆይ! ቤቶች የሚገነቡት  በይስሙላና በውጫዊ ገፅታ ሳይሆን በተረጋጋ መንፈስና በሰኪናህ እንደሆነ እወቂ! ቤቶች በሀብት ብዛት ሳይሆን በኢማን በረካ ፀንተው ይቃናሉ። ስለዚህም (ልጄ) አንቺ ልትፈልጊው የሚገባው ትልቁ ነገር የበዛ ሀብት ያለውን ሰው ሳይሆን፣ አላህን አብልጦ የሚፈራውን ሰው ነው! አንድ ወጣትም ሊፈልገው የሚገባው ትልቁ ነገር ውብ ፊትን ሳይሆን፣ ውብ ልብን ነው! እንዲሁም ቤተሰብ በአጠቃላይ ለልጃቸው ሊመርጡ የሚገባው  ከአጪዎች መካከል እጅግ ሀብታሙን ሳይሆን፣ አደራ ጠባቂውንና አላህን ፈሪውን ነው...» ወላሂ እጅግ ጠቃሚ ቁም ነገር ከምታገኙባቸው የህይወት ቅርስ ስለሆነ ፕሮግራሙን እየገባችሁ ተከታተሉ! ሸይኹን ​አላህ ይጠብቃቸው፤ መልካም ምንዳን ይክፈላቸው፤ በእውቀታቸውና በሥራቸውም በረካ ያድርግላቸው...!

- የአላህ መጽሐፍ ቁርአን ወደ እኛ መቅረቡ እንዴት ያለ የሚያምርና ማራኪ ነው፣ ልባችን ግን ከእሱ የራቀ ነው! ቁርዓንን ማስተንተን ትልቅ ጸጋ ነው፣ ዋጋውን የተነፈጉ ሰዎች ግን በትክክል የማያቁት
- የአላህ መጽሐፍ ቁርአን ወደ እኛ መቅረቡ እንዴት ያለ የሚያምርና ማራኪ ነው፣ ልባችን ግን ከእሱ የራቀ ነው! ቁርዓንን ማስተንተን ትልቅ ጸጋ ነው፣ ዋጋውን የተነፈጉ ሰዎች ግን በትክክል የማያቁት ናቸው። አንቀጾቹን የሚያዩ ዓይኖች ብቻ አይደሉም፣ ነገር ግን ልብ መመሪያውን ቆም ብሎ በማሰብ፣ ምክሩን ማስተንተን፣ በብስራቶቹና በማስጠንቀቂያዎቹ መነሳሳት፣ እና በዚህ ሕይወትና በመጨረሻው ዓለም ውስጥ አንድን ሰው የሚጠቅመውን ማግኘት ነው። ቁርዓን የልብ ጓደኛ፣ የነፍስ ምንጭ እና የመንገዱ ብርሃን ነው። አንድ ባሪያ ከቁርዓን ጋር ባለው ጓደኝነት የበለጠ ውብ በሆነ ቁጥር፣ አላህ ትርጉሞቹንና መመሪያዎቹን የበለጠ ይከፍትለታል፣ ልቡን ያድስለታል፣ ኢማኑን እና ግንዛቤውን ይጨምራል። አላህ ሆይ! ክቡር የሆነውን ቁርዓን የልባችን ብርሃን፣ የሐዘናችን ማስወገጃ እና ጭንቀታችንን የሚያስወግድ አድርግልን። ከቁርአን ሰዎች መካከልም አድርገን፣ የአንተ እና የመረጥካቸው ሰዎች አድርገን ያረብ!! t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

⭐️ ክፍል  🔢    🔢🔢 "እገሌን እገሌ ሙብተዲዕ ብሎታል እገሌ ደግም አላለውም ሙብተዲዕ ያላለውን ወደ ተባለው ታስጠጋዋለህ?" የሚለውን የኡስታዝ ንግግር ካሰፈርክ በኋላ ይህ ማለት "አንድን ሰው ሙብተዲዕ ለማለት የጋራ ስምምነት ያስፈልጋል ማለቱ ነው" በማለት የፃፍከው ያንተ የግንዛቤ ዝግጠት፣ ስርዓት አልበኝነትህና ሰዎችን የምታጠምበት ሴረኛ ብዥታህ ነው። እስኪ በአላህ ልጠይቅህ ፦ -የንግግሩ ተዘዋዋሪ መልዕክት ይህን ያስይዛል ብንል እንኳ- "የአንድ ሰው ንግግር ተዘዋዋሪ መልዕክቱ ባለቤቱ እስካላመነበት ድረስ እንደ ቀጥተኛ ንግግሩ አይወሰድም" የሚለውን መርህ አታውቅም ወይ? አላህን አትፈራም!? ሴራህን ምን ከባድ አደረገው!! 🔢🔢 "ኢብኑ ሙነወር ሙዋዘናን ለማስረፅ በረሱልﷺ ላይ ዋሽቷል" ትላለህ። አንተ አታላይ! ኢብኑ ሙነወር በዚያው የድምፅ ፋይል "ረድ ሲደረግ ሙዋዘና (እርምት በሚሰጥ ጊዜ መልስ የሚሰጥበትን አካል ጥሩና መጥፎ ጎኑን ማውሳት) አይፈቅድም" ብሎ መግለፁን አልሰማህም ነው? ስለዚህ ጉዳይ ዙሪያ በቻናሉም በቂ ማብራሪያ ሰጥቷል። ሲቀጥል "የተወሳው የረሱልﷺ ንግግር በኸዋሪጆች እንዳትሸወዱ ብሎ ይበልጥ ለማስጠንቀቅ ነው" እያለ በግልፅ ነውኮ የተናገረው። ድምፁ በሪከርድ ተቀምጦ ሳለ ለምን በዚህ ልክ መዋሸትና መቅጠፍ አስፈለገ!? ትንሽ እንኳ አታፍርም ፈጣሪህን!? 🔢🔢 ሌላው "ሸይኽ ረቢዕ አሻዒራዎችን አወድሰዋል ብሎ ዋሽቶባቸዋል" "ሸይኹል አልባኒ ሰይድ ቁጥብን አወድሰዋል" ብለህ ያወሳኻው ካንተው ከራስህ የሆነ ቅጥፈት ነው። ምክኒያቱም እነዚህ ሁለቱ ኢማሞችም ይሁኑ ሌሎች አኢማዎች በከፊል የቢድዓ ባለቤቶች ላይ አንዳንዴ የተገደበን ውዳሴ አንዳንዳንዴ ደግሞ ያለ ገደብ ማወደሳቸው በጣም የታወቀ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፦ ሸይኹል አልባኒ ሰይድ ቁጥብን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦ "ይህ ታላቁ ኡስታዝ ሰይድ ቁጥብ ነው" [ሙኽተሰሩል ዑሉው - ገፅ 59] እንደዚሁ ሸይኽ ረቢዕ በአሽዓሪይነታቸው ታዋቂ የሆኑትን አስ'ሱዩጢይን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦ "በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ የፃፏቸው ድርሳናቶቻቸው (ኪታቦቻቸው) ተቀባይነት አላቸው" [መጅሙዑል ኩቱብ ወርረሳኢል 3/283] ምክኒያቱም የቢድዓ ሰዎችን እና ኪታቦቻቸውን በተገደበ መልኩ ማወደስ ወይም ልምድ ተደርጎ ሳይያዝ ያለምንም ገደብ ማወደስ ከሱና አያስወጣም። የቢድዓ ባለቤቶችን  ያወደሰ ከሱና ውጭ የሆነ ሙብተዲዕ ነው አይባልም። እንዲሁ በዘፈቀደ ንግግሩ ልቅ አይደረግም። 🔢🔢 "ኢብኑ ሙነወር ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ኣደም ከቀርዷዊ ንግግር ይወስዳሉ" "ብሎ ዋሽቶባቸዋል" ያልከው ፀሃይ ረፋድ ላይ ለማንም ግልፅ እንደምትሆነው ፍንትው ያለ ቅጥፈትህ ነው። ቅጥፈትህን ምን የገዘፈ አደረገው!! ምን አይነት አይን ያወጣ ቀጣፊ ነህ ባክህ!? ሸይኹ ከቀርዷዊ ንግግር መውሰዳቸው በኪታባቸው [ዘኺረቱል ዑቅባ 22/171 - 172] ባቡ ዘካቲል ወሪቅ [ሐዲስ ቁጥር 2473] ን ሲያብራሩ ተፅፎ የተቀመጠኮ ነው። ኢብኑ ሙነወር በቻናሉ ይህንን እስከ ገፁ ድረስ ከማስፈሩ ጋር በርሱ ላይ በዚህ ልክ መቅጠፍህ ካመላከተ የሚያመላክተው በዚያ ኢላማውን በማይስተውና የመታው መዳኛው አዳጋች በሆነው ተወርዋሪ ቀስቱ ያደረሰብህን የህመም መጠንና ያንተ ብቸኛ አላማህ እንዲህ አይነት ፀያፍ ውሸት እስከመዋሸት ቢያደርስህም እንኳ እርሱን መጣልና መጣል ብቻ እንደሆነ ነው። 🔢🔢 "ሰለፊዮችን መዳኺላ ብሎ ተሳድቧል" ያልከው ካንተ የሆነ ውሸት ነው። ውድቀትህን ምን የበዛ አደረገው!? አዎ ኢብኑ ሙነወር ለማንም ይሁን ለማን ማንኛውንም አይነት ተዓሱብ (አጉል ወገንተኝነት) ይቃወማል። ከፊል ወጣቶች በሐቅም በባጢልም ለኸይኽ ረቢዕ ወገንተኝነትን ሲያንፀባርቁ "መድኸሊይ አትሁን!" ሲል መክሯል። ይህ የተስተካከለ ምክር ነው። ምንድነው የፈለግከው!? ይህ (አጉል ወገንተኝነትን መቃወም) የቀደምቶች መንገድ አይደለምን? ይህን ነው ከእርሱ ያየነው። ሲቀጥል ምን እንደፈለገበት በቻናሉ በበቂ መልኩ አብራርቷልኮ። 🔢🔢 ሌላው "ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲል መድኸሊይን ተችቷል" ያልከው በመጀመሪያ ይህም ካንተ የሆነ ውሸት ነው። እውነተኛ ከሆንክ ማስረጃህን አቅርብ። ሲቀጥል ሸይኽ ረቢዕኮ ብርቱ የሆነን ትችት በሸይኽ ሙሐመድ አልመድኸሊይ ላይ ሰንዝረዋል። ሸይኽ ረቢዕ ሙመይዕ ሙብተዲዕ ናቸው ትላለህ!? ትዳፈራለህ ወይ!? 🔢🔢 "እርሱ የአላህን ንግግር ጠምዝዟል" ትላለህ ሱብሓነላህ!! ለአላህ ያለህን ፍራቻ ምን አናሳ አደረገው!! ይህ አንተ ከአደብ እጣ እንደሌለህ ነው የሚያሳየው። ለአላህ ጥራት ይገባው ኡስታዝ የእርሱን ንግግር ከመጠምዘዝ።  ልጠይቅህ ፦ ሚዛን የሚደፋ ጥቅም ወደ ሙስሊሞች እስካመጣ ድረስ ከማንም አካል ጋር ትብብር ማድረግ እንደሚቻል ከማመላከት አንቀጿን ያስወጣት ምንድነው? 🔢🔢 በክር አቡ ዘይድ፣ ሸይኽ ረቢዕንና ሰይድ ቁጥብን በተመለከተ ያወሳሃውማ ካንተ የእውር ድንብር ጉዞና መድረቅረቅ ጭምር ነው። ይህን በተመለከተ የተከበረው ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ አልከሚሲ በቂና ምጡቅ ማብራሪያ ስለሰጠህ ከዚህ ወሬን ማስረዘም አልሻል። 🔢🔢 "የጀርሕ እና የተዕዲልን ባለቤትነት ከዑለማኦች ውድቅ አድርጓል" ትላለህ። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ካንተና አንተን ከመሰሉ እውተኛ አንደበት የሌላቸው፣ የአላህ ፍራቻ የሳሳባቸው፣ የመጣላቸውን ሁሉ የሚናገሩና ስለራሳቸው -ልክ እንደ እብድ- "ማይክ በሚጨብጡና ወንበር ላይ በሚወጡ ጊዜ የሚናገሩትን እንደማያውቁ" የገለፁ ከሆኑት ጉዶች ነው ውድቅ ያደረገው። ✅ በመጨረሻም "እነዚህ ኢብኑ ሙነወር ከሙብተዲዖች ሰልፍ እንደሆነ የሚጠቁሙ ከፊል ጥመቶቹ ናቸው" ትላለህ። የት አሉና!? እንዲሁ ካንተ የሆነ ደረቅ ሙግት፣ ውሸትና ቅጥፈት ሰለፊዮችን ከሙብተዲዖች ሰልፍ ያደርጋል እንዴ!? ዓቅልህ የት ሄደ ሰውየ!? ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለም ወይ!? ✅ የሰለፊያ ወጣቶች ሆይ! በምቀኝነት እሳት ከተቀጣጠለችው ልቦቻቸው የመነጨ የሆነን የወደቀና ፈር የለቀቀ የኢጅቲሃዳቸውን ውጤት ካልተሸከማቹህ እያሉ ሰዎችን ሱሪ ባንገት የሚሉትን፣ የአህለሱናዎችን ጀማዓ መበታተንና ወጣቶችን የሙሪድነት ምርኮኛ ማድረግ የሚፈልጉትን አዲሶችን ሓዳዲዮች ተጠንቀቁ!! ተጠንቀቁ!! እላቹኋለሁ። 🤲  በሐቅ ላይ አንድ እንዲያደርገንና በሱና ላይ እንዲያፀናን የታላቁን ዓርሽ ባለቤት ተከበረውን አላህ እለምነዋለሁ። በመልዕክተኛው ﷺ በባልደረቦቻቸውና በተከታዮቻቸው ላይ የአላህ ውዳሴውና ሰላሙ ይስፈን። ✍️ የሰለፍዮች ወዳጅ አቡ ዒምራን    📆  ታህሳስ 05/2018 ዓ.ል       ❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️ ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy

🔢🔢أما قولك "فلان بدعه فلان الخ" ثم قولك "يعني لا بد من اشتراط الإجماع فى التبديع الخ" فهذا من قلة فهمك وسوء أدبك ومن تلبيساتك الخادعة المضلة، أسألك بالله! - على فرض كونه هذا لازمَ قوله -  أما تعلم أن لازم القول ليس بقول ما لم يلتزمه القائل!؟ ألا تتقي الله يا حسين!؟ ما أعظم مكيدتك!! 🔢🔢أما قولك إنه كذب على الرسول👑الخ فيا غشاش أما علمت أن ابن منور قد بيّن فى ذاك المقطع نفسه أن الموازنة فى حال الرد لا تجوز فضلا عن أن يقررها، وبين هذا الأمر فى قناته بيانا كافيا، وأيضا هو قد وضح أن كلامه👑 هذا  على الخوارج لزيادة التحذير والتنفير من الاغترار بهم،  لما ذا الكذب والبهتان -وصوته مسجل- ؟ أما تستحي من الله!؟ 🔢🔢وأما ما ذكرته من أنه "كذب على الشيخ ربيع المدخلي 📍 بأنه أثنى على الأشاعرة" "وأنه كذب على الإمام الألباني بأنه أثنى على سيد قطب الخ" فهذا أيضا من كذباتك أنت،  فثناء هذين الإمامين وغيرهما من الأئمة على بعض أهل البدع ثناء مقيدا تارة ومطلقا أخرى معروف جدا، فمثلا يقول الشيخ الألباني عن سيد قطب "فهذا هو الأستاذ الكبير سيد قطب" [مختصر العلو ٥٩] وكذلك الشيخ ربيع يقول فى ترجمة السيوطي الأشعري "...وتصانيفه في كل فن من الفنون مقبولة..،" [مجموع الكتب والرسائل ٢٨٣/٣]  لأن الثناء على أهل البدع وكتبهم ثناء مقيدا، أو مطلقا من غير اتخاذه عادة له لا يخرج من السنة، فالذي يثني على أهل البدع لا يقال إنه مبتدع خارج من السنة، ما يطلق الكلام هكذا على عواهنه يا رجل، ما هكذا يا سعد تورد الإبل!! 🔢🔢وقولك "إنه كذب على العلامة محمد علي آدم الإتيوبي بأنه ينقل عن القرضاوي" كذب واضح منك وضوح الشمس فى رابعة النهار، ما أعظم فريتك يا كذاب! فنقل الشيخ 🤎  عن القرضاوي ثابت مسطر فى كتابه ذخيرة العقبى بشرح المجتبى [٢٢/ ١٧١ - ١٧٢] فى باب زكاة الورق حينما يشرح حديثا رقمه ٢٤٧٣، وافتراءك على الأستاذ مع أنه أثبت هذا مع ذكر صحيفته فى قناته إن دل إنما يدل على قدر ألمك بسهمه الثاقب الذى قل من يبرأ إذا أصابه، وعلى أنك إنما تريد مجرد إسقاطه ولو أداك إلى مثل هذا الكذب الفاحش، 🔢🔢وقولك "إنه رمى السلفيين بأنهم مداخلة الخ" أيضا كذب منك، ما أكثر زلاتك!! فنعم ابن منور 🇧🇼 ينكر أيّ تعصب لأيّ شخص من الأشخاص، ونصح الشباب حين رأى بعض من يتعصب له بالحق والباطل فقال لا تكن مدخليا!! وهذا نصح سديد منه، ما هذا الذى تريده يا هذا أليس هذا - أعني عدم التعصب لأي كان - منهج السلف؟ وهذا الذي رأيناه منه ووضح ما أراده فى قناته بما يشفى ويكفي، 🔢🔢وما ذكرته من أنه طعن فى الشيخ محمد هادي المدخلي الخ " أولا هذا أيضا كذب منك هات برهانك إن كنت صادقا، وثانيا الشيخ ربيع طعن أشد الطعن فى الشيخ محمد بن هادي المدخلي فهل تتجرأ فتقول إن ربيعا مميع ومبتدع!؟ 🔢🔢أما قولك "إنه حرف كلام الله الخ" فيا سبحان الله ما أقل ورعك أيها الطائش!! وهذا قد يدل على كونك لا حظ لك من الأدب، حاشا لله من أن يحرف الأستاذ الكريم كلام الله، أسألك ما الذي أخرج الآية عن عمومها إذا كان في التعاون مع أي كان مصلحة راجحة عائدة للمسلمين!؟ 🔢🔢وأما ما ذكرته بما يتعلق ببكر أبو زيد والشيخ ربيع مع سيد قطب، من تخبطاتك وتعنتاتك التي قد بينها لك الأستاذ الفاضل خضر أحمد الكميسي 🇧🇼 بساطع البيان فلا أريد إطالة الكلام حوله، 🔢🔢وقولك "إنه نفى أهلية الجرح والتعديل الخ" إنما نفى أهلية الجرح والتعديل منكم ومن أمثالكم الذين لا صدق ولا ورع عندهم، ويتكلمون بكل ما بدا لهم، والذين أفصحوا عن أنفسهم أنهم لا يدرون ما يقولون حين صعود المنبر -كالمجانين- وأخذ ميكرافون، ✅وأخيرا تقول "هذه بعض انحرافاته الدالة على انضمامه إلى صفوف المبتدعة الخ" أين هي!؟ هل مجرد الادعاء والكذب والبهتان منك يجعل السلفيين من صفوف المبتدعة، أين ذهب عقلك؟ أليس منكم رجل رشيد!؟ ✅ أقول لكم يا شباب السلفيين الحذر الحذر من الحدادية الجدد الذين يلزمون الناس بنتائج اجتهاداتهم الخاطئة الهابطة الصادرة من قلوب اشتعلت بنار الحسد والحقد، ويريدون تمزيق جماعة أهل السنة والجماعة وجعل الشباب أسير التقليد، 🤲أسأل الله الكريم رب العرش العظيم أن يجمع شملنا على الحق ويرزقنا الثبات على السنة وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم، 🖊كتبه محب السلفيين أبو عمران الأثري      رابطة القناة⬅       ❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️ ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy

        🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲 🛜❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️               ☪☪☪☪☪        ⭐️ ክፍል  🔢 ✔️ ይህ ከለተሞ አጋፋሪዎች አንዱና የውሸት ካዝና የሆነው ሑሰይን ስልጤ -እንደእርሱ አስተሳሰብ- ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከሱና ውጭ ስለሆነባቸው ነጥቦች ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ላይ የተሰጠ እርምት ነው። 1️⃣  በመጀመሪያ በንግግሩ መግቢያ "ቀደምቶች -ወደ አላህ መቃረብን በማሰብ- የቢድዓ ሰዎችን መጥላትና ከእነርሱ መራቅ ላይ የጋራ ስምምነት አላቸው" ሲል ያወሳው ንግግር ምንም እንከን የሌለበትና እኛም እስከዛሬም ይሁን ወደፊት የምናምንበት ነው ኢንሻአላህ። ነገር ግን ልጠይቅህና ሑሰይን፦ ኢብኑ ሙነወር ይህንን መሰረት ነቅፎ የቢድዓ ሰዎችን መውደድና መቅረብ ይፈቀዳል ብሏል ወይ? በፍፁም! ካላለ ለምንድነው ይህን ንግግር ያጣቀስከውና አስከትለህም "ይህንን የተቃረነ..." ብለህ የፃፍከው? "አይ ብሏል" ካልክ ደግሞ ማስረጃህን ማቅረብ ይጠበቅብሃል። 2️⃣ "የቢድዓ ሰዎችን ያወደሰ ወደ እነርሱ ይጠጋል" የሚለው ከታላቁ ዓሊም ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ይዘህ ያጣቀስከው ንግግር በውስጡ ሰፊ ዝርዝር ያለበትና በቦታው የተዳሰሰ ጉዳይ ነው። ቀደም ሲል በዚህ ዙሪያ እዚህ ከመድገም በሚያብቃቃኝ ልክ ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ  ሐፊዘሁላሁ በቂ ማብራሪያ ልኮልሃል ብየ አስባለሁ። (17ኛው ነጥብ ላይ በስሱ ተወስቷል) 3️⃣ "ኢብኑ ሙነወር በተብዲዕ እና በጀርሕ ወተዕዲል ነጥብ ተፈትኗል" ያልከው (ከዕውነት የራቀ ጉዳይ ነው።) በእውነቱ "በነዚህ ነጥቦች የተፈተኑ" ለመባል ተገቢዎቹ ከሰለፊዮች ይልቅ እናንተው ናቹህ። ይህ አላህ ሐቅን ከማየት አይኑን የጋረደውና ልቡን  ያወረበት ሰው ካልሆነ በስተቀር ለማንም አካል ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው። 4️⃣ ኢብኑ ሙነወርንና ከእርሱ ጋር ያሉትን በአላዋቂነት መግለፅህ ካንተ እና አንተን ከመሰሉ ሐቅን ከመቀበል በኩራትና ምቀኝነት የተበረዘ መሃይምነት የከለከላቸው፣ በተቃረናቸው አካል ላይ በዒልምና በአደብ መልስ መስጠት ከተሳናቸው መንገድ የሳቱ አካሎች የተለመደ ጉዳይ ነው። እንዲህ አይነቱ አካል የበርካቶች የሂዳያ ሰበብ የሆኑትን አንፀባራቂ ኮከቦች በአላዋቂነት ማንቋሸሹ የሚደንቅ አይደለም። 5️⃣ "ኢብኑ ሙነወር ከኢብኑ መስዑድ መርከዝ ተከላክሏል" ያልከው ግልፅ ቅጥፈት ነው። ይልቁን ከእርሱ የምናውቀው ሐቅን በግልፅ መናገርና ከእነርሱም ይሁን ከማንኛውም የቀደምቶችን ጎዳና ከታቀረነ አካል ማስጠንቀቁን ነው። እርግጥ ነው እርሱ እንደናንተ ልማድ መልስ ሲሰጥ የሌለባቸውን በመለጠፍ መሆን የለበትም የሚል አቋም አለው። ሌላው "ሸይኹን አናቀውም.." ስትል በጣም አስደነቅከኝ። ቆይ አንተ እና መሰሎችህ የእርሱን ሸይኽ አለማወቃቹህ "ሸይኽ የሌለው ጠማማ ሙብተዲዕ ነው" ያስብላል ማለት ነው!? ሱብሓነላህ!! 6️⃣ "ዑለማኦችን ይተቻል" ስትል የሌለባቸውን በመለጠፍ ከሆነ ፍላጎትህ ይህ ገሃድ የወጣ ቅጥፈት ነው። ያለባቸውን ጥመት ማጋለጡንና ያመጡትን ቢድዓ በማብራራት ለወጣቶች ማስገንዘቡን ከሆነ "ዑለማኦችን ተችቷል" የምትለው ይህ ሊመሰገንበት የሚገባው መልካም ስራው እንጅ ሊወገዝበት ፈፅሞ አይገባም። 7️⃣ "ከመርከዙ ሰዎች በመከላከል ብዙ ፅሁፎችን ፅፏል" ያልከውም ግልፅ ቅጥፈት ነው። ብዙ ፅሁፎች ይቅርና አንድም ፅሁፍ አልፃፈም። በዕውር ድንብሩ በሚፈነጨው የለተሞ መንጋ ላይ የሰጠውን እርምት ከሆነ "ከመርከዙ ሰዎች መከላከል" እያል የምትጠራው ይህ የግንዛቤህ ችግር ነው። (አረዳድህ በዚህ ልክ ከሆነ) አንተ መንሃጅህ ይቅርና አዕምሮህ እራሱ መጠገኑ አስቸጋሪ የሆነ ክፍተት እንዳለበት ነው የሚጠቁመው። ነቃ በልና ጊዜው ሳያልፍብህ ነፍስህን አድናት። 8️⃣ "የቢድዓ ሰዎችን ማወደስ ከሱና አያስወጣም ይላል..." ያልከው ከዕውቀትህ አናሳነትና ተከታዮችህን የምታምታታበት ብዥታህ ነው። በዚህ ዙሪያ ቀደም ሲል ጠቁሜሃለሁ ኡስታዝ ኸዲር የላከልህን ማብራሪያ ተመልከት። ሌላው ኢብኑ ሙነወር በብዙ ዑለማኦች ላይ ቀጥፎባቸዋል ስትል የቀጣጠፍከው ወደፊት በዝርዝር ስታወሳው እመጣበታለሁ ኢንሻአላህ። 9️⃣ "ኢብኑ ሙነወር መጀመሪያ ላይ የመርከዙ ሰዎች ወደ ኢኽዋኖች ተጠግተዋል ሲል ገልፆ ነበር" ስትል የእነርሱን ሑክም ይሰጣሉ ብሏል ማለት ከሆነ ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው። አይ ያስጠነቅቅ ነበር ለማለት ከሆነ የፈለግከው አሁንምኮ ባቅሙ ልክ እያስጠነቀቀ ነው ያለው። ደግሞ ሌሎችን "ንቁ!" ትላለህ! ልትነቃኮ የሚገባህ አንተው ነበርክ። 1️⃣0️⃣ሌላው "በእነርሱ ላይ ረድ ከመስጠት አቁሟል" ትላለህ። መች አቆመና ይልቁን በዚህ አመት እራሱ ፅፎባቸዋልኮ። ነገር ግን የእርሱ ረድ እንደናንተ ረድ አሰጣጥ በስድብ፣ ሰውን በማንቋሸሽና በጉራ የተበረዘ ሳይሆን ሲቀር "ረድ አቁሟል" በማለት ከሰስከው። ደግሞኮ ረድ መስጠት የነፍስ ወከፍ ግዴታ አለመሆኑንና እርሱ ከእናንተ በፊት የነዚህን አካሎች ጥፋት ማጋለጡን ጠንቀቅህ ታቃለህ። በመሰረቱ ዝም ቢልም እንኳ ሊወቀስ አይገባውም። ምክኒያቱም ዝም ማለቱ በከፊል ወንድሞቹ ረድ እና ማብራሪያ በመደገፍ ወይም በመማር ማስተማር እና አሕባሽን በመሰሉ በጥመት አንጃዎች ላይ ረድ በማድረግ ቢዚ በመሆኑ ነውና። ልጠይቅህና (እንዳስፈላጊነቱ መልስ ከመስተጠት አላቆመም) ነገር ግን ዝም ቢል  ይህ ዝምታዝው ከሱና ያስወጣዋል ወይ? 1️⃣1️⃣ "ለመርከዙ ሰዎች ምክኒያት ይደረድር ጀመር" ስትል አሁንም የፈልግከው በሐቅም በባጢልም ማለትህ ከሆነ ይህም የወጣለት ውሸት ነው። ካልሆነ እናንተ መረን ስትዘሉ "በዲናቹህ ያለአግባብ ድካ አትለፉ፣ በሰዎች ላይ ስትናገሩ የቢድዓ ባለቤቶችም እንኳ ቢሆኑ ወሰን አትለፉ" ብሎ እርምት መስጠቱ ይህ አሁንም ወደፊትም የምንናገርበት የሆነ ጥርጥር የሌለበት እውነት ነው። 1️⃣2️⃣"እነ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድንና መሰል የሱና መሻኢኾችን ተችቷል ... ወደ ሓዳዲያም አስጠግቷቸዋል" ያልከው ይህ ከመጠቅ እይታውና ሐቅን ግልፅ ከማድረጉ ነው የሚቆጠረው። ምክኒያቱም እነዚህ አካሎች ጥቂት የማይባሉ የሓዳዲያ መገለጫዎች ይንፀባረቅባቸዋልና። በዚህ ዙሪያ በሌላ ጥናት እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ። 1️⃣3️⃣"ከዚያም የሙብተዲዖችን መርሆች ማሰራጨት ያዘ" ያልከው ከፀያፍ ቅጥፈቶችህ አንዱ ነው። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ቢድዓን ማሰራጨት ይቅርና) ከወጣትነቱ ጀምሮ ከኢስላምና ከረሱልﷺ ሱና ዘብ ቁሞ ከመከላከል ተወግዶ አያቅም። ይህ አላህ ፊት የምንመሰክርበት ጉዳይ ነው። ከእርሱ ኸይርን እንጅ አናውቅም። እኛ እንዲህ ነው የምናስበው። የውስጡን መርማሪው አላህ ነው። በአላህ ላይ ማንንም አናጥራራም። 1️⃣4️⃣ሌላው "ጀርሕ እና ተዕዲል ጥረትን (ኢጅቲሃድን) ያስተናግዳል፤ በዚህም ሰዎችን ማስገደድ (ኢልዛም ማድረግ) አይገባም" ብሏል ያልከው። ይህ ቀደምቶችም የኋለኞችም የሱና ዑለማኦችና ታላላቅ የሐዲስ ሊቆች የሄዱበት ፍንትው ያለ እውነት ነው። ኢብኑ ሙነወር አዲስን ነገር አላመጣም። በዚህ ዙሪያ ውይይት ከፈለግክ የሰለፊዮች በር ክፍት ነው። ነገር ግን እናንተ የፍርሃት ጥጎች ናችሁ እንጅ። ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy