ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
916
Подписчики
Нет данных24 часа
-67 дней
+5630 дней
Архив постов
የጀርቡዕና የለተሞ መንጋ ሙሪድነት ተጧጥፎ ቀጥሏል። በመሰረቱ ሐቀኛ የመሆን መመዘኛው የእውቀት ብዛትና ማነስ ሳይሆን ቁርአንና ሐዲሥን በቀደምቶች አረዳድ መገንዘብና በዚያም ላይ መፅናት ነው። በጣም
የጀርቡዕና የለተሞ መንጋ ሙሪድነት ተጧጥፎ ቀጥሏል። በመሰረቱ ሐቀኛ የመሆን መመዘኛው የእውቀት ብዛትና ማነስ ሳይሆን ቁርአንና ሐዲሥን በቀደምቶች አረዳድ መገንዘብና በዚያም ላይ መፅናት ነው። በጣም የሚገርመው በዚህ አይነት የሙሪድነት ትብታብ የተጠፈሩ ሰዎች ሁሌም ስለሚደግፉት አካል መጮኽ እንጅ የራሳቸው የዕውቀት ፍለጋ ጉዳይ አጀንዳቸው አይደለም። ስማቸውን እንኳ አስተካክለው ሳይፅፉ ነው እንደዚህ የሰውን እውቀት ገምጋሚ፣ ከርካሚና ፈላጭ ቆራጭ ሁነው የተቀመጡት። ተመልከቱ ጀርቡዒዩ الله ولي المتقين ለማለት ፈልጎ ይመስላል ሁለት ዋው መርቆላቸው ከዓረበኛ ይልቅ ቻይነኛ ፅሁፍ አስመስሎታል። የእነ ሲሉ ሰማሁ ብየ የልጅ ልጅ ደግሞ "Idris" ለማለት አንድ ኑን ጨምራለት "Endris" ብላ ሰጅላለች። እስኪ መጀመሪያ የሰዎችን ትካሻ ከማለካካት በፊት እኔ ማን ነኝ? የዕውቀት ደረጃየ ምን ያክል ነው? እውቀት ፍለጋየስ አጥጋቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመልከት። አረ ተው ልብ አድርጉ። እንዲሁ ስላመቸ ብቻ አትለቅልቁ። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

አንድ ከልብ የመነጨ ምክር እህቶቼ! አብዛህኛውን ጊዜ በአለማስታወል የምንሰራቸው ትልቅ ስህተት አለ እሱም ምንድነው ከአንድ ሰው ጋር ለመግባባትም ሆነ ከዚያም አልፎ ከተግባባንም ቡሀላ፣ ስለ ጓደኛሽ ወይም ሌላም አካል ሊሆን ይችላል፣ለነዛ ለምንግባባቸው ሰዎች ስለ እከሌ ደካማ ጎን ወይም ደግሞ ስለምንወዳት ብቻ ስለሷ ማንነት ሂደን ዝርግፍ አርገን ማውራት ይሄ አግባብም አይደለም። ይልቁንም ይሄ ከስህተት አልፎ እራስንም ማስገመት ነው፣ምክንያቱም ዛሬ መጥተሽ ስለ እከሌ ያወራሽ፣ነገ ስለምትነግሪው ሰው ሄደሽ ማውራትሽ ምንም ጥርጥር የለውም እናም ይሄ ባህሪ አብህኛው ሴቶች የተጠቃንበት ነገር ነው፣ እናም ልንቆጠብና ከእንደዚህ አይነት ቆሻሻ ባህሪ እራሳችንን ልናቅብ ይገባል። ይሄን ስል የሆነች እህት ለምንካት ወይም የመሳሰሉትን አይደለም ነገር ግን እኔም እንደናተው ሴት እንደመሆኔ በዙሪያዬ ብዙ የማየውና የማስተውለው ነገር ይኖራል በዛን ሰዓት ላይ ከንፈር እየመጠጡ ማዘን ሳይሆን ደካማ ጎኖቻችንን በመነጋገር ከእራሳችን ላይ ያንን ችግር መቅረፍ ስላለብን ነው። በተለይ ደግሞ ከወንዶች አጠገብ ሄዶ እሷኮ እንዲህ ናት ምናምን ብሎ ዝርዝር አርጎ መናገር ይሄ ደግሞ ከአክላቅ የዘቀጠ ተግባር ነው እንኳን አንድ ኡስታዝ ወይም የሡና ወንድም ሄዶ እንዲህ፣ እንዲህ ብሎ መናገር ቀርቶ ለኛ ሀላል ለሚሆኑን ባል፣አባት፣ ወንድም እንኳን ስለ ሌላ ሴት ማውራት እንደ ሌለብን አይደል ዲናችን የሚያስተምረን!? ታዳ እንደዚህ አይነትን ተግባር የምናደርግ እህቶች ከየትኛው ቁርአንና ሐዲስ የአመጣነው ወይም ያስተማረንን ነው እየተከተልን ያለነው። በዚህ ላይም ስህተት እንደሆነ እያወቃችሁ ስሜታችሁን መቆጣጠር አቅቷችሁ የምታወሩት ብዙ ጊዜ ወንዶች ሚስጥር አያወጡም በኔና በሱ ይቀራልም ብላችሁ የተሳሳተ አስተሳሰባችሁ ሊሆን ይችላል። ይሄ ግን ስህተት ነው ስሙ ወንድ የሆነ ሁሉ ወንድ ነው ማለት አይደለም አሏህ የአዘነላቸው ሲቀሩ አሁን ላይ እናተ የተናገራችሁትን ሚስጥ ለራሱ አላማ የሚያውሉ ብዙ ናቸው። ያ አላማ አልሳካ ሲላቸው እናተን አሳልፈው ይሰሸጧችኋል። ከዚያም እሰቡት ያቺ ስለሷ የተናገራችሁ እህቶች የአወራችሁትን ስትሰማ የምትወዳችሁና አሏህ ያዘነላት ከአልሆነች በስተቀር የተባለባትን ሰምታ ዝም አትልም እናም ይሄ በትንሹ ... ነው፣ ሊፈጠር የሚችለው ከዚህም አልፎ ብዙ ውርደትና ዝምድናን መቁረት ደረጃ ሊዳርግ ይችላልና እባካችሁ እህቶቼዋ አሏህ ይዘንላችሁ ከዚህ ተግባር እንቆጠብ ከወንዶች ጋር ያለንንም ግንኙነት ለደሩሪያት ከአልሆነ በስተቀር ከማንም ጋር አለመገናኘትን እንምረጥ፣ለቂርአትም ቢሆን አልሃምዱሊላህ አሁን ላይ ብዙ አሊም የሆኑ እህቶች እየወጡልን ነው ከነሱ ጋር ተከባብረን ዒልማችንን እንማር እላለሁ። ወሏሁ አዕለም..! የተሳሳትኩት ወይም እርማት ከአላችሁ በቦት ሀሳባችሁን ልታካፍሉኝ ትችላላችሁ..! ♛... https://t.me/Qudwatii1

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:- በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን :: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::      ☎️ AMU Muslim Students Union: 0950805051 ☎️ Main Campus — Emran: 0916218328 ☎️ Chamo Campus — semir: 0953136409 ☎️ Kulfo Campus — Osama: 0901175690 ☎️Abaya Campus — Muhammad: 0963638759 ☎️Sawla Campus — Abdul-aziz: 0988873341 ወደ ግቢ የምትቀላቀሉ እህቶች የሴት ተወካዮችን በነዚህ ወንድሞች በኩል ማግኘት እንደምትችሉ ለማሳወቅ  እንወዳለን። https://t.me/amumsu1

🍃በቁርአን እንፅናና 🌸አብሽር አትከፋ አትዘን ለሸይጣን መንገድን አትክፈትለት በቁርአን ተፅናና ሸይጣን በሙዕሚን ሀዘን ይደሰታልና "إن الشيطان لكم عدو مبين" ☆ባለህ ተብቃቃ የሰው ልጅ ባገኘው ልክ ሳይሆን በአምነቱ ልክ ነው ደስታን ሚያገኘው ያንተ ሪዝቅ ተከትባ ነው ያለችው አንተ ብቻ ከጌታህ ያለህን አላቃ አሳምር "وفي السماء رزقكم وما توعدون" " إن ربك يبسط الرزق لمن يشاء ويقدر" "وأمر أهلك بصلاة واصطبر عليها لا نسألك رزقا نحن نرزقك " ☆ያሰብከው ያለምከው አልሳካ አልሆን ብሎሃል አብሽር ነገራቶችህን ወደ ጌታህ አስጠጋ እሱጋ መፍትሄ አለና "يدبر الامر" ☆ዱንያ ጊዜያዊና የፈተና አገር ናት አጅ አትስጣት " وما الحيات الدنيا إلا متاع الغرور" ☆አብሽር ሚከሰቱ ነገራቶች ሁሉም ከይር አላቸው እኛ አይመስለንም እንጂ እሱ አዋቂ ጥበበኛ አምላክ ነው "وعسى أن تكرهوا شيئا وهو خير لكم وعسى أن تحبو شيئا وهو شر لكم والله يعلم وأنتم لا تعلمون " "إنه حكيم عليم" አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡ በቀራ:216 ☆ታገስ አላህ ከታጋሾች ጋ ነው ታጋሾችንም ይወዳል "إن الله مع الصابرين " "إن الله يحب الصابرين " @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16532

🌹 ወንድሜ ለባለቤትህ “እወድሻለሁ” በላት! 🌹 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💌 ጀግናው ባል ሁሌም ሚስትህን እንዲህ በላት፦ «እወድሻለሁ!» 🌸 ሴቶች መታቀፍን፣ መንከባከብን፣ በፍቅር መታየትንና ፍቅርን በግልጽ ቃላት መስማትን ይወዳሉ። ስለዚህ ይህንን ከባለቤትህ አትንፈጋት! ፍቅርህን በቃላት ለመግለጽ ከተቆጠብክ፣ በአንተና በእሷ መካከል የመራራቅ ግርግዳ ልትገነባ ትችላለህ፤ የፍቅራችሁም ጣዕም ሊቀንስ ይችላል። 🌹 “እወድሻለሁ” የሚለው ቃል ምንም አያስከፍልህም፤ በሚስትህ ዘንድ ግን ከዓለምና ከውስጡ ካለው ሁሉ የሚበልጥ ዋጋ ሊኖረው ይችላል! ይህ ቃል ቁጣዋን ሊያረግብ፣ ልቧን በደስታ ሊሞላና ወደ አንተ ያላትን ቅርርብ ሊያጠናክር ይችላል። 🌹 በስሜትህ ለጋስ ሁን! ሴት ፍቅርን መስማት አትሰለችም፤ ሺህ ጊዜ ቢደገምላትም እንኳን ከልብ የመጣ የፍቅር ቃል ለእሷ ደስታ ሊሆን ይችላል! 🌹 ፍቅር ዝምተኛ ተግባራት ብቻ አይደለም። ፍቅር ልብን የሚያረካ፣ ነፍስን የሚያነቃቃ፣ በሁለታችሁ መካከል ያለውን የፍቅር ቃል ኪዳን እንደገና የሚያድስ ጣፋጭ ቃልም ጭምር ነው። 🥀 ጀግናው ባል ሆይ! ሚስትህን በድርጊትህ ብቻ ሳይሆን በቃልህም አፍቅራት። አመስግናት፣ አበረታታት፣ አስደስታት፤ እናም ከልብህ፦ 🌹 «እወድሻለሁ፣ የሕይወቴ ውድ ሰው ነሽ!» 🥀በላት! ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌹 አላህ በትዳራችን መካከል ፍቅርን፣ ርህራሄንና መተሳሰብን ያብዛልን። 🌹 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭───────── ┆ የኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ ┆  የተመራረጡ ሙሀደራዎች  ╰───────────╯ ┌⧿⧿⛉ ├✓46 ሙሀደራዎች የያዘ ├✓279MB ብቻ ├╶╶╶ ├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ │ይጠቀሙ! │ ┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ │ተቋዳሽ ይሁኑ! └─────────── ┌╼──────────── ┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን ┃ ┡🖇http://t.me/Yusuf_App1 └╼────────────╯

🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎 💗 የተከበራችሁ ወንዲሞች እና እህቶች ነገ ጁምዓ በተለመደው ሰአታችን ከዝሁር በሗላ የዳዕዋ ፕሮግራም አለ። 🎀 ሌሎች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ መልዕክቱን ሸርርር አርጉት ባረ
🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎 💗 የተከበራችሁ ወንዲሞች እና እህቶች ነገ ጁምዓ በተለመደው ሰአታችን ከዝሁር በሗላ የዳዕዋ ፕሮግራም አለ። 🎀 ሌሎች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ መልዕክቱን ሸርርር አርጉት ባረከላሁ ፊኩም🤍🤲 የፕሮግራም ሰአት:- ⏱ በኢትዮ ከቀኑ 7:30pm ፕሮግራሙ የሚተላለፋው በቴሌግራም😘😂 በቀጥታ ስርጭት ነው። ሊንክ💗💗💗💗💗💗 https://t.me/nuruya76 https://t.me/nuruya76

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن جَآءَكُمۡ فَاسِقُۢ بِنَبَإٖ فَتَبَيَّنُوٓاْ أَن تُصِيبُواْ قَوۡمَۢا بِجَهَٰلَةٖ فَتُصۡبِحُواْ عَلَىٰ مَا فَعَلۡتُمۡ نَٰدِمِينَ — سورة الحجرات (49:6) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ — አል ሑጅራት (49:6)

«ያስደንቃል አባት» ---------------- ሁሉን የሚቀይር በአንድት የቃል ሀባ፡ ልጁ ሰላም ነኝ ሲል የሚፈካ አበባ፡ ላንተ የተሰጠው ምን ተአምር ነው አባ⁉️ አባት የቻለውን፤ ነሚችል አባት ነው
«ያስደንቃል አባት» ---------------- ሁሉን የሚቀይር በአንድት የቃል ሀባ፡ ልጁ ሰላም ነኝ ሲል የሚፈካ አበባ፡ ላንተ የተሰጠው ምን ተአምር ነው አባ⁉️ አባት የቻለውን፤ ነሚችል አባት ነው ሌላ የለም የትም፡ አባት ግን ዘወትር አይወራለትም፡ ሁሉም እናት ይላል አትመለከትም⁉️ የጥርስ አለመኖር ጉረሮን ላይከድነው፡ ግዙፍ ውለታውን ማንም ላይመጥነው፡ ባይወራለትም አባት ግን አባት ነው፡ ቤቱን የሚያደምቀው፤ እራሱን አፍዝዞ እንደቆዬ ቀለም፡ አምሮቱን ውጦ እንጂ፤ እንደ ሰው መብለጭለጭ ጠልቶትኮ አይደለም፡ በሆዱ ችሎ እንጅ፤ ሀዘኑን በደሉን አምቆ እሚከርመው፡ ጡትኮ አይወጣም አባት የረገመው፡ ማንም ሲበድለው፤ ነገውን በማሰብ እድሜውን ቢፈጅም፡ በአባት እንባ ላይ የተሰራ ህይወት ለማንም አይበጅም፡ በምኑ ይፅናና ጠቦ ሲያስቸግረው የኑሮ ሰንሰለት፡ ማልቀስኮ አይችልም በእንባ እንዳይወጣለት፡ እረፍት እያማረው፤ ሁልጊዜ ለራሱ ልፋት ቢሰርግም፡ አባት ልጁን እንጂ ጓደኛ አይፈልግም፡ ስለ አባት ለማውራት ፊደልን ሰድሮ፡ ስለ አባት ለመፃፍ ሀሳብን ወድሮ፡ አይበቃም አመታት አምናና ዘንድሮ፡ ስለ አባት ማንነት ለመተንተን በቃል፡ ከቆመበት ቦታ ካለበት ከፍታ መቆም ይጠይቃል፡ ከአባት እቅፍ መራቅ፤       በጣም ነው የሚያመው፡ ፈገግታው ብቻ ነው፤        መንፈስ የሚያክመው፡ ከአሏህ የተቸረ ብሩክ ልዩ ቅባት፡ ሰው የመሆን ቅኔ የግዙፍ ዛፍ ነባት፡ ልጄ ብቻ ሲለን ያስደንቃል አባት፡ ......ኑር..... t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም በዳይ ይቅርታ ጠየቀ ተብሎም ወዳጅ አይደረግም

ፖድካስት ቁጥር -①- በዒልም መንገድ ላይ! 🎙(በ ኡስታዝ ዓብዱ ረዛቅ እና በ ወንድም አቡ ሱፍያን የተደረገ ፖድካስት) 1. ጀማሪ ተማሪ ኪታብ ሲቀራ ምን ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት። የተለያዩ ሸርሆችን ማንበብ አለበት ወይንስ መትኑ ላይ ብቻ ነው ትኩረት ሚያደርገው? (00:00) 2. የምንማራቸው የእውቀት ዘርፎች ቅደም ተከተላቸው ቢነገረን? (02:09) 3. ማንኛውንም የዒልም አይነት መማር ግዴታ ነውን? (04:47) 4. ልብን ማርጠብ ከዒልም ጋር ግንኙነት አለውን? (05:44) 5. ዒልም ስንማር እንደት መነየት አለብን? እንዴትስ ኒያችንን ማስተካከል እንችላለን? (06:47) 6. ቁርኣን ሒፍዝ ጀምሮ ይከብዳል ወይም በተለያዩ ሰበቦች  ለሚያቋርጡ ሰዎች ምን ምክር ትሰጠናለህ? (09:48) 7. ዒልም በመፈለግ ብዙ ግዜ አሳልፋለሁ፣ ደርሶችንም እከታተላለሁ፣ ግን አይገባኝም። እንዴት ማድረግ አለብኝ? ምን ትመክረኛለህ? (12:35) 8. የትኛው የሀገራችን ቦታ ነው የጠራ የአህሉ ሱና ኡስታዞች የምናገኘው፣ ከቢድዐ፣ ከመውሊድ፣ ከቀብር ሺርካ ሺርክ የጠራ የት ይገኛል? (14:50) 9. ለአንድ  የ 18 አመት ገደማ ልጅ … በአሁኑ ሰአት በኦንላይን በቴሌግራም ላይ ቂርአት መማር ይሻላል ወይስ ደረሳ ሆኖ ገጠር ሂዶ መማር ይሻላል? (15:51) 10. ያወቅነውን/ የተማርነውን እንዴት ነው ወደ ተግባር መቀየር የምንችለው? (19:52) 11. አንድ ሰው ቁርአ፣ ኪታብ እየቀራ ዳዕዋዎችን እያዳመጠ መፅሀፍቶችን እያነበበ ነገር ግን ህይወቱ  ላይ ለውጥ የማይታይበት አላህን ፊሪ የማይሆንበት ኢማኑ እየቀነሰ የሚሄድበት ምክንያቱና ችግሩ ምንድን ነው መፍትሄውስ? (22:14) 12. ቁርኣን ነዞር ሳይቀሩ ኪታብ የሚቀሩ አሉ ይህ ትክክል ነውን? (24:23) 13. ፊቅህ እና ሐዲሥ እንዴት እንማር በቅደም ተከተል ብታብራራልኝ? (29:07) 14. አደብ ለጧሊበል ዒልም ምን ያህል አስፈላጊ ነው? (32:13) 15. ተምረን ያሳለፍነውን እንዴት ሙራጀዓ እናድርግ? (38:32) 16. ኪታብ ስንቀራ የሆነ አገላለፅ ከከበደን ምን እናድርግ? (43:25) 17. ብዙም ያልቀራ ሰው ወደ ሌላ ሀገር ለዒልም መጓዙ ይመከራል? (50:04) 18. የወላጆች ፍቃድ ሳይኖር ለዒልም ፍለጋ ከሀገር መውጣት እንዴት ይታያል? (52:52) 19. ለዒልም እንቅፉት የሚሆኑ ነገራቶች የተወሰኑት ቢዘረዘሩ፣ እንድንርቃቸው? (55:37) 20. ትክክለኛውን ዒልም ለማገኘት ምን ማድረግ አለብኝ? በአጭር ጊዜ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖረኝ የሚረዳኝን ነገር ጠቁሙኝ? (1:03:48) 21. ቁርኣን የሚሐፍዝ ሰው መጠበቅ ያለበት አዳቦች ምን ምን ናቸው? (1:06:55) 22. ዒልምን መፈለግ ከስራ ጋር እንዴት አንድ ላይ ማስሄድ ይቻላል? (1:09:15) 23. የማንበብ ችሎታችንን እንዴት ማዳበር እንችላለን? እንዴት እናንብብ? (1:13:39) 24. አንድ ጀማሪ ተማሪ በረድ ላይ ቢዚ መሆን አለበትን? (1:19:48) 25. ጧሊበል ዒልም ለጊዜው ምን አይነት እይታ ሊኖረው ይገባል? (1:24:33) 26. በጦለበል ዒልም ላይ ፀንቶ ለመቀጠል የሚያግዙ ነጥቦች ምን ምን ናቸው? (1:27:22) 27. እኛ አሁን ሀገር ውጭ ሁነን ከኦንላይን እየተማርን ለወደፊት በተሻለ ሁኔታ እንማረዋለን ብለን ኪታቦችን መግዛታችን - አሁን ባለመጠቀማችንና በማስቀመጣችን ተጠያቂ እንሆናለን? (1:29:04) 28. የቀሩትን ኪታብ ሙራጀዓ ሲያደርጉ ሌሎችን በሚወሰውስ መልኩ ድምፅን ከፍ ማድረግ እንዴት ነው? (1:30:40) = ስለ ቀልባችን/ የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Sle_qelbachn1

ሴት ልጅን መጨበጥ ... بسم الله الرحمن الرحيم እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ። ﺱ : ﻣﺎ ﺣﻜﻢ ﻣﺼﺎﻓﺤﺔ ﺍﻟﻄﺎﻟﺐ ﻟﺰﻣﻴﻠﺘﻪ ﻓﻲ ﺍﻟﺪﺭﺍﺳﺔ؟ ﻭﻣﺎﺫﺍ ﻳﻔﻌﻞ ﻟﻮ ﻣﺪﺕ ﻳﺪﻫﺎ ﻟﻠﺴﻼﻡ ﻋﻠﻴﻪ؟ ጥያቄ ፦ አንድ ተማሪ በትምህርት ቦታ ላይ ፤ ጓደኛውን (ሴት ተማሪን) መጨበጡ ሸሪዓዊ ፍርዱ ምንድነው? ሰላም ልትለው እጇን ከዘረጋችስ ምን ያድርግ❓ 📚 ﺝ : ﻻ ﺗﺠﻮﺯ ﺍﻟﺪﺭﺍﺳﺔ ﺍﻟﻤﺨﺘﻠﻄﺔ ﻣﻊ ﺍﻟﻔﺘﻴﺎﺕ ﻓﻲ ﻣﺤﻞ ﻭﺍﺣﺪ، ﺃﻭ ﻓﻲ ﻣﺪﺭﺳﺔ ﻭﺍﺣﺪﺓ، ﺃﻭ ﻓﻲ ﻛﺮﺍﺱ ﻭﺍﺣﺪﺓ، ﺑﻞ ﻫﺬﺍ ﻣﻦ ﺃﻋﻈﻢ ﺃﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﻔﺘﻨﺔ، ﻓﻼ ﻳﺠﻮﺯ ﻟﻠﻄﺎﻟﺐ ﻭﻻ ﻟﻠﻄﺎﻟﺒﺔ ﻫﺬﺍ ﺍﻻﺷﺘﺮﺍﻙ، ﻟﻤﺎ ﻓﻴﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﻔﺘﻦ . ﻭﻟﻴﺲ ﻟﻠﻤﺴﻠﻢ ﺃﻥ ﻳﺼﺎﻓﺢ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺍﻷﺟﻨﺒﻴﺔ ﻋﻨﻪ ﻭﻟﻮ ﻣﺪﺕ ﻳﺪﻫﺎ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻳﺨﺒﺮﻫﺎ ﺃﻥ ﺍﻟﻤﺼﺎﻓﺤﺔ ﻻ ﺗﺠﻮﺯ ﻟﻠﺮﺟﺎﻝ ﺍﻷﺟﺎﻧﺐ؛ ﻟﻤﺎ ﺛﺒﺖ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ﺃﻧﻪ ﻗﺎﻝ ﺣﻴﻦ ﺑﻴﻌﺘﻪ ﻟﻠﻨﺴﺎﺀ : ﺇﻧﻲ ﻻ ﺃﺻﺎﻓﺢ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ . ﻭﺛﺒﺖ ﻋﻦ ﻋﺎﺋﺸﺔ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ - ﺃﻧﻬﺎ ﻗﺎﻟﺖ : ‏( ﻭﺍﻟﻠﻪ ﻣﺎ ﻣﺴﺖ ﻳﺪ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ ﻳﺪ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻗﻂ، ﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﻳﺒﺎﻳﻌﻬﻦ ﺇﻻ ﺑﺎﻟﻜﻼﻡ ‏) ﻭﻗﺪ ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ : ﻟَﻘَﺪْ ﻛَﺎﻥَ ﻟَﻜُﻢْ ﻓِﻲ ﺭَﺳُﻮﻝِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃُﺳْﻮَﺓٌ ﺣَﺴَﻨَﺔٌ ﻟِﻤَﻦْ ﻛَﺎﻥَ ﻳَﺮْﺟُﻮ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡَ ﺍﻟْﺂﺧِﺮَ ﻭَﺫَﻛَﺮَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻛَﺜِﻴﺮًﺍ ‏[ ﺍﻷﺣﺰﺍﺏ 21: ‏] ﻭﻷﻥ ﺍﻟﻤﺼﺎﻓﺤﺔ ﻟﻠﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﻏﻴﺮ ﻣﺤﺎﺭﻣﻬﻦ ﻣﻦ ﻭﺳﺎﺋﻞ ﺍﻟﻔﺘﻨﺔ ﻟﻠﻄﺮﻓﻴﻦ، ﻓﻮﺟﺐ ﺗﺮﻛﻬﺎ . ﺃﻣﺎ ﺍﻟﺴﻼﻡ ﺍﻟﺸﺮﻋﻲ ﺍﻟﺬﻱ ﻟﻴﺲ ﻓﻴﻪ ﻓﺘﻨﺔ ﻭﻣﻦ ﺩﻭﻥ ﻣﺼﺎﻓﺤﺔ ﻭﻻ ﺭﻳﺒﺔ ﻭﻻ ﺧﻀﻮﻉ ﺑﺎﻟﻘﻮﻝ ﻭﻣﻊ ﺍﻟﺤﺠﺎﺏ ﻭﻋﺪﻡ ﺍﻟﺨﻠﻮﺓ، ﻓﻼ ﺑﺄﺱ ﺑﻪ، ﻟﻘﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ : ﻳَﺎ ﻧِﺴَﺎﺀَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲِّ ﻟَﺴْﺘُﻦَّ ﻛَﺄَﺣَﺪٍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨِّﺴَﺎﺀِ ﺇِﻥِ ﺍﺗَّﻘَﻴْﺘُﻦَّ ﻓَﻼ ﺗَﺨْﻀَﻌْﻦَ ﺑِﺎﻟْﻘَﻮْﻝِ ﻓَﻴَﻄْﻤَﻊَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻓِﻲ ﻗَﻠْﺒِﻪِ ﻣَﺮَﺽٌ ﻭَﻗُﻠْﻦَ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﻣَﻌْﺮُﻭﻓًﺎ ‏[ ﺍﻷﺣﺰﺍﺏ 32: ‏] ﻭﻷﻥ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻓﻲ ﻋﻬﺪ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ﻛﻦ ﻳﺴﻠﻤﻦ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﻳﺴﺘﻔﺘﻴﻨﻪ ﻓﻴﻤﺎ ﻳﺸﻜﻞ ﻋﻠﻴﻬﻦ، ﻭﻫﻜﺬﺍ ﻛﺎﻧﺖ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻳﺴﺘﻔﺘﻴﻦ ﺃﺻﺤﺎﺏ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ ﻓﻴﻤﺎ ﻳﺸﻜﻞ ﻋﻠﻴﻬﻦ . ﺃﻣﺎ ﻣﺼﺎﻓﺤﺔ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻟﻠﻨﺴﺎﺀ ﻭﻟﻤﺤﺎﺭﻣﻬﺎ ﻣﻦ ﺍﻟﺮﺟﺎﻝ ﻛﺄﺑﻴﻬﺎ ﻭﺃﺧﻴﻬﺎ ﻭﻋﻤﻬﺎ ﻭﻏﻴﺮﻫﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻤﺤﺎﺭﻡ، ﻓﻠﻴﺲ ﻓﻲ ﺫﻟﻚ ﺑﺄﺱ . ﻭﺍﻟﻠﻪ ﻭﻟﻲ ﺍﻟﺘﻮﻓﻴﻖ‏. ﻧﺸﺮﺕ ﺑﺎﻟﻤﺠﻠﺔ ﺍﻟﻌﺮﺑﻴﺔ ﻓﻲ ﺑﺎﺏ " ﻓﺎﺳﺄﻟﻮﺍ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺬﻛﺮ ." ‏( ﻣﺠﻤﻮﻉ ﻓﺘﺎﻭﻯ ﻭﻣﻘﺎﻻﺕ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﺑﻦ ﺑﺎﺯ : /4 247 ‏) ﺍﻷﺧﻼﻕ ﺍﻟﻤﺬﻣﻮﻣﺔ ﺍﻟﻨﻈﺮ ﻭﺍﻟﺨﻠﻮﺓ ﻭﺍﻻﺧﺘﻼﻁ መልስ ፦ ኢማም ኢብን ባዝ የማይጠገበውን ምክር (ምላሽ) እንደሚከተለው ሳይሸፋፍኑ ለገሱ!!! 📚 በአንድ ቦታ ላይ ወይም በአንድ ትምህርት ቤት ወይም በአንድ ወንበር ላይ ከሴቶች ጋር በመቀላቀል መማር አይቻልም።❗ እንደሁም ይህ (መደባለቅ) ፈተናን ከሚያመጡ ትላልቅ ምክንያቶች ውስጥ ነው። ለወንድ ተማሪም ይሁን ለሴት ተማሪ የዚህ አይነት መጋራት (አብሮ መሆን) መቀላቀል አይቻልም። ምክንያቱም፦ በውስጡ ብዙ ፈተና ስላለ ነው። አንድ ሙስሊም የሆነ አካል "አጂነብይ" (በትዳር ሊጣመራት የተፈቀደችለት) የሆነችን ሴት መጨበጥ የለበትም። እጇን እንኳን ልትጨብጠው በሚል ብትዘረጋለት ፤ "አጂነብይ" ወንድን መጨበጥ እንደሌለባት ይንገራት። ምክንያቱም ፦ ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ተረጋግጦ በመጣ ሐዲስ ላይ ፦ ከሰሃቦቻቸው ጋር "ሙባዓያ" (ቃል ኪዳን) በተገባቡ ጊዜ ፤ የሴቶቹ ቦታ ላይ « እኔ ሴትን አልጨብጥም አሉ‼️» ዐኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) ከርሷ ተረጋግጦ በመጣ ሐዲስ አለች ፦ (( "ወላሂ" (በአላህ ይሁንብኝ !!! በፍጹም ! የአላህ መልህክተኛ እጅ የሴትን እጅ አልነካችም‼️ሴቶቹን በንግግር ቢሆን እንጂ ቃል የሚግባቡ አልነበረም። " )) በእርግጥም አላህ እንዲህ ብሏል ፦ (( " ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው ፤ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ፤ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ። " )) [አል-አሕዛብ 21] ለጋብቻ የተፈቀዱ የሆኑ ሴቶችን መጨበጥ ሁለቱንም አካሎች ወደ ፈተና ከሚያደርሱ ነገሮች ውስጥ ነው። (መጨባበጥን) መተው ግድ ይሆናል። ሸሪዓዊ ሰላምታ ከሆነ ግን ፦ 👉 በንግግር ሰዓት መለሳለስና መቅለስለስ የሌለበት ከሆነ ፤ 👉 ከመጨባበጥ ውጪ ከሆነ ፤ 👉 በሒጃብ ከመሸፈን ጋር ከሆነ ፤ 👉 ሴቲቱና ወንዱ ለብቻቸው ካለመገለል ጋር ከሆነ በዚህ ላይ ችግር የለውም። አሸናፊና የላቀ ለሆነው "አላህ" ንግግር ሲባል ፦ (( " የነብዩ ሴቶች ሆይ ! ከሴቶች እንደ ማናቸውም አይደላችሁም ፤ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ) ፤ ያ በልቡ ውስጥበሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም ፤ መልካምንም ንግግር ተናገሩ። " )) [ሱረቱል አል-አሕዛብ 32] በነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ዘመን ሴቶቹ "ለነብዩ" ሰላምታን ያቀርቡ (ያወርዱ) ነበር ። ያስቸገራቸውን ጉዳይም ይጠይቁሃቸው ነበር። ልክ እንደዚሁ የነብዩን ባልደረቦች/ሰሃቦችን/ ሴቶቹ ባስቸገራቸው ነገር ላይ ይጠይቋቸው ነበር። ሴት ልጅ ፦ ሴትን ፥ ከወንድ በትዳር ልትጣመራቸው ያልተፈቀዱላትን ወንዶች ፦ አባቷን ፣ ወንድሟን ፣ አጎቷን ... የመሳሰሉትን ቤተሰቦቿን "መሐሪሞቿን" ብትጨብጥ ችግር የለውም። መገጠም ወዳጅና (ረዳት) በሆነው አላህ ነው !!! [መጅሙዓ ፈታዋ (ኢብን ባዝ) 247/4] ...https://t.me/TABRAKEE

​السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ ​በ 2019 ዓ.ል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አድስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ!! ​ዩኒቨርሲቲያችን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 9 እና 10 አዲስ የፍሬሽማን ተማሪዎችን  ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በመሆኑም ​የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ ለሁላችሁም የ «እንኳን ደህና መጣችሁ!» መልዕክቱን እያስተላለፈ ፣ ወደ ግቢ በምትገቡበትና በምትደርሱበት ወቅት ምንም ዓይነት እንግልትና ምቾት የሚነሳ ነገር እንዳይገጥማችሁ ሙሉ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። ​በመሆኑም ስለ ዩኒቨርሲቲው፣ ስላለው ሁኔታና ማንኛውም ዓይነት አካዳሚያዊ ወይም ዲናዊ መረጃ ለሚፈልግ አዲስ  ተማሪ ከታች በተቀመጡት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ሙሉ እገዛና መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን፦ ​ 📞 ለወንድሞች የመረጃና እገዛ መስመሮች፦ • ​📲 ወንድም መስዑድ ሰይድ፦ 0975292817 • ​📲 ወንድም ዑመር አወል፦ 0946505128 • ​📲 ወንድም ሙሀመድ ሀሰን፦ 0924033273 • ​📲 ወንድም ሀቢብ ማህሙድ፦ 0903830776 • ​📲 ወንድም  ሙሀመድ አወል (Qafar)፦ 099 337 5010 ​ • ​📲 ወንድም  ሙኒር ሙሀመድ  (Afan oromo)፦ +251946878432 ​ 📢 ልዩ ማሳሰቢያ ለእህቶቻችን፦ ​እህቶቻችን ቀጥታ የአጋዥ እህቶችን ስልክ ቁጥር ለማግኘት በ📲 0990333299  በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ፦ ​📌 ወደ ኸይር ያመላከተ የሰሪውን ያክል ምንዳ ያገኛል ! የቻናል ባለቤት የሆናችሁ  ይህ መልዕክት አዲስ ለሚገቡትና እርዳታ ለሚፈልጉት ወንድምና እህቶቻችን ሁሉ እንዲደርስ Share በማድረግ አጅሩን እንዲትጋሩ በትህትና እንጠይቃለን። ​✨ የጀማዓችን ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል፦ 👉 https://t.me/wdumuslimstu ​​✨ የጀማዓችን ይፋዊ ቴሌግራም ግሩፕ፦ 👉 https://t.me/WDUMStudent وَالسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ነብዩሏህ ሱለይማን ነው ።

غريب وعجيب! ذكر  ابن كثير عند حديثه عن وفيات سنة ثلاثمئة للهجرة ، محمد بن يحيى قال: "وكان يُعرف محمد بن يحيى هذا بحامل كفنه ، وسبب ذلك ما ذكره الخطيب البغدادي ، قال: بلغني أنَّه تُوفِّي فغسِّل وكُفِّن وصُلِّيَ عليه ودُفن، فلمَّا كان الليل جاءه نبَّاش ، ففتح عليه قبره ،  فلمَّا حلَّ عنه كفنه استوى جالساً ، وفرَّ النبَّاش هاربًا من الفزع،  ونهض محمد بن يحيى هذا ، وأخذ معه كفنه وخرج من القبر ، وقصدً منزله ، فوجد أهله وهم يبكون عليه ، فدقَّ عليهم الباب ، فقالوا: مَن هذا؟ فقال: أنا فلان. فقالوا: يا هذا ، لا يحلُّ لك أن تزيدنا حزنًا إلى حزننا. فقال : افتحوا ، فواللّه أنا فلان ، فعرفوا صوته ، وفتحوا له ، فلما رأوه فرحوا به فرحًا شديداً ، وأبدل اللّه حزنهم سروراً ، وذكرَ لهم ما كان من أمره ،  وكأنه كان قد أصابته سكتة ، ولم يكن قد مات حقيقة، فقدَّر اللّه بحوله وقدرته وقوَّته له هذا النبَّاش ، ففتح عليه قبره، فكان ذلك سبب حياته بعد ذلك مدة، ثم كانت وفاته في هذه السنة." البداية والنهاية / لابن كثير إذا ارادالله لك الخير جائك من حيث لاتشعر.

متى تبرأ ذمم العلماء من الرد على المخالف؟ بيان لمنهج أهل السنة في فقه الردود و التحذير من أهل البدع
قال إبراهيم الرحيلي : ﴿ الرد على المخالف من فروض الكفايات فإذا قام به أحد العلماء وتحقق المقصود الشرعي برده على المخالف وتحذير اﻷمة ، فقد برئت ذمم العلماء بذلك على ماهو مقرر عند العلماء في سائر فروض الكفايات ﴾ قال العلامة ربيع السنة : نعم إذا تحقق المقصود الشرعي برد هذا الواحد فقد برئت ذمة الباقين من المسلمين ،لكن إذا لم يتحقق المقصود الشرعي برد الواحد على المخالف بأن يعاند هذا المبتدع المردود عليه ، وبأن يوجد في الساحة أناس من أدعياء العلم يدعمون المردود عليه ويفرحون بردوده الظالمة الباطلة على ذلك العالم الراد للبدع والأباطيل ويوجد علماء ساكتون لم يبينوا خطأ وأباطيل المردود عليه ، بل يستغل المردود عليه هذا السكوت ويوهم الناس أن هؤلاء الساكتين معه ويؤيدونه ، ويوهمهم بأنه لو كان على الباطل لأدانوه ، فإنه حينئذ قطعا يجب على العلماء الساكتين أن يبينو للناس الحق نصيحة لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم. ونصرة للحق وحسما لمادة الفتن و الاختلاف التي نشأت عن السكوت أو التأييد المبطن لصاحب الباطل اللذين أديا إلى عدم تحقق المقصود الذي يسقط الحرج عن الباقين. ولا يجوز أن يقال : فقد برئت ذمم الباقين. فإذا لم يتحقق المقصود برد واحد أو عشرة من العلماء لم تبرأ ذمة بقية العلماء حتى ينهضوا أو ينهض منهم من يتحقق به المقصود وتنطفئ بهم الفتنة وبأن يظهر الحق للناس طلاب العلم والعوام كما يظهر لهم الباطل. فالقول بتحقق المقصود والحال هذه ، والبلبلة والاضطراب الشديد قائمين أمر عجيب وأعجب منه قول القائل ﴿ فقد برئت ذمة العلماء ﴾ وكان يجب على الدكتور إبراهيم والعلماء الساكتين وغيرهم أن يتحركوا لمواجهة الفتنة أو الفتن الضاربة أطنابها وأن يكون هذا الواقع المؤلم حافزا لهم على القيام بالواجب الكفائي. ولا يبعد أن يكون سبب هذه الفتنة الكبيرة وما ترتب عليها هو سكوت الساكتين الذين يرفضون أن يقوموا بهذا الواجب الكفائي الذي لم يتحقق المقصود منه برد شخص واحد ، وتأمل فقه أهل السنة السابقين وقيامهم مجتمعين بهذا الواجب العظيم. بيان مافي نصيحة إبراهيم الرحيلي من الخلل واﻹخلال ص ٦٢/٦١ #ربيع_السنة #ربيع_المدخلي

*تأثر وبكاء سماحة الشيخ أبوزيد محمد حمزة رحمه الله وهو يحكي قصة نبشه لقبر البر أبو البتول ..* ........ (البر أبو البتول) صاحب قبة كان يُعبد من دون الله، يُستغاث به، وينذر له .. وقد تم نبش القبر بإيعاز من الرئيس جعفر نميري رحمه الله .. قام الشيخ أبوزيد رحمه الله بهدم القبة القابعة داخل مباني البرلمان ونقل الرفات .. وذكر الشيخ أبوزيد أنه - وللتمويه - قام بحفر خمس قبور ودفن الرفات في إحداها ..

◾️ቅመው የተቃሙ‼️ ➖➖➖➖➖➖➖ ጫትን መውደዳቸው ይገርማል ይደንቃል ሰው እንዴት ጠላቱን ልቡ ላይ ያትማል ካልገደልከኝ ብሎ ደጃፋን ይጠናል ስንት ወንዶች አይተናል ቅመው የተቃሙ መንገድ ለቀው ጠፍተው ጠመው የጠመሙ። 🔘ጫት፦ ብክነት ድህነትን መከራን ያወርሳል አመንምኖ አድርቆ ውበትን ያረግፋል አእምሮን በማወክ ማስተዋል ያግዳል እንቅልፍም ያሳጣል እረፍትን ይነሳል ከአላማ አሰነካሎ ቦዘኔ ያደርጋል 🔘ጫት፦ ጎጂ ለመሆኑ አያጠራጥርም አኮላሽ መኾኑም አያከራክርም በሽታ መሆኑን ዘንግተው ስተው ስንቶቹ ተመገቡት መድሀኒት ነው ብለው። ድብርት ያስወግዳል ብለው የሚሉት ዘላቂ አይደለም ይጠፋል በቅፅበት ድብርት የለቀቀ ቢመስል ለጊዜው ምርቃናው ሲጠፋ ጭንቀት ነው ሚወረው ወዳጄ ልምከርህ ስማኝ አድምጠኝ ጫት መቃምን ራቅ ጎጂ ነው እመነኝ ከኪሳራ ውጪ ምንም ትርፍ አታገኝ የሕመም መድሐኒት መጠኑ ልኬቱ እንደ በሽታው አይነት ይለያል ብርታቱ ጉንጩን ሞልቶ የሚቅም የጫት ሱሰኛ ቀንም እረፍት የለው ለሊትም አይተኛ የቂማ መዘዙ ቢያወጉት አያልቅም ጉዳቱን ጥፋቱን ቃሚውም አይክድም የጫትን ጉዳት የሚቃወም ካለ ወይ በሽተኛ ነው ወይ የተታለለ ይህ በእንዲህ እያለ… ሱናን ለመከተል አሻፍርኝ ያለው በሺርክ በቢድዓ የሚጨማለቀው ልብሱን በማስረዘም መንገድ የሚጠርገው ፂሙን እየላጨ ሴት ልጅ የመሰለው የሼሆቹ ሙሪድ ያ የጫት ምርኮኛው ሸሊላ እያለ ድቤ የሚወግረው በሀቅ ላይ መፅናት ልቡ እቢ ያለው ለሸሪአ እውቀት ምንም ግድ የሌለው ሰላቱ መስጅድ ላይ ሄዶ የማይሰግደው… ተዉሂድን ያዝ ሲሉት ሰበብ ሲደርድር ምስኪን ሲለምነው ብር የለኝ የሚል ኑሮ ተወደደ ብሎ የሚያማርር ለጫት ግን ያወጣል በቀን መቶ ሀምሳ ብር ደግሞም ብሎ ይላል ጌታየ ምን ነካህ ሀብት እፍልጋለሀ ተው ስጠኝ እባክህ ከሰው በታች ሆኘ እዳልቀር ከምድርህ ብሎ ይፍክራል ጫቴን እየበላሁ አንተን እንድዛህ ጫት የቃመ ጊዜ ምድሩ የሚጠበው አለምን በሙሉ የያዘ እሚመስለው ፎቁን ሱቁን ሁሉ የተቆጣጠርው ውሰዱ እያለ የሚያከፋፍለው በቅዠት ሲዋልል ውሎ የሚያመሸው ስካሩ ሲለቅ ግን ያ ሁሉ ባዶ ነው። ✍️ ቢንት አሕመድ

ሁለት የተዋደዱ ሰዎች ሁሉ በመጨረሻ ይለያያሉ። ከመለያየት በስተቀር ያለው ሁሉ ቀላል ነው።የምንወዳቸውን ሰዎች አንድ በአንድ ማጣታችን፣ ምንም ቅርበት ለዘላለም እንደማይቆይ ያስተምረናል። አንዳንድ ሰዎች ከአጠገባችን ቢለዩም፣ ትዝታቸው ከልባችን አይለይም። መለያየት የሕይወት ክፍል ቢሆንም፣ መቀበሉ ግን ሁሌም ቀላል አይሆንም። ለገጠመን ሐዘን አላህ የሚወደውን ነገር እንጂ ሌላን አንልም። #ትዝብት