ዮሳብ
Открыть в Telegram
Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
230
Подписчики
Нет данных24 часа
+107 дней
+730 дней
Загружаем данные
Похожие каналы
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
ноябрь '26нояб. '26
ноябрь '26
+1
в 0 каналах
октябрь '26
+16
в 1 каналах
Get PRO
сентябрь '26
+7
в 0 каналах
Get PRO
август '26
+11
в 1 каналах
Get PRO
июль '26
+133
в 0 каналах
Get PRO
июнь '260
в 0 каналах
Get PRO
май '26
+89
в 2 каналах
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 03 ноября | +1 | |||
| 02 ноября | 0 | |||
| 01 ноября | 0 |
Посты канала
| 2 | መዝሙር 42:5
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። | 42 |
| 3 | የተሰደደ ኢየሱስ ለስደተኞች ተስፋ ነው!
የተገፋ ኢየሱስ ለተገፉት መጠጊያ ነው! እግዚአብሔር(ኢየሱስ) እንደ ድካሞች ቤት የሌለው ነው!
የተወደደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕፃን ሲኾን እንግዳና ስደተኛ ነው! 👣
የአብ ልጅ በሰዎች ዘንድ የተናቀ ነው! 😔
የእናቱ ሐዘንም የልቅሶ ምስጋና ኾነኝ። 🙏
ሰቆቃው ድንግል | 53 |
| 4 | Нет текста... | 78 |
| 5 | ካፌው ጥግ ላይ ሁለት ወንዶች ተቀምጠዋል ☕️። አንደኛው ሻዩን በስሱ እየነካካ በሃሳብ ባህር ሰጥሟል 🤔፤ ሁለተኛው ደግሞ ፈገግ እያለ አሻግሮ መስኮቱን ይመለከታል 👀። በመካከላቸው የነበረው ጸጥታ ረቂቅ ጥያቄ አዝሏል 🤫።
ግን እንዴት? አለ ያ የመጀመሪያው፣ ድምፁ ቅሬታ አርግዟል 😔። እግሯ ስር አበባ ብነሰንስላት፣ ክብሯን እንደ አይኔ ብጠብቀው... አሰልቺ ሆንኩባት ። ያኛው ግን—በአደባባይ ፊት የሚነሳት ሰውዬው ልቧን አንጠልጥሎ ይዞታል 🤐። ሴቶች ለምንድነው ማክበርን እንደ ድክመት፣ መናቅን እንደ ወንድነት የሚቆጥሩት?
ጓደኛው ሻዩን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው ☕️።አየህ... አንድ ወንድ ሲያፈቅር ራሱን ሙሉ በሙሉ ሲተው፣ የራሱን አጥር አፍርሶ የሷ ጥላ ብቻ ሲሆን፣ እንደ ክፍት መጽሐፍ ይሆንባታል 📖። ገጹን ሳትገልጠው መጨረሻውን የምታውቀው መጽሐፍ ደግሞ ማንበቡን አታቋርጠውም? ያኛው ‘ጨካኝ’ የሚመስለው ግን የተዘጋ ሳጥን ነው 📦። ዛሬ ሙቀት፣ ነገ ቅዝቃዜ እየሰጠ አእምሮዋን በእንቆቅልሽ ይጠምደዋል ። ሰው ደግሞ በቀላሉ በእጁ የገባውን ሳይሆን፣ አጥብቆ የደከመበትን ነገር ዋጋ የመስጠት እንግዳ አባዜ አለበት ።
የተጋነነ ንቀት እኮ ነው!» አለ ተጎጂው፣ ጥርሱን ነክሶ 😏።
ንቀቱ አይደለም ሲል መለሰ ጓደኛው፣ አይን አይኑን እያየ 👁️👁️። «ያ ሰውዬ የሚያሳየው ‘አንቺ ብትኖሪም ባትኖሪም ህይወቴ ይቀጥላል’ የሚል ጨካኝ በራስ መተማመን አለ 💪። ያ መተማመን በስህተት ጥንካሬ መስሎ ይታያታል። አንተ የሰጠሃት ከመጠን ያለፈ ልስላሴ ግን ሳታውቀው እንደ ፍርሃት ተተረጎመብህ 😨። አንዳንዴ ደግሞ፣ በልጅነቷ ፍቅርን በሰላም አግኝታ የማታውቅ ሴት፣ ፍቅር ያለ ጦርነት እና ያለ ጭንቀት ሊገኝ እንደሚችል አታምንም ⚔️️። እሱን ለማሸነፍ ስትታገል ራሷን ‘ጀግና’ ታደርጋለች 🦸♀️።
ታዲያ መጨረሻውስ?»
መጨረሻውማ ግልጽ ነው አለ ፈገግ እያለ 😊። አውሎ ነፋስ ሲያልፍ ሁሉም ሰው የሚፈልገው ጸጥታ ያለበትን ወደብ ነው 🌊⚓️። በስሜት አዙሪት ውስጥ የደከመች ነፍስ፣ አንድ ቀን መናቅ ሳይሆን እውነተኛ ክብር መዳኛዋ እንደሆነ መረዳቷ አይቀርም 💡። ግን ያኔ... አንተ በመስኮትህ ስር ቆመህ አትጠብቃትም 🪟።
ሻዩ ቀዝቅዟል ️፤ ጥያቄው ግን መልሱን አግኝቶ ከካፌው ጭስ ጋር አብሮ በኖ ጠፋ ።
Yosab | 74 |
| 6 | ሻይ ቡና እያልን ☕🍵 ወንድም ከልቡ እንደሚወዳት ታላቅ ወንድምሽ አስቢው ዮሳብ ነኝ 🤝።
አየሽ የኔ ቆንጆ... 🌸 ህይወት ላይ ትልቁ ውበትሽ መልክሽ ወይም አለባበስሽ ብቻ ሳይሆን፣ ራስሽን የምታስቀምጪበት ከፍታ ነው ።
ለማንም ሰው በቀላሉ የምትደረስ፣ እንደ ንፋስ 🌬️ በማንም እጅ የምትወዛወዝ አትሁኚ። ከማንም ጋር ያለምክንያት መሳሳቅ፣ መተቃቀፍና ወሰን የለሽ ቅርበት ማሳየት ተግባቢነት ሳይሆን የራስሽን ዋጋ በቅናሽ ገበያ ላይ መዘርገፍ ነው 📉።
በወንዶች ወሬ መሀል፦ «እሷማ ቀላል ነች፣ ማዋራቱን ለኔ ተዉት...» ተብለሽ እንደ ተራ ፈተና የምትታዪ ሴት አትሁኚ 🚫። ይልቁንስ ስምሽ ሲነሳ፦
«እሷማ አትቀልድም፣ ገደቧን የምታውቅ ከባድ ልጅ ነች!» ተብሎ በአክብሮትና በግርማ ሞገስ የሚፈራ ድንበር ይኑርሽ 🛡️።
ድንበር ማበጀት ራስ ወዳድነት ወይም ደረቅ መሆን አይደለም፤ የራስን ክብር እንደ አልማዝ 💎 በውድ ሳጥን ውስጥ ቆልፎ ማስቀመጥ እንጂ። በቀላሉ የሚገኝ ነገር ዋጋው ይረክሳል፤ ከፍ ብሎ ያለውን ግን ማንም ቢሆን አንገቱን ቀና አድርጎ በአክብሮት ያየዋል 🙇♂️።
አንቺ የከበረ ሴት ነሽ ። ስለዚህ ወሰንሽ ይከበር፣ ግርማ ሞገስሽ አይጉደል፣ ክብረሻንም ለማንም በቀላሉ አትስጪ! | 109 |
| 7 | Видеосообщение | 1 |
| 8 | አንድ ወንድ ሴትን በእውነት ሲወዳት፣ በምኞት አይን ብቻ አያያትም… በልቡ፣ በጣም ርኅሩኅ እና ውድ ሰው እንደሆነች አድርጎ ያያትታል… ሁልጊዜም ያከብራታል እና ይንከባከባታል፤ ይህም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው…
ከእያንዳንዱ ጉዳት ይጠብቃታል፣ እና በእቅፉ ውስጥ ደህንነት እና ዋጋ እንዲሰማት ያደርጋል…
እንደ ልበ ቀናው ጉረኛው ይይዛታል… በቃላት ሳይሆን በድርጊቶቹ… በጸጥታ ይደግፋታል፣ በጭራሽ ብቻዋን እንዳልሆነች እንድታውቅ ያደርጋል…
ፍቅሩ ለእሷ በሚያደርገው ነገር ሁሉ ስለሚታይ “እወድሻለሁ” ማለት አያስፈልገውም። | 103 |
| 9 | መድረሻ የሌለው ሰው አይራመድም፣ ይሮጣል እንጂ 🏃♂️። የት እንደምንደርስ ሳይሆን የምንሸሸውን ነገር እንዳናይ ፍጥነታችንን እንጨምረዋለን ። መሄጃ ማጣትን ያህል ጉልበት የሚሰጥ፣ ነፍስንም የሚያስቸኩል ነገር ከወዴት ይገኛል? 🤔
በውስጡ የተቀጣጠለው ባዶነት እንዳይውጠው፣ መሯሯጥን መሸሸጊያ ያደርጋታል—ከራሱ እውነት ጋር ፊት ለፊት ላለመጋፈጥ የሚደረግ የደመነፍስ ሽሽት 🎭።
ነገው የጨለመበት፣ በገሃዱ ዓለም የነገ ተስፋ ያልተቀደደለት ሰው ደግሞ ከሁሉ በላይ ነገን አብዝቶ ይናፍቃል ። ዛሬው የታከተው ልብ፣ ዛሬው መከራ የሆነበት ህሊና ከነገ በቀር ምን ምርጫ አለው? በሌለው ነገ ውስጥ ተዓምር ይፈልጋል፤ ያልተጻፈበትን ባዶ ነጭ ወረቀት ያህል ተስፋውን ያሰፍርበታል 📄።
ይህ ሁሉ መጣደፍ ግን ለምንድን ነው? 🧐
ምናልባት ሕይወት አንድ ቀን አስገራሚ ካርታዋን አውጥታ “እንካ፣ ያጣኸው መንገድ ይሄው” ትለን ይሆን? 🗺️ ወይስ ድካማችንን አይታ ከማታውቀው ኪሷ አዲስ ጸሐይ፣ ያልተነበበ ዕድል፣ ያልተጠበቀ እረፍት ታመጣ ይሆን? በሚል የዋህ ጉጉት ነው። ሰው መድረሻውን ሲያጣ እንኳ የተስፋውን ክር በጥፍሩ ይዞ የሚጓዘው ለዚህ ነው 🏃♂️።
ምናልባት አንድ ቀን... ያ የተጣደፈው እርምጃ ቆም የሚልበት፣ ጭጋጉ ተገፎ አድማሱ የሚጠራበት፣ ነገም ከተስፋነት አልፎ በእጃችን የሚጨበጥበት አዲስ ምዕራፍ ይወለድ ይሆናል ። እስከዚያው ግን ባዶነት ያስፈጠነን መንገድ፣ የት እንደምንደርስ በማናውቀው ፍጥነት ይዞን ይነጉዳል 🌪️።
✍️ ዲ/ን አንዱአለም (Yosa ) | 120 |
| 10 | ሰው ጠላቱን መሸሽ ይቀለዋል🗡️። እራስን ግን የት ተደብቀው ያመልጡታል? ራሴን ይዤ የምገባበት ስፍራ ሁሉ በዚያው በገዛ ፍላጎቴ፣ በቁጣዬ፣ በስስትና በስሜቴ አውሎ ንፋስ ይናወጣል🌪️።
ትልቁ አደጋ ያለው ጠላት ውጭ ሆኖ ሲወረውር ሳይሆን፣ ከውስጥ ሆኖ በሩን ሲከፍት ነው🚪። ምኞቴ ከኋላ እየገፋ ወደማልጠገበው ገደል ያመጣኛል፤ እብሪቴ በራሴ መንገድ ካልሄድኩ ብሎ ያፈነግጣል፤ ልቤ ደግሞ ሺህ ምክንያቶችን እየደረደረ ጥፋቴን ያሳምርልኛል። በዚህ ሁሉ መሃል ስታገል፣ ትልቁ እስረኛም አሳሪውም እኔው ራሴ መሆኔ ይገባኛል🔗።
የዳዊት ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ማረኝ... እኔን ከእኔ ጠብቀኝ!🙏
እኔን ከራሴ አላዋቂነት፣ እኔን ከራሴ እብሪት፣ እኔን ካልጠገበው ስጋዊ ምኞቴ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፤ ከሌሎች ጠላቶችማ አንተ ጋሻ ትሆነኛለህ🛡️። ነገር ግን በገዛ እጄ ከምሰራው ወጥመድ፣ በገዛ ምላሴ ከማቀጣጥለው እሳት🔥፣ ጽድቅ መስሎ ከሚሸውደኝ ውሸቴ ማነው የሚጠብቀኝ?
የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ወደዚህ የተሰበረ ልቤ ግባ💔። የመንፈሴን መሪ ጨብጠው፤ እኔ ከምመራው ህይወት አንተ የምትመራው መንገድ ይሻለኛልና🛤️። ራሴን እምቢ እንድል፣ አንተን ግን እሺ እንድል አድርገኝ🙌። ዛሬም ነገም፣ በየሰከንዱ፣ በየእርምጃዬ... እኔን ከእኔ ጠብቀኝ።
✍ዲ/ን አንዱዓለም (Yosab) | 105 |
| 11 | በዙሪያዬ ያለው ዓለም ሁሉ ጸጥ ቢልልኝ ምነኛ ተመኘው 🤫 ፣ትንሿ! ድምፅሽ፣ ፈገግታሽ 😊፣ እና ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያለሽ ማንነት በፍቅር ጣለኝ ❤️ ! ስስቴ 🌸 ፦ለእኔ ልዩ የሚያደርጉሽን ትናንሽ ነገሮች ልንገርሽ።የአይኖችሽ ተፈጥሮ 👁️ አንቺን ይበልጥ ቆንጆ እንድትሆኝኢ ሆን ተብሎ እግዚር የፈጠረችዉ ይመስላልሉ 🙏 ።የቆዳሽ ተፈጥሮአዊ ውበት ✨ ማንኛዉንም ዓይንት የመኳኳያ ውበት ሊጨምርለት የማይችል ይመስላል :: መልክሽ ፀሐይ ከመጥለቋ ጥቂት ቀደም ብሎ ያለውን ☀️ የሚያበራ የብርሃን ሙቀት ያስታውሳል ስትስቂ ጥርሶችሽ ፈገግታሽን ይበልጥ ለማብራት የተፈጠሩ ይመስላሉ ለአፍታ በዙሪያዬ ያለውን ሁሉ ነገር ያስረሳሉ :: የኔዋ ፣ድምፅሽ 🎵 ረጋ እንዳለ ዜማ ነው ተራ ቃላት እንኳ ከአንቺ ሲወጡ በጣም ያምራሉ:: ስለ አይኖችሽ በመቶዎች በሚቆጠሩ መንገዶች ላደንቅ እችላለሁ፤ ነገር ግን በግልፅ አንድ ቀላል እውነት ይበቃል አይኖችሽን ማየት እጅግ ደስ ያሰኘኛል 😍 :: አይቼው የማላውቀው ለዩ ዓይነት ስብዕና አለሽ 🧠፤ አንቺን ይበልጥ እያወቁት በሄዱ ቁጥር ይበልጥ ውብ የሚያደርግ ዓይነት:: ውበት መጀመሪያ የሚታይ ነገር ሊሆን ይቻላል ነገር ግን አንቺ እኔን አብሬሽ እንድቆይ የሚያደርገኝ ስብዕና አለሽ📚። ውጫዊ ገጽታሽ የታሪክ መጀመሪያ ምዕራፍ ቢሆነ፣ ስብዕናሽ ደግሞ ፍቅሬን እንድቀጥል የሚያደርገኝ ዋናው ክፍል ይሆናል📖። ልዩ የሚያደርግሽን ነገር ለመግለጽ ብነሳ፣ ከፊትሽ አልጀምርም ነገር ግን አሁን የመጨረሻ ዉብ የሆነው ስብዕናሽ ስለሆነ በመጨረሻዉ አረኩት ::
ትንሿ ...እውድሻለሁ !💕
....Yosab... | 127 |
| 12 | መሆን ...አለመሆን ¿ | 147 |
| 13 | ጀግና በፍርሃት አይሸበርም፤ ይልቁኑ ፍርሃት ራሱ የጀግናውን ወኔና ቁርጠኝነት አይቶ ይደነግጣል! ጀግንነት ማለት በቃል ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ ህይወትን በጥበብ በመምራት፣ ችግሮችን በጽናት በመሻገርና በዙሪያውላሉት ሰዎች ብርሃን በመሆን የሚኖር ህያው ታሪክ ነው። በጥበብ ያጌጠ ህይወት ደግሞ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እንደ ወይን ጠጅ እያደገ፣ እየጣፈጠ እና እያበራ ይሄዳል።
ዛሬ ደግሞ የዚሁ ድንቅና ባለጥበብ ጀግና የልደት ቀን ነው!
መንገድህ ሁልጊዜም በብርሃንና በጥበብ ይሙላ፤ የቆምክበት ምድር ሁሉ ለሌሎች ተስፋና ጥንካሬ ይሁን። በፍርሃት ቦታ የሌለው ወኔህ፣ በታላቅ ጥበብ ያጌጠው ህይወትህ እና ደግነትህ ለብዙዎች አርአያ ሆኖ ይቀጥል። በሄድክበት ሁሉ ስኬት፣ ደስታ፣ ሰላምና ረጅም ዕድሜ አብረውህ ይሁኑ።
መልካም ልደት! 🎂🎉 | 245 |
| 14 | ወደ መስታወቱ በቀረብኩ ቁጥር አዲስ ሰበብ እፈልጋለሁ 🪞
"ዛሬስ ቢሆን መጨረሻዬ ነው" ብዬ ለራሴ ቃል የገባሁበትን ስህተት፣ ነገ ደግሞ በሌላ መንገድ ደግሜው እገኛለሁ ። በተመሳሳይ ጉድጓድ ውስጥ ደጋግሞ መውደቅ ስልችት የሚል ህመም አለው ። የሰው ልጅ ለራሱ እንኳን ይቅርታ ማድረግ የሚሰለችበት፣ በራሱ ድካም ተስፋ ቆርጦ እጁን የሚሰጥበት አንድ ወሰን አለው 🚫።
"እንዲያው እስከ መቼ?" ብለን ራሳችንን በካስን ቁጥር፣ የውስጣችን ድምፅ "በቃህ! ላንተ ይቅርታ አይገባህም" የሚል የፍርድ ውሳኔ ያስተላልፋል ⚖️። ራሳችንን መውደድ እስኪያቅተን፣ በገዛ ሕሊናችን ፊት መቆም እስኪያፍረን ድረስ በሀጢያት ተደጋጋሚነት እንዝልፋለን 🌧️።
ነገር ግን... በዚያው በደከምንበትና ተስፋ በቆረጥንበት ቅጽበት ሌላ ድንቅ እውነት ይመጣል ።
እኛ ለራሳችን ይቅርታ ማድረጉ ሰልችቶን፣ ፊታችንን አዙረን መሸሽ ስንጀምር፤ እግዚአብሔር ግን አሁንም በቆምንበት ቦታ ይበልጥ በቅርበት ይቆማል 🤲። እኛ በራሳችን ላይ በር ስንዘጋ፣ እሱ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቀናል ።
ለመሆኑ እኛን ከኛ በላይ ምን ያህል ቢወደን ነው ይቅርታ ማድረግ የማይሰለቸው? 💭
የሰው ልጅ ፍቅር ድንበር አለው፤ የሰው ልጅ ትዕግሥት ወሰን አለው 📏። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ስህተታችንን የሚቆጥር ሳይሆን ድካማችንን የሚረዳ፣ በሰራነው ሀጢያት ልክ ሳይሆን በምሕረቱ ስፋት ልክ የሚቀበለን ልዩ ፍቅር ነው ። ራሳችንን ከምንወደው በላይ እሱ ይወደናል፤ ለዚያም ነው እኛ ተስፋ ስንቆርጥ እሱ አሁንም ተስፋ የሚያደርግብን ።
ይህ እኮ ይቅርታ ብቻ አይደለም፤ በፍቅር የመሸነፍ ድንቅ ምሥጢር እንጂ! 🤫
ዲ/ን አንዱአለም (Yosab) | 234 |
| 15 | እውነተኛ ፅፀት ወደ እውነተኛ ንስሐ እና የልብ መታደስ ይመራል 🙏። የእግዚአብሔር ምሕረት ሁልጊዜ ክፍት ቢሆንም፣ ምሕረቱን ለመቀበል ግን የልብ መጸጸት እና መመለስ ያስፈልገናል 💖።
ዲያቆን አንዱዓለም (Yosab) | 173 |
| 16 | Нет текста... | 174 |
| 17 | Нет текста... | 226 |
| 18 | ፍቅርን አገኘሁት ! | 9 |
| 19 | በመተያየት መጽናናት
መተያየት ያፀናል ያጽናናል፡፡ ጳውሎስ የቁም እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ሲወሰድ በመንገድ ላይ ክርስቲያኖችን አየ፡- “ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና” ይላል (የሐዋ.ሥ. 28 15)፡፡ ጳውሎስን የሚያህል ሐዋርያ በማየት ከተጽናና እኛማ እንዴት!? ክርስቲያን ሲገናኝ ምንም ባያደርግም በመተያየቱ ብቻ የሚያገኘው መጽናናት አለ፡፡ መጽናናት ከችግሩ በላይ በሆነ ምክንያት መደሰት ነው፡፡ ወይም መከራው እያለ ከመከራው በላይ በሆነ ምክንያት ማረፍ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም መጽናናት በእሳት ውስጥ ያለ ገነት ነው፡፡ ጳውሎስ ሰንሰለቱ በእጁ አለ፣ ነገር ግን ተጽናና፣ ክሱ አልተለወጠም፣ ነገር ግን ተጽናና፡፡ እግዚአብሔር የሚያጽናናን ችግሩን በማስወገድ ብቻ ሳይሆን ችግሩ እያለም ደስታን በመስጠት ያጽናናል፡፡ ችግሩን ስናይ እግዚአብሔር ይሰወርብናል፣ እግዚአብሔርን ስናይ ደሞ ችግራችን አንሶ እንበረታን፡፡ አንዳችን ለአንዳችን መጽናኛ አድርጎናልና እባካችሁ እንተያይ፣ ኅብረት እናድርግ፡፡
"ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤"
ሮሜ 1:11 | 72 |
| 20 | ✝የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።
ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።
"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር ! እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ | 236 |
